ወንጀልን በትክክለኛ በስሙ ሳንጠራ ፍትሕ አይገኝም፤ በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ነው – ያሬድ ኃይለማርያም

18ethiopia promo superJumbo v2
Jawar Mohammed mission is inciting Hate and Genocide

ሰሞኑን አርቲስት እና የመብት ተሟጋች ታማኝ በየነ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ በኦሮሚያ ክልል በተደጋጋሚ ስለተፈጸሙት በዘር ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች ውይይት አድርገን ነበር። በዛ አጭር ውይይት ላይ የአርቲስት አጫሉን ግድያ ተከትሎ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች የተፈጸፈው ጭፍጨፋ ዘር ተኮር (Genocide) ነው በሚል አስረግጠን ተናግረን ነበር። ለዛም ዝርዝር ማስረጃዎችን ከአርባ ጉጉ፣ በደኖ እና ወተር ጭፍጨፋዎች አንስቶ እስከ ትላንቱ ድረስ የተፈጸሙትን ጥቃቶች በምን ምክንያት ዘር ተኮር ወንጀል ሊፈረጁ እንደሚችሉ ለማስረዳት ሞክረናል።

ይህን ውይይት ተከትሎ አስገራሚ ሃሳቦች እና ወቀሳዎች ከተለያዩ አቅጣጫዎች ሲሰነዘሩብን አድምጫለሁ። ገሚሱ ስለወንጀሎቹ ስያሜ፣ መስፈርቶቹ እና የሕግ ትርጓሚ ግንዛቤ ካለመኖር ይመስላል። ቀሪዎቹ ወቃሾች ደግሞ አስመሳይነት እና ፖለቲካዊ መሽኮርመም ብለው ይሻላል። የተወሰኑ ሰዎች ደግሞ ነገሮችን አዛብቶ መረዳት ይመስላል። በዛው ልክ አይናቸውን በጨው አጥበው የክህደት (denial) መከራከሪያ የሚያነሱም አይቻለሁ። ለማንኛውም እኔና ታማኝ በየነ ከሌሎች ሁለት እንግዶች ጋይ ያደረግነውን አጭር ውይይት ላልሰማችሁትም ሆነ ሰምታችሁ ነገሩ ብዥታ ለፈጠረባችሁ ሰዎች በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የተፈጸሙት ጭፍጨፋዎች ዘር ተኮር መሆናቸውን ባጭሩ ላስረዳ።

ከዛ በፊት ትንሽ ስለ ዘር ተኮር ጥቃት ወይም Genocide የጋራ ግንዛቤ እንዲኖረን ትንሽ ልግለጽ። ይህ የዘር ተኮር ጭፍጨፋ አለም አቀፍ ወንጀል ነው። እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በDecember 9, 1948, የተባበሩት መንግስታት አጽድቆ ባወጣው the Convention on the Prevention and Punishment of tGhe Crime of Genocide የስምምነት ሰነድ በዘር ላይ ያነጣጠረው ጥቃት አለም አቀፍ ወንጀል ተደርጎ ተደንግጓል። በዚህ ሰነድ ላይም በዘር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ምን ማለት እንደሆነ በግልጽ ተቀምጧል። በዚህ ሰነድ አንቀጽ ሁለት ላይ በዘር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ወይም genocide ማለት አንድን በብሔሩ፣ በኃይማኖቱ፣ በዘሩ፣ በቀለሙ ወይም በሌላ በማንነቱ ተለይቶ የታወቀን ሕዝብ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ለማጥፋት በማሰብ በዛ ማህበረሰብ አባላት ላይ ግድያ፣ ከፍተኛ የአካል ማጉደል፣ ወይም የአዕምሮ ጉዳት ማድረስ፣ ሆን ብሎ በዛ በተለየ ሕዝብ ሕይወት ላይ አደጋ ሊያደርሱ የሚችሉ ተግባራትን በመፈጸም፣ ያ ህዝብ እንዳይዋለድ እና ቁጥሩ እንዳይጨምር ታስቦ ወልደትን የሚገድብ እርምጃ ሲፈጸም እና የዛን ማህበረሰብ ሕጻናት ልጆች በጉልበት በመንጠቅ ለሌላ ማህበረሰብ አሳልፎ መስጠትን እንደሚጨምር ይገልጻል። ከእኔ የግርድፍ ትርጓሜ ባለፈ እንግሊዘኛውን ማንበብ ለምትፈልጉ እነሆ፤

Genocide means any of the following acts committed with intent to destroy, in whole or in part, a national, ethnical, racial or religious group, as such:
(a) Killing members of the group;
(b) Causing serious bodily or mental harm to members of the group;
(c) Deliberately inflicting on the group conditions of life calculated to bring about its physical destruction in whole or in part;
(d) Imposing measures intended to prevent births within the group;
(e) Forcibly transferring children of the group to another group.
በዚሁ ድንጋጌ አንቀጽ ፫ ላይም በዘር ማጥፋት ወንጀል የሚያስጠይቁት ተግባራትን ይዘረዝራል። እነሱም ከላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወይም genocide ድርጊት የፈጸመ፣ ወንጀሉ እንዲፈጸም የዶለተ (Conspiracy to commit genocide)፣ በቀጥታ እና በአደባባይ በዘር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንዲፈጸም ያነሳሳ እና ቅስቀሳ ያደረገ (Direct and public incitement to commit genocide); የዘር ማጥፋቱን ወንጀል ለመፈጸም ሙከራ ያደረገ (Attempt to commit genocide); የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲፈጸም በማናቸውም መልኩ ተሳትፎ ያደረገ (Complicity in genocide).
እነዚህ መነሻ ሃሳቦች ይዘን እስኪ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሩቁን ጊዜ ትተን ትላንት ከአጫሉ ግድያ ማግስት የተፈጸሙትን ጥቃቶች እንፈትሽ።
፩ኛ/ በመጀመሪያ ደረጃ ሁሉም ሰው እንዲረዳው የሚያስፈልገው የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲባል ብሔርን ወይም ጎሳን ብቻ መሰረት ያደረገ አይደልም። በኃይማኖት ወይም በሌሎች የልዩነት መሰረቶችም ላይ ያተኮረ ሊሆን ይችላል። የግድ የአንድ ብሔረሰብ ሰዎች ላይ ብቻ ያነጣጠረ መሆን የለበትም። ከዚህ አንጻር ሰሞኑን በኦሮሚያ የተፈጸመው ጥቃት በአንዳንድ አካባቢዎች በአማራ ብሔረሰብ ተወላጆች ላይ ብቻ አነጣጥሯል። በሌላ አካባቢዎች ኦሮሞ ባልሆኑ የክልሉ ነዋሪዎች (አማራ፣ ትግሬ፣ ጉራጌ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ሌሎችም) ላይ አነጣጥሯል። በተወሰኑ ስፍራዎች ደግሞ ክርስቲያን (የኦሮሞ ክርቲያኖችን ጨምሮ) በሆኑ ሰዎች ላይ አነጣጥሯል። ስለዚህ ጥቃቱ የብሔር እና የኃይማኖት ይዘት ነበረው።
፪ኛ/ የአጥቂዎቹ ማንነት በተመለከተ የሚነሳ ክርክር አለ። በዘር ማጥፋት ወንጀል ላይ የሚታየው የተጠቂው ዘር እና የአጥቂው ሃሳብ እንጂ የአጥቂው ማንነት አይደለም። ጥቃቱን የሚፈጽመው ማንም ሊሆን ይችላል። የአንድ ዘር ወይም ብሔር ወይም ኃይማኖት አባል ወይም ከተለያየ ዘር እና ኃይማኖት የተወጣጡ ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ። ዋናው ነገር አጥቂው ጥቃቱን ሲፈጽም ዋና መነሻ ሃሳቡ እና አላማው ምንድን ነው የሚለው ነው። የአጥቂው ቡድን ማንነቱ ሳይሆን ሃሳቡ ነው የሚታየው። በተጨማሪም የዘር እልቂት ጥቃት ተፈጽሟል ሲባል የግድ አንድ ዘር በሙሉ ተነስቶ ሌላን ዘር አጠፋ ማለት አይደለም። ይህንን ብዙ ሰዎች ካለማወቅም ይሁን ሆን ብለው ሲያምታቱት ይስተዋላል። በኦሮሚያ ክልል በተደጋጋሚ በተፈጸሙትም ሆነ አሁን በተፈጸመው ጥቃት ተሳታፊዎቹ፣ አቀነባባሪዎቹ እና ዋናውን ድርጊት የፈጸሙት ሰዎች የኦሮሞ አክራሪ ብሔረተኞች መሆናቸው ግልጽ እና የሚያከራክር አይደለም። እነዚህ ሰዎች የተደራጁ ቡድኖች ናቸው እንጂ የኦሮሞን ሕዝብ ወይም አንድን ኃይማኖት የሚወክሉ ሰዎች አይደሉም። ስለዚህ ድርጊቱ የዘር ጥቃት ለመባል የአጥቂ ወገኖች የአንድ ብሔር አባላት ሰዎች በጠቅላላ ተሰባስበው የፈጸሙት ነው ወይም አንድ ብሔር ነው ሌላውን ያጠቃው ለማለት አይደለም ወይም እንዲህ ያለ ትርጓሜ አይሰጥም። ዋናው ነገር ፈጻሚዎቹ አንድን ዘር ወይም ኃይማንት ለማጥቃት አስበው የተደራጁ ቡድኖች መሆናቸው ነው። ይሄ ደግሞ በአደባባይ ጭምር ነፍጠኛን ግደሉ፣ ክልሉን ከሌሎች ብሄሮች አጽዱ፣ ክርስቲያኖችን አስወግዱ የሚሉ ቅስቀሳዎች በአደባባይ፣ በመገናኛ ብዙሃን እና በማህበራዊ ድህረ ገጾች ይካሄዱ እንደነበር እና ድርጊቱም በዚሁ አግባብ መፈጸሙ ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው። በመንግስትም ተደጋግሞ ተገልጿል።
፫ኛ/ ሌላው በክልሉ ውስጥ የተፈጸመው ጭፍጨፋ ዘር ተኮር መሆኑን የሚያሳዩት ከቅድመ ዝግጅት አንስቶ ድርጊቱ በተፈጸመባቸው ወቅቶች የታዩና በበቂ ማስረጃ የሚደገጉ ተጨባጭ ኩነቶች ናቸው። እነዚህም፤
+ ክፍፍል እና ፈረጃ (classification and symbolization) አገሪቷ ውስጥ ለሰላሳ አመታት የቆየው የዘር ተኮር ፖለቲካ ሕዝቡን በማንነቱ እንዲከፋፈል አድርጎታል። በተጨማሪም በተለያዩ ሚዲያዎችም ሆነ በተደጋጋሚ በመንግስት አካላትም አንድን ማህበረሰብ ነፍጠኛ፣ መጤ፣ ወራሪ፣ ጡት ቆራጭ የሚሉ እና ሌሎች ስያሜዎችን እየሰጡ ጥላቻ በዛ ማህበረሰብ ላይ እንዲፈጠር ተደርጓል። ይህንን ኦቦ ለማ መገርሳ በአንድ መድረክ ንግግራቸው ላይ በደንብ አድርገው ከነስጋታቸው ገልጸውታል፤
+ ከሰውነት ተራ ማውጣት ወይም ማበደን (dehumanization)፤ ይህ ነገር በሁለት መልኩ ተፈጽሟል። አንደኛው ለታዳጊ ወጣቶች እና ተማሪዎች አንድን ማህበረሰብ እንደ ሰው እንዳይቆጥሩ እና ጭራቅ አድርገው እንዲስሉ ብዙ ሥራ ተሰርቷል። ነፍጠጫ የሚሉትን የአማራውን ሕዝብ በታሪክ አገሪቱን ካስተዳደሩ ገዢዎች ጋር በማቆራኘት እራፊ ልብስ እና ቁራጭ ዳቦ የጠረረበትን ድሃ የአማራ ገበሬ እንደ ሰው ሳይሆን እንደ በዝባዥ፣ ጡት ቆራጭ፣ መሬት ወራሪ፣ ዘራፊ እና አፈናቃይ አድርገው እንዲያስቡ በመንግስት ደረጃ በተዋቀሩ ሚዲያዎችና ሹማምንት ሳይቀር ብዙ ቅስቀሳ እና ጥላቻ ሲሰበክ ቆይቷል። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ እነዚህን በጥላቻ ያነጿቸውን ወጣቶች ሌላውን የህብረተሰብ ክፍል እንደ ጠላት አድርገው እንዲቆጥሩ እና የጭካኔ እርምጃ በሌሎች ላይ እንዲወስዱ ወደ አውሬነት ባህሪ ቀይረዋቸዋል። በዚህም ሳቢያ በዚሁ ሰሞን በእኛው ዘመን ወጣቶች ጡት ቆርጠዋል፣ ቆዳ ገፈዋል፣ ሰውነት ቆራርጠው ገድለዋል፣ ሙሉ ቤተሰብ አርደው ከነቤታቸው በእሳት አጋይተዋል።
+ ለጥቃት መደራጀት (organization)፤ ይህ የዘር ተኮር ጭፍጨፋ ለመፈጸም የተደራጀ ቅስቀሳ እና ዝግጅት ተካሂዷል። በዚህም ላይ የክልል የመንግስት አካላት፣ የታጠቁ አማጺያን እንደ ኦነግ ሽኔ አይነት፣ በቄሮ ስም የተደራጁ ወጣቶች፣ እንደ OMN ያሉ ሚዲያዎች እና ሌሎች አካላትም በተቀናጀ እና በተደራጀ መልኩ ተሳትፎ አድርገዋል። ለዚህም በመንግስት ከተገለጹት ማስረጃዎች ባለፈ እጅግ በርካታ መረጃዎች ተገኝተዋል።
+ ሌላው አብሮ መታየት ያለበት ፍሬ ጉዳይ ለሰላሳ አመት የተዘራው የዘር ተኮር ልዩነት ባለፉት ሁሉት እና ሦስት አመታት አፍጦ ወጥቶ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሳይቀር በግልጽ መነጣጠል እና መፈራረጅ (ethnic polarization) ሲካሄድ ቆይቷል። በአንዳንድ ቦታዎችም ዘር ተኮር ግጭቶች ከመከሰትም አልፎ ዘር ተኮር አፈናዎች ተካሂደዋል። የደንቢዶሎ ተማሪዎች አፈና ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው። ከዛም አልፎ ቀደም ሲል ከቡሬ ሆራ ዩንቨርሲቲ ከሁለት መቶ በላይ የአማራ ተማሪዎች በተለየ ሁኔታ ተነጥለው የተባረሩበት እና ባርዳር ሜዳ ላይ የፈሰሱበት ክስተት፣ በአማራ ክልልም ባሉ ዩንቨርሲቲዎች እንዲሁ የኦሮሞ ብሔር ተማሪዎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች መፈጸማቸው የዚህ ማሳያ ነው።
+ ይህ ዘር ተኮር ጥቃት ድንገት የፈነዳ ክስተት ሳይሆን ብዙ ዝግጅት የተደረገበት እና በአካባቢው ባሉ የመንግስት አካላትም ጭምር የተደገፈ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ። ባለሥልጣናቱ አንዳንድ ቦታ ቀጥተኛ ተሳታፊ ነበሩ። አንዳንድ ቦታዎች ደግሞ በዝምታ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል። ይህ አይነቱ ነገር በመንግስት አካላት መፈጸሙ አይገርምም። ምክንያቱም የክልሉ ምክትል ፕሬዚደንት አቶ ሽመልስም ሆኑ ሌሎች ባለስልጣናት በየመድረኩ ነፍጠኛን ሰብረናል ሲሉ ከታች ያለው ካድሬ እና ወጣቱ ነገሩን የሚረዳበት መንጋድ ምን ሊሆን እንደሚችል ግልጽ ነው። እነሱ ሰብረነዋል ያሉትን ነፍጠኛ በOMN እና በአንዳንድ የኦሮሞ አክራሪ ፖለቲከኞች ገና ያልተሰበረ ነፍጠኛ ከጎረቤትህ አለ ሲሉት ወጣቱ ያንን የተፈረጀ ሰው ሊሰብር፣ ሊያጠፋ እና ሊገድል ቢነሳ ምን ይደንቃል? ብዙ ወጣቶች በመንግስት ተሿሚዎች እና በሚከተሏቸው የፖለቲካ መሪዎች የተፈረጀን እና የተኮነን ሰው መግደል እና ንብረቱን ማቃጠል እንደ ተፈቀደና ትክክለኛ እርምጃ (legitimate action) አድርገው ቆጥረውታል።
+ የመጨረሻው ሃሳብ እውነታን መካድ ወይም አለመቀበል ወይም እውነታውን ላለማየት እና ላለመናገር እራስን ማታለል (denial) ነው። ይሄንን አይነት ነገር በመንግስት እካላት፣ በድርግት ፈጻሚዎቹ ወገን በቆሙ ሰዎች እና አብሮ ለመኖር፣ ለመቻላል፣ ቂም እና በቀልን ለማስቀረት እውነታውን ከመናገር መቆጠብ ወይም እንዳላዩ ሆኖ ማለፍ ወይም ወንጀሉን በሌላ ስም ብንጠራው ይሻላሉ በሚሉ ሰዎች የሚንጸባረቅ ሙግት ነው። አጥቂው ማን እንደሆነ ይታወቃል፣ የአጥቂው ቡድን አላማ (intention) ግልጽ እና በዘር ላይ ያነጣጠረ መሆኑ እራሱ አድራጊው ሳያፈር በአደባባይ ይናገራል፣ መሬት ላይ የተፈጸመውን ድርጊት በዘር ላይ ያነጣጠረ መሆኑ በበቂ ማስረጃ ይገለጻል፣ አንዳንድ ለህሊናቸው ያደሩ የመንግስት ተሿሚዎችም እውነታውን ይናገራሉ ነገር ግን ድርጊቱን እና ወንጀሉን የዘር ማጥፋት ብሎ መሰየም በአገሪቱ ፖለቲካ እና የወደፊት መስተጋብሮች ውስጥ የሚያሳድረውን ነገር ከወዲሁ በማስላት አይ ሌላ የዳሞ ስም እንስጠው የሚል እጅግ ደካማ የሆነ መሟገቻ ይቀርባል። ይሄ አይነቱ አካሄድ ኢትዮጵያን ከዘር ተኮር ጥቃት የሚታደጋቢ ቢሆን ኖሮ ከአርባ ጉጉ፣ ከበደኖ እና ከአርሲው ጭፍጨፋ በኋላ የተከሰቱት ተመሳሳይ ዘግናኝ ጭፍጨፋዎች ባልተፈጸሙ ነበር።
13
ሃሳቤን ለማጠቃለል ያህል አዎ ደግሜ ደጋግሜ እናገራለሁ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ እኩይ እና በብሔር ፖለቲካ በሰከሩ ጥቂት አክራሪ ቡድኖች በተቀነባበረ መልኩ አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ተደጋግሞ የዘር ተኮር ጭፍጨፋ ተፈጽሟል። ጭፍጨፋው የዘር ተኮር ነው ለመባል በሺዎች ወይም በሚሊዮን የሚቆጠር ሰው መታረድ የለበትም። ሕጉም ይህን እንደ መስፈርት አያስቀምጥም። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ባይታረዱም በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በማንነታቸው ምክንያት ከቂያቸው ተፈናቅለው እና ይሄ የእናንተ ክልል አይደለም ተብለው ተባረዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል። ለዚህም ከበቂ በላይ ማስረጃዎች አሉ።
10
መፍትሔ፤ መንግስት በዚህ ድርጊት ላይ የተሳተፉ ያላቸውን ሰዎች ለፍርድ የማቅረቡ ሥራ የሚበረታታ እና የሚደገፍ ነው፡፡ ይሁንና ይህ ድርጊት በየስድስት ወሩ እየተቀሰቀሰ የንጹሃን ዜጎች ደም በየሜዳው የሚፈስበት ክስተት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊባበቃ ይገባዋል። በመሆኑም ከችግሩ ስፋት፣ ጥልቀት እና ውስብስብነት አንጻር ይህ ዘር ላይ ያተኮረ ጥቃት ለአቃቤ ሕግ እና ለፖሊስ ምርመራ ብቻ የሚተው መሆን የለበትም። እነዚህ ጥቃቶች ትኩረት ሰጥቶ የሚያጠራ፣ የሚመረምር እና የመፍትሄ ሃሳብ የሚያመነጭ ገለልተኛ አጣሪ ኮሚሽን ሊቋቋም እና ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ከሚመሩት የሰብአዊ መብት ተቋም ጋር አብሮ በጋራ እንዲሰራ መደረግ አለበት። የችግሩ ምንጭ እና የአደጋውን መጠን በቅጡ አጥንቶ አጥፊዎቹንም ለፍርድ የማቅረቡ ሥራ ለይምሰል ሳይሆን በማያዳግም መልኩ ማስተማሪያም እንዲሆን ይረዳል።
11 1
ኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ጥቃት በስሙ ጠርተን እናውግዝ!

8 Comments

 1. በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት ክስ ለመመስረት ሁላችን መተባበር አለብን። ከኣዴነች አቢቤ ፍቶህ ይገኛል ብሎ መጠበቅ ሞኝነት ነው።

 2. አቶ ያሬድ
  ለሙያህ ታላቅ አክብሮት አለኝ:: በስም እንጥራው ከተባለ በአርሲ ባሌና ሻሸመኔ የተካሄደው የዘር ሳይሆን የሀይማኖታዊ ጭፍጨፋና የንብረት ማውደም ነው::የአርሲ ኦርቶዶክስ ሊቀጳጳስ በትክክል ገልፀውታል::ገዳዮች የሸዋን ክርስቲያን ኦሮሞዎችንም ጭምር ነው የፈጁት::ብሄራቸው ኦሮሞም ሆነውም ተገድለዋል ::ንብረታቸውም ወድሟል:: ይህን ያካሄዱት የጃዋር ፅንፈኛ መንጋዎች ናቸው:: ሁሉም ሰላማዊ ኦሮሞን አይጨምርም:: ለእኔ ትልቁ ችግር በኦሮሚያ ብልፅግና ውስጥ ተደብቀው ፀረ ኢትዮጵያዊነት የሚያራምዱ የጃዋር ቡድንን ማፅዳት ሀገርን ከማፍረስ አደጋ ይከላከላል::ጃዋርን ለፍርድ ማቅረብ ትልቅ እርምጃም ቢሆን ሰንሰለቱን መበጣጠስ ለወደፊት መረጋጋት ይረዳል ::

 3. አማር እና ኦርቶዶክስ ክርስትና ተከታዮች በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸውን እያጡ ነው፡፡ ማስረጃውን አይናችን ላይ እያየን ነው፡፡ ምስክር መጠየቅ አይስፈልገንም፡፡ ለጠ/ሚሩ ችግሩን መፍትሄ ለፈለግ እና እርምጃ ለመውሰድ መጅመርያ እውነታውን መቀበልና ለሕዝብ በትክክል መግልጽ አለበት፡፡ እንደዚሁ ሲደባብስ 3 ዓመት የበለጠ ጥፋት ላይ አድርሶናል አሁንም ማቆሚያ አይኖረውም፡፡ ኦሮሞ ዛፍ ላይ ሰው ዘቅዝቆ ሲሰቅል አሁንም በአጣና ላይ ሚስማር ተክሎ ሰላማዊውን ህዝብ ሰላም ሲነሳ አብይ ለተከሰቱት አሰቃቂ የአማራ እና ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ጭፍጨፋ እስከአሁን መፍትሔ ያለው ፕላስተር መለጠፍ ነው፡፡
  በአገር እኩልነት የሚያምን ክሆነ እዛው አስተዳደር ውስጥ የተቀመጡትን እና ሹማምንቱን ህዝብ በኦሮሞ ሲገድል ሰላሙን ሲያጣ ቁጭ ብለው ጥረሳቸውን መፋቅ ትተው ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት መተግብር አለባቸው፡፡ በጸጥታ ስምሪት ላይ የተሰማሩት በብሂር ላይ ያተኮረ ነው የሚመስለውም፡፡ ያለኦሮሞ መቀጠር ክልክል ነው እንዴ? ከውያኔ ዘር ፕለቲካ ይብቃን ብለን አልነበር እንዴ?
  አብይ የፖሊስ መዋቅሩን ሁሉንም ዚጋ እንዲወክል ማድረግ የግድ ይለዋል፡፡ ጠ/ሚሩ በእርግጥ በወያኔ ጸበል የተጠመቀ ስለሆነ ወያኔን በኦሮም መተካቱን እንደትልቅ ለውጥ ሊያየው ይችል ይሁናል፡፡ ለካ የዋኒ ፓሊስ አለማየትም ይናፍቃል።
  የዝር አተኩሮ ያለውን የመንግሥት ሥራ በተልይ ጎልቶ የሚታየው በፓሊስ አመራርና ቅጥረኝ ሥራ ውስጥ ተስግስገው የህዝብን እሮሮ የሚያበዙትን፣ መሰሪ የዝር ፕለቲካቸውን የሚፈትፍቱትትን መንጥሮ ማውጣት አለበት፡፡
  የጠ/ሚሩ ዋንኛ ተግባሩ ግን “የኦሮማይ ሃገር” እንመሰርታለን እያሉ ኦሮምያ መጀመርያ እያሉ ኢትዮጵያዊነትን ለሚያጥላሉ ለሚያንቋሽሹ የአገራችንን ታሪክ እያንቋሽሹ ኦነግ እና መሰል ድርጅቶችን ንቃተ ህሊና ለሊላቸው ወጣት ኦሮሞዎች የሚሰጡትን ጭፍን የቅዥት “ኦሮሚያ” የሚባል ህልም ግንባታ ማስተማርም ሲያስፈልግም እርምጃ መውሰድ የግድ ይላቸዋል፡፡ በአጠቃላይ ጠ/ሚሩ ኦሮሞ ሕብረተስብ ላይ ብዙ ሥራ ይጠበቅባቸዋል፡፡

 4. It amazes me how the so-called Amhara intellectuals are always looking for the easy way out. It amazes me how the so-called orthodox Christians are in deep sleep. Spending their time looking for the definition of Genocide instead of finding real solution. Asking a solution from PM Abiy adm. Which is controlled by a die-hard protestants who are trying to destroy Orthodox and Amhara day and night. Trying to work a solution with the people who created and orchestrated the genocide. Believing in individuals for a solution who are expelling orthodox Christians even from the capital city and imprisoning individuals who are trying to protect themselves from the herd onslaught as we speak. Amhara should know what to do by now. Orthodox Christians should know what to do by know before it becomes to late. Sodomites and Satanists are destroying Ethiopia. Orthodox Christians should find the real solution to save the country. Reporting the genocide as a genocide does not go beyond becoming part of the larger statistics. Even there still arguments about the holocaust, Armenian genocide etc. etc.… The only loser is the victim. For others it just statistics. Remember Only Tutsis stopped the genocide of Tutsis, nobody else. And by the way it is the Orthodox Christians responsibility to stop the criminals from stealing the egg not PM Abiy. As I noted in the recent video, the only thing left for PM Abiy to prove that he is real qeerro is taking selfie while he is burning houses.

  • It amazes me how the so-called orthodox Christians are in deep sleep. Spending their time looking for the definition of Genocide instead of finding real solution.

 5. በሀገራችን በተፈጸሙት ዘግናኝ እና ኣረመናዊ ወንጀሎች የወንጀል ህጉ ተፈጽሚነት/ or Justice system / ከ Retribution and deterrence principles ኣንጻር እስካሁን የተጫወተው ሚና ኣልታየኝም።
  እንደሚገባኝ በቂም፣ በጥላቻ ፣ ዘርን ወይም ሀይማኖትን መነሻ ኣድርጎ ግድያ የፈጸመ ለመፈጸሙ በህጉ መሰረት / due process of law )ከተረጋገጠበት ገዳዩ ከነ ኣስገዳዩ የሞት ቅጣት እጅግ ቢያንስ የእድሜ ልክ ጽኑ እስ ራት ተፈርዶበት በፈጸመው ወንጀል ልክ የጁን በኣደባባይ ሲያገኝ እና ለሌላው ትምህርት መስጠት ይገባው ነበር ።
  ይህ ባለመሆኑ ኣንዴ ብቻ ኣይደለም በተደጋጋሚ ማንም ተከበብኩ ባለ ቁጥር የንጹሃን ደም እንደ ጎርፍ ባልፈሰሰ።
  የህግ ባለሙያዎች ፣ ኣስተማሪዎች ፣ ጠበቆች …..etc በዚህ ጉዳይ ልዪ ትኩረት ለምን እንዳልሰጣችሁት ሊገባኝ ኣልቻለም።
  ኣሁን ለሚፈጠረው ካልደረሳችሁ ፣ ነገ የናንተን ቤት ማንኩዋኩዋቱ ኣይቀርም !!

 6. Dear Ato Yared Hailemariam,

  Good job, as usual!!! However, these days, I am very surprised at people who are doing their best to deny the fact that genocide was committed in Oromioa region. These people are not fascist TPLFites or OLFites, but people whom we know yesterday as freedom fighters. A case in point is the organizers of demonstrations in Washington DC, Berlin, Canada, London etc who were trying their best not to call a spade a spade, i.e that genocide was committed in Arsi, Shashemene etc . It is good to be tolerant and considerate. But how long and at what cost? Please put yourselves in the shoes of Ethiopians who lost their lives at the hands of the wild animals in Oromia. What do you think surviving members of these families would say about you people who deny the reality?
  For the people who deny that genocide was committed in Oromia: You said genocide was not committed back in October, 2019, when more than 90 people were killed becauase of who they were and the religion they follow. Now, you are saying the same thing. If we will have a situation like Rwanda next time, God forbid but very likely, you will regret your fear of calling a spade a spade although it will be too late.

 7. Dear Yared

  Thank you for educating us. The Rwandan genocide of April 7, 2004 was triggered by the shooting down of the plane carrying the presidents of Rwanda and Burundi. Well, the Ethiopian Genocide of ሰኔ 2012 began with the cowardly and orchestrated murder of ሀጫሉ ሀንዴሳ. Let us call it what it is . GENOCIDE. The trauma , grief, loss of loved ones , and damage to. property Perpetrated by the dregs of society will remain etched in our collective memories. If we chose to bicker about the definition of genocide and ignore the big green elephant in the room, there is nothing that will prevent the perpetrators from repeating the same heinous act again. Let us do something before it is too late. President Bill Clinton was guilt ridden for not stopping the genocide in Rwanda. In an April 5, 2015 Foreign Policy Article he was quoted as saying he.” didn’t fully appreciate the depth and speed with which Rwandans were
  engulfed by this unimaginable terror.”

  Let’s fully appreciate the recent genocide in Ethiopia and do something about it to prevent history from repeating itself.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.