የስፖርት አጫጭር የውጭ ወሬዎች  (ከወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ)

መርሻ ደምሴ(ከወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ)
(ደራሲ፣ጋዜጠኛና ማህብራዊ ሃያሲ)

 

ዊልያን ከኢንተርሚያሚ ያቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ

11 2

ዊልያን የአሜሪካው ክለብ ኢንተር ሚያሚ ለሦስት አመት ለክለቡ እንዲፈርም ያቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አደርጓል።

Daily Telegraph እንደገለፀው ዊልያን በሜጀር ሊግ ሶከር ተሳታፊ የሆነው የኢንተር ሚያሚ ክለብ ያቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ ያደረገው በአውሮፓ ለመቆየት ፍላጎት ስላለው ነው ተብሏል።

የ31 አመቱ ብራዚላዊ ተጨዋች ፤በቸልሲ ቤት ያለው ውል ከዚህ የውድድር አመት

ፍፃሜ በኋላ ያበቃል።ዊልያን ከውድድሩ ፍፃሜ በኋላ ወደ አርሴናል ወይንም ወደ ቶትንሀም ይዛወራል ተብሎ ይጠበቃል።

የእንግሊዙ ሌጀንድ ዴቪድ ቤከም ክለብ እንደሆነ የሚነገርለት ኢንተር ሚያሚ ዊልያንን ለማስፈረም ከፍተኛ ወጪ ለማውጣት ከወዲሁ ተዘጋጅቶ ነበረው።

ፓሪስ ሴንት ዠርመን ራሽፎርድ ላይ ትኩረት አድርጓል

11 3

የፓሪስ ሴንት ዠርመን አሠልጣኝ ቶማስ ቱቸል ፥የማንችስተር ዩናይትዱን አጥቂ ማርኮስ ራሽፎርድን ፥በሚከፈተው የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ፥ከፍተኛ ትኩረት ያደረጉበት ተጨዋች መሆኑን The Independent ይፋ አድርጓል።

የክለቡ ባለቤት ተጨዋቹን እንደሚፈልጉት ፥ ይሁንና እንደ ራሽፎርድ አይነት ጥሩ ተጨዋቾች ፥ ክለቦች መልቀቅ እንደማይፈልጉ ገልጸዋል።

የ22 አመቱን ተጨዋች ለማስፈረም  ፓሪስ ሴንት ዠርመን ለረዥም ጊዜ ሲፈልገው እንደነበር ነው የተጠቆመው።

ራሽፎርድ በማንችስተር ዩናይትድ ክለብ ከፍተኛ ተፈላጊ ተጨዋች ነው። ክለቡ ተጨዋቹን ልሽጠው እንኳን ቢል ከ100 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ያወጣል።ፓሪስ ሴንት ዠርመን ግን ፥በዋጋው ላይ ለመስማማት ዝግጁ ነው።ማንችስተር ዩናይትድ ግን ተጨዋቹን የመልቀቅ ፍላጎት የለውም።

 

ቸልሲ ጆቪችን ያስፈርማል?

ቸልሲ የሪያል ማድሪዱን አጥቂ ሉካ ጆቪችን የማስፈረም ፍላጎት ያለው መሆኑን Mundo Deportivo ይፋ አድርጓል።

የ22 አመቱ ጆቪችን ሪያል ማድሪድ በ55 ሚሊዮን ፓውንድ ነበር ከአንትራክ ፍራንክ ፈርት ነበር ባለፈው በጋ ላይ ያስፈረመው።ነገር ግን ጆቪች ለስፔኑ ክለብ 25 ጨዋታ አድርጎ ሁለት ግቦችን ብቻ ነው ያስቆጠረው።

ቸልሲ በአሁኑ ወቅት የአርቢ ሌብዚንግ ክለብ አጥቂ የሆነውን ቲሞ ዋርነርን በ55 ሚሊዮን ፓውንድ ማስፈረሙ ይታወሳል።

ቤን ቺልዌልን ለማስፈረም ዩናይትድ ጥረት ማድረግ አለበት

13 1

የሌስተር ሲቲውን የግራ ተከላካይ የሆነውን ቤን ቺልዌልን ለማስፈረም የማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ኦሊግነር ሶልሻየር መስዋት መክፈል እንዳለበት The Daily Mirror ዘግቧል።

ሌስተር ሲቲ ይፋ እንዳደረገው ለቤን ቺልዌል ዝውውር 60 ሚሊዮን ፓውንድ ይፈልጋል።

The Sun ይፋ እንዳደረገው ከሆነ ተጨዋቹን ለማስፈረም ከማንችስተር ዩናይትድ በተጨማሪ ቸልሲና ማንችስተር ሲቲ ከፍተኛ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሏል።

በአሁኑ ወቅት ከብራንደን ዊልያምስ ጋር በማንችስተር ዩናይትድ ቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ለመግባት ትግል ያደርግ የነበረው ሉክ ሾው የሌስተር ሲቲው ቤን ቺልዌል ወደ ክለቡ የሚመጣ ከሆነ የማንችስተር ዩናይትድን ክለብ ይለቅ ይሆን?ቤን ቺልዌልስ ማረፊያው የት ይሆን ? ቸልሲ፣ማንችስተር ሲቲ ወይስ ማንችስተር ዩናይትድ ወደፊት በሂደት የምናየው ይሆናል።

ዛላታን ኢብራሞቪች  በኤሲ ሚላን እርግጠኛ አይደለም

14 1

ዛላታን ኢብራሞቪች  በኤሲ ሚላን  ስለ ወደ ፊት ሁኔታው እርግጠኛ አለመሆኑን ገልጿል።

የ38 አመቱ ዛላታን ኢብራሞቪች  ከአሜሪካው ክለብ ከኤልኤ ጋላክሲ ወደ ሴሪ«ሀ» ው ክለብ ኤሲሚላን የተዛወረው ባለፈው ታህሣሥ ወር ላይ ነበር።ወደ ክለብ ሲዘዋወር የነበረው ስምምነት እስከ ውድድሩ ማብቂያ ድረስ እንደሆነና በተጨማሪነት ውሉን እስከ ጎርጎሮሳውያኑ 2021 ድረስ ሊያራዝም እንደሚችል ተገልጾ ነበር።

«ለቡድኑ ውጤት ለማምጣት መጫወቴን በቡድኑ ውስጥ እቀጥላለሁ»በማለት ለSky in Italy ገልጿል።

«ለቀጣዩ አመት ?እስቲ እናያለን።አሁን ውሌ ሊጠናቀቅ ሦስት አመት ነው የቀረኝ።እስካሁን ማንም ያናገረኝ የለም።በሚላን ውስጥ ስላለኝ ስለወደፊቱ ሁኔታ የማውቀው ነገር የለም።መጫወቴን ግን እቀጥላለሁ።ምርጥ ሆኜ ለመጨረስ ነው ፍላጎቴ።ከዛ በኋላ የሚሆነውን እናያለን» በማለት አስተያየቱን አጠቃሏል።

ማካኔ ሻልካን ይለቃል፤ ሊቨርፑልና ቸልሲ ማራፊያው ነው 

15 1

አማካይ ተጨዋቹ ዌስቶን ማካኔ ሻልካን በቅርቡ በሚከፈተው የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ላይ ክለቡን እንደሚለቅ ታውቋል።ሊቨርፑልና ቸልሲ የተጨዋቹ ማራፊያ  እንደሚሆን ከወዲሁ ተገልጿል።

በጎርጎሮሳውያኑ 2016 ከጀርመኑ ሻልካ ጋር በ20 ሚሊዮን ፓውንድ የተቀላቀለው አሜሪካዊው ተጨዋች በአጠቃላይ 91 ጨዋታዎችን አድርጓል።

የ21 አመቱ ተጨዋች ለአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን 19 ጨዋታዎችን አድርጓል።

 

 

ሀቨርቴዝ ወደ ቸልሲ የሚዛወረው ሻምፕዮንስ ሊግ ካለፈ ብቻ ነው

የበርካታ ክለቦችን ቀልብ የሳበው ካኢ ሀቨርቴዝ ወደ ቸልሲ የሚዛወረው በቀጣዩ የውድድር ዘመን በሻምፕዮንስ ሊግ ቡድኑ ካለፈ ብቻ ነው በማለት  Bild ገልጿል።

የካኢ ሀቨርቴዝ ፈላጊ የሆነው ቸልሲ ከባየር ሌቨርኩዘን የማስፈረም ፍላጎት አለው።ይሁንና ክለቡ ባየር ሌቨርኩዘን ለተጨዋቹ ዝውውር ባቀረበው በ90 ሚሊዮን ፓውንድ የማስፈረም ፍላጎት ግን የለውም።

ሀቨርቴዝ የጀርመኑን ክለብ ባየር ሌቨርኩዘንን የመልቀቅ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው ተገልጿል።

የ21 አመቱ ተጨዋች በጀርመኑ ክለብ የሁለት አመት ውል ይቀረዋል።

ሌቨርኩዘን በቀጣዩ

የውድድር ዘመን ከሻምፕዮንስ ሊግ ተሳታፊነት ውጪ መሆኑ ይታወሳል።

 

ሊቨርፑል ኩሊባሊንአይፈልግም 

16 1

ሊቨርፑል የመሐል ተከላካይ የሆነውን የናፖሊውን ካሊዲዮን ኩሊባሊን ማስፈረም እንደማይፈልገው Sky Sports ገልጿል።በሌላ በኩል ሌላው የመሐል ተከላካይ ዴጃን ሎቨራን  አንፊልድን ለቋል።

በርካታ ዘገባዎች ጀርገን ክሎፕ በቀዳሚነት የሚፈልጉት ተጨዋች እንደሆነና ለማስፈረም አሰልጣኙ ከያዛቸው ስም ዝርዝር ውስጥ ይገኝ ነበር ።

ነገር ግን የሊቨርፑል ክለብ ባለው ፖሊሲ የ29 አመት ለሆነ ተጨዋች ከ60 ሚሊዮን ፓውንድ መክፈል ስለማይችል ይህን ፍላጎቱን መተዉ ታውቋል።

ኩሉባሊ ዘንድሮ ባሳየው ድንቅ ብቃት የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦችን ቀልብ ስቧል።

ማንችስተር ሲቲ ፣ማንችስተር ዩናይትድና ፓሪስ ሴንት ዠርመን የተጨዋቹ ፈላጊ ክለቦች ናቸው።

የናፖሊው ክለብ ፕሬዝዳንት የኩሊባሊ የዝውውር ዋጋ 60 ሚሊዮን ፓውንድ ሳይሆን 90 ሚሊዮን ፓውንድ እንደሆነ ገልጸዋል።

ሊቨርፑል አራት የመሐል ተከላካዮች አሉት ሎቨራን፣ቨርጅል ቫን ዳይክ፣ጆኤል ማቲፔና ጆ ጎሜዝ ናቸው።ሎቨራን አራተኛው ተመራጭ ተጨዋች ነው።

በጎርጎሮሳውያኑ 2020 የካቲት ወር ከዋትፎርድ ጋር በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ላይ ተጫውቶ 3ለ0 በተሸነፈበት ጨዋታ ብቻ ነው የተሰለፈው።

የ31 አመቱ ክሮሺያዊው ተጨዋች በቀጣዩ ሳምንት ክለቡን ይልቃል ተብሏል።የአንድ አመት ውል ብቻ ነው የቀረው።ስለዚህ በእሱ ቦታ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ሌላ ተጨዋች ያስፈልገዋል።ኩሉባሊ ግን አይደለም።

✅  ማንችስተር ዩናይትድ ጉንዶዚን ያስፈርም ይሆን?

17 1

ማንችስተር ዩናይትድ ማቲዮ ጉንዶዚን ፥ከአርሴናል የማስፈረም ፍላጎት ያለው መሆኑን ፥ የፈረንሣዩ ተነባቢ L’Equipe ይፋ አድርጓል።

የቡድኑ አስተዳዳር ወደ ሜዳ እንዳይገባ ወስኖበታል።ምክንያቱ ደግሞ ቡድኑ በብራይተን በተሸነፈበት ወቅት ፥ ባሳየው ያልተገባ ፀባይ ምክንያት ነው።

ከዛ በኋላ ያሉ ጨዋታዎችን ከቡድኑ አባላት ውጪ እንዲሆን ተደርጎ ነበር።

Daily Mail እንደዘገበው አሰልጣኙ ማይክል አርቴታ ፥ተጨዋቹ ከፈፀመው አሳዛኝ ድርጊት ባሻገር ፤ በልምምድ ቦታ ላይ ፥ከተጨዋቹ ጋር መግባባት ባለመቻሉ ፥ተጨዋቹን የመሸጥ ፍላጎት እንዳለው ይፋ ማድረጉን ጋዜጣው መዘገቡ ይታወሳል።

ባየር ሙኒክ ቤሊንግሀምን የማስፈረም ፍላጎት የለውም

18

የጀርመኑ ሻምፕዮን ባየር ሙኒክ የበርሚንገሀሙን የ16 አመቱን ጁዴ ቤሊንግሀምን የማስፈረም ፍላጎት እንደሌለው The Sun ገልጿል።

በዚህ የውድድር ዘመን በሻምፕዮንሺፑ ላይ ፥ድንቅ ብቃቱን በማሳየት ማንችስተር ዩናይትድና ቦሩሺያ ዶርቱሙንድን ለመሳብ በቅቷል።አሁንም ሁለቱ ክለቦች ተጨዋቹን የማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው።

አማካይ ተጨዋቹ በዚህ የውድድር ዘመን ፥ለሰማያውያኖቹ 34 ጨዋታ አድርጎ፥ አራት ግብ ሲያስቆጥር ፥ሁለት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አቀብሏል።

ከማንችስተር ዩናይትድ በተሻለ  መልኩ ፥ ቦሩሺያ ዶርቱሙንድ ተጨዋቹን ያስፈርማል ተብሎ ይጠበቃል።

ቸልሲ ጎሜዝን ይፈልጋል

19

የማንችስተር ዩናይትዱ አንጄሎ ጎሜዝ በክለቡ ውስጥ የመቀጠል ፍላጎት ስለሌለው ክለቡ እንዲለቅ ተፈቅዶለታል።

The Independent እንደገለፀው ቸልሲ ይህን ወጣት ተጨዋች የማስፈረም ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።

ኦሊግነር ሶልሻየር እንደገለፀው ጎሜዝ ውሉን የማደስ ፍላጎት ስለሌለው  ከረቡዕ ሰኔ 24 ቀን ጀምሮ ኦልትራፎርድን ለቋል በማለት ገልጿል።

 

 

ጁቭ አቦሚያንግን

    አይፈልግም 

ጁቭንቱስ ፔየሪ ኤሜሪክ ኦቦሚያንግን  እንደሚፈልገው ሲገለጽ መቆየቱ ይታወሳል።

Bleacher Report እንደዘገበው ከሆነ ደግሞ ፤ጁቭንቱስ ፔየሪ ኤሜሪክ ኦቦሚያንግን እንደማይፈልገው ይፋ አድርጓል።

የአርሴናሉ አጥቂ በአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች ፤ የሚፈልግ ቢሆንም  የቢያንኮነሪው

ክለብ ፤ ከኦቦሚያንግን ይልቅ የናፖሊውን አጥቂ አርካዲዩዝ ሚልክን  ማስፈረም ክለቡ ይፈልጋል ሲል ዘግቧል።

✅  ሲቲ ለሳኜ ውል ማፍረሻ ገንዘብ አይቀነስም

20

ማንችስተር ሲቲ  ሌሮይ ሳኜ  አዲስ ውል እንዲፈርም ያቀረበለትን ጥያቄ ባለመቀበሉ በዚህ የዝውውር መስኮት ክለቡን እንደሚለቅ ሲገለጽ መቆየቱ ይታወሳል።

ሳኜ ክለቡን መልቀቅ የሚፈልገው በባየር ሙኒክ ውስጥ ቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ለመግባት በመፈለጉ ነው።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በዚህ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ወይንም ደግሞ በቀጣዩ አመት ውሉን ሲያጠናቅቅ ሊለቅ እንደሚችል ገልጾ ነበር።

Daily Telegraph እንደዘገበው የ24 አመቱ ጀርመናዊው ኢንተርናሽናል ሌሮይ ሳኜ በኢታድ ስታዲዮም የሚያቆየውን አዲስ ተጨማሪ ውል እንዲፈርም ክለቡ ያቀረበለትን ጥያቄ በመንተራስ ፔፕ ጋርዲዮላ በዚህ የዝውውር መስኮት ከክለቦች ጋር በሚደረገው የውል ማፍረሻ ድርድር የሚወሰን ይሆናል ብሏል።

ባየር ሙኒክ ተጨዋቹን በጥብቅ የሚፈልገው ቢሆንም ማንችስተር ስቲ በአነስተኛ ዋጋ የመሸጥ ፍላጎት የለውም።በመሆኑም ሌሮይ ሳኜ በዚህ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ወደ ባየር ሙኒክ ካልተዘዋወረ በቀጣዩ አመት በጋ ላይ ወደ ባየር ሚኒክ የሚዘዋወር ይሆናል።

ሶልሻየር ለዋን ቢሳካ ያለውን አድናቆት ገልፀ

21 1

ኦሊግነር ሶልሻየር ዋን ቢሳካን ያስፈረመው ክሪስታል ፓላስ ከማንችስተር ሲቲ ጋር በነበረው ጨዋታ ባሳየው ብቃት እንደ ነበር ገልጿል።

በዚህም 50 ሚሊዮን ፓውንድ በመክፈል ያለፈው አመት ላይ ነበር በሰኔ ወር ተጨዋቹን ያስፈረመው።

ኖርዌጂያኑ አሰልጣኝ «እሱ የተለየ ተከላካይ ነው። የተመለከትኩት ባለፈው የውድድር ዘመን ላይ ነበር።ከሁለት ጨዋታዎች በላይ ተመልክቼዋለሁ።

በተለይም ከማንችስተር ሲቲው ሳኜ ጋር የነበረው ሁኔታ ዋው በጣም ድንቅ ነበር እሱን ለማለፍ አስቸጋሪ ነበር » በማለት ለተጨዋቹ ያለውን አድናቆት በመግለጽ  ለቡድኑ ማስፈረሙን ገልጿል።

✅  ቫሌንሺያ ኬፓን ይፈልጋል

22 2

ቫሌንሺያ የዓለማችን ውድ በረኛ የሆነውን የቸልሲውን ኬፓ አሪዛላባላጋን ፤ ለሁለት አመት በውሰት ወይንም በግዥ የማስፈረም ፍላጎት እንዳለው Daily Mail ገልጿል።

ጋዜጣው የሰማያውያኖቹ ክለብ ያለፈው አመት ፤የአውሮፓ ሻምፕዮንስ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ የደረሰውን የአያክሱን በረኛ ፤አንድሪ ኦናናን የማስፈረም ፍላጎት ስላለው ኬፓ አሪዛላባላጋ ክለቡን የመልቀቅ ፍላጎት አለው።

ቲያጎ ወደ ፕሪምየር ሊግ የመዛወር ፍላጎት አለው

ቲያጎ አልካንትራን በባየር ሙኒክ አዲስ ውል የመፈረም ፍላጎት ስሌለው የክለቡን ጓደኞቹን ተሰናብቶ ለቋል።ትኩረቱ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ላይ የመጫወት ፍላጎት ነው ያለው መሆኑን The Sun ዘግቧል።

የ29 አመቱን ተጨዋች ሊቨርፑል ይፈልገዋል።እሱ በመጨረሻ የኳስ ዘመኑ ላይ ቶፕ ክለብ ገብቶ መጫወት ይሻል።

 

መሲ ያበቃል ወይስ ይቀጥላል

የባርሴሎና ስፖርት ክለብ ፕሬዝዳንት መሲ ያበቃል ወይስ ይቀጥላል በርቶሚዎ ስለ ሊዮናል መሲ በሰጡት አስተያየት በቀጣዩ የዝውውር መስኮት ሊዮናል መሲ በባርሴናል ያለው ውል ያበቃል ወይስ ይቀጥላል?

በርቶሚዎ ስለተጨዋቹ በሰጡት አስተያየት «አንድ ክለብ ውስጥ የእግር ኳስ ታሪካቸውን የሚቋጩ ወይንም በክለባችን ውስጥ ሕይወታቸውን ከሚደመድሙ ተጨዋቾች መካከል ሊዮናል አንድሬስ መሲ ይሆናል»በማለት ሰጥተዋል።

ከልጅነቱ ጀምሮ ባርሴሎና ነው ያደገው አሁን ደግሞ ክለቡን የሚያገለግለው መሲ በዚሁ ክለብ እንደሚያበቃ ነው የተናገሩት።

መሲን ከሮናልዶ ጋር ነው የሚያነፃፅሩት ሮናልዶ ደግሞ ከሊዝበን ተነስቶ ማንችስተር ዩናይትድ ፤ሪያል ማድሪድ ፣ጁቭንቱስ ስኬታማ ጊዜ እያሳለፈ ነው የሚገኘው።

መሲ ክለብ አለመቀያየሩ የምንግዜም ምርጥ የሚለውን ክብርና ስም ለሮናልዶ የሚሰጡ ወገኖች አሉ።የበርቶሚዎ አስተያየት «መሲ የኳስ ሕይወት በዛው የሚያበቃ ከሆነ ሮናልዶ በተለያዩ ክለቦች እንደመፈተኑ በተለያዩ ሊጎች የመፈተኑና ስኬታማነቱ በማየታችን መጠን መሲ ለሮናልዶ ይህን ክብር እንሰጣለን

ፔሌ ማራዶና የዓለማችን ምንግዜም ምርጡ ተጨዋች የሚባለው የዓለም ዋንጫን ሦስት ጊዜ በማሸነፉ

ሊዮናል መሲ በተቃራኒው ከብሔራዊ ቡድን ጋር ጥሩ ሪኮርድ የለውም የዓለም ዋንጫ ቢያነሳ ሊዮናል መሲ የምንግዜም ምርጡ የዓለማችን ተጨዋች ይባል ነበር።

በባርሴሎና በማጣው ውጤት ከሁሉም የተሻለ ተጨዋች ነው።ምናልባት መሲ በባርሴሎና የሚቋጭ ከሆነ በባርሴሎና ታሪክ የምንግዜም ምርጡ ተጨዋች ይሆናል።ስታዲዮሞች በእሱ ስም ሊጠሩ ይችላሉ።አሁን 32 አመቱ በቅርቡ በወጡ መረጃዎች ምናልባት ለተጨማሪ 2 አመት እንደሚፈርም ተነግሮ ነበር።

«አሁን ደግሞ በርቶሚዎ መሲ እስከ እግር ኳስ ሕይወቱ መጨረሻ ድረስ ከእኛ ጋር ይቆያል የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።

መሲ በመጀመሪያ ላይ ማንችስተር ሲቲ እንደሚገባ ነበር የተገለፀው መሲ ከባርሴሎና ጋር የምክለያይ ከሆነ ወደ አርጀንቲና ኒው ኦልድ ቦይስ ሊመለስ ይችላል።አሁን ግን በርቶሚዎ በተናገሩት መረጃ መሰረት መሲ የእግር ኳስ ሕይወቱን በባርሴሎና የሚቋጭ ከሆነ በባርሴሎና ቡድን ውስጥ ታሪካዊ ሆኖ  ልናየው እንችላለን።

 

አሌክሳንደር አርኖልድ ከተከላካይ አማካይ ቦታ

የሊቨርፑሉ አሌክሳንደር አርኖልድ በአማካይ ቦታ ስፍራ ላይ የመጫወት አቅም እንዳለው የቀድሞ የሊቨርፑል አማካይ ተጨዋችና አሰልጣኝ

ግራም ሱናስ ገለጹ።

 

አርኖልድ በተከላካይ መስመር የሚጫወት ነው።በጣም ጥሩ ተጨዋች ነው።ተፈጥሯዊ ይበልጥ ስኬታማ መሆን የሚችለው የመስመር ተጨዋች ነው።አሁንም የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግና የሻምፕዮንስ ሊግ በ21 አመቱ በማሸነፍ ስኬታማ ነው የዓለማችን ምርጥ የቀኝ መስመር ተከላካይ ነው።እንደዛ በግሉ ስኬታማ ይበልጥ የመስመር ተጨዋች ወደ ፊት ተገፍቶ ቢጫወት የሚል አስተያየት በዘንድሮው ውድድር ከተከላካይ መስመር ተነስቶ በአጠቃላይ 12 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ማቀበል ችሏል።በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ቀዳሚው የማንችስተር ሲቲው ኬቨን ዴ ብራይን ነው።17 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አቀብሏል።አሌክሳንደር አሮንልድ በሊቨርፑል ቡድን ውስጥ በታዳጊ ቡድን ነው የጀመረው የአማካይ ቦታ ነው  የጀመረው።ኳስ ሲቆጠጠር ፤ክሮስ ሲያደርግ ቅጣት ሲመታ ኮርና ሲያወጣ ነው።7 ቁጥር ወይንም የመስመር አማካይ ከዚህ የተሻለ ብዙ ጎሎችን ሊያስቆጥርና ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ሊያቀብል ይችላል። የቀድሞ የሊቨርፑል ተጨዋች ግራም ሱናስ የፊት መስመር ቢጫወት ብቃቱን ያሳያል

 

 

 

 

 

 

 

ማሪዮ ማንዙኪች ከኳታሩ ክለብ አልዱሀሊ ጋር ተለያይቷል

በጋራ ስምምነት ነው የተለያየው ጥር ላይ ነበር ወደ ኳታር ያመራው።ከዛ በኋላ በኳታር ሊግ ለአልዱሀሊ በመሰለፍ ጥሩ ጊዜ አላሳለፍም።

በጁቭንቱስ፣በአትሌቲኮ ማድሪድ፣በባየር ሙኒክ ጥሩ ጊዜ አሳልፏል።በአውሮፓ ሻምፕዮንስ ለጁቭንቱስ ምርጥ ግብ አስቆጥሯል።

ማንችስተር ዩናይትድ

 

….,,,,,,,,,,,,,,, …

 

 

 

 

➡️ዣቭ ሄርናንዴዝ በአልሳድ ፈረመ፤ኪኬ ሲቲየን  ይቀጥላሉ

23

በስፔን የላሊጋ ውድድር ላይ፤

በጥሩ አቋም ላይ የማይገኘው

ባርሴሎናን ፤ ከአሰልጣኝ ኪኬ ሲቲየን ይረከባል የተባለው ዣቭ ሄርናንዴዝ ፤ በአልሳድ ለተጨማሪ አንድ አመት ፈረመ።

የቀድሞ የባርሴሎና ተጨዋች ዣቭ ሄርናንዴዝ በተጨዋችነት ዘመኑ ፤ በባርሴሎና ክለብ የእግር ኳስ ጨዋታውን እንደአጠናቀቀ ፤ ለኳታሩ አልሳድ ክለብ ሲጫወት ቆይቶ ነው ታኬታውን በራሱ ፍቃድ የሰቀለው።ከዛም በአሰልጣኝነት ዘመኑ ጥሩ ጊዜ በማሳለፍ ቡድኑን  በመያዝ የአንድ ዋንጫ ባለቤት እንዲሆን አስችሏል።

ኪኬ ሲቲየን ኤርኔስቶ ቫልቭርዲን ከመተካታቸው በፊትም ቢሆን፤ በቀዳሚነት ባርሴሎናን ይረከባል ተብሎ ነበር ።ዣቭ ሄርናንዴዝ ግን «በአሁኑ ወቅት ባርሴሎናን የመረከቡ አቅሙ የለኝም »በማለት ጥያቄውን በወቅቱ ውድቅ አድርጎ ነበር።

ዣቭ ሄርናንዴዝ ሰሞኑን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጭ«ቀጣዩ አላማዬ ባርሴሎናን ማሰልጠን ነው።የምወስዳቸው

የአሰልጣኞች ስልጠናዎች ፤ ልምዴን ማካበትና ማዳበር ላይ ነው ትኩረት የማደርገው።

ቀጣዩ  አለማዬ ባርሴሎናን መረከብ ነው »ብሏል።ዣቭ ሄርናንዴዝ የአንድ አመቱን ውል እንዳጠናቀቀ ባርሴሎናን ይረከባል ተብሏል።

የማንችስተር ሲቲው ፔፕ ጋርዲዮላ ፤ በጎርጎሮሳውያኑ 2008 ቡድኑን ተረክቦ

በተደጋጋሚ  ውጤታ

ማ ካደረገው በኋላ ፤ ቡድኑ አሰልጣኝ ቢቀያይርም ጥሩ ብቃትና የቀድሞ የአጨዋወት ስልቱንም ማሳየት አልቻሉም።

ይሁንና አሠልጣኙ  ኪኬ ሲቲየን  ዘንድሮ ባርሴሎና የላሊጋ ሻምፕዮና እንኳን ባይሆን ፤ በቡድኑ ውስጥ እንደ ሚቀጥሉ ፤ የክለቡ ፕሬዝዳንት በርቶሚዎ ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንቱ እንደገለጹት

«ኪኬ ሲቲየን ተስፋ ሰጪ የሆነ ነገሮችን በቡድናቸው ላይ ስላየን ፤ሙሉ ለሙሉ የቦርዱ ድጋፍ እንደማይለያቸው እገልጻለሁ » በማለት በቡድኑ ውስጥ አሠልጣኙ እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።ይህ ማለት ዣቭ  በአልሳድ ክለብ ውስጥ

ያለውን የአንድ አመት ውል እስከሚያጠናቅቅ ድረስ ቡድኑን ይዘው ይቀጥላሉ ማለት ነው።

በአሁኑ ወቅት ባርሴሎና ከሪያል ማድሪድ በአራት ነጥብ ዝቅ ብሎ የሁለተኛ ስፍራ ላይ ነው የሚገኘው።

➡️«መሲ የኳስ ሕይወቱ በባርሴሎና ያበቃል»

በርቶሚዎ

24የባርሴሎና ስፖርት ክለብ ፕሬዝዳንት በርቶሚዎ ፤ ሰሞኑን እንደገለጹት ፥ «ሊዮናል መሲ የኳስ ሕይወቱ በባርሴሎና ያበቃል»ሲሉ ገልጸዋል።

በቀጣዩ የዝውውር መስኮት ሲከፈት ፥ የቡድኑ አምበል ሊዮናል መሲ በባርሴሎና ውስጥ ያለው ቆይታ ያበቃል?  ወይስ ይቀጥላል ?የሚለው ጥያቄ አብዛኛው የስፖርት ተንተኞችን ሲያወያይ ቆይቷል።

ከዚህ በፊት ሲገለፅ የነበረው ፤ መሲ ከባርሴሎና ጋር የሚለያይ ከሆነ ወደ ማንችስተር ሲቲ ያመራል ተብሎ ነበር።የቀድሞ የባርሳ ሌጀንድ ፔፕ ጋርዲዮላ ግን ውሸት እንደሆነና ተጨዋቹ በባርሴሎና እንዲቀጥል እንደሚፈልግ ተናግሮ ነበር።በኋላ ላይ ደግሞ ፥ ወደ አርጀንቲናው ኒው ኦልድ ቦይስ ፥ሊመለስ ይችላል ሲባል ነበር።

በቅርቡ ደግሞ የሁለት አመት ተጨማሪ ውል በባርሴሎና እንደሚፈርም ተገልጿል።

ሰሞኑን ደግሞ የባርሴሎና ስፖርት ክለብ ፕሬዝዳንት በርቶሚዎ እንደገለጹት  «አንድ ክለብ ውስጥ የእግር ኳስ ታሪካቸውን የሚቋጩ ፤ ወይንም በክለባችን ውስጥ ሕይወታቸውን ከሚደመድሙ ተጨዋቾች መካከል ሊዮናል አንድሬስ መሲ ይሆናል»በማለት ሰጥተዋል።

«መሲ የኳስ ሕይወት በዛው በባርሴሎና የሚያበቃ ይሆናል» ብለዋል።

ምናልባት የ32 አመቱ ሊዮናል መሲ በባርሴሎና የኳስ ሕይወቱን የሚቋጭ ከሆነ በባርሴሎና ታሪክ የምንግዜም ምርጡ ተጨዋች ይሆናል።ስታዲዮሞች በእሱ ስም ሊጠሩ ይችላሉ።ሐውልትም በክለቡ ውስጥ ሊሰራለት ይችላል።

➡️ባየር ሙኒክ ለሦስተኛው ዋንጫ ይዘጋጃል

 

በዋናው ቡንድስሊጋ የዋንጫ ባለቤት የሆነው ባየር ሙኒክ ቅዳሜ ዕለትም የጀርመን እግር ኳስ ዋንጫን ዲ ኤፍ ፔ ዋንጫን አሸንፎ ወስዷል።

በርሊን ውስጥ በተከናወነው ባየር ሙኒክ ባየር ሌቨርኩዘንን 4ለ2 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ፤ለባየር ሌቨርኩዘን ተጠብቆ የነበረው ካይ ኸቨርትዝ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ በተጨማሪው አምስተኛው ደቂቃ ላይ ለቡድኑ ሁለተኛውን ግብ አስቆጥሯል።

የመጀመሪያውን ግብ በ73ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ስፌን ቤንደር ነው።ከጨዋታው በኋላ በሰጠው አስተያየት ቡድኑ ደካማ መሆኑን ገልጿል።

«በመጀመሪያው 45 ደቂቃ ደካማ ነው።ጉጉ አልነበረንም ፈዘን ነበር።የጨዋታው ስልትም አልመጥነንም በሁለተኛው አጋማሽ ያገኘነውን እድል አልተጠቀምንም ብንጠቀምም የተሻለ ውጤት እናገኝ ነበር።

ባየሮች ዛሬ የተሻሉ ነበሩ።

ለባየር ሞኒክ ተከላካዩ ዴቪድ አላባ በ16 ኛው ፣ሰርጌ ናብሬ በ24 ኛው እንዲሁም በ59 እና በ89ነኛው ደቂቃ ግብ አዳኙ ሮበርት ሌቫንዶቨስኪ አራት ግቦችን አስቆጥረዋል።

የባየር ሙኒክና የጀርመን ብሔራዊ ቡድን በረኛ ማኑኤል ኑኤር ሁለተኛ ዋንጫ ስላሸነፉ የተሰማውን ሲገልጹ « ከነዚህ በርካታ ጨዋታዎች በኋላ በጨዋታ ብልጫ በማሸነፋችን ደስታም እፎይታም ተሰምቶናል።ያ ለእኛ በጣም የተለየ ነው።በአቋማችን ኩራት ይሰመናል» ብሏል።

ባየር ሙኒክን ከነበረበት ችግር አውጥተው ለጣምራ ድል ያበቁት አሰልጣኝ አንሲ ፍሊክ በበኩላቸው ስለ ቡድናቸው ስኬት እንዲ ብለዋል። «በጣም ተደስቻለው።በቡድኔ አባላትም ሆነ በስልጣና ጓዶቼ

ተሰምቶኛል።በደንብ የተቀናጀን ይመስለኛል።

በስተመጨረሻ ስኬታማ አስፈላጊው የሆነው ጥሩ የሆነ ስሜት በዛ ላይ ደስ ብሎን ነው የተጫወትነው።ዛሬ መከነውን የምንፈልገው ቀጣዩ እርምጃችን ነው።»ሲሉ ተናግረዋል።

ባየር ሙኒክ ለቀጣዩ

ሻምፕዮንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ከእንግሊዙ ቸልሲ ጋር ይጫወታል።

በመጀመሪያው ዙር ተጨዋቹ 3ለ0 አሸንፎ ወጥቷል።የ55 አመቱ  አሰልጣኝ አንሲ ፍሊክ ከሁለት ሳምንት እረፍት በኋላ ሲመለሱ ቡድናቸውን በሻምፕዮንስ ሊግ ውጤታማ ማድረግ ቀጣዩ ግባቸው መሆኑን ተናግረዋል።ዘንድሮ በኮሮና ተዋህሲ ስርጭት ምክንያት ከዚህ በፊት የነበረው።የደርሶ መልስ ግጥሚያ ፤ሩብና ግማሽ ፍጻሜ የሻምፕዮንስ ሊግ ውድድር አይኖርም።የሩብና ግማሽ ፍጻሜ  ጥሎ ማለፍ ይሆናል።ውድድሮቹ ልክ የዛሬ ወር ይጀምራሉ።ሩብ ፍጻሜ፣ ግማሽ ፍጻሜ ና የዋንጫ ጨዋታዎች ፖርቹጋል ሊዛበን ከተማ ውስጥ ተገልጧል። በሻምፕዮንስ ሊግ ወደ ሩብ ፍጻሜ ማለፋቸውን ካረጋገጡት ቡድኖች ባሻገር አራት ግጥሚያዎች ይቀራሉ።ሩብ ፍጻሜ ለማለፍ ባየር ሙኒክ ከቸልሲ፤ ማንችስተር ሲቲ ከሪያል ማድሪድ ፤ጁቭንቱስ ከ ኦሎምፒክ ሊዮን፤ባርሴሎና ከናፖሊ ጋር የመልስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።እነዚህ ጨዋታዎች በፖርቹጋል ሊዛበን ከተማ ይሁን በሌላ እስካሁን የተገለፀ የለም።ከዚህ በፊት ሩብ ፍጻሜ ማለፋቸውን ያረጋገጡት አራት ቡድኖች ላይዝብሽ፤በርጋሞ፤ፓሪስ ሴንት ዠርመንና አትሌቲኮ ማድሪድን ይቀላቀላሉ።

የሻምፕዮንስ ሊግ የፍጻሜ ግጥሚያ ለነሐሴ 17 ቀጠሮ ተይዟል።

 

ኢትዮጵያ መቼ ይሆን ከዲሽ ቤት የምትላቀቀው?

መርሻ ደምሴ(ከወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ)

(ደራሲ፣ጋዜጠኛና ማህብራዊ ሃያሲ)

 

 

በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ የሚገኙ የተለያዩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ኮሮናን በማስመልከት የተለያዩ አዝናኝ ፕሮግራሞቻቸውን በነፃ በማስተላለፍ ይገኛሉ።ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ዛሬም የስፖርት አፍቃሪው እንደ ዛሬ አሥራ አምስትና ሃያ አመቱ ሁሉ ዛሬም ከዲሽ ቤት  መላቀቅ አልቻለም።ያውም በኮሮና ወቅት!

በተለይ እንግሊዝን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራቶች በካርድ የሚሠሩ አዝናኝ የፊልም፣

የሙዚቃና የእግር ኳስ እንዲሁም  ሌሎች የስፖርትናየኢንተርቴንመንት ቻናሎቻቸውን በነፃ በመልቀቅ ላይ ናቸው።

ከዚህ ሌላ መንግሥታዊ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች አዳዲስ የመዝናኛ ቻናሎችን በተጨማሪ በመክፈት  በኮሮና ምክንያት የሚከሰቱየጭንቀት ነገሮችን በማስወገድ ጉሉ ድርሻ አለው።ከዚህ ሌላ በቤት ውስጥ እንዲወሰኑ በማድረጉ በኩል ጠቀሜታው ነው።ይህ እንግዲህ በኢንተርኔት የሚታዩትን የLive Stream ተጠቃሚዎችን አይጨምርም።

ከሁለት አመት በፊት የጄቲቪ (JTV) ባለቤት ጆሲን በዓለም ላይ ተወዳጅ የሆኑ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን በቀጥታ ወይንም የመጀመሪያው 45 ደቂቃ እንደተጠናቀቀ ብናስተላልፍ ምን ይመስለሀል? ብዬው ጠይቄው

ነበር።እኔ ውጭ ካለኝ ልምድ (Experience)  አንፃር በመሞርከዝ ነበርይህን ጥያቄ ለጆሲ ያነሳሁት።ጆሲ ኮፒ ራይትን በመፍራት በወቅቱ ፍቃደኛ ሳይሆን ቀረ።ይህ ፍራቻ የሁሉም የግል ቴሌቪዥኖች ሊሆን ስለሚችል እኔም በጉዳዩ ላይ ብዙም ልገፋበት አልፈለኩም ነበር።በበኩሌ በመልሱ ደስተኛ ብቻ ሳይሆንመልሱ ለእኔ

አሳማኝ አይደለም።ምክንያቱም ሌሎች ሀገሮች እንዴት እንደሚሰሩ ስለማውቅ ብቻ አይደለም፤ መልስ የማላገኝባቸው ብዙ የማነሳቸው ጥያቄዎች ስለነበሩኝ ነው።

ለመሆኑ እኛ ሀገር ኮፒ ራይት ለእግር ኳስ ብቻ ነው የሚሰራው?የውጭ የሰው መጽሐፍ የፊቱን ከቨር አስካን አድርገው እስከነነፍሱ የሚታተምበት ሀገር አይደል? ጥቀስ ከተባልኩ አንድ ሁለት ብዬ በርካታ መጽሐፍቶችን መጥቀስ እችላለው።ለአብነት ያህል «የአና ማስታወሻ» የሚለውን የእንግሊዘኛውን መጽሐፍ መጥቀስ በቂ ነው።

ሌላው ቀርቶ የኢትዮጵያና የውጭ ዘፋኞች ክሊፖች፣

ፊልሞች፣ዜናዎች  ወዘተ.ዳውንሎድ እየተደረገ ለግለሰቦች ከ6 በር እስከ 15 ብር መሸጥ አይደለም፤በኢትዮጵያ ቴሌቪዥኖች እየተለቀቁ እያየን አይደለ? እናማ  ለእነዚኛዎቹ ኮፒ ራይት አይሰራም?

የእኔ አመለካከት በኢንተርኔት ብቻ ከሚተላለፍ ኅብረተሰቡ ብዙ የኢንተርኔት አክሰስ ስለሌለው

በኢትዮጵያ ቴሌቪዥኖች ቢተላለፍ መልካም ነው በሚል ሁኔታ ነው።( በነገራችን በተለይ የግሉ ቴሌቪዥን Live Stream እንጂ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ናቸው ማለት ይከብዳል።ምክንያቱም እንደ መንግስት  ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ማሟላት የሚገባቸውን ነገሮች ስለማያሟሉ ነው ።

ይህን ሀሳብ ያቀረብኩት ያለምክንያት አይደለም ።ውጭ እያለው በድህረ ገፅ(website) ላይና በLive Stream ላይ ጥናቶች  አድረግ ስለነበር በወቅቱ ወሰን ቲቪ(wosentv)

በሚለው የLive Stream ቻናሎቼ ላይ የቀጥታ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ፣የስፔን የላሊጋ፣የጣሊያን ሴሪ«ሀ»፣

የጀርመን ቡንድስሊጋ ወዘተ.

ስርጭቶችን፤ሀይላቶችን፣

የተቀረፁ የቆዩ ጨዋታዎችን።

ዳውንሎድ በማድረግ  በቀጥታ በእኔ በሆነው wosentv የLive Stream  ቻናሎቼ ላይ እያስተላለፍኩ በዓለም ላይ እንዲታይ አደርግ ነበር።

ገንዘብ ባላገኝበትም በዓለም ላይ በኢንተርኔት በርካታ ተጠቃሚዎችን ፍላጎት ለማርካት ችዬ ነበር።አሁንም እነዚህ  የኳስ ፣የዜናና የፊልም ቻናሎች ኢንተርኔት ያላችሁ ጎግል Google በ wosentv ሰርች በማድረግ የፈለጋችሁትን የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ፣የስፔን የላሊጋ፣የጀርመን ቡንድስሊጋ ወዘተ.ጨዋታን በቀጥታ የሚተላለፉ ስለሆነ መመልከት ትችላላችሁ።እነዚህ የሚተላለፉት ኳሶች ልክ  እኔ ከዚህ በፊት የራሴን የLive Stream እንደማስተላልፈው አይነት እነሱም በቀጥታ ነው የሚያስተላልፉት።ይህን ልምዴን በመጠቀም ፤ኳስ ለሚወደው ወገኔ፤አንድ ነገር ለማድረግ ፈልጌ ነበር።ይሁንና እንዳሰብኩት ግንአልተሳካም ።

አብዛኛው ህብረተሰባችን በድህነት ላይ ያለ በመሆኑ ኢንተርኔት የማግኘት አቅሙ አነስተኛ ስለሆነ፤ይህን ወደ ሰርቨር ለማዞር ከኢትዮ ቴሌኮምኒኬሽን ጋር ብነጋገርም ፤እነሱም በድህረ ገጻቸው ላይ  ፤ከዚህ በፊት እንዳሉኝ ድህረ ገፆች ፤ለኢንተርኔት ተጠቃሚዎች የሚያገለግል እንድሰራ ብቻ ነው የጠየቁኝ።በዚሁ በኩል አልተስማማውም።ምክንያቱም ያለኝ ድህረ ገፅ ለዚህ በቂ ስለሆነ ብቻ ነው።

ሰርቨሩን ለማግኘት ሞክሬ ከብሮዳክስቲንግ ኤጄንሲ ካልተፈቀደልኝ በስተቀር መሥራት እንደማልችል ስለተገለጸልኝ። በውድ የገዛዋቸውና ቀረጥ ከፍያ ወደ ሀገር ቤት ያስገባዋቸውን፤

የLive Stream ዕቃዎችን  ሌላው ቀርቶ በገዛሁበት ዋጋ በሀገራችን ውስጥ የግል ቴሌቪዥኖች ፤ ገዝተው እንዲጠቀሙ ፤ልሸጥላቸው ፈልጌ ዕውቀቱ በአብዛኛው ስላልነበራቸው ፍቃደኛ አልሆኑም።

የግል ቴሌቪዥኖች  ኢትዮጵያ ውስጥ እየሰሩ ያሉት ፤

ዩቲዩብ ላይ ቪዲዮዎች እንደሚጫነው ሁሉ ፤ኤዲት አድርገው በተሰጣቸው ሰርቨር ላይ መልቀቅ ብቻ ነው።ስለሆነም ሀገራችን

ወደ ከፍተኛ ደረጃ የዓለም ኅብረተሰብ የደረሰበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ያላቸው የኢንተርኔት ኮኔክሽን ደካማ መሆን ፤አሉታዊ ተፅ ፅኖ እንዳደረገባቸው ፤አንዳንድ ካጠናዋቸው የግል  ቴሌቪዥኝ ጣቢያዎች መረዳት ችያለው።

በዚህም መሰረት የLive Stream  ዕቃዎቹንሊገዙኝ ፍቃደኛ ስላልሆኑ፤ዕቃዎቹን

መልሼ ወደ አመጣሁበት ሀገር በፖስታ ቤት ልኬዋለው።

ውጭ  እንግዲህ ያላችሁ የኳስ አፍቃሪዎች wosentv  የቀጥታ ጨዋታዎች አሁንም ለኢንተርኔት ተጠቃሚዎች በነፃ እየተላለፈ ይገኛል።ከዚህም አልፎ የተለያዩ የመንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ፤የእንግሊዝ መንግሥትን ጨምሮ በርካታ ተመልካች ያለው የፕሪምየር ሊግጨዋታዎች  በነፃ  እየተላለፉ በመሆኑ ድህረ ገጾቼን መጎብኘት ትችላላችሁ።

ወደ ኢትዮጵያ ስንመለስ

ትልቁ  የቴሌቪዥኖች መሳቢያ ቆርቆሮዎች(ትልቁ ዲሽ )ወይም ሌባው ዲሽ ያላቸው የእንግሊዝ፣የስፔንና የጀርመን ቡንድስሊጋ ወዘተ. ጨዋታዎችን ኢትዮጵያ ውስጥ በቀጥታ በአንድ የዩክሬን ቻናል ላይ በነፃ እያዩ ይገኛሉ።

የእኛ ሀገር የቴሌቪዥን ጣቢያዎች  ጨዋታዎችን በራሳቸው ቻናሎች በነፃ ለምን አያስተላልፉም ነው የእኔ ጥያቄ !ምክንያቱም ወቅቱ ኮሮና በመሆኑ ያለ ተመልካች ውድድር ቢካሄድም በነፃ በቴሌቪዥን እየታየ  ባለበት ዓለም።እንደ ጥንቱ ነፍሳቸውን ይማረውና እነ ደምሴ ዳምጤ፣ይንበርበሩ ምትኬና ጎርፍነህ ይመር ብሔራዊ ቡድናችን የተጫወተ ይመስል እንደሚያስተላልፉት ሁሉ፤በሬዲዮ እግር ኳስን ኢትዮጵያ ውስጥ ማስተላለፍ የተለመደ ሆኗል።

የመንግሥት ሚዲያዎች ያሰለቹን  ወሬ ቢኖር ይኸው መከረኛ የኮሮና ወሬ ነው።

«በኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽኝ በስፋት እየተሰራጫ ነው።ኅብረተሰቡ መዘናጋትና ጥንቃቄ አለማድረግ ይታይበታል።በየሆቴሉ፣በየግሮሰሪው፣በየኳስ ማሳያ ወዘተ. ሰዉ እየተሰባሰበ እያየ ነው የሚገኘው…ፖሊስ እርምጃ ይውሰድ» በማለት የአዞ እንባ የሚያነቡ፤መፍትኤ ከመጠቆም ይልቅ መንግሥት እርምጃ እንዲወስድ ሰውን ማስበርገግና ዝባዝንኬ ወሪያቸውን እንዲደመጥላቸው ሲፈልጉ ይታያሉ።በርግጥ መንግሥት ከአራት በላይ አትሰባሰቡ የሚል አዋጅ አውጥቷል።ሰዉ እንዳይሰባሰብ፣በቤቱ እንዲወሰን ምን የተደረገለት ነገር አለ?

እዚህ ላይ የጋዜጠኞቻችን የብቃት ጉዳይ አጠያያቂ መሆኑን መዘንጋት የለብንም።

ሥነጽሑፍም ሆነ ጋዜጠኝነት በቀዳሚነት ተሰጦ ይጠይቃል።ለዚህም ነው ኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጨምሮ በሙያው ያለፉ ወገኖች

እስካሁን ድረስ የድምፅ ቅላጼ በኤሌክትሮኒስ ሚዲያ ላይ

በቀዳሚነት ከማለፊያ መመዘኛ ነጥቦች አንዱ በማድረግ

በዋናነት እየሰሩበት የሚገኘው።

በእርግጥ በሙያው ዙሪያ

ትምህርት የምንወስደው

ያለንን ተሰጦ ለማሳደግ ነው።ሌላ ምክንያት ምንም

የለውም።

በጋዜጠኝነት ተሰጦ ከሌለው ፒኤችዲ(ዶክትሬት )ካለው ይልቅ ለእኔ ተሰጦ ያለው የአራተኛ ክፍል እንደነበረው ጳውሎስ

ኞኞን የመሰለ ሰው በሙያው ላይ ባሰማራ ይበልጥብኛል።ቢኤ ዲግሪ፣አድቫንስ ዲፕሎማ ወዘተ. አለኝ ብሎ የሚኮፈስ

የሀገራችን ጋዜጠኞች ሙያው ውስጥ ገብተው  ማጠፊያ ሲያጥራቸው ነው የሚታየው።

የሚሰቡ ፕሮግራም ይዘው ቀርበው በድምጻቸውና በመልካቸው የተነሳ አድማጮቻቸውን ወይንም ተመልካቾቻቸውን መሳብ ያልቻሉ በርካቶች ናቸው።አብዛኛው ሰውም ሌላ ቻናል ለመቀየር የሚገደደውም  በዚህ የተነሳ ነው።

አንዳንድ የመንግስትና የግል የስፖርተኛ ጋዜጠኞች እንግሊዘኛ ቋንቋ ስላወቁ ወይንም  ጥሩ ምላስ ስላላቸውና በወያኔ አቃጣሪነታቸው የተነሳ ዕድሉን ስላገኙ ሌላው ዕድል የሌለውን የሚያንቋሽሹ፤ ኳስ በአግባቡ እንኳን መምታት የማይችሉ የሌላውን ስፖርተኛ ሞራል የሚነኩ፤ውጭ ሀገር ሄዶ

አፈር ድሜ  ግጦ ተምሮ የመጣውን ከእሱ ከመማር

ይልቅ አራሳቸውን ኮፍሰው የተማሩትን እያጣጣሉ የሚኖሩ ተንታኝ ተብዬዎችም አሉላችሁ።

ኮተቤ የውሸት ዲፕሎማና ዲግሪ  ይዘው  ስለ ሳይንሳዊ

አሰለጣጠንብቻ ቢያወሩ የማይደክማቸው፤ብዙ የሚያወሩ ኳስ ሲሰጧቸው መሳቂያ የሚሆኑም በርካታ ናቸው።

አንዳንድ ጋዜጠኞች ውጭ ሲወጡ

ደግሞ በሥራ ከማሳለፍ ይልቅ ወሬ የሚወዱ ፤የግል ጋዜጠኞችን እያንቋሸሹ በአንፃሩሠርቶ ከማሳየት ይልቅ

በጉራ ከተማ  ለከተማ  ከመዞር ባሻገር በጋዜጠኞች አውቶብስ ከመሄድ ይልቅ ከጀግኖች አትሌቶቻችን ጋርአብሮ በመሄድ ጉራ የሚነፉ፤ሲከለከሉ ለስድብና ለዱላ የሚጋበዙ፤

በድርጊታቸው  አንገት የሚያስደፋ ሀሳዛኝ ድርጊት ሲፈፅሙም አስተውያለሁ።

ሌላው ቀርቶ አይደለም በእንግሊዘኛ በአማርኛ የተሰጣቸውን ፎርም መሙላት የማይችሉ ፤ውድድርሮችን መመልከት የቻሉት ለወያኔ ታማኝ በመሆናቸው ብቻ ነበር።

በጣም የሚያሳዝነው የአየር

መንገዶችን  ፓሲንግን ለማለፍ የሚሰጠውን ፎርም ሞልተው ማለፍ ሲሳናቸው የተመለከትኳቸው የመንግስት ጋዜጠኞች በርካታ ናቸው።

«አንድ ሰው በዱላ ሲቀጠቀጥ ቆመህ ተመልከት »የሚል አመለካከት ስለሌለኝ ነው ይህን ለማለት የፈለኩት ።

ይህ እንግዲህ በስፖርት ጋዜጠኞቻችን ላይ ያየሁትን ነው።በሌላው ጋዜጠኛ ላይም ይሄ ሁኔታ ይታያል የሚል እምነት አለኝ።ፈረንጅ እንደ ኢትዮጵያ በወሬ በማቃጠር፤

በማጎብደድ ስለማያምኑ ውጭ መሄድ የምትፈልጉ ማንኛውም ጋዜጠኛ ፤ድጋፍ ምናምን የማያስፈልግበት ጊዜ ይኖራል።

በሥራ ላይ ካተኮራችሁ ካለናንተ ተማኝና ተሰሚ  ሰው በእነሱ ዘንድ አይኖርም።

ስለዚህ በዚህ በኩል ከልምድ አንፃር ነው  ምክሬን

ለመለገስ የሞከርኩት ።

አለዛ ግን ጋዜጠኛው ምላስ ስላለው ብቻ የባጥ የቆጡን እያወራ ቢኮፈስ በፈረንጆቹ ዘንድ እነሱ የሥራ ሰው ስለሆኑ እየሳቁ “ተወው አውደልድሎ ይሂድ!” ነው የሚሉት።

የትኛውም አካል ለፕሪንቲንግ ሚዲያ አክብሮት አላቸው።አብዛኛዎቹ የሚዲያ ኦፊሰሮቻቸው ፤በፕሪንቲንግ ሚዲያ ላይ ብዙ ውጣውረዶችን ያለፉ በመሆኑ ፤ አቅማቸው በቻለው መንገድ የፕሪንቲንግ ሚዲያ ጋዜጠኞችን መርዳትና ማስተማር ይፈልጋሉ።በዚህ ላይ ኤሌክትሮኒስ ሚዲያዎች በዓለም ላይ ተዋቂ የተባሉት ሁሉ ጥራት ባለው ሁኔታ ያዘጋጁትን ኢቨንታቸውንስለሚያስተላልፉላቸው ብዙም ትኩረት እንደማይሰጡት በአንድ ወቅት በዚህ ዙሪያ ሰፊ ክርክር ተነስቶ ማብራሪያ

እንደተሰጠበት አስታውሳለው።

እኛ ሀገር ግን የግሉን ወደ ጎን በመተው  በተለየያዩ ስም የተሰገሰጉ የወያኔ ታማኝ ጋዜጠኞችን መላክ የተለመደ ሆኗል።

ዛሬ ኅብረተሰባችን ስለ ኮሮና ወረርሽኝ ያለው ግንዛቤ ከኢትዮጵያ ጋዜጠኞች በተሻለ መልኩ ነው ያለው። ለዚህም ነው

የራሱን ጥንቃቄ እያደረገ  ያለጭንቀት እየተንቀሳቀሰ  የሚገኘው።የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ግን ከህፃናቶች በባሰ መልኩ እራሳቸው

ጭንቀት ላይ ሆ ነው ሌላውንም ጭንቀት ላይ ይከታል።

ከኮቪድ-19  ውጭ  ኢትዮጵያ ውስጥ የተመጣጠነ ምግብ ካለማግኘት፤በመኪና አደጋ፤

በሰው እጅ፤በድንገተኛ አደጋ ፤በሌላ  በሽታ፤ጤነኛ የሆነው ሰው በሐኪሞች ስእተት ወዘተ. በትንሹ በየቀኑ 100 ሰው አይሞትም ?

ሌላው ቀርቶ ጋዜጠኞቻችን

ቃለ መጠይቅ ከዚህ በፊት ስለኮቪድ -19 ያደረጉት ዶክተር ምን ተናግሮ እንደነበር እንኳን የሚያስታውሱት ነገር የለም ።ሰዉን ማስተማርና መረጃ መስጠት ብቻ ሳይሆን እኛም ከምናነበውና ቃለመጠይቅ ከምናደርገው ሰዉ ጋር መማር እንደሚኖርብን ለማስገንዘብ እወዳለሁ።

በተለይም ጋዜጠኞች ከሙስና የጸዱ መሆን አለባቸው።ብዙውን ጊዜ ጊዜጠኞቻችን በሙስና

ይታማሉ።ይሄ ተብሎ ተብሎ ያለቀ ቢሆንም አሁን ግን ሙስናው ዓይን አውጥቶ መሄድ ጀምሯል።በፊት በአየር ላይ በሚለቀቁ ፕሮግራሞች፤ቃለ መጠይቆች፤የዘፈን ክሊፖች ወዘተ.እያንቆለጳጰሱና እላይ ከፍ ከፍ እያደረጉ በተደጋጋሚ መልቀቅ በፊትም ነበር አሁንም አለ።

አዲስ ሆኖ ብቅ ያለው ነገር አየር ላይ የሚለቀቁ ማስታወቂያዎች ላይ የሚደረገው ሙስና ሌላው ነው።እዛው መሥሪያ ቤት ካለ ግለሰብ ወይንም የማስታወቂያው ሰሪ ጋር በፐርሰንቴጅ በመደራደር አየር ላይ በተደጋጋሚ ከሚለቀቅላቸው ማስታወቂያ በተጨማሪ የማስታወቂያው ደንበኛውን እንደ ጣኦት ማምለክ ተጀምሯል።

ማስታወቂያ መሥራት እራሱ አንዱ የሙስና ምንጭ ነው።

የኳስ ቻናሎችን ማስታወቂያ እየሰሩ ።በአንፃሩ በዓለም ላይ አይደለም አሁን ኮቪድ -19  ከመከሰቱ በፊትም ደሀ ሀገሮች ኳስ ጨዋታዎችን በቀጥታ ሲያስተላልፉ ማንም የሚናገራቸው አካል አልነበረም ።ለምሳሌ ጎረቤት ሀገር ግብፅ፣ካሜሮን፣ጋና፣

ሴኔጋል ወዘተ.ራሱን የቻለ የስፖርት ቻናል አላቸው።ቀጥታ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ፣የስፔን ላሊጋ፣የጣሊያን ሴሪ«ሀ»፤የጀርመንቡንድስሊጋ፣የፈረንሣይ ሊግ 1  እንዲሁም የራሳቸውን የእግር ኳስ ውድድሮችን በሁለትና በሦስት ቻናሎች ያሳያሉ።

ከእነሱ የሚጠበቀው በቀጥታ የሚሰራጨውን ማስታወቂያ እንዳለ መልቀቅ ብቻ ነው።

ወይ ከእነሱ አልተማርን፤ ወይ እንስራ ሲባል አየሰሩ፤ወይ እናስተምር ስንል የመማር ፍላጎት የላቸው።እራሳቸውን

ይኮፍሱና በባዶ ቤት አካኪ ዘራፍ ማለት ብቻ ነው።ይህ ብቻ አይደለም የራሳችንን ኳስ ለማስተላለፍ እንኳን ክለቦቻችን በነፃ እንዲተላለፍላቸው ከመፍቀድ ይልቅ ገንዘብ ላይ ያተኩራሉ።

ለእግር ኳሳችን አለማደግ እንደዋንኛ መንስኤ አድርገው የሚያቀርቡት የአስተዳደር ችግር፣የአሰለጣጠን ችግር፣

የፋይናንስ ችግር የማይባል ነገር የለም።ቅድሚያ ስፖርተኛ የመሆን ፍላጎት ያለው ልጅ ማግኘት ያስፈልጋል።ከዚህ ሌላ እንደ ቀደምት ስፖርተኞች

የማሊያና የሀገር ፍቅር ያለው ስፖርተኛ ማፍራት ይቻላል።

የአሁኖቹ ስፖርተኞች እንደ በፊቱ የማሊያና የሀገር ፍቅር ስሜት የሌላቸው ናቸው።

እንዲያውም በእናታቸው ማዕፀን ውስጥ እያሉ ገንዘብ የለመዱ በመሆናቸው ፤ከሀገርና ከማሊያ ፍቅር ይልቅ ሁሉም ትኩረት የሚያደረጉት ገንዘብ ላይ ብቻ ሆኗል።

የውጭ ጨዋታዎችን መመልከት ለትልልቅ ተጨዋቾች ብቻ ሳይሆን ነገ ትልቅ ቦታ የሚደርሱ ተጨዋቾችን ለማግኘት ከፍተኛ አስተዋጾ አለው።

ሌላው ቀርቶ እነ መሲንና እነ ሮናልዶን ማግኘት ባንችልም በአትሌቲክሱ  ምሩዕ ይፈጠር ኃይሌ ገብረስላሴን፤ ኃይሌ ገብረስላሴንቀነኒሳ በቀለን ተካ፤ቀነኒሳ በቀለን  ዛሬ የሚተካው ማን ነው? በሴቶችም ደራርቱ፣ጌጤና ወርቅነሽን ጡርነሽና መሰረት ተኳቸው።

እነሱን ደግሞ አልማዝ አያና ተካች አልማዝ አያናን ምን ይተካት?እግር ኳሱም እንደዛው ነው።የእነ መንግሥቱ ወርቁ ጊዜ የሚባለውን ትተን ።እኛ ያየናቸው ተካበ ዘውዴ፣ለማ ክብረት፣ሙልጌታ ከበደ፣

ሙልጌታ ወልደየስ፣

ገብረመድህን ኃይሌ፣ዳኛቸው ደምሴ፣ካሳዬ አራጌ፣አሸናፊ በጋሻው ፣አሸናፊ ሲሳይ፣

ዮርዳኖስ አባይ፣ ሚሊዮን በጋሻው፣ፋሲል ተካልኝና ሁለቱ አንዋሮችን  እያልን አንዱ ሌላውን እየተኩ በርካታ ድንቅ ተጨዋቾችን ሀገራችን አፍርታ ነበር ።ዛሬ ላይ ግን ሆነን እነማንን እንጥራ ???

ኳስ እንደመጥፎ መታየት የለበትም።እንዲያውም ስፖርተኛ የሆነ ሰው ከሱስ የራቀ ሆኖ ዲሲፕሊንድ ሆኖ ነው የሚያደገው።

ዛሬ በየቤተሰቡ ያሉ በርካታ የድሀ ልጆችን በየሰፈሩ የሚያደርጉትን የኳስ

እንቅስቃሴ ለማሳደግ ቴሌቪዥኖችን መመልከት አለባቸው ።በቴሌቪዥን ለማስተላለፍ ኮፒ ራይት ከፈራችሁ? የተላለፈውን ኳስ የመጀመሪያውን 45 ደቂቃ ልክ እንዳለቀ ፤ጨዋታው በተለያዩ ድህረ ገፅ ወይንም ዩቲዩብ ላይ ስለሚለቀቅ ፤ዳውንሎድ አድርጋችሁ በቴሌቪዥን ጣቢያዎቻችሁ ልቀቁ።ጊዜው የወሬ ሳይሆን የሥራ ነው። ሌላው ቀርቶ በዚህ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ሁሉም የቀጥታ ስርጭት በዓለም ላይ በነፃ እየለቀቁ ባለበት በአሁኑ ወቅት፤ለዚህ ምስጊን ሕዝብ ጭንቀትና ወሬን ከማስተላለፍ ይልቅ እናንተም እባካችሁ በነፃ  ጨዋታዎችን ልቀቁ።

የኢትዮጵያ መንግሥት በኮቪድ-19 ምክንያት ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ ውስጥ እየገባ ሕዝቡን እየረዳ ነው።እናንተ ደግሞ ከአፍሪካ ያላለፈ በዓለም ላይ እውቅና ለሌለው ለአንድ የአፍሪካ ቻናል ገቢ ለማስታወቂያ ብላችሁ ማስታወቂያ ቢከለክለኝስ?

በማለት ከመተቸት ይልቅ አብሮ ማሟሟቅን ትወዳላችሁ።

እነሱ አፍሪካን አላግባብ እየጋጡ  ከኢትዮጵያ ላይ ከምንበላው …  ለማስታወቂያ እንካችሁ እያሏችሁ ነው።አሁን ሰዉ ባኗል።ሌባውን ዲሽ እቤቱ ሰቅሎ ሌሎች ሀገሮች በነፃ የሚያስተላልፉትን ወመመልከት  ላይ ይገኛል።

እናንተ ግን ገቢያ እንዳንገደል በሚል ሁኔታ

አብራችሁ እንደልማዳችሁ እያጨበጨባችሁ ቀጥሉ …አበቃው።ክብረት ይስጥልኝ።

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.