“ለስልጣን ሲባል ኢትዮጵያዊነታችን ተወስዶ ማንነታችን ብሔር እንዲሆን ተደርጓል”ኦባንግ ሜቶ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች

Obang “ለስልጣን ሲባል ኢትዮጵያዊነታችን ተወስዶ ማንነታችን ብሔር እንዲሆን ተደርጓል”ኦባንግ ሜቶ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች
አዲስ አበባ፡- ለስልጣን ሲባል ኢትዮጵያዊነታችን ተወስዶ ማንነታችን ብሔር እንዲሆን ተደርጓል ሲሉ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ሜቶ ገለጹ ።አሁን መገዳደል ላይ የተደረሰው በውሸት ማንነት እንደሆነም አስታወቁ።
አቶ ኦባንግ ሜቶ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳመለከቱት፣ ጥቂት ሰዎች ተበድለናል ብለው ተነስተው ጫካ ገቡ። ከጫካ ሲወጡ እና ስልጣን ለመያዝ ስትራቴጂ ሲነድፉ ህዝቡን መከፋፋል ላይ አተኮሩ። የጋራ የሚባል ነገር ሁሉ የእነርሱ ጠላት መሆኑን አስቀመጡ። እኩልነት፣ ኢትዮጵያዊነት፣ ጥሩዎቹ የአብሮነት ታሪኮች ተሰወሩ። ትልቁን ነገር የኢትዮጵያውያንን ማንነት ከህዝቡ ነጠቁ።
“ፖለቲካ ጨዋታ ነው። ጨዋታው ደግሞ ከማሸነፍ ጋር የተያያዘ ነው። ነገር ግን ማሸነፍ ሲታሰብ አገር እና ትውልድን ከመጉዳት አንፃር መሆን አልነበረበትም” ያሉት አቶ ኦባንግ፣ በኢትዮጵያ ግን ለማሸነፍ ሲባል አገር የምትፈርስበት እና ትውልድ የሚጎዳበት መንገድ መመረጡን አስታውቀዋል።
የምንገዳደልበት የተሰጠንን የውሸት ማንነት ተቀብለን ነው። እውነቱ ግን ከዚህ የራቀ ነው ያሉት አቶ ኦባንግ፣ አያቶቻችን ብሔርን ሳያስቡ በፍቅር ተጋብተዋል። የሰውን ብሔር ሳያውቁ ሰው በመሆኑ ብቻ አግብተው ልጅ መውለዳቸውን አመልክተዋል። በፊት ዕቁብ፣ ዕድር፣ ቡና መጣጣት፣ በአንድ ትሪ ያለምንም ድንበር መብላት
ነበር። ሁሉም ከሰውነት አንፃር ይታይ ነበር። አሁን ይሄን ማንነት ተነጥቀናል። እከሌ ያንተ ጠላት ነው። እከሌ ይሄንን በደል ፈፅሞብሃል መባሉ በብዙዎች ውስጥ ገብቶ የአብሮነት ስጋት መፍጠሩን አስታውቀዋል።
“ፈጣሪ ሰውን ፈጥሯል። ሰው ያለሰው መኖር አይችልም። ዝሆን ስትወልድ ብትሞት፤ የተወለደው የዝሆን ግልገል ያለማንም ድጋፍ ወዲያው መሄድ እና ማደግ ይችላል። የተወለደው የዝሆን ልጅ ራሱን ለመመገብ አያዳግተውም። ሰው ግን ተወልዶ ቢጣል ያለሰው ማደግ አይችልም። ቆሞ ከመሄዱ በፊት መታቀፍ አለበት። መብላት እስከሚጀምር የሚያጎርሰው ይፈልጋል። ሰው ያለሰው አይሆንም። ሰው ከእንስሳት የተለየ ፍጥረት ነው። ሰው ዕውቀት፣ ኃይል እና ኃላፊነት ያለው ፍጥረት ነው። ሰው እንደ ሰው ሊታሰብ ይገባል” ብለዋል።

4 Comments

 1. ወያኔ ሆን ብሎ ባቆመው ባኖሌ ሃውልት ላይ የአበባ ጉንጉን የሚያስቀምጥ ጭራቅ ህዝብ ባለበት ሰው በሰውነቱ ይታያል ብሎ መገመት ይከብዳል። አንድነትና አብሮ መኖርን ሽሮ በክልል ፓለቲካ ለ 27 ዓመት ሲዘራና ሲታጨድ የኖረው የወያኔና የኦሮሞ ለኦሮሞ ብቻ ተስፈኖች ሴራ ገና ብዙ መዘዝ ያመጣል። ቡራዪ ላይ ጡት የቆረጠው፤ ሴት ልጅ የደፈረና ያረደው፤ ጌዲዪ ላይ አያሌ ቤ/ክርስቲያኖችን ያወደመው፤ ሻሸመኔ ላይ ምንም የማያውቀውን ሰው ዘቅዝቆ የሰቀለው ያ ቡድን ነው አሁን በሻሸመኔ፤ በአርሲ፤ በባሌ፤ በጅማ እና በሌሎችም የኦሮሚያ ክልል በሚባሉ ስፍራዎች ቤት የሚያቃጥለው፤ ሰው የሚገለው፤ የሃብት ዘረፋ የሚያደርገውና በሰው ሰቆቃ የሚስቀው። የሚያሳዝነው በውጭም ሆነ በሃገር ውስጥ በኦሮሞ ነጻነት ስም እንዘጥ እንዘጥ የሚሉት የሚፈልጉትንም ሆነ የሚያደርጉትን አለማወቃቸው ነው። በአንድ በኩል ከወያኔ ጋር ተጣምረው አሃዳዊነትን ይቃወማሉ። ዞረው ደግሞ ኦሮሚያ ለኦሮሞ ብቻ ይላሉ። ይህ በፈጠራ ታሪክ ራሱን ያሰከረው የከተማ ጀሌ ሁሌ የሚያናፍሰው ወሬ ከሃገራችን ውጡልን ነው። አንድ በቅርብ በኦሮሞ የፓለቲካ አክራሪዎች የተበተነ በራሪ ወረቀት እንዲህ ይላል ” ማንም ኦሮሞ ሰፋሪና መጤን ደብቆ ቢገኝ ወይም ከሰፋሪ ላይ ሃብትና ንብረታቸውን ቢገዛ እንገለዋለን፤ እንፋለመዋለን” ይላል። ታዲያ የሳይኮሎጂ ግቡ በሌላው ላይ ግፍ እየሰሩ አልወጣ ያሉትን ሁሉ በማስፈራራትና በዛቻ ያለዚያም በዚህም በዛም አንገት በማረድ ባዶ እጃቸውን እንዲወጡ ማድረግ ነው።
  የኦሮሞና የወያኔ ሰዎች እጅግ ከመደንቆራቸው የተነሳ ” ሰፋሪ ኮሎኒያሊስቶች” እያሉ የሚጠሩት ይህ ተሰባጥሮ ለዘመናት የኖረ ህዝብ በኦፌኮና በኦነግ እንዲሁም በመሳሰሉት የዘርና የክልል አምላኪ ፓለቲከኞች የስልጣን ጥማት በመታረድ ላይ ይገኛል። ዘመቻው ክርስቲያን የሆነ (ይህ ኦሮሞንም ይጨምራል)፤ ጉራጌው፤ አማራው፤ ሌላው ባጠቃላይ በኦሮሞ ቆንጨራ አንጋቾች እይታ ንጽህ ኦሮሞ አይደለም የሚባለው ይገደላል፤ ንብረቱን ይዘረፋል፤ ከሞትና ከመሰደድ የተረፈውን ደግሞ እለት በእለት ከተጠለሉበት ቤ/ክርስቲያን ሳይቀር እየደወሉና ወረቀት እየበተኑ ያስፈራሩታል። Native Colonialism ነው በሚኒሊክ ጊዜ መከራ ያመጣብን እያሉ የሚያቅራሩት የኦሮሞ ጽንፈኞች ጊዜ ሰጥቷቸው በስልጣን ላይ ይሁኑ እንጂ የዶ/ር አብይን መንግስት የአማራ መንግስት እያሉ እንደሚጠሩት በየጊዜው ሰምተናል። እጅግ የሚዘገንነው ጠ/ሚሩ አማራ አቅፎ እያደረ ኦሮሞ መሆን አይችልም ብለው በአደባባይ ማበዳቸውን ማሰማታቸው ነው። የኢትዮጵያን ህዝብ ፍቅር ገዝቶት አያውቅም። ሃይል እንጂ። ጠ/ሚሩም እንደ ቆሎ ተማሪ በየስፍራው እየደረሱ በእምንተ ማሪያም ማለታቸው ምንም ፋይዳ የለውም። ጠንካራና እልፍ ቃላቸውን በተግባር በመለወጥ አመራር እስካልሰጡ ድረስ ሰሞኑን ያየነው እልቂት በላቀና በከፋ ሁኔታ መደገሙ አይቀሬ ነው። በቀለ ገርባ፤ ጃዋር፤ የጫቱ ፕሮፌሰር፤ እና በግድ ክርስቲያን እንድሆን ተጠመኩ የሚለው ሌላው ሸውራራ ምሁር ነይ ባይና ጀሌ እሳት ለኳሾች ሁሉ እዚያም ቤት እሳት እንዳለ እስካላወቁ ድረስ የኦሮሚያ ፓሊስና ልዪ ሃይል ለሰላምና ለዜጎች አንድነት ቆሞ ሰውን ከጥቃት ይከላከላል ብሎ ማመን ነፋስ አቅጣጫ አይለውጥም እንደማለት ነው። ቂልነት! እነርሱ ቆመው እያዪ ነው ሰው ያለቀው፤ ስልክ ሲደወል ፓሊሱ አያነሳ፤ አስተዳዳሪው አይመልስም። በተናበበ መልኩ ነው ሰው እንዲታረድና ንብረት እንዲወድም የሆነው። ቆሞ ከመሞት ተደራጅቶ እየተከላከሉ ማለፍም ወኔ ነው።

  እውቁ የመብት ተሟጋች አቶ ኦባንግ ሜቶ እንዳለው ዜግነታችን ተወስዶ በዘር ፓለቲካ ለወያኔ ጥቅም ሲባል በመመንዘሩ ሰው በሰውነቱ የሚመዘንበት ጊዜ ያበቃ ይመስላል። በሰሜን አሜሪካ፤ በአውሮፓ፤ በእስያ፤ በሌላውም የአለም ክፍል ነፍሴ አውጪኝ በማለት አለዚያም በየምክንያቱ የተሰገሰገው ሃበሻ በዘርና በቋንቋው መገሻለጡን ትቶ አንድ ቢሆን ሃገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጭ አስደማሚ ነገር መስራት በተቻለ ነበር። ግን ፓለቲካ ሾተላይ ነው። ትላንት ለሱዳንና ለሌሎችም ሃገሮች ድንበር እየቆረሰ ሲሰጥ የነበረው ከሃዲው ወያኔ ዛሬ የዶ/ር አብይን መንግስት ሃገሪቱን ለግብጽ ሸጠ ሲሉ አለማፈራቸው። የኦሮሞና የወያኔ የፓለቲካ አክራሪዎች ጠብ ሶስት ነገሮች ናቸው። 1. የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያንና አማኞቿ 2. ኤትዮጵያዊነት -ራሱ ስሙ ያማቸዋል 3. ሰፊው የአማራ ህዝብ ነው። ሌላው ሁሉ የማደናገሪያ ሃሳብና ድርጊት ነው። የኦሮሞ ጽንፈኞች ዳዎን ዳዎን አስቴር አወቀ የሚሉ ምኑንም የማያውቁ ብዙ አስቴሮች በምድሪቱ እንዳሉ የማይረዳቸው ደንቆሮዎች ናቸው። ለዛም ነው በሃገር ቤት እልፍ ኦሮሞዎችን በማስገደድ ስማቸው እንዲቀይሩ (includes spelling their names) ፤ የግዕዙን ፊደል ጠልተው በላቲን መጻፍ የጀመሩት። እኔ አንዳንድ ጊዜ እስቲ ይገንጠሉና ይዪት ተዋቸው ያው አሁንም ሞት ያኔም ሞት እላለሁ። ምን እንዳይመጣ ነው። ለነገሩ አሁንም እኮ በክልሎች የተገነጠ ህዝብ ነው ያለው! በቃኝ

 2. “የምንገዳደልበት የተሰጠንን የውሸት ማንነት ተቀብለን ነው።” ይህ ያንተ ቃል ከሆነ፣ “እኔ ሻንቅላ አልተባልኩም፣ አማራ እንጂ አኟክ አይደለሁም” ማለትህ ስለሆነ በማንነት ቀውስ ታውረሃልና የአዕምሮ ሃኪም መጎብኘት አለብህ። ምን ሺህ ጊዜ ለነፍጠኞች ብታጎበድድ መጠቀሚነትህ ሲያበቅ እንደናፕኪን ወደ ቆሻሻ መጣያ ትወረወራለህ፣ ካሁኑ እወቀው! አድርባይ መጨረሻው እንደማያምር እንኳን አንተ ከጎባና ዳጬ እስክ ናጋሶ ጊዳዳ ያሉ ለሃበሻ ወዶገብ ከፍተኛ ጋልቱዎች ከዚህ እጣ ፋንታ አልተረፉም!
  አኙክነት፣ ኦሮሞነት፣ ሶማሌነት፣ ትግሬነት፣ ወዘተ “የውሸት ማንነት” እንዴት እንደሆኑ እንኳን አንተ፣ ቃሉን ያጎረሱህ ዘረኞች እንኳ በቅጡ አያዉቁትም። እነዚህ ማንነቶች ከሌሉ፣ ኢትዮጵያዊነትም የለም፣ አረብነትም፣ እንግሊዛዊነትም፣ ጀርመናዊነት፣ ቻይናዊነት፣ ሁሉ የሉም ማለት ነው። የዐለም ህዝብ በሙሉ ከኢትዮጵያዊነት ዉጪ ሌላ ማንነት የለውም ማለት ነው። የበላይነት አባዜ እና የማንነት ቀውስ ውስጥ የተዘፈቁ የአዕምሮ በሽተኞች አስታማሚ ሆነህ ራስህን ስለሰጠህ ቻለው!

  • ተጋዳላይ ኣባ ጫላ !
   የኦባንግ ኣስተሳሰብ ክፍት የሆነ ፣ነገን የሚያይ ፣ ስልጡን ኣይምሮን ይጠይቃል ።እንዳንተ ኣይነት በምናብ በሚኒሊክ ጊዜ የሚኖር በጥላቻ የታጨቀ ኣይምሮ ፣ በተሸናፊነት ስነ ልቦና የተጠናወተ ትናትን ብቻ የሚያይ ጋር interface ሊኖራች ሁ ኣይችልም።የሁለት ኣለም ሰዎች!

 3. Abba Caala,

  እኔማ፣ ስፈራ ስቸር፣ ጽሑፉን ካነበብኩበት የትላንትናው እለት ጀምሮ እጄ ተቆላልፎብኝ፣ ግን አንተ ያበጠው ይፈንዳ ምናባቱንስና ግድርድርነት፣ እውነት መፍረጥ አለበት ብለህ ንግግሩን እንደ ናረች ኳስ ስትለጋው፣ እኔም እፎይ አልኩኝ::

  Unity in diversity!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.