ትእግስቱ የማያልቅበት ጨዋ ሕዝብ – መስፍን ወልደ ማርያም

ሰኔ 2012
Mesfinየሚሰሙኝ ከሆነ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዶር. ዓቢይ አሕመድ፣ ለአዲስ አበባ ከንቲባም፣ ለወይዘሮ ሙፈሪያት የሰላም ሚኒስትር፣ ምናልባት ሌሎች መኖሪያ ቤት መፍረስ የተጠናወታቸው ባለሥልጣኖች ካሉ ለነሱም የኅሊናዬን ጩኸት አስሰማለሁ፤
የሚያዩኝና የሚያዝኑልኝ ከሆነም ተንበርክኬ እለምናቸዋለሁ!
በዚህ የክረምት ወቅት፣ በዚህ የማትታይ ጉድ ዓለምን በሙሉ አንበርክካ በየዕለቱ ሰዎችን በምትጨርስበት ዘመን፣ በዚህ ዘመን እጃችሁን ቶሎ-ቶሎ ታጠቡ፤ አፍና አፍንጫችሁን ሸፍኑ፣ ስትገናኙ ተራራቁ በተባለበት ዘመን፣ በዚህ ሰው ሁሉ ሥራ ፈትቶ በቦዘነበት ዘመን፣ በዓባይ ጉዳይ ከግብጽ ጋር በተፋጠጥንበት ዘመን፣ የድሆችን ቤት በጉልበት ማፍረስና ድሆችን ማስለቀስ አቤቱታቸው የላይኛው ጌታ ዘንድ እንደሚደርስ ባለማወቅ ነው? ወይስ ኮሮና በቂ አልሆነምና ነው? እግዚአብሔር እንደሆነ ከኮሮና የባሰ ለመልቀቅ ችግር የለበትም፡፡
ዶር. ዓቢይ ስለይቅርታ የሚናገረው ስለነዚህ ደሀዎች አይሠራም? ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ትልልቅ ዓላማዎች አንዱም እነዚህን እንባቸው የእግዚአብሔርን ደጃፍ የሚያጨቀይ ደሀዎችን አይነካም?
በመጨረሻም እነዚህን ደሀዎቸ እግዚአብሔር አያያቸውም ብላችሁ ተስባላችሁ? ወይስ አይቶ መልስ ሳይሰጥ ይቀራል ብላችሁ ታምናላችሁ?
እግዚአብሔር ነገን ይግለጥላችሁ!

2 Comments

 1. እናመሰግናለን፡፡ ፕሮፌሰር አንዳንዴ ፖለቲካ ጉዳይ ላይ የሚሰጡት፣ የሚጽፉት ፕሮፊሰር ምን ኒካቸው ቢያስብለንም አንድ የማይታሙበት ነገር ቢኖር ለዜጎች ሰብአዊ እኩልነት እድሜ ልካቸውን የታገሉ ብቸኛ ኢትዮጵያዊ ግለስብ ናቸው፡፡ ስለ ወርቃማ አገልግልዎትም ከልብ እናመሰግናለን።

 2. ለመጣው ነብሰገዳይ ሁሉ እጅ መንሻ አላጣም፣ ማለትም እንደየአስፈላጊነቱ:
  1. ሱማልያ ጅል ተጨማላቂ የማታድግ ጨቅላ፣ ለዙፋናውያን እጅ መንሻ
  2. 60ዎቹን ግደልዋቸው፣ Stalin, the champion of Nationalities፣ የደርግ አማካሪነትን ለማጥበቅ
  3.አማራ የሚባል የለም ደገኛ እንጂ፣ እንዲሁም በሚስቴ በኩል ዓድዋ እንትጮ ነኝ፣ ከወያነ ጋራ ለመዛመድ
  4. ጨዋ ህዝብ፣ PP”ን አወድሶ ለመጠጋት
  ተራ አገልጋይነት ይውደም

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.