አቶ አለማየሁ በላይነህ በብዕር ስሙ “ጉዱ ካሳ” በመባል የሚታወቀው ፀሃፊ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ECADF ድህረ ገፅ ገለፀ

gudu kassa
አቶ አለማየሁ በላይነህ (ጉዱ ካሳ)

አቶ አለማየሁ በላይነህ (ጉዱ ካሳ) በርከት ያሉ ፅሁፎችን በዘ-ሃብሻ ድህረ ገፅ ላይ አስተዋፅዎ ሲያደርግ የነበረ ድንቅ የኢትዮጵያ ልጅ ነበር። ለህገሩ ለህዝቡ ነፃነት የበኩሉን ጥረት ሲያደርግ ኖሯል:: በፀሃፊው አቶ አለማየሁ በላይነህ ሞት ሃዘናችን ጥልቅ ሲሆን ለቤተሰቦቹ ፣ ለሙያ አጋሮቹ፣ ለወዳጆቹ መፅናናትን እንመኛለን።

ዘ-ሐበሻ ድህረ ገፅ አስተዳደር

——————-

ከፅሁፎቹ በትቂቱ

1 2 3 

 

11 Comments

 1. እጅግ የሚያሳዝንና ልብ የሚሰብር ዜና!!!!
  አይይ ይ ወንድሜን። ምን አገኘህ ይሆን? ፈጣሪ ነፍስህን በአፀደ ገነት ያኑርልን፣ ለቤተስብና መላው ወገን አድናቂዎችህ መፅናናቱን ከልብ እመኛለሁ። ያሳዝናል በጣም። ያገራችንን ቁርጥ ሳታውቅ በመለየትህ እጅግ አዝናለሁ። በውይይታችን ብዙ ተማምረንበታልም ብዬ አስብ ነበር። ህይወት እንዲህ ዱብዳ ናት. ያሳዝናል።
  አባዊርቱ ነኝ

 2. የ ጉዱ ካሣን ነፍስ ይማርልን። አስተዋይን እና ጥሩ ኢትዮጵያዊ ነበር። በ ሁለቱም ቋንቋዎች አዝናኝ ፅሁፎቹን ብዙ ጊዜ አነባቸው ነበር።ትልቅ ሰው ነው ያጣንው።

 3. ነፍስ ይማር! ውይ ወንድሜን! የድንገት አደጋ ንው? ይሄው ነው ህይወት እግዚአብሔር:: ነፍስህን በገንት ያኑርልን፡፡

 4. የወንድማችንን ነፍስ እግዚአብሔር አምላክ በአፀደ ገነት ያኑርልን!

 5. በጣም ያሳዝናል፣ በአሳብ ባንስማማም ጉብዝናውን ከማድነቅ አላገደኝም። እግዚአብሔር ያዘኑትን ያጽናና።
  ዘሐበሻ እና ECADF የሟቹን ዜና ዕረፍት እንደሚገባ ማጠናቀር ነበረባችሁ።

 6. እጅግ በጣም ያሳዝናል! ያለመታከት በራሱ ዕምነት ለውድ ሀገሩ ኢትዮጵያ ነጻነት ድምፁን ከፍ አድርጎ አሰምቷል፡፡ ነፍሱን በዐፀደ ገነቱ ፈጣሪ በሰላም ያኑራት፡፡

 7. እጅግ በጣም አዝናለሁ እግዚአብሔር ነፍስህን በአፀደ ገነት ያኑረው ለቤተስቦቹ በሙሉ መፅናናትን ይስጥልን

 8. እጅግ በጣም አዝናለሁ እግዚአብሔር ነፍስህን በአፀደ ገነት ያኑረው ለቤተስቦቹ በሙሉ መፅናናትን ይስጥልን

 9. በጉዱ ካሳ እልፈት ምክንያት አንዳች ነገር ያለማለት ይከብዳል።በተለያየ ጽሑፎቹ የምናውቀው ወገናቸን በቅርብ ከአነበብነው መጣጣፉ አንጻር ስንገምተው ከአጠገባችን በድንገት የተነጠቀ ፣ በቅርብ ሰትና ደቂቃ አይተነው የተሰወረ ፣እንጂ የሕይወት እልፈቱን ለመቀበል ያዳግታል።ለዴሞክራሲ ለፍትህ ለኤኮኖሚ ለፃነት የምትፍጨረጨረዋ ኢትዮጵያችን፣ብዙ ውይይት ፣የሓሳብ ፍጭት፣እሰጥ አገባ ያስፈልጋታል።በዚህ በኩል ጉዱ ካሳ የእሱን ድርሻ እስከ መቼውም ላናገኘው ነው።የፈጠነ መልሱ፣ኢትዮጵያን አትንኩ እልኩ፣ታሪክ ማገናዘቡ በዘመን አይሽሬ ነት ከብዙዎቻችን ጋር ይዘልቃል።በሐሳብ ተለያይተን በቃላት ስንፋለጥ፣ስንስማማና ስንፋረስ ሁሉ በሜዳ ላይ ጉዱ ካሳ የፊት አጥቂው ነበር።ለቤተሰቡ፣ለዘመድ አዝማድ፣ለወዳጆቹ፣ለጽሑፍ አድናቂዎችህ መጽናናትን እንመኛለን።ጉዱ ካሳን ነፍስ ይማር።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.