የኢትዮጵያ አየር መንገድ እቃ ጫኝ አውሮፕላን በሻንጋይ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ እቃ በሚጭነበት ወቅት በእሳት ተያያዘ

et cargoየኢትዮጵያ አየር መንገድ እቃ ጫኝ አውሮፕላን በቻይና ሻንጋይ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ እቃ በሚጭነበት ወቅት በእሳት ተያያዘ።
ሁሉም የአውሮፕላኑ ሰራተኞ በመልካም ደህንነት ላይ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል።
አየር መንገዱ አደጋውን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ቦይንግ 777 ኢቲ ኤ አር ኤች እቃ ጫኝ አውሮፕላን እቃ ሲጭን በነበረበት ወቅት በእሳት መያያዙን ገልጿል።
አውሮፕላኑ ከሻንጋይ ወደ ሳኦ ፓሎ መደበኛ የካርጎ በረራ ለማድረግ ዝግጅት ላይ የነበረ መሆኑ ነው የተነገረው።
በአውሮፕላኑ ላይ የተከሰተውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠርም ከሚመለከታቸው ሁሉም አካላት ጋር ኢትዮጵያ በትብብር መስራቷን አየር መንገዱ አስታውቋል።
ኤፍ.ቢ.ሲ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.