የትግራይ ክልል መሥተዳድር መግለጫ 

debre የትግራይ ክልል መሥተዳድር መግለጫ በትግራይ ሊደረግ የታቀደዉን ምርጫ ለማደናቀፍ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት የኤርትራ መንግሥትና ሌሎች ሃይሎች በተቀናጀ ሁኔታ እየሰሩ ነዉ ሲሉ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል ገለፁ። በትግራይ ተወላጅ ባለሃብቶች እና አጠቃላይ የክልሉ ኤኮኖሚ ላይ አሻጥር እየተፈፀመ ነዉ።

በትግራይ ሊደረግ የታቀደዉን ምርጫ ለማደናቀፍ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት የኤርትራ መንግሥትና ሌሎች ሃይሎች በተቀናጀ ሁኔታ እየሰሩ ነዉ ሲሉ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል ገለፁ። ም/ል ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ መንግሥታዊ መገናኛ ብዙኃን በኩል ባስተላለፉት መልክት በተለይም በክልሉ ድንበር እና አዋሳኝ አካባቢዎች ምርጫዉን ለማደናቀፍ የታቀዱ እንቅስቃሴዎች እየታዩ ነዉ ብለዋል። ከዚህ ዉጭ በትግራዊ ተወላጅ ባለሃብቶች ላይ እና አጠቃላይ የክልሉ ኤኮኖሚ አሻጥር እየተፈፀመ ነዉ ያሉት ምክትል መስተዳድሩ መንገድ የመዝጋት እንቅስቃሴን ጨምሮ የትምህርት ተቋማትን ስራ የማደናቀፍ ተግባር እየተከወነ ነዉ ሲሉ ደብረፂዮን ከሰዋል።

ሚሊዮን ሃይለሥላሴ

አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ \

DW

2 Comments

  1. እነዚህ ሰዎች ለመገንጠል ሳያስቡ አልቀሩም የድጋፍ ኮሚቴ ተቁዋቁሞ እንዲፋጠን እገዛ ቢደርግላቸው።

  2. The TPLF should not be allowed to destabilize Ethiopia from its current base in Makelle. Prime minister Abiy Ahmed should flex his muscles and impose some kind of punitive measures against the TPLF thugs hiding in and operating from Makelle. The Oromo groups working with the TPLF are fringe ones and will vanish if the TPLF is dealt with. The recent trip by prime minister Abiy Ahmed to Eritrea has caused fear in the TPLF rank and file because they suspect that the Eritrean president would urge tough measures against the TPLF.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.