በኦሮሚያ ክልል ከሰሞኑ የደረሰው ውድመት የመንግስት ሪፖርት

115887539 10218143647444466 1144185640356231667 n
በኦሮሚያ ክልል ከሰሞኑ በደረሰው ጥቃት የወደመውን ንብረት የኦሮሚያ ክልል የመጀመሪያ ሪፖርት ይፋ አድርጓል። በዚህም መሰረት
* 1022 መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል፣ ተሰባብረዋል፤
* 227 ሆቴሎች ተቃጥለዋል፣ተሰባብረዋል፤
* 6 ፋብሪካዎች ተቃጥለዋል፤
* 104 የመንግስት መስሪያ ቤቶች ወድመዋል፤
* 20 የመንግስት እና
* 273 የግል መኪናዎች ተቃጥለዋል ፣ ተሰባብረዋል፤
* ከ10 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ከቦታቸው ተፈናቅለዋል፤
ይህን ጉዳት ካደረሱት ውስጥ ፥
* 7126 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፤
* 500 ክሶች ተከፍተዋል።
ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው አካባቢዎች መካከል
ሻሸመኔ ፣ ዝዋይ፣ መቱ ፣ ጅማ ፣አርሲ ነገሌ ከፍተኛው ውድመት የታየባቸው ናቸው።
ከተከሳሾቹ ውስጥ የከተማ ከንቲባን ጨምሮ የወረዳ አመራሮች እና የፀጥታ ሀይሎች ይገኙበታል።
(አቶ ጌታቸው ባልቻ የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኀላፊ ለኢሳት ከተናገሩት)

2 Comments

  1. ይህን ፎቶ አስሬ ነው የምትለጥፉት፤ አንድን ወገን በአንድ መልክ ብቻ ለመቅረጽ የምታደርጉት ሙከራ ስህተት ብቻ ሳይሆን ያለብንን ችግር ማባባስ ነው። ዓላማችሁ ይኸ ይመስለኛል።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.