የምንፈልገው ጣናን ሁለት የሚያህል ሐይቅ እንጂ በሁለት ሳምንት የሚሞላ ኩሬ አደለም! – ሰርፀ ደስታ

dam 2 የምንፈልገው ጣናን ሁለት የሚያህል ሐይቅ እንጂ በሁለት ሳምንት የሚሞላ ኩሬ አደለም!  ሰርፀ ደስታብዙ ጊዜ የማዝነው እንደፈለጋቸው በሚዘውሩን ሳይሆን ዝም ብለን በምንነዳቸው በእኛው ነው፡፡ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የመጀመሪያውን ዙር የግድብ ሙሌት በድል አጠናቀናል አይነት ቀረርቶ በያለበት ሲሰማ አይች እጅግ አዝኛለሁ፡፡ እንዲህ በትንሽ ነገር እንደፈለጋቸው እየዘወሩን መሠረታዊ ጉዳዮችን እንዳናስብ ሆነናል፡፡ በመጀመሪያ በሁለት ሳምነት ስለሚሞላ ኩሬ ሳይሆን ሕልማችን የጣናን ሁለት የሚያህል ሐይቅ ፈጥረን 6000 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት ነው፡፡ ለዛም ነው በዓለም ዙሪያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ከጠላት ጋር እየተናነቁ ያሉት፡፡ በሁለተኛ ደረጃ አሁን ይሄ ሞላን ብሎ ማውራት ፋይዳው ምን እንደሆነ እኔ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ ለዘንድሮ ይበቃናል ከዚህ በኋላ ያለውን ውሃ አንነካብሽም የሚል መልዕክት ለግብጽ ማስተላለፍ ካልሆነ ለኢትዮጵያውያን ምኑ እንደሚያስደስታቸው አላውቅም፡፡ በሶስተኛ ደረጃ ግን ታላቅን ሕልም እንዲህ በተራ ቅንጥብጣቢ ጉዳዮች ማራከስ ነው፡፡

ኢትዮጵያውያን መጠየቅ ያለባቸው የግድቡ ሙሌት ከዚህ በኋላ ያለማቋረጥ እንዲቀጥል እንጂ ሁለት ሳምንት ሙሌት ተሳክቷል እያሉ ለማቅራራት አደለም፡፡ ለዚህ ነው እንዴ ይሄ ሁሉ ግብግብ? በሁለት ሳምነት ለሚሞላ ኩሬ ነበር እንዴ ፊርማ ሳይፈጸም ሙሌት እንጀምራልን አትጀምሩም በሚል ዓለም ዓቀፍ ዜና እስከሚሆን የደረሰን ግብግብ ዜጎች እየተፋለሙ ያሉት፡፡ ይቅርታ ዜጎች የምለው መንግስት ነኝ ከሚለው አካል ብዙዎች ከዚህ በተቃራኒ እየሰሩ ስለሆነ ጭምር ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስቴር የተባለውም ለፖለቲካ ፍጆታ የተጀመረ ግድብ ሲለው እንደነበር ታውቋል፡፡ በዚህ ጉዳይ መንግስት በተባለው በኩል በእርግጥም ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረጉ ያሉ ባለስልጣናት ቢኖሩም በየ አገሩ የሚገኙ ምሁራን ተጽኖ ትልቁን ድርሻ ይይዛል፡፡ ዛሬ ግን አንድ ኩሬ ውሃ አጠራቅመናል እንኳን ደስ አላችሁ የሚሉን በኢትዮጵያ ጉዳይ ትልቅ ጥያቄ ያለባቸው ሰዎች ናቸው፡፡

ኢትዮጵያውያን ሁሉ ልታስተውሉት የሚገባ ቁልፍ ጉዳይ ኢትዮጵያ በዚህ ግድብ እንዳይሳካላት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ያሉ ግለሰቦችና ቡድኖች በመንግስት መዋቅር ውስጥ ጭምር እንዳሉ ነው፡፡ በዜጎች ላይ ትልቅ ሰቆቃና ግፍ የደረሰው የዚሁ ጥረት እንዱ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ትልቅ ከለላ እየተሰጠ ያለው መንግስት ነኝ በሚለው አካል ነው፡፡ አሁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን በብዙ መልኩ እንዲተበተብ እያደረገው ያለው  ዋና ነኝ የሚለው ራሱ አብይ ነው፡፡ ሬድዋን ሁሴንን ከኤርትራ፣ ዲና ሙፍቲን ከኬኒያ አምጥቶ ያስቀመጠው ለግብፅ እንጂ ለኢትዮጵያ ነው ብዬ ለማሰብ እቸገራለሁ፡፡ የምናውቀው ነገር አለና፡፡ አብይ በጣም ብዙ የሚዲያ ቲፎዞ እየተጠቀመ እንደሆነና አገርን ወደ አደገኛ ሁኔታ እየወሰደ ያለ ሰው እንደሆነ ዛሬም ካልገባን ችግሩ ከእኛ ነው፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት አዲስ ምዕራፍ ከፋች የሚመስል ወሬ ነግሮን በተግባር ግን በፍጥነት ሲያደርግ የነበረው የመንግስትን መዋቅሮች ሁሉ በጸረ-ኢትዮጵያ የኦሮሞ ፖለቲካ የጥላቻና ዘረኝነት እቅድ አስፈጻሚዎች መሙላት ነው፡፡ አሁንም ቀጥሎበታል፡፡

እውነታው ይሄ ነው፡፡ ውጤቱም ይሄው የምናወየው ነው፡፡ በተራ የከተማ ፓርክ ሕዝቡን ያስቦረቀዋል፡፡ አጋጣሚውን ግን ለጸረ-ኢትዮጵያውያን በፍጥነት ሲያመቻች ነው እያየን ያለነው፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያውይን መሆናቸውን የሚናገሩ ዜጎች በኢትዮጵያ ለከፍተኛ አደጋ ተጋልጠዋል፡፡ ላለፉት ሁለት ዓመታት ያለማቋረጥ የምናያቸው እውነቶች በየትኛውም መስፈርት የአብይን ጸረ-ኢትዮጵያ አለመሆን አያሳይም፡፡ ወሳኝ የሆነ ግንኙነቱ ከአረቦች በተለይም ከኢሚሬት ጋር ነው፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሳይቀር ለአረቦች ክፍት ሆኗል እየተባለ ነው፣ ዜጎች በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች አብይ ከለላ በሆነላቸው ጸረ-ኢትዮጵያ የኦሮሞ እላማውያንና ኦነጋውያን ያለመቋረጥ እየተገደሉ ንብረታቸው እየወደመ ነው፣ ትልልቅ ሸፍጣዊ ወንጀሎች እየተሰሩ ነው፤ ለምሳሌ የአማራ ክልል ባለስልጣናትና የአገሪቱ ታማጆር ሹም ሞት፡፡ ከዛም በፊት የዛሬው የሕዳሴ ግድብ መሐንዲስ የስመኘው ሞት፣ የተማሪዎች በየዩኒቨርሲቲው በማንነታቸው መገደል፣ ታፍኖ መጥፋት፡፡ ሌሎች ብዙ፡፡ በአጠቃላይ ኢትዮጵያን ለጠላቶቿ ተላልፋ የምትሰጥበትን ሂደት እያመቻቸ ያለ መንግስ ነኝ የሚል አካል ነው ዘሬ ኢትዮጵያ የተያዘቸው፡፡

ሰሞኑን እንኳን በአስተዋልነው የዚህ ሁሉ ሰው እልቂትና ቤት ንብረት ውደመት ወንጀለኞችን ተጠያቂ ላለማድረግና የሌለ ማሳከሪያ ለመፍጠር የሚደረገውን ቁማር እያስተዋልን ነው፡፡ የሰሞኑ ሴራ እቅድ በእርግጥም ኢትዮጵያን ወደለየለት ትርምስ ለመክተትና የዘመናት ሕልማቸውን ለማሳካት ነበር፡፡ ለዚህ ደግሞ ዛሬ በአስከሬን መልሳችኋል አልመለስንም ቁማር መሠል ክስ ተብሎ ያዝናቸው የሚሏቸው ግለሰቦችና ከነሱ ጋር የተያያዙ ቡድኖች ዋና መሪ ሆነው የተሳተፉበት ነው፡፡ እነዚህን ግለሰቦችና ቡድናቸውን በቀጥታ በዋናው መሠረታዊ ወንጀላቸው ላለመጠየቅ ዙሪያ ጥምጥም እያደናገረና የዚህ ሁሉ ዜጋ ሕልፈትና ንብረት ውድመት ዋና ተዋናይ የሆኑትን ከለላ ሲሆን እያስተዋልን ነው፡፡ በውል የማይታወቅ ሸኔ ይለናል፡፡ ሸኔ የሚባል ካለ መሪው ማን ነው? በቀለ ገርባና ጀዋር አደሉም? በሽምግልና ሰበብ በመንግስት በጀት በየቦታው እየተንቀሳቀሱ ምን ሲሰሩ ነበር? በሄዱበት ሁሉ ሕዝብ እየሰበሰቡ ምን ሲያሴሩ እንደነበር እኮ አይተናል፡፡  ዛሬ የሐጫሉን ጨምሮ ከዛ በኋላ በሌሎች በርካታ ክርስቲያን ዜጎች ላይ የደረሰው ጭፍጨፋ እነጀዋር እንዳቀነባበሩት እየታወቀ ሆን ተብሎ በጉዳዮ የሌሉበትና የማይመለከታቸውን ሰዎችና ቡድኖች ይሄው የበለጠ ወንጀለኛ እያደረግ ሲከስ እያየን ነው፡፡

ሰሞኑን በጀዋር ቤት ሳተላይት ተገኘ ወሬ ደግሞ ሰምተናል፡፡ መንግስት ነኝ የሚለው ይሄን አያውቅም ነበር? ባለፈው ጥቅምት ወር ከሆነው ተመሳሳይ ጭፍጨፋ በፊት አንዳንድ የሌሎች አገራት ጉዳዩን እየተናገሩት አልነበረም? ወደ 700 ሺ የሚጠጉ የሞባይል ስልኮች ወደ አገር ቤት ጭፍቸፋው ወደተፈጸመባቸው ቦታዎች እንደገቡ ተናግረው ነበር፡፡ በወቅቱ እኔንም ያልገባኝ መሥመሩን ማን ይሰጣቸዋል የሚለው ነበር፡፡ የሄን የአንዳንድ መንግስታት ዲፕሎማቶች ሲያስጠነቀቁ ነበር፡፡ እንግዲህ ይሄን አላውቅም ነው እያለን ያለው መንግስት ነኝ የሚለው? ዛሬ የአልሸባብንና አይሲስን አሸባሪዎች በቁጥጥር ሥር አዋልኩ እያለ የሚዘፍነው ደህንነት ነኝ የሚለው ይሄን አያውቅም? ተያዙ የተባሉትስ ከማን ጋር ነው እየሰሩ ያሉት (ከተያዙ ማለቴ ነው ዜናው የሆነ ሌላ ቁማር ስለሚመስል)?

የሆነ ሆኖ ኢትዮጵያውያን ሆይ እንዲህ በተራ ወሬ አንታለል፡፡ የአባይ ግድብን አስመልክቶ የምንፈልገው የጣናን ሁለት የሚያህል ሐይቅ እንጂ በሁለት ሳምንት የሚሞላ ኩሬ አደለም፡፡  የኢትዮጵያንና ዜጎቿን መሠረታዊ ደህንነት የሚያስጠብቁትን እንጂ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያሉ ኢትዮጵያን እያወደሙ ያሉትን ወሬ እየሰማን አንታለል፡፡ በኢትዮጵያ መንግስት መዋቅር ያሉ የፀረ-ኢትዮጵያ ዓላማ አራማጆች ተወግደው ለአገርና ሕዝብ በሚቆረቆሩ ዜጎች መተካት አለባቸው፡፡ ስለ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አደገኝነት በተደጋጋሚ አንስቻለሁ፡፡ አሁን ደግሞ እያየሁ ያለሁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚባለው ነው፡፡ በተራ ነገር የምንደለል ማንም የሚነዳን አንሁን! በተግባር የተገለጠ እውነተኛ ቃል እንጂ በአታላዮች የሚነገርን  ውሸት አዚም አይሁንብን፡፡  ዛሬ ወቅቱ እጅግ አስከፊ ነው፡፡ ዜጎች በግፍ ተገድለዋል፣ ቤት ንብረታቸው ወድሟል፣ አሸባሪዎቹ በመንግስ በሚደረግላቸው ከለላ ከፈጸሙት አሳቃቂ ግፍ በተጨማሪ በመንግስት መዋቅር የዜጎች ቤት እየፈረሰ ዜጎች ሜዳ መጣላቸው እንደቀጠለ ነው፡፡ ይሄንንስ ማን ይዳኘዋል፡፡ የእነ እስክንድር ዘሬ ወንጀለኛ መባል ይሄን ወንጀል የሰሩትን መቃወም ነበር፡፡  አሁን ደግሞ ከክረምቱ በላይ ይሄው አለምን እያስጨነቀ ያለው በሽታ በዜጎች ላይ ተጋርጧል፡፡ ለቴሌቪዥን እይታና ለአስመሳይነት አስቸኳይ ጊዜ አውጃለሁ የሚለን መንግስት ተብዬ ዜጎችን ለማረድና ንብረታቸውን ለማውደም አደባባይ የወጣው መንጋ ግን በፖሊስ ተብዬዎች ታጅቦ የፈለገውን ሲሰራ አይተናል፡፡ ይሄን እውነት መጀመሪያ እንቀበል፡፡ የመንግስት መዋቅር በወሮበሎች እየፈረሰ ነው፡፡ ይሄን የሚናገሩ ዛሬ አጋጣሚውን ተጠቅሞ እየለቀመ ያለው መንግስት የሚባለው ቁማርተኛ ቡድን እንደሆን ለአፍታም መዘንጋት ያለብን አይመስለኝም፡፡

እደግመዋለሁ የምንፈልገው የጣናን ሁለት የሚያህል ሐይቅ እንጂ በሁለት ሳምንት የሚሞላ ኩሬ አደለም፡፡ ስለዚህ የወሀ ሙሌቱ መቀጠል አለበት፡፡ ይሄ ጉዳይ ለግብጽ ሲባል የሚደረግ ሸፍጥ እንጂ አንድም ትልቅ የምስራቸው ሆኖ ሊያስነግረው የሚችል ነገር የለውም!

ቅዱስ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን! ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

ሰርፀ ደስታ

 

13 Comments

 1. lol! interesting. እኒም ገርሞኛል የውሃው ፍጥነት ሆኖም ለይምሰልም ቢሆን ዜናው ደስ ይላል እባክህ፡፡ ለጂቡቲ እየሸበችብን ህዝባችን በራሽን የሚያገኝበት ነገር አይገባኝም፡፡ እስቲ የአባይን ግድብ ውጤት ለጊዚው ደስታውን እናጣጥም ያው ኢትዮጵያ ነዳጅ ተገኘ ተብለንም ፈንጥዘን ነበር፡፡ በዚህ ጆሮ የሚያደማ ዜና በሚሰማበት ሰአት ጥሩ ወሬ መስማት እውነትም ባይሆን ደስ ይላል ለጊዚው እባክህ፡፡
  በብድር ር ሰበብ የስልምናን ሃይማኖት ወሃቢ መስፋፋት የአቢይን ቂይ ምንጣፍ ዘርግቶ መቀበልና የሚሰራውን ሽፍጥ ግልጽ ነው፡፡ በጣም መጻፍ ያለበት አገራችንን እየሽረሽረ ያለ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡
  የኔ ጥያቄ አሰርን እያሉ ከሚቀዱን በሚዲያ ግድግዳ አስደግፈው ያሳዩን! እፍረትና መሳቀቅ ያሳደሩባቸው፡፡ ያ ነፍሰገዳይ ጫታም ጅዋር እውነት እስር ቤት ነው? እቤቱ ይሆናል አስረነው የሚሉን፡፡ በሙሉ በነፍስ ማጥፋት የተያዙትን ያሳዩን፡፡

  • የኮሮና ቫይረስ መድሃኒትም ተገኝቶአል አልተባለም? “ደሃ በህልሙ ቂቤ ባይጠጣ …” እንደተባለው፣ ይህን ድሃ ህዝብ ያጃጅሉታል!

 2. ይህ ሊበረታታ የሚገባ ታላቅ ድል ነው!! እዚህ መድረስ በራሱ ቀላል ነገር አይደለም!! በዚህም ይቆማል አልተባለም፡፡ ግድቡን በታሰበው ጊዜ ለማጠናቀቅ አሁን ያለው ሁኔታ ከፍተኛ ብርታት የሚሰጥ ታላቅ ብስራት ነው፡፡ የመተቸት እና የመውቀስ አመል ስለተጠናወተን ብቻ የተገኘውን ድርብ ድል ለማጣጣል እንሞክራለን!! ምክንያቱም በቃ ታመናል!!

 3. ሰርጸ ደስታ የምትባል ፍጹም ጨለምተኛ የሆንህ ሰው፣ አሁን ይህን እንዴት ትተቻለህ!! የከሰርክ!!

 4. Beka aemiroachin hulu denzizo ke tichit besteker minim ayitayenim? Woy beshita beshita beshita beshita! Meche yihon kezih beshitachin yeminifewosew? Yezih zur mulet min malet endehone yene Al Ahramin yesemonun ena ye zarewun zegeba liyunet mayet new. Sertse hoy lantem ቅዱስ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጥህ :: Yetemarkewun timirt le hageritu bemitekim guday lay awulew enji zim bilo lemechoh timirt ayasfeligim…

 5. Sertse! By the way, have you bought a one birr bondfor the dam? As most diaspora, you are specialized in talk.

 6. Do you know even the time of filling is not appropriate. This time is time of heavy eroded soil. The dam is filled partly with this eroded materials partly. Appropriate time of filling is when the soil is trapped by grass and pure water is flowing. Sudan as well as Egypt like the removal of sedimentary soil during this time from their water. They want pure water of august and the whole winter.

 7. ሰርፀ የተሰኘ ሰው የሚጫጭራቸውን ወደ ኋላ ሄዶ ማየት ማንነቱን ለማወቅ ይጠቅማል። ለእርሱ “ኦሮሞ” እና “ዐቢይ” ከጨለማ ጋር ይያያዝበታል። ጨለማው ግን ከልቡ እንደሚሰርፅ አልገባውም፤ ስሙን መቀየር ይኖርበታል። ህዳሴ ግድብ በየወቅቱ የተወሰነ ውሃ እየተሞላ በስድስት ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል። ይኸን ያሉት ኢንጂኔሮች እንጂ ዶ/ር ዐቢይ አይደለም። ሰርፀና አምሳያው አቻምየለህ የት ትምህርት ቤት እንደተማሩ ባውቅ ደስ ይለኛል። ፈጽሞ ኋላ ቀር እና ጨለምተኛ ናቸው። ያልተስማማቸውን (አማራነት ላይ ጥያቈ ያነሳ ወይም ምኒልክ ፍጹም ናቸው ያላለ) ሁሉ መወንጀልን የሙሉ ጊዜ ሥራቸው አድርገውታል።

 8. አቶ ሰርፀ እንዴት ነው ነገሩ? እስከሚገባኝ ሙሌቱ በአመት ይጠናቀቃል ሳይሆን ለአመት በጀት የተደረገለት ከፍታ ደለሉንም፣ ምኑንም ይዞ የታሰበለት ከፍታ ላይ በሁለት ሳምንት  ደርሷል ማለት ኩሬ አስብሎ ማናናቅ ምን ማለት ነው? የሰባት አመት አሞላል እቅድ አይደለም እንዴ? ወይስ የሰባት አመታቱ የሙሌት እቅድ ተለውጧል ሳናውቀው? ወይስ የሆነ የሽሙጥ በትር መሆኑ ነው? ይህ አቢይ ቆራጥ እየሆነ ሲመጣና በኡትዮጵያዊነቱ መሬቷን ጠበቅ አርጎ እየረገጠ እያየን ያልጠበኳቸው ሰዎች ያልተጠበቀ ትችት ያዘንባሉ። የአንባቢንም የአረዳድ ክህሎት መናቅ የበጎ አይደለም። ሥራፈት አስመሰለቦትሳ!!!

 9. Are you mentally retarded to understand all the way we came through despite the coordinated effort of the mighty US and the mighty Egypt. We have already set a new reality on the ground Egypt or US cound not contest. Hey! Pls wake up from your deep hibernation!

 10. አቶ ሰርፀ ፈጣሪ ሲፈጥርህ ለትችት ነው።ፈጣሪ ከአሉባልታ ያላቅቅህ አሜን።

 11. Absolutely nonsense. The dam is built as designed. We are not creating lakes. We do have somany hugh lakes. We are building lakes that generate our soul-electricity

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.