ይድረስ ለአቃቢት ጄኔራል አዳነች አቤቤ በግልባጭ ለአቶ ታዬ ደንደአ – ከአባዊርቱ!

abebeየተከበሩ አቃቢት ጄኔራል!
በመጀመርያ አዲሱ የሥራ ዘመንዎ ታሪካዊ ግዳጆን የሚወጥቡት፣ ኢትዮጵያዊነት ከጎጥ በላይና ህግ የሚከበርበት እንዲሆንልዎ ከልብ እመኛለሁ። በእድሜ ብዙ ብበልጥሽም ፣ ኩሩነትሽንና ግስላነትሺንም በማጤን በአንቱታ ጀምሬ  እጨርሰዋለሁና በጽሞና ይከታተሉኝ።
አንዳንዶቻችን ሚዲያ የምነመጣው ለአገራችን መልካም ጤንነት ሲሆን አለመታደል ሆኖ በዲጂታል መናፍስትም ስለተሞላ አስቸጋሪና አስጨናቂ  ጊዜ ላይ ነው ያለነው። ወደ ሀተታ ዝርዝር ሳልገባ መፍትሄ ያልኳቸውን እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ትውልደ ዖሮሞ እስቲ አንድ፣ ሁለት ልወርውር።
1) ትላንትና አቶ ታዬ ደንደአ እስካሁን በጥልቅ ያልተረዳሁትን የኦነግ ሸኔን አመጣጥና ከህውሀት ጋር ያላቸውን ዝምድና በጥልቀት ስላሰሙን አድናቆቴን በመጀመርያ እገልጻለሁ። እንግዲህ እኒህ የዖሮሞን ህዝብ በአደባባይ የካዱ ከሀዲዎች በቀጥታ ከዛ ጀግና ጨቅላ ሀጫሉ እልፈት ጋር አያይዛችሁ፣ መረጃና ማስረጃ ሰብስባችሁ ባለበት በዚህ ወሳኝ ወቅት የ ፕሮ መረራና የኦቦ ዳውድ “አባሎቻችን ይፈቱልን” ምልጃ አይሉት “ዶርሲሣ” ከቶ ሊገባኝ አልቻለም። ምንም የህግ እውቀቱ ባይኖረኝም አይምሮዬ የሚነግረኝ እነዚህ ግለሰቦች በገደምዳሜው ሳይሆን በግልጽ ” ያሰራችሁዋቸው ወንጀለኞች ማለትም በቀለና ጁዋር አልፎም ሰላሳ ምናምን ደመነፍሶች አባሎቻችን ስለሆኑ ይፈቱልን” ማለታቸውም አይደል? ኢትዮጵያን ወክለው  የአቃቢት ጄኔራልነቱን ማእረግ ወስደው  በብቃትና ድፍረት ህግ እያስከበሩልን ያሉቱ አዳነች አቤቤ ሆይ ይህን ከግምት አስገብተው እነዚህን ግለሰቦች ከወንድሞቻቸው ቀላቅለው ይህን አቤቱታ ያቀረቡበትን ዝርዝር ምርመራ እንዲያደርጉባቸው በሀጫሉ ነፍስ ይዤዎታለሁ። ይህን የማንአለብኝነት የጥጋብ ጎማ የሚያስተነፍሱትና ለሁሉም መቀጣጫ የሚሆነው ህግ እንደዚህ ሲከበር ነው። ይህ በጭራሽ የዴሞክራሲ መብት ሊሆን ከቶ አይችልም ። በምን ስሌት ነው የታሰረና እስካሁን እንደሰማነው በነፍስ ግድያና ተባባሪነት  የተመሰከረባቸውን “አባሎቻችን ይፈቱልን” ብሎ ማለት? ዛሬ ይህን ያሉ ነገ ደግሞ ሌላ የጽልመት ሰራዊት ፈተው በህዝባችን መልቀቃቸውም አይደል? የባለፈው ዝምታም አይደል ለንዲህ አይነት አንገት የሚያስደፋና በዖሮሞነት ቀና ብለን የፈረንጅን ሆነ የገዛ ወገናችንን አይን ማየት ያቃተን? እስከመቼ? ስለ ባለፈው ትእግስት ብዛትና ሙሌት እየተወያያችሁ ዛሬውኑ እንዲህ ሲደግሙን ይህን በቸልታ ማለፍ የለባችሁም። ዶር አቢይ ወደ ስልጣን ከመጡ  በሁዋላና ልጆቻችን ቁልፍ የሆነ የስልጣን እርከን ላይ ካረፉ በሁዋላ የዖነግ ስያሜ ብንታደለው ኖሮ ከዖሮሞ ህዝብ ነጻ አውጪነት ወደግለሰብ አይምሮ ነጻነት በተቀየረ ነበር። ለዚህ አልታደልንም. ይሁን። እነሱም ከጌቶቻቸው ህውሀቶች ክፉ ትምህርት ወስደው ነው።  ሆኖም ይህ ሁሉ እልቂትና ንብረትም ከወደመ በሁዋላ ዛሬ ላይ ቆመው “አባሎቻችን ይፈቱ” ብሎ ነገር የጤንነት አይመስለኝም። ባይሆን ፍርዳቸው በአስቸኳይ ይታይልን ያባት ነው።  በዛ መንደላቀቁ ክብርት አቃቢት ህግ። ህጉን ያስከብሩልን አደራ የፈለገው ዋጋ ይከፈልበት ካስፈለገ።
2) ከላይ ተያያዥ የሆነ ጉዳይም አለኝ። ዶር ገመቹ የተባለው ሰውዬ ከዚህ ቀደም ማህተም ያሰርነውን ትውልደ ዖሮሞ አማሮች ናቸው ማለቱን መቼስ ሳይሰሙ አይቀሩም። ያኔ አዳናቂዎቹ (በተለይም ያቺ መናጢ ክፉ ቤቲ የምትባል ጋዜጠኛ ተብዬ) ሰውዬውን እርምት እንደ ማድረግ ሲሳሳቅለት ነበር። ጁዋር ተከብቤአለሁም ብሎም ይሁን ከሀጫሉ እልቂት ማግስት ማተብ ያሰሩ ክርስትያን የሸዋ ዖሮሞዎች እንደሌሎች አማራና ጉራጌ ወገኖቻችን እኩል ጭዳ ሆነዋል። ያ አልበቃ ብሎ ይህ የአዋቂ ገልቱ ሰውዬ ዛሬም ከሀጫሉ እልፈት በሁዋላ የሀጫሉ ነፍሰገዳዮች “ነፍጠኞች” ናቸው የሚል በዜና መስኮት ሰምቻለሁ። እንግዲህ ወንጀለኞቹ ተይዘው ምርመራ በሚደረግበት ሀገር ነው ይህ ሰውዬ እንዲህ የሚለን። ምን ማለት ነው? መልእክቱስ ለማን ነው? ምን እንዲደረግለት ተመኝቶ ነው ይህ ሰውዬ እንዲህ የሚለን? እንዲህ በርግጠኝነት ” ነፍጠኞች ” ናቸው የሚለንን ምሁር ወደምርመራ ወስዳችሁ ምናልባት” ምሁራዊ ” ማስረጃውን ከአንደበቱ እንድትቀበሉ ከልብ አሳስባለሁ። እናንተው ደጃፍ ቁጭ ብሎ እንዲህ በልበ ሙሉነት የሚነግረን ሰውዬ እያለ ጃል መሮን ሆነ የጃል መሮን አስተዳዳሪዎች ፍለጋ በቄለም ደኖችና መቀሌ ሆቴል ቤቶች መሄድ ትርጉም አልባ ይሆናል። ልብ ያለው ያስምርበት።
3) የእስክንድርን ወንጀል እንደሰማሁት የ 10000 ነዋሪዎች ፔቲሺን ማስፈረም – በወፊቱና አናብስት ቅየራ ምርጫን በተመለከተ ከሆነ እዳው ገብስ ነው። በዚህ ምክንያት ከሆነ የታሰረው ፍርድቤት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጠው በትህትና አሳስባለሁ። አስሩ ሺህ ፊርማ ግን አስር ሺህ ጎበዝ አለቆች አሰልፎ ለነውጥ ከሆነ ወንጀል ነው። እኔ በበኩሌ” 360 ዲግሪ”  እየተሽከረከሩ ይህን ሰውዬ ለክፉ አላማ ሊጠቀሙበት በግልጽ ትእይንት የሚሳዩን እያሉ የዚህ ሰውዬ ጉዳይ እልባት ስለማያገኝ ሀቁን አፍረጥርጣችሁ በአስቸኳይ ህዝባችንን አሳውቁልን። የዶር አቢይ መንግስት ይሁን የኦቦ ሽመልስ አብዲሣ አስተዳደር አሁን ገና ስለሆነ አይነጥላቸው የተገፈፈው በአራቱ ማእዘን የተቃጣብንን አደጋ አንድ ላይ መመከቱ አስቸጋሪ ይሆናል ብዬ እጨነቃለሁ። ሆኖም የእስክንድርና ጁዋር አይነቱ ባስቸኳይ እልባት ማግኘት ስላለበት ፈጣሪ ብርታቱን ይስጣችሁ።
4)  ከሰሞኑ ሌላው ጉድ ያስባለን ጉዳይ የሸኔና ህውሀት አንድነት በግልጽ በሸኔ ሰልፈኞች አንደበት በፈረንጁ አገር ተነግሮናል። አቶ ታዬ ደንደአ መድከምም አልነበረበትም ።ከአንደበታቸው በድምጽ ማጉያ ሰምተን ተሸማቀናልና።  ይህ እንዲህ ከሆነ የሸኔ አፈቀላጤዎች እንደ ብርሀነመስቀል አበበ ስኚና  አሉላ ሰለሞን አይነት ጉዶች በአሜሪካው ፍርድቤት ለመገተር ምን እቅድ ይዛችሁዋል? ይህንንም ከእለታዊው ብሪፋችሁ በየቀኑ ለህዝባችን ይነገርልን። መላው ህዝባችን አብሯችሁ ይቆማል እስከ መጨረሻው በዚህ ጉዳይም።
በመጨረሻም!
ይህ ለውጥ ሲጀመር ጠረኑ ሁሉ ፍጹም የኢትዮጵያዊ መአዛና ሽታ ነበረው። እያደር ከዚህ ከመልካሙ ሱስ ከሚያሲዝ ጣእም ወደ እሬትነት እያደር ውስጣችሁ ባሉት ግለሰቦች ተቀይሮ አይናችን እያየ፣ ጆሯችን እየሰማ ተደናግጠን ሰንብተናል። የዚህ ጀግና ሀጫሉ ህልፈት ማስተማር ያለበት፣ እናንተም ደጋግማችሁ እንደምትነግሩን ማንም ይሁን ማን ከኢትዮጵያ በታች ስለሆነ የምትሄዱበትን መንገድ የሚያደናቅፍ ማንኛውንም ግለሰብ ይሁን ቡድን አስቀድማችሁ ለህዝባችን አስታውቁ። የመቻቻል ጊዜ አከተመ። አይሆንም ። እስቲ በባለፉት ግድያዎችና ውድመቶች ፈጣሪ በቃችሁ ይበለን። የዖሮምያ አስተዳደር ይሁን የአቢይ ካቢኔና መንግስትቤቶች በባውዛ በደንብ መፈተሽ አለባቸው። ገራገሩ የዖሮሞ ሰፊው ህዝባችን ሆነ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ይህን ቁምስቅል ዲዘርቭ አያደርገውም።
አቶ ታዬ የጀመሩትን  ገለጻዎች አጥብቀው ይቀጥሉበት። ብዙዎቻችን የተሸረቡትን ሴራዎች ጠንቅቀን አናውቅም ። የርስዎ ቀጥተኝነትና ግልጽነት ሀሞቱ ፈሶ በየቤቱ የሚተክዘውን ተስፋ አሰንቀው ምናልባት  ከዝምታ ወደ አገሩ ጉዳይ ተከታታይነት ብርታት ይሆናሉ ብዬ ከልቤ አምናለሁ።
ክብርት አቃቢት ጄኔራል አዳነች አቤቤ! አያያዝዎና  አካሄድዎ ድንቅ ነው። ዝንፍ እንደማይሉ ሲያውቁ የፈሪ ዱላ በአቃቂርና ዘለፋ ወይም በሽሙጥ ቢያጅቡዎትም  የሰንበሌጥ አጥራቸውን እያፈራረሱ ለታሪክ የሚቀመጥ ፍትህ ያጎናጽፉን ዘንድ በጠፉት ደሀ ነፍሶችና ሀጫሉን በመሰለ ቆራጥ ልጅ ነፍስ እየተማጸንኩ እሰናበታለሁ!
ሽንፈት ለመሀይማን ጨካኞችና አድርባዮች!
ድል ለመላው ሳያልፍለት በኑሮ፣ ኮረና፣ በራሱ ወገን ለሚሰቃየው ሰፊው ህዝባችን!!!
የኢትዮጵያ ትንሳኤ እሩቅ አይሆንም
አመሰግናለሁ

16 Comments

 1. ሰላምታዬ ይድረሶት!
  በተራ ቁጥር 2 የጠቀሱት ነፈዝ ሙሁር ኣይነት በየዩኒቬርሲቲው ተሰግስገው የገማ ኣስተሳሰባቸውን ለንሱ ብቻ ሳይቀር ለሚያፈሩት ተማሪ ሊያስተላልፉ እንደሚችሉ ግምት የተወሰደ ኣይመስለኝም።
  በፌዴራል በጀት የሚቀሳቀሱ ዩኒቬርሲቲዎች ያሉ ኣስተማሪዎች ፤እንደ በቀለ ገለባ ፣ጎጃም ከሚለማ ግብጽ ብትለማ እመርጣለሁ የሚሉ ፣ በጥንብ ዘረኛ ኣስተሳሰባቸው እንዳሽቸው, በተለይ ትግራይ ያሉ, ሲለፍፉ እየታዩ የሚመለከተው የፌዴራል መስሪያ ቤት ዝም ብሎ ማየቱ የዘወትር ጥያቄዬ ነው ።ከመራራ ዛፍ እንዴት ጣፋጭ ፍሬ ይጠበቃል። Get rid of them .Lock them up if need be.

  • Brother, I think you used Zega as your name which is my mokshe. Is there anyway we can differentiate each other.If done by mistake,please disregard this .Thank you.

 2. ወንድሜ ዜጋ ትንሽ ማረምያ ቢጤ እንዲሆንልህ፣ አቶ በቀለ አይደለም “ጎጃም ከሚለማ ሲናይ ትልማ ” ያለው – አቶ በቀለ ከሚያደንቃቸው የህውሀት ሰውዬ አንዱ ነው። ለነገሩ እንደው አንጋቾቻቸው እንዳይቀላምዱብህ ከሚል እንጅ ቢለውስ ምን ይገርማል ብለህ ነው። አፋን ዖሮሞን የመሰለ የፍቅርና ርህራሄ መገለጫን ቋንቋ እንዳይለማ በቋንቋ እድገት ተፃራሪ የቆመ ግለሰብ ሲናይ ትልማ ቢልስ ምን ይገርም ኖሯል?

 3. I saw the appreciation that the writer of the above thanks giving person. He himself tells us that he is an Oromo. it is good to be an Oromo if you stand in Oromiya and speak in favor of the oppressed people of the country and denounce all oppressions that existed in this country for over a century. Simply telling to others that I am Oromo doesn’t mean that you are Oromo in action. Oromoness is not simply blood relations to Oromo. It is beyond that – thinking as Oromo thinks and feels understanding the psychological make up of the people and the associated factors to be labeled as Oromo. Speaking against the political interest of Oromo and supporting groups working to kneel down Oromo and taking advantages will not make you an Oromo. So, be yourself and speak instead of speaking in the language of Oromos historical enemies.

 4. RE: ” Speaking against the political interest of Oromo and supporting groups working to kneel down Oromo and taking advantages will not make you an Oromo. So, be yourself and speak instead of speaking in the language of Oromos historical enemies”

  @Synonymous for IGRONAMUS, this begs for teachable moment and I will make an exception to respond in the language of your masters – you have asked for it. 
  What are the political interests of the Oromos? Let’s see how your “scholars” like Abebe segni manifest them:

  – Giving orders to illiterate kids how to destroy oromos’  infrastructure in a language you losers deem “alien” or not representing “oromos’ ” political interest”?

  – Taking orders from TPLFites that destroyed the very foundation of  oromos’ interest that you purport to safeguard ?

  – Entrenching hate and propogating interethnic divisions alien to the oromo nation?

  You took offence in my Amharic expression – the lingua-franca of the country for centuries – and came to this lame conclusion that it is not representing your political interest? Of course , it CAN’T. How can it be? In your exclusive narrow mind, alike Gerba, proficiency in Amharic is like betraying oromoness or as you cowardly put it ” not representing oromo’s political interest”. I bet one of  that political interest is making your masters – TPLFite goons – happy. As we all know, TPLF’s main political aspiration was to destroy the Amhara nation and their centre of gravity – the Orthodox church. In your shallow and fickle mind, I should have boycotted the geez alphabet and addressed AG Abebee in Qubie or English; right? That is what you pathetically call “…be yourself”, right? Well, I am myself – an oromo whose ancestors took part in enriching አማርኛ to what it is today. I feel and seriously believe Geez is for all of us to use and enrich.  If anything, I am saddened Geez is not effectively deployed to enrich Oromifa and who knows, it may actually bring Afan Oromo to a national stage one of these days.  And I don’t expect a brain educated by the likes of ” Dr” Gemechu Magarssa understands or appreciates that. You are at the wrong front porch Anonymous. If I were you, I would run to console your masters who are currently bewildered and agrieved በአባይ ሙሌትና ድንቅ የፈጣሪና አቢቹ ሥራ!
  ማፈርያ ተላላኪ። እስቲ በአማርኛችን ልጨምርልህ መቼስ እንደ ስምህ ከጽልመት ጋር ነው የማወራውና።

  ቋንቋ መግቢያያ እንጅ አይደለም ንብረት
  ፅልመት ላይረዳ የኔው መዋተት
  እስቲ “ማል ጄ’ዳማ” በከንቱ መድከሜ
  ገልቱን ለማስተማር ያውም በዚህ እድሜ
  የጤና አይደለም ካልሆነ ታምሜ።

  እስቲ ተማማሩበት….ፖለቲካል ኢንተረስት ይልልኛል ደሞ። ቅሌታሞች። 

  • ቋንቋ መግባቢያ ብቻ አይደለም። ይህ አባባል የደንቆሮዎች ማታለያ ነው። Language is the vehicle of the culture, customs and identity of the people. If you kill a language, you kill also the culture, history and identity of those people. ሃበሻ ጌቶችህ ኦሮምኛ ቋንቋን ለማጥፋት 100 አመት የጣሩበት ምክንያት መግባቢያ ስለሆነ/እንዳይሆን ስለተፈለገ አይደለም። የኦሮሞን ማንነት ለማጥፋት ስለታቀደ ነው / It is called cultural genocide!

 5. @Synonymous with IGNORAMUS rather……
  የሚመጥንህ መጠርያ ይሆናል ከሚል ግምት ነው- ስድብ እንዳልሆነ ልብ ይሏል።

 6. እሰየው፡፡ በጣም አስፈላጊ ልመናም ጥያቄም ነው፡፡ ጽሁፍዎት እንዲደርሳት የሚተባበርዎት ቢያገኙ ጥሩ ነበር፡፡ በፓስታ ቢሆንም መላክ ነው፡፡ የተቸገርነው እኮ ጠቃሚ ምክር ሰጪ ነው፡፡
  ችግሩ እኮ አገራችን ህግ አለ ወይ ነው ጣያቄው? አቤቤ አስተዋይ ትክክለኛ ፍ ርድ ሰጪ ልትሆን ትችላለች ነገር ግን የትኛውን ህግ ነው የምታስከብረው? የየትኛውን መንግሥት ህግ ጠቅሳ ነው ለፍርድ የምትደርሰው? የአብይ መንግሥት በጊዚያዊነት ይሁን ወደፊት እድል ይኑረው ለመቆየት አገራችን በተለይ በወቅቱ የምናያቸውን ችግሮች ሁሉ የሚዳስስ ህገመንግሥት ያስፈልጋል፡፡ ፓሊሱ ሹሙ ሰው ሲታረድ ቁጭ ብሎ የሚያየው፡ የተሰጣቸውን ድርሻ ለዜጎች የማይተግብሩት የዚሁ ህግ ለልባ መሆናችን ነው፡፡ እንደሚመስለኝ ህግን በሚመለከት የሆነ ነገር መደረግ አለበት፡፡ በወያኔ ህገመንግሥት ላይ ተፈናጠን ፍትህ ይኖራል ማለት ትንሽ ይከብዳል፡፡
  ሌላው ይሄን ያህል ሰው በቁጥጥር ሥር አውለናል የሚል እውነትነቱን የሚያጠራጥር ዜና አይስጡን፡፡ ቁጥር እየተሰጣቸው ግድግዳ ላይ አስደግፈው ለህዝብ መታየት አለባቸው፡፡ መቀጣጫ እንዲሆንም የእድሜ ልክ እሥራት ጥብቅ የእስር ቤት ውስጥ እንዲሆኑ ማድረግ ማስፈራራትም ይሆናል በዛውም መቀጣጫ ይሆናል፡፡ (የሞት ፍርድ ላይ በጣም ተቃዋሚ ነኝ።

 7. @Kuni, ምን ህግ አለ? የፍትሀብሄሩ ሆነ ወንጀለኛው አሳምሮ አለ እንጅ። ከንጉሱ ዘመን ሲዋረድ የመጣ – በጎጣጎጥ መርዝ አንቀጻት ወያኔና ወዳጆቹዋ ባይበራርዟት። የጠፋው ወይም የተዳከመው የነበረው ህግ አስከባሪው ይመስለኛል። እኔ በዚህ ጉዳይ ብዙ በሀሳብ ደክሜበት የተረዳሁት ቢኖር ለውጡን በትከሻቸው ይዘው ለ ሁለት አመት ተኩል የሚያንገዳግዱን እጅግ ጥቂት መሆናቸውን ነው። 27 አመታት እነዚህ ከሀዲ ህውሀቶች አገራችንን በትምህርት ሆን ብለው ገድለው በጃንሆይ ጊዜ የተጻፈውን ወንጀለኛ መቅጫ እንኳ የማይረዱ የካድሬ ደናቁርት ዳኞች ተንሰራፍተው በመሆኑና በንዋይና ጥቅማጥቅም ከርሳቸውን የሚሞሉ አቡካቶዎች በመብዛታቸው ይመስለኛል። አቢይ የተረከቡት በሁሉም መስክ ባዶ ቤትን ነው። የሰውዬውን ስብእና ለመረመረ እውቀትን የሚሹ፣ ቀናና ቀጥተኛ መሆናቸውን ነው። በግልጽ ይታያል እኮ። ከጀርባቸው ሴረኛና ጥቅመኛ ከበዛ ምንስ አይነት ፍትህ ይመጣል ያሰኛል። ከአቃቢ ህግ እንኳ አሁን ገና ነው ቆራጥ ሰው ያገኘነው። የተበላሸብንን ነገር ሳስበው ያስተክዛል። ህውሀት ሆን ብላ ነው አገራችንን አዘቅት የከተተችው። የረባ ትምህርት በሌለበት ሀገር ምንስ አይነት ዳኛና ጠበቃ ልናፈልቅ ኖሯል ሌባና ቀማኛ ካልሆነ በቀር። እኛ የከፍተኛ ፍቤት ፕሬዙደንት መአዛን ድምፅ የሰማ አለ? ጓዳ ለጓዳ እነዛ ክፉዎች ያጠለሹትን የህግ ስትራክቸርና ምሶሶዎች ለማቃናት እራሳቸውን ቀብረው እያጠኑ አለመሆኑን ማ አያቸው? ይህ ሁሉ እየሆነ ነው ኢትዮጵያ በነፍስ መኖሯን ፈጣሪንና ይህን አቢይን እንደማመስገን ጣት ይቀሰርበታል። ስንቱን አስተካክሎስ ይዘልቀዋል። እሱንም ሆነ ይቺን ቆራጥ አቃቢት ህግ ብርታት ይስጥልን። እስቲ አስበው 26 ሚሊዮን ወጣት አለ ትምህርት ቤት ቁጭ ብሏል በኮረና ምክንያት። እንቅልፍ አይነሳም? አሁን ማ ይሙት ሁሉ ቢተባበር ከዚህ ሰውዬ ጋር ወገን ተአምር አይፈጥርም? ተምች ሁላ!!

 8. አባዊር ‘የፍትሀብሄሩ ሆነ ወንጀለኛው አሳምሮ አለ እንጅ። ከንጉሱ ዘመን ሲዋረድ የመጣ – በጎጣጎጥ መርዝ አንቀጻት ወያኔና ወዳጆቹዋ ባይበራርዟት።” እስማማለሁ፡፡ ህግ አለን አስፈጻሚ ነው ያጣነው ካሉ ፍርሃቴን አስታግሰውልኛል፡
  ዶሮ ዘዝቅዝቆ መያዝም የወንጀለኛ መቅጫ መሆኑን ይጠቅሳል ታዲያ የዶሮ ነጋዴ በውንጀሉ ሲቀጣ አይተን እንውቃለን? በቀላሉ የትራፊክ ህግ እናክብራለን እኢትዮጵያ? የሰከረ ፓሊስ አስቁሞ ተሽከርካሪን ምቆም አቅቶት ሲንገዳገድ አይቻልሁ (ክ3 ዓመት በፍት) ነገሩን ማቅለሌ ሳይሆን አገራችን ምን በህግ እንደሚክበር ለማስታውስም እቸገራሉ፡፡
  አቤቤ ላይ እርስዎ ከፍተኛ ተስፋ አለዎት እስየው! ይሁንልን፡፡ ጠጣር ትመስላለች፡፡ እግዜር ያጠንክራት፡፡ ቀላል ጉዳይ አይደለም ትከቻዋ ላይ ያለው፡፡ አበቤን ጉዳዩን በገዳ ሽምግልና ይዘናዋል ብለው እንዳይጠልፏት መተማመኛ የለንም፡፡ Lets hope the best.

 9. @anonymous= =synonyme d’ignorant= aba caala =ተጋዳላይ ክብሮም እንደወረወረው “አበሻ ጌቶችህ ኦሮምኛ ቋንቋን ለማጥፋት 100 አመት የጣሩበት ምክንያት መግባቢያ ስለሆነ/እንዳይሆን ስለተፈለገ አይደለም። የኦሮሞን ማንነት ለማጥፋት ስለታቀደ ነው / It is called cultural genocide!”

  እንዲህ የጽልመት ጭምብልህን አስወልቅሀለሁ የኛ anonymous! ሙ!!!

  የዖሮሞ ማንነት ሆነ የማንነቱ መገለጫውስ የሚጠፋውና እናንተ “ዖሮሚያ ” በምትሉት ውሱን አጥር የሚቀበረው ያንተ ቢጤው በቀለ ገርባ በሚያቀነቅነው “ዖሮሚፋን በማጀት እናቆየው፣ ቋንቋውን የማያውቅ ካገበየያችሁ እትመልሱለት በአማርኛ ያለ ቀን ነው። እንዴት እንዲህ ተብሎ ማንነት ሆነ የማንነት መገለጫ ይጎለብታል? ማነውስ የዖሮሞን ማንነት እያጠፋ ያለው? የአጼ ዮሀንስ መንግስት አማርኛን የመንግስታቸው ልሣን ያደረጉት ትግርኛ ላይ ከልቸራል ጄኖሳይድ አውጀው ነው በለንና እረፈዋ። ጃንሆይ ደግሞ ለምን ይሆን ዖሮሚፋን ብሄራዊ ያላደረጉት ያውም ዖሮሞ ሆነው? አማርኛ ኢትዮጵኛ ነው ብለው ሰፋ አድርገው ስለተገነዘቡትና በሁሉም ግዛታቸው በሰፊው ሲወርድ ሲዋረድ እድገቱን ጠብቆ ስለመጣ እንጂ በ ዖሮሚፋ ተመቅኝተው አልነበረም አንት ” ኦፊንቤክኔ ነፈዝ”። በጥቂቱ ደግሞ ጉግል እንዲህ ይልሀል”…. defines cultural genocide as “acts and measures undertaken to destroy nations’ or ethnic groups’ culture through spiritual, national, and cultural destruction.”
  ይህን የአርመኖቹን አይነት ወንጀል እንኳ የፈጸሙት ዛሬ መቀሌ በመላለስ የምታሽቃብጡላቸውና ሀጫሉን ያስበሉብን የቀን ጅቦች መሆናቸውን ልቦናህ ያውቀዋል። እነርሱ ደግሞ ህውሀት ተብዬ የአረብ አደግዳጊዎች ሲሆኑ የ “አበሻነት” ስያሜው የሚመጥነው እነሱኑ ሲሆን ጌትነታቸው ደግሞ ለአንተው አንጋቻቸው “አባ ጫላ” አልፎ ተርፎም ለአበበ ሰኚ፣ ጁዋር፣ ፀ አራርሣና ህ ገቢሣ አይነት ደመነፍሶች እንጂ ለኔ ቢጤው ኩሩ ኢትዮጵያዊ ትውልደ ዖሮሞ ከቶ ሊሆን አይችልም! ደፋር!!!

  • “አማርኛ ብቻ ኢትዮጵኛ ነው…” ማለት ሌላው አይደለም ማለት ነው እኮ ነው ጅሎ!

   “ሀጫሉን ያስበሉብን የቀን ጅቦች መሆናቸውን ልቦናህ ያውቀዋል” እዚህ ላይ ልቦና፣ ደመነፍስ ምናምን አይደለም የሚሰራው! ጥርት ያለ ሃቀኛ ፖሊሳዊ ምርመራ፣ ህግ እና ህጋዊነት ብቻ! የአቢይን ወንጀል ተቃዋሚዎቹ ላይ ለማላከክ ያለአንዳች ማስረጃ ሰማይ ድረስ መጮሃችሁ ራሱ የወንጀሉ ፈጻሚዎች መሆናችሁን ያሳብቃል፣ ቢገባህ! እስቲ ከፒፒ ፕሮፓጋንዳ ዉጪ ስለገዳዮቹ አንዲት ቅንጣት ማስረጃ አላችሁ?? እስቲ ልቦና ካለህ ልጠይቅህና፣ የሃጫሉ አሟሟት (ፎረንሲክ ኤቪደንስ የወንጀሉ ቦታ፣ የግዲያ መሳሪያና አመታቱ፣ ምስክሮች፣ የሬሳ ምርመራ) ሁሉ በፖሊሳዊ ጥበብ ሳይመረመር በጥቂት ሰአታት ውስጥ ገዳዩ ማን እንደሆነ የሚነግረን መንግስት እና አቃቤህግ፣ የወንጀሉ ፈጻሚ እና አስፈጻሚ ለመሆናቸው ማረጋገጫ አይደለም??! ማንንም መንገደኛ አቅርቦ “በነእንትና ታዝዤ የገደልኩ እኔ ነኝ” እንዲል አድርጎ ማስረጃ አገኘሁ ብሎ ማስጨፈር በህግ ፊት አያስከድም! ህግ እና ህገመንግስት በሚሰራበት ሃገር፣ “ወንጀለኛ” ብሎ የሚፈርጀው ፍርድ ቤት ብቻ ነው! ቲቪ ላይ ቀርቦ የደቦ ፍርድ አይጠየቅም! ትያትር ነው! ህሊና ያለውማ ይህን አይነት ቅጥፈት እንደወረደ ወስዶ አያስተጋባም፣ አልፎም ያለምንም አመንክዮ በታሰሩት ላይ አይፎክርም!
   ተቃዋሚዎችን በሸር እና ሴራ ወንጅሎ መግደልን ከወያኔ የተማራችሁት ስለሆነ ትያትሩ ማንንም አያስደምምም! ኦሮሞን እንድህዝብ እየወነጀላችሁ ሃገር ትቅጥላለች ማለት እንደማይቻል፣ የደንቆሮ ስብስብ ሃገር እያፈረሳችሁ መሆኑ ግን ለአፍታም አይታያችሁም! በርቱበት!

   • አባ ጫላ አንተ ደግሞ ዘንድሮም ተመልሰህ ያው ነህ። ቋንቋ መግባቢያ እንጂ ማንነትን መለውጫ አይደለም፡፡ እንግሊዘኛ በጽፍህ በመናገርህ ፍረንጅ ነህ? አታደናቁረን እባክህ! ዘመዶችህ በቢላዋ የሚያርዱት ባህላቸውን አጥተው ነው? ወይስ መማር የሚገባቸውን እኢትዮጵያዊ ባህልና ታሪክ ባለማውቅ መደናቆር መርጠው ነው፡፡
    ይሄ ተቀማን እያልክ የአዞ እንባህን እንዳንተ ካለው አይጠበቅም፡፡ ቀንደኛ ኦኒጋዊት ነህ እሰይ ይሁንልህ እስቲ ቆም ብልህ ኦነግ ያደረሰውን ጥፋት አስበው? ትግላችሁ የትም የትም አታያደርሱን ። ከእቂት በስተቀር፡፡ መንግሥት በተቻልው መንገድ እርዳትም እየሰጠን ኦነግ የሚባለውን ድርጅት ማፍረካክስ አለበት፡፡ወንድሚድ ጫላ እንተሳሰብ እንጂ? በህግ አምላክ!

 10. “ምንም የህግ እውቀቱ ባይኖረኝም አይምሮዬ የሚነግረኝ …” ማለትህ በደመነፍስ ተነሳስተህ “የህግ ባለሙያዋን የተከበሩ አቃቢት ጄኔራል” ምክር ለመለገስ መንደፋደፍህ ጀብደኝነትህን ያረጋግጣል! በደመነፍስ የሚነዳው እንስሳ ብቻ ነው፣ የሰው ልጅማ በህግ እና ስርዐት ይመራል!
  ለመሆኑ ወያኔን እንድዚያ እየኮነንክ፣ ላለፉት 27 አመታት የወያኔ ቀኝ እጅ ሆነው ተቃዋሚ ብለው ያሰቡትን ሁሉ ሲያሳድዱ፣ ሲያስሩ፣ ሲገርፉ፣ ጥፍር ሲነቅሉ እና ሲያኮላሹ፣ sadistic የሆነ ሰቆቃ ሲያደርሱ እና ከሃገር ሲያባርሩ፣ ህዝብን ከመሬቱ አፈናቅለው ሲሸጡ፣ ሃገሪቱን ሙልጭ አድርገው የዘረፉት፣ ያው አንተ ዛሬ ያዙልኝ ግረፉልኝ፣ ግደሉልኝ የምትላቸው የቀድሞው የወያኔ ጉዳይ አስፈጻሚዎች አይደሉም???????? የሃጫሉም ገዳዮች እነዚሁ ናቸው! በለው እያልክ ማጓራትህ ከብትነት ነው!!

 11. ምን ይገርማል የናንተ መቀላመድ? አምናም ያን መልካም አምባቸውን አቢይ ነው የገደለው እያላችሁ የአማራን ጭምብል ለብሳችሁ ስታደናቁሩን አልነበረም? ያ አቢይ ገደለ ወይም አስገደለ ለሀጫሉም ልትግቱን ትሞክራላችሁ? ክፋቱ ዛሬ ሁሉ ነቅቷል። ያመነም ካለ ተፀፅቷል። ልትነቁ የማትችሉት ህውሀትና ጀሌዎቹ – አያ ጅቦና ግልገል ልጆቹ ብቻ ናችሁ። ጠብቅ ብቻ ይቺ የናቃችሁዋት ጄኔራል ጉድ ስትሰራችሁ። ቂቂቂቂ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.