“ጃዋርና እስክንድር እየተናበቡ ሀገር ለማተራመስ ይሠራሉ” – ወ/ሮ ዐቃቤ ህግ አዳነች አቤቤ – ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

abebeየወ/ሮ አዳነች ይህን ዓይነቱ መንግሥታዊ ንግግር የዶ/ር አቢይን ከባልደራስ ጋር የሚያደርገውን ጦርነት ያወጀበትን የቁጣ ንግግር የተንተራሰ ለመሆኑ ዋቢ መጥቀስ አያሻም – እየተናበቡ ሀገርን በማፍረስ ላይ የሚገኙትስ እነሱ ራሳቸው ናቸው፡፡ ይህ ንግግር በተውኔቱ ዓለም ቢገለጽ ደምበኛ ሼክስፒራዊ ትራጂ ኮሜዲ ነው፡፡ እንደነዚህ ዓይነት ሽል መንጣሪዎች እየመሯት ሀገራችን ወደገደል እንጂ ወደ ብልጽግናና ዕድገት አታመራም፡፡ ምኞት ግን አይከለከልም – ሊያውም ከማስመሰል የራቀ ቀናና ትክክለኛ ምኞት ካለ፡፡

ጥቅምት 2012ዓ.ም ከ100 በላይ ንጹሓን አማሮችንና ለዘብተኛ የኦሮሞ ክርስቲያኖችን እንዲሁምና ምናልባትም ከሌሎች ነገዶችም የተወሰኑ ዕድለቢሶችን  ያስጨፈጨፈው በወቅቱ “ሁለተኛው የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር” ጃዋር መሀመድ በመንግሥት ዕቅፍ ውስጥ ሆኖ ያሻውን ሲያዝዝና ሲናዝ ለተመለከተ ቅን ታዛቢ በቅርቡ የአክራሪ ኦሮሞዎች አማራ ላይ ባደረሱት ዕልቂትና የንብረት ውድመት ሳቢያ “ራሳችሁን ጠብቁ፤ ተደራጅታችሁ አካባቢያችሁን ከጥቃት ታደጉ…” ብሎ አዲስ አበባን ከውድመት ለመከላከል የሞከረን አንድ ዜጋ በመናጆነት ማሰር በርግጥም የክፍለ ዘመኑ ቧልታይና ድንቃይ የልጆች ትያትር የሚመስል አስቂኝ ግን  መራር ቀልድ ነው፡፡ እንደዚህ ያለ ዐይን ያወጣ መድሎና ወገንተኝነት በመንግሥት ደረጃ ከታዬ በግልማ እንዴት የባሰ አይሆን! ሀፍረትን መሸጥ እንደዚህ ነው፡፡

እንደ አንዳንዶች ግንዛቤ እስክንድር ነጋ የአዲስ አበባ ወጣቶችን ባያስጠነቅቅ ኖሮ ከተማችን ይሄኔ ከገጠር በአይሱዙ ተጭነው በመጡ የጥፋት ኃይሎች እንደ አሌፖና ደማስቆስ የዶግ አመድ ሆና ነበር፡፡ ይህን የንጹሓን ዜጎች ዕልቂትና የንብረት ውድመት መከላከልም እንደወንጀል ተቆጥሮ ወጣቱን “ራስህን ተከላከል፤ አካባቢህንም ጠብቅ” ብለው ያነቁ ከእስክርቢቶም በስተቀር አንድም የጦር መሣሪያ የሌላቸው ዜጎች በፖለቲካ አመለካከታቸውና በዘር ሐረጋቸው ምክንያት ብቻ ለእስርና እንግልት ተዳርገዋል፡፡ ይህን መንግሥት የሚመራው ደግሞ እንደዓሣ በባህር እንደሰው በምድር ነዋሪ የሆነው ዶክተር አቢይ ነው፡፡ የሚገርም ተፈጥሮ፡፡

በበኩሌ ከአቢይ መንግሥት ምንም አልጠብቅም፡፡ ተስፋችንን ሁሉ እያሟጠጠው ነው፡፡ ሰውዬው እጅግ አደገኛ የጭቃ እሾህ መሆኑን በተደጋጋሚ በተግባር በማሳየቱ ከእንግዲህ አቢይ ኢትዮጵያን ወደ ወርቃማ ጊዜዋ ያሻግራታል ብሎ ራስን ማታለል ሲበዛ የዋህነት ነው፡፡ ልጁ በነገሮች መሳከር ሳቢያ ድንገት እጁ የገባችዋን ዕድሜ ልኩን ሲቃዥባት የኖረውን የሰባተኛ ንጉሥነት ሥልጣን ላለማጣት ሲል የማይቀጥፈውና መስሎ ለመገኘት የማይጥረው ነገር የለም፡፡ ይሉኝታን ባወጣ ሸጦ ስለበላ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው በአንድ ጊዜ ጅብም አህያም፤ እሳትም ውኃም ለመሆን ከመሞከር አይመለስም፡፡ ይህን ቦታ ከመያዙ በፊት እርግጥ ነው ጥሩ ሰው ሊሆን ይችል ይሆናል፡፡ ወንበሩን ከያዘ በኋላ የሚታይበት ጠባይ ግን እጅግ የተለዬና አስመሳይነት የበዛበት ለመሆኑ የሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ በግልጽ የሚናገረው እውነት ነው፡፡ ለዚህም ነው የተበደለ ሲያይ አብሮ እያነባና ዕንባም ከጉንጭ እየጠረገ፣ የኦርቶዶክስ መስቀልንም ከሙስሊሙ ክታብና ሙስባሃ አጣምሮ እየሳመ፣ የጴንጤን መዝሙር ከማጀት እስካደባባይ እየዘመረና እያዘመረ፣ ምናልባትም ታልሙድንና ቶራን ከጽዮናውያን ምኩራቦች እያስተረጎመና እያስነበበ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ተከላም የዋሃንን እያነሆለለ፣ … በየሥነ ግጥም ምሽቶችና የድርሰት ምርቃቶችም በመገኘት የአርት ሰዎችን እየቀፈለ … በሌላ በኩል ደግሞ የሥልጣን ተቀናቃኞችን በሥውር እየገደለና እያስገደለ፣ በዘር ልክፍት የደዌ ግርሻ አክራሪ ወጣት ኦሮሞዎችን በየሥልጣን ቦታው እየመደበና ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚሸቱ ጥሩ ጥሩ ዜጎችን ግን ከጥቅምም ከሥራም እያገለለ፣ አዲስ አበባንና ሀብቷን ከየገጠሩ ተጠራርቶ ለመጣ የቄሮና አባገዳ ግሪሣና መንጋ እያከፋፈለ… አማራን ግን ከነስሙም አታንሱብኝ እያለ፣ የአማራን ክልል ሀብትና ሥልጣን ለታማኝ አሽከሮቹ እንደራሴዎች እያቃረጠ … አይሆኑ ሆኖ የምናየው፡፡ ልጁ አስገራሚ ተፈጥሮ ያለው ሰው ነው፡፡ ሰይጣን ለተንኮሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ መጥቀሱን የማያምኑ የዋሃን ዜጎች በአቢይ የማስመሰል “ጥበብ”ና በሚያሣየው የሃይማኖተኛነት ውስጠ-ወይራዊ ስብዕና በመማለል በኔ እንደሚፈርዱብኝ አውቃለሁ፡፡ በዚህ ጉዳይ ከጥቂት ጓደኞቼም ጋር ስከራከር ባለመስማማት ራሴን ከክርክሩ አገልላለሁ፡፡ የወደደ ሲጠላ እንዲህ ነው፡፡

በመጀመሪያው አካባቢ እርግጥ ነው እኔም መስሎኝ ተታልዬ እንደነበር አልደብቅም፡፡ እየቆዬ የተረዳሁት ግን አቢይ ማለት የጨለማው ገዢ ሊቀ ሣጥናኤል ዓላማውን እንዲያስፈጽሙለት ከልጅነታቸው ጀምሮ አርሞና ኮትኩቶ ለቁም ነገር ካበቃቸው ምድራዊ ሰብኣውያን ፍጡራን መካከል አንዱ መሆኑን ነው፡፡ እኔ ይህን እውነት በሚገባ አምኜበታለሁ፡፡ ምናልባት ይህን የኔን እውነት ከሰይጣን ከራሱና ከእግዚአብሔር በስተቀር ሌላ ሰው አያውቀው ይሆናል – ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ ምክንያቱም የአቢይ ልዝብ ሰይናጣዊ አንደበት ሌላውን ሁሉ ተውትና ፕሮፌስር አለማየሁ ገ/ማርያምን ሳይቀር አንበርክኳል፤ ምትክ የለሹን ለሀገር እንስፍስፍ ታማኝ በየነን በፍቅሩ ጫማው ሥር ጥሏል፤ ፕሮፌሰር እንደሻው ነጋን የመሰለ አክሮባቲስት አሽከሩ አድርጓል፤ በርካታ የተቃውሞው ጎራ ሚዲያዎችን አፍ አሲዞ በራሳቸው ጊዜ እንዲዘጉ አድርጓል፡፡ ብዙዎችን አሁን ድረስ በፍቅሩ እያማለለ እንዲያለቅሱለት በማድረግ ላይ ነው፡፡ ሰይጣን እስከዚህ ድረስ ሰውን ያጃጅላል፡፡ ለእግዚአብሔር ብቻ አይደለም – ለሰይጣንም የሚሳነው የለም! ዋናው እምነት ነው፡፡ ካመንክበት እንኳንስ ሰይጣንና አቢይ ድንጋይም ብዙ ተዓምር ይሠራልሃል፡፡ እውነት ነው፡፡ እርግጥ ነው አንዳንድ እውነቶች በገሃድ እስኪከሰቱ ጊዜ ይወስዳል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሩብ ክፍለ ዘመን አሸብራቂ ታጋይ: ማሙሸት አማረ - ሸንቁጥ አየለ

ኢትዮጵያ የተደገሰላት የመከራ ድግስ ቀላል እንዳይመስለን – የቆማጢት ልጅ “እማዬ እጄን አሳከከኝ” ብትላት “ልጄ እኔም በአንድ ቀን አልተቆመጥኩም!” ያለችው ሦርያንና ሩዋዳን ለኛ ለጀለንፎዎቹ ለማስታወስ ፈልጋ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ከሆነ በኋላ እዬዬ ዋጋ የለውም – ለዚያም ከበቃን እንዲያውም፡፡ አንድ መራር እውነት ላስታውስህ፡- የፌዴራል ተብዬውን ዋና ዋና የፈላጭ ቆራጭ የሥልጣን ቦታዎች የተቆጣጠረው ኦህዲድ/ኦነግ ባለፉት 40 እና 50 ዓመታት አማራና ኢትዮጵያ ላይ የዘረኝነት የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ሲነዛበት በነበረው ወጣት ኃይል ነው፡፡ ታከለም በለው ሽመልስ፣ አቢይም በለው ደቻሣና ቀልቤሣ …. ሁሉም የዚያን ወያኔ ወለድ የአኖሌ ትርክት እየተቀለበ የበቀል ጥማቱን ለማራገፍ ጊዜ ይጠብቅ የነበረና በአማራው ላይ ታሪክ ለመሥራት ያቆበቆበ ትውልድ ነው፡፡ ልዩነቱ አንዱ ወለጋ ጫካ ውስጥ ሲሆን ሌላውና ጓዳችን ውስጥ በራሳችን ስንቅና ትጥቅ እየተዋጋን ያለው ኃይል አዲስ አበባ ላይ የፌዴራል ተብዬውን መዋቅር ይዞ እንደልቡ የሚፏልል መሆኑ ነው፡፡ ይህ የምለው ነገር ውሸት በሆነና እኔ ቀጣፊ በተባልኩ፡፡ ኢትዮጵያ ሲባል እንደኮረንቲ የሚነዝረው፣ አማራ ሲባል እንደ ዛር አዶ ከብሬ የሚያስጓራው ትውልድ ሥልጣን ይዞ ኢትዮጵያም ሆነች አማራ ሰላም ያገኛሉ ብሎ ማሰብ ደግሞ በትንሹና በተለመደው አገላለጽ ከእባብ ዕንቁላል የዕርግብ ጫጩት ይፈለፈላል ብሎ  እንደመጠበቅ ነው – ትልቅ ጅልነት፡፡

እነሱሴም ሆኑ እነ “ስንኖር ኢትዮጵያ፣ ስንሞትም ኢትዮጵያ” ነገረ ሥራቸውን እያየናቸው ነው – እነሱም ብልጥ ሆነው ሞተው እንዴት ሕዝብን እያታለሉ እንደሆነ በቀላሉ መረዳት አይከብድም፡፡ የ30 እና የ40 ዓመት ውርጋጥ የሦስት ሽህ ዘመን የጋራ የአብሮነት ታሪክ ያለውን ያንቀላፋ ግን ያልሞተ ሕዝብ ለማሞኘት የተጓዙትን ርቀትና ያስመዘገቡትን ስኬት ስንመለከት በርግጥም ዕድል ሲሰምርና ዕድል ሲያንጋድድ ልዩ ምስል  ሊፈጠር እንደሚችል ከሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ መረዳት አያቅተንም፡፡ ሆኖም ሁሉም ነገር አላፊ መሆኑ ያጽናናናል፡፡ እንደመጽሐፉ – ለመትከል ጊዜ አለው፤ የተተከለውን ለመንቀልም ጊዜ አለው፡፡ ለመነሣት ጊዜ አለው፤ ለመውደቅም ጊዜ አለው፡፡ ሮም በአንድ ቀን እንዳልፈረሰች ሁሉ በአንድ ቀንም አልተገነባችምና የሞኞች ግዝፈት ብልኆች ከዳተኝነታቸው እስኪላቀቁ ድረስ ነው፡፡  የሚያዋጣው በፋሲካ ሰሞን ከተቀጠረችዋ የቤት ሠራተኛ ትምህርት መቅሰምና ራስን ከታሪክ ሂደቶች ጋር ለማስተካከል መሞከር ነው – ብዙም ሳይረፍድ፡፡ ታሪክ ጨካኝ ነው – ምሕረትን አያውቅም፡፡ ከአጼ ኃይለ ሥላሤ፣ ከደርግና ከወያኔ ያልተማረ ንክር ያለ ደንቆሮ ነው፡፡ መለስና መንግሥቱ ኃ/ማርያም በተሰሚነታቸውና ጠርዝ ባልነበረው ዐረመኔያዊ አምባገነንነታቸው ያልቻሉትን የታሪክ ዱላ ጮርቃው አቢይ ይችለዋል ብሎ ማሰብ አነሰ ሲባል ሞኝነት አሊያም ካድማስ ወዲያ ማዶ አገር እንደሌለ የሚስቆጥር አላዋቂነት ነው፡፡

እነዚህ በሥልጣን አራራ ያበዱና በፍቅረ ንዋይ የሰከሩ ዘረኞች የዘመናችን ጴጥሮሶች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ከመፋፈራረሷ በፊት ከሦስት ጊዜ በላይ ይክዷታል፡፡እጅግ አስፈሪ ኃይል ማዕከላዊ መንግሥቱን ተቆጣጥሯል፡፡ ሀገራችን በሰሜንም በደቡብም በምሥራቅም በምዕራብም እንደሌጦ ተወጥራ ትገኛለች፡፡ እነጃዋርና እነአቢይ የሥልት እንጂ የዓላማ ልዩነትና የጠብ መንስኤ የላቸውም – ጥላቸው የሥጋ ጥል ነው፡፡ ዓላማቸው አንድና አንድ ነው – እሱም በኢትዮጵያ ፍርስራሽ ሌሎችን በገዳ ሥርዓት የሚያንበረክክ ታላቋን ኦሮሚያ መመሥረት ነው፡፡ ልዩነት ካልነው ሌላው ልዩነት አንዳቸው ዓላማቸው በፍጥነት እንዲሳካ ሲፈልግ ሌላኛው በእርጋታና በዘዴ እንዲሆን መፈለጉ ነው፤ ሌላው ልዩነት የሥልጣንና ሀብት ክፍፍል ነው፡፡ እንጂ እዚያም ውስጥ ያሉት እዚህኛው ውስጥ አሉ፡፡ እዚህኛው ውስጥ ያሉት እዚያኛውም ውስጥ አሉ፡፡ አባተ ኪሾ እውነቱን ነበር፤ “ኤርትራውያንን ጭነህ ላክ” ቢሉት “እናንተው ለዩዋቸው እንጂ እኔ በምን አባቴን አውቃቸዋለሁ” ብሎ ትግሬዎቹንም ከአዋሣ ጠፍንጎ ለወያኔ ላከላቸው ይባል ነበር ያኔ፡፡ አሁንም እንደዚያ ነው፡፡ ነገር ይደጋገማል – ኦነግ ሸኔን ከኦነግ ኦህዲድ መለየት የሚችል ማሽን ተፈጥሮ ከሆነ የቸርች ኦፍ ሴተን መሥራች የቀሲስ አንቷን ሌቪ ሙት-መንፈስ ይንገረን፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያውያን የአንድነት ዓለም አቀፍ ዘመቻና  የአብይ ድጋፍ ሰልፍ ሰልፍ ከፋፋይነት - ሰርፀ ደስታ

ልድገመው – በወያኔ ተንኮልና ሤራ የኦሮሞና የትግሬ ወጣት ሲኮመኩም ያደገው አማራን አምርሮ እንዲጠላ የሚያስችል የዘረኝነት መርዝ ነው፡፡ ኢትዮጵያም ፈርዶባት ከአማራ ጋር አያይዘው እንድትጠላ ስላደረጓት ወጣቶቹ ለዚህች ጥንታዊት ሀገር ያላቸው ጥላቻም የዚያኑ ያህል ነው፡፡ መፍትሔው ለሰማይ ለምድር የከበደ ይመስላል፡፡ በኪነ ጥበቡ ውለን እናድራለን እንጂ እንደነዚህ ሰዎች ሁኔታ ቢሆን ኖሮ አዲስ አበባ በደም ባህር ላይ የምትንሣፈፍ ፍርስራሽ ከተማ በሆነች ነበር፤  አንድም ፎቅ ቆሞ ባልተገኘ፡፡ ይህን መከላከል ወንጀል የሆነው እንግዲህ በፌዴራል መንግሥቱ ውስጥ በተሰገሰገው አፍቃሬ ኦነግ ሸኔ ቲም ለማ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ እጅግ ይገርማል፡፡

ኦሮሚያ በሚባለው አካባቢ ሲሰለጥን የነበረው ያ ሁሉ ለመቁጠር የሚያስቸግር ሠራዊት ለምን ዓላማ እንደሠለጠነ ሰሞኑን ትልቅ ፍንጭ እየሰጠን ነው – ቤተ ክርስቲያን ሲያቃጥሉ የነበሩት እነዚሁ ሥልጡኖች እንደነበሩ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡ አማራ ራሱን እንዳይከላከል በበጀትና በተላላኪ ምስለኔዎች እያሽመደመዱ ኦሮሚያ ተብየውን ክልላዊ መንግሥት ግን ልክ እንደ አንዱ አውሮፓዊ ኃያል አገር ለማድረግ ምን ያህል የተናበበ ሥራ ይሠሩ እንደነበር የምናውቀው ነው – ይህንን እውነት የሚክድ በርግጥም አድርባይና ሆዳም ነው ወይም ከዕውቀት የፀዳ እልም ያለ ደንቆሮ፡፡ ሁሉም ፈዞና ደንግዞ እያየ ያለው ይህ ድራማ መጨረሻ ምን ሊሆን እንደሚችል ሰሞኑን በቂ ምልክቶችን ስላየን ሌላው ቆሞ ከማየት ተቆጥቦ ራሱን መከላከል ወደሚያስችለው ዝግጅት መግባት እንዳለበት በዚህ አጋጣሚ ማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡ ራስን ከጥቃት መከላከል በአሁኒቷ የኦህዲድ ኢትዮጵያ ወንጀል ቢሆንም ሜዳ ላይ ተገትሮ አንገትን ለግብጽ ገጀራ መስጠት ግን ለማንም አይመከርም፡፡ አልሞት ባይ ተጋዳይነት በወንበዴ መንግሥት ሲጨፈለቅ ራስን ከዕልቂት ለማዳን ሥልት ነድፎ መንቀሳቀስ ቢያንስ ዘር ለማትረፍ ይረዳልና ሁሉም በዚህ ረገድ ማድረግ ያለበትን ብዙ ሳይረፍድ ያድርግ፡፡ ከሩዋንዳ እንማር፡፡ አሁኑኑ!!

እርግጥ ነው ከፍ ሲል እንደተገለጸው የኦሮሞው ማዕከላዊ መንግሥት ራስን መከላከልን አይፈቅድም፡፡ ሰሞኑን አየነው፡፡ “ዝም ብላችሁ ታረዱ እንጂ መሸሽም ሆነ ንብረት እንዳይቃጠል መከላከል አትችሉም” የማለት ያህል አስገራሚ ትዕዛዝ ሲሰጡ ታዝበናል፡፡ ቄሮዎች አማሮችን ሲያርዱና ንብረታቸውን ሲዘርፉና ሲያቃጥሉ የሚሸሸውን ሰው የሚያግዱና ከዘረፋ ለማስጣል የሚሞከረውን ሀብት ንብረት እንዳይወጣ ሲከለክሉ የነበሩት የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት እንደነበሩ በስፋት ተነግሯል፡፡ የመንግሥትን ቅርጽ ከያዘ የዘር ፍጅት ለማምለጥ ደግሞ ዕድሉ በጣም ጠባብ ነው፡፡ የኔ ነው ብለህ የምትጠጋው ኃይል ከሸሸኸው ኃይል በባሰ ወይም በተካከከለ ሁኔታ ሕይወትህን ሲቀጥፍ ወይም ሲያመናጭቅህ መፈጠርን ያስጠላል፤ የፈጣሪንም ኅልውና እስከመጠራጠር ሳይቀር ይፈታተናል፡፡ ሰሞኑን የሆነው ይሄው ነው፡፡ የነገው ደግሞ ከዚህ የከፋ መሆኑ አይጠረጠርም፡፡ አማራነትና ኢትዮጵያዊነት ወንጀል ሆነዋልና ለመጨረሻው የአልሞትባይ ተጋዳይ ፍልሚያ እንዘጋጅ፡፡ ቁርጡን ካወቅነው የትግሉ ውጤት የሚያዘነብልበትን አቅጣጫ ለመተንበይ ቀላል ነው፡፡

ራስን ከጥቃት መከላከል ወንጀል የሆነባት ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት፡፡ ከአሁን በኋላ ይህን መንግሥት ማመን አስቸጋሪ ብቻ ሣይሆን በፍጹም የሚቻል አይደለም፡፡ ቄሮ ሲመጣብህ መሸሽና አንገትን ከቆንጨራ ለማዳን መሞከርም በህግ የሚያስቀጣ አንቀጽ የሌለው ወንጀል ሊሆን ነው፡፡ አክራሪ ኦሮሞ ሲመጣብህ ቆሞ መጠበቅና የሚደርስብህን በጸጋ መቀበል ህግን እንደማክበር ከተቆጠረ ከእንግዲህ አገር አለኝ ማለት አንችልም፡፡ መንግሥት እነጃዋርን አሰራቸው ማለትም አይቻልም፡፡ የሚደረግላቸው ክብካቤ ልዩ እንደሆነ እየሰማንና እያየን ነው – ከርቸሌ ገብቶ ያልታሰሩ የቅንጅት አባላትን ሲሾም ሲሽር እንደነበረው እንደኢንጂኔር ኃይሉ ሻውል ጃዋር እስር ቤት ውስጥም ሆኖ የመንግሥትነት ጠባዩ የለቀቀው አይመስልም – እንደምናየው ከእስረኛ ዓለም አቀፍ አያያዝ በተለዬ ሁኔታ በቪ8 እና በተለዬ አክብሮትና አጀብ ነው ወደ ፍርድ ቤት እንኳን የሚመላለሰው፤ ተፅዕኖው ቀላል አይደለም፤ በዚህ አኳኋን በቅርብ እንደሚፈታም መገመት አይከብድም፡፡ ለምሣሌ በበቀደም አንድ የጊዜ ቀጠሮ ለነእስክንድር ተጨማሪ ምርመራ 13 ቀን ሲፈቀድ ለነበቀለ ገርባ ግን 11 ቀን ነው፡፡ ምን አለፋችሁ – ይህን በዘረኝነት የጠነባ የአቢይ መንግሥት በሰላም ካልተገላገልን የኢትዮጵያ ትንሣኤ መቼም እውን አይሆንም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የብአዴንና  የኦህዴድ አገልጋይነት እስክምን ድረስ  - ይገረም አለሙ  

ይልቁንስ ትንቢትን ማክሸፍ የሚቻል ከሆነ በየሃይማኖታችን አጥብቀን እንጸልይ፡፡ መጪው ጊዜ ካለፈው እጅጉን ከባድ ነው፡፡ ትልቅ ሰውም የለም፤ ሃይማኖትም የለም፤ ሃይማኖተኛም የለም፡፡ በሁሉም ከስረናል፡፡ አንድ ነገር ቢነሳ ማንም አያድነን፡፡ ዓለም ደግሞ የባለጌዎች መናኸሪያ ከሆነች ቆየች፡፡ እንጂ የንጹሓንን ደም ለማፍሰስ አውስትራሊያና አሜሪካ መሽገው ጃዝ የሚሉ ተኩላዎችን ለማስቆም የሚከብድ ሆኖ አልነበረም፡፡ ዘመኑ የመጨረሻው መሆኑን እንድናምን የሚያስገድደንም ይሄው የጭካኔ ትስስር ነው፡፡

ማኅበረሰቡ በሞራል ላሽቋል፤ በሃይማኖት ወድቋል፤ ባህልና ወጉን ተነጥቋል፤ ማኅበራዊ ወግ-ሥራታዊ ተራክቦው ከሞላ ጎደል ተበጣጥሷል፡፡ በቀደምለት ዮንሐስ አካባቢ ገዳም ሰፈር በሚባለው ልዩ ቦታ የታዘብኩት ክስተት ኢትዮጵያ እንደሀገርም እንደህዝብም  ትልቅ ችግር ላይ መውደቋን አጉልቶ የሚያሳይ ነው፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው – እኔ በራሴ ተሸከርካሪ ቀስ ብዬ እያለፍኩ ነው፡፡ አንድ የቆመ ዲኤክስ መኪና ተነስቶ ሊሄድ ማርሽ እያስገባ ነው፡፡ መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ ሁለት የጉሊት ሴቶች ተንደርድረው ሲመጡ አያለሁ፡፡ ሣር ቢጤ ይዘዋል፡፡ አንደኛዋ ማንም ሳይነካት ከመኪናው የኋላ ኮፈን ጋር በዘዴ ተጋጨችና ተምበልብላ ወደቀች፡፡ መኪናው አልገጨም፤ የጀመረውንም እንቅስቃሴ ወዲያውኑ አቆመ፡፡ ትያትር የማይ መሰለኝ፡፡ ይህንን የአጭበርባሪዎች ዘዴ በፊትም አውቀዋለሁ፡፡ እንደዚህ ሲገጥመኝ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ ያቺ በራሷ ጊዜ ጎማው ሥር የወደቀችው ሴትም ጓደኛዋም ያገር ያለህ እያሉ ጩኸታቸውን ማቅለጥ ጀመሩ፡፡ ሹፌሩ ደነገጠ፡፡ ሕዝብ መሰባሰብ ጀመረ፡፡ እኔ ንዴት ብልጭ አለብኝና ከራሴ መኪና ወርጄ በጩኸት ወደ ጀማው ተቀላቀልኩና ሕዝብና መንግሥት ህግና ሥርዓትም ያለ መስሎኝ “እነዚህን ሴቶች ከመነሻው አይቻቸዋለሁ፡፡ ትያትር እየሠሩ ነው፡፡ ልጁ አልገጫቸውም፡፡ …” እያልኩ ምስክርነቴን ባደባባይ መስጠት ጀመርኩ፡፡ ፖሊሶችም ነበሩ፡፡ የአካባቢው ሰው ግን እኔን ሳይሆን ሴትዮዋን ደግፎ ይንጫጫ ጀመር፡፡ ትያትሩ መንደር አቀፍ መሆኑ ገባኝ፤ እርግጥ ነው ሰፈሩ ዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች መኖሪያ ይመስላል – ያን ያህል የሞራል ዝቅጠት ይኖራል ብሎ መገመት ግን ይከብዳል፤ እየሆነ ያለው ግን ሌላና አስደንጋጭም ነው፡፡ አንዳንዶች እንዲያውም በኔ ይዝቱ ገባ፡፡ ሁኔታው ሳያምረኝ ሲቀር እያበድኩ እየተከንኩ አካባቢውን ለቅቄ ሄድኩ፡፡ ራቅ ብዬ ስከታተል የተወሰኑ ሰዎች ተገጨች የተባለችውን አጭበርባሪ በመኪናው ጭነው ሄዱ፡፡ ቀጥሎ የሚሆነውን መገመት ቀላል ነው፡- መንገድ ላይ ይደራደሩና “ማገገሚያና መታከሚያ ጥቂት ገንዘብ ስጣትና እዚሁ ተስማሙ” ይባልና ገንዘብ ተቀብለው ባለመኪናውን ይሸኙታል፤ “ገጪው”ም ከህጋዊና ህክምናዊ ውጣ ውረድ በመገላገሉ ያላመነበትን ነገር አድርጎ ከውጣ ውረድ ይድናል፡፡ እስከዚህ በስብሰናል፡፡

በየመሥሪያ ቤቱ፣ በየእምነት ቤቱ፣ በየምናምኑ … ሁሉ እንደዚህ ያለ ንቅዘት በስፋትና በጥልቀት ይታያል፡፡ ይህን መበስበስ ለማስወገድና ወደ ትክክለኛው ስብዕና ለመምጣት ራሱ ብዙ ጊዜንና ብዙ ትግስትን፣ ብዙ የተማረ የሰው ኃይልንና በጀትን፣ ብዙ ቆራጥነትንና የሀገርና የወገን ፍቅርን፣ … በጣም ብዙ ብዙ ነገርን ይጠይቃል፡፡ አቢይም የዚህ የበሰበሰ ማኅበረሰብ ውጤት ነውና በውሸታምነቱ የተቆራኘው የአጋንንት መንፈስ ከየትም እንዳላመጣው በዚህ አጋጣሚ መመስከር ይቻላል፡፡ በወለድነው እንጦራለን፤ የዘራነውንም እናጭዳለን … በዚህ መሀል ግን አዲዮስ ሀገር፤ አዲዮስ የመንግሥት ህዝባዊ አገልጋይነት፤ አዲዮስ የሞራልና የሥርዓት ዕሤቶች…. አዲዮስ ህግና መንግሥት … የአሥር ዓመት ሕጻን ልጁን የደፈረና የደበደበ ዋና ሳጅን የዘጠኝ ዓመት እሥራት ብቻ የሚፈረድባት ሀገር ዱሮውንስ ምን ሀገር ሆነች …. ውይ ኢትዮጵያ! ቺድ! በቃኝ እባክህን፡፡ ሳይጠጡ የምታሰክር፣ ሳይኖሩባት የምታስረጅ ሀገር!!

ma74085@gmail.com

13 Comments

 1. የማይመስል ነገር ለሚስትህ አትንገር ይላሉ አበው። በምንም የሂሳብ ስሌት ጃዋርና እስክንድር ሊናበቡ አይችሉም። ሁለቱም ለየብቻ የቆሙ ናቸው። ግን ሊበሉት የፈለጉትን አሞራ ጅግራ ነው ይሉታል አይነት ሰለሆነ ጠቅላይ አቃቤዋ የፈጠራ ወሬ ነው የሚናገሩት። እውነት ነው ሁሉቱም ቆመናል ለሚሉት ዓላማ ሊፋለሙ ችለው ይሆናል። በተለይ ጃዋር “አምጸናል። አሳምጸናል” በማለት መናገሩን ልብ እንበል። ወያኔ በስልት ከሥልጣን ላይ ያሽቀነጠሩት እነዚህ የኦሮሞ ብሄርተኞች ቢዘፈን አይዘፍኑ፤ ቢለቀስ አያለቅሱ እንዲሁ የሚያረጉት ጠፍቷቸው ሌት ተቀን “ኦሮሚያ” ኦነግ እያሉ ሲያቅራሩ በውጭና በሃገር ውስጥ ማየት እጅግ ያስጠላል። የሰው ልጅ መኖሩ የሚመዘነው በክልል ፓለቲካና በቋንቋ፤ እንዲሁም በሃይማኖት ከሆነ ሰው እንስሳና ግ ዑዝ ነገር እንጂ ሰው አይደለም። ነዳጅ በጣሳ፤ ስለት በእጅ፤ ቀኑን ሙሉ እንደመልካም አናጢ ጣውላ ይዞ ሰውን ለመግደል ምስማር ሲተክል በመዋል በደቦ እየዞረ ውድመት የሚያደርስ ዘረኛ ትውልድ ለራሱም ሆነ ቁሜለታለሁ ለሚለው ጠንጋራ የዘር ፓለቲካ አይጠቅምም።
  በአንድ ውጭ ሃገር የኢትዮጵያን ባንዲራ በያዙና በኦሮሞ አላማ አንጋቾች መካከል የሃሳብ ግጭት ተነሳና የቃላት ልውውጡ ወደ ቡጢ ተቀይሮ ፓሊስ ይመጣል። የሃገሬው ኗሪና አልፎ አግዳሚው እያየ ያልፋል። በድንገት አንድ ነጭ ምንድነው ችግሩ ይላል። አይ እንዲህ እና እንዲያ በማለት ሌላው የገባው ነጭ ያስረዳዋል። ድምጽን ከፍ አርጎ “እነዚህን ጠራርጎ ወደ መጡበት መላክ ነው” ብሎ ተጨማሪ እርግማን እያሰማ አልፎ ሄደ። የሚገርመው በዓለም ዙሪያ ጠንጋራ የፓለቲካ እይታ ያላቸው ዘረኞች ሃገር በጥባጭ፤ የሰው ሰላምን የሚነሱ መሆናቸው ነው። በርግጥም ያሰኛል። አሁን ማን ይሙት ነጩና አረቡ ህዝብ ለጥቁር ህዝብ እርስ በርስ መፋለም ይገደዋል? ጭራሽ! ደንቆሮ ህዝብ ግን እርስ በርሱ እየተፈላለገ ከእጣ እጣት ይበልጣል በሚል የዘር፤ የጎሳ፤ የሃይማኖት ፓለቲካ ይሸራገዳል። ማን ያዝንለታል ቤትንና የደረሰ ማሳን እያቃጠለ ተራብኩ ቢል።
  ከሃገር ውስጥ የምናያቸው ምስሎችና ቪዲዮዎች፤ የምንሰማው ዲስኩርና የጠለፋ ፓለቲካ አያድርስ ነው። አንተ ጉራጌ ነህ ውጣ፤ አንቺ አማራ ነሽ ውጭ፤ አንተ ትግሬ ነህ ውጣ ምን ማለት ነው? የት ነው የሚወጡት። እንደዛስ ከሆነ እንዴት የኦሮሞ ዲያስፓራዎች ኦሮሞን በመወከል በውጭ ሃገራት ይሰለፋሉ እነርሱም ይውጡ ቢባሉ ምን ይሰማቸው ይሆን? እነዚህ የፓለቲካ ውሾች ሰው ተወልዶ ባደገበት ሃገር ሃገርህ አይደለም ውጣልን የሚሉት የፓለቲካ ዘይቤ እውርነት ነው። ግን ፓለቲካ እንደ ቀትር ጥላ መሆኑን የጅምላ ሃገር አቃጣዪችና ገዳዮች አይረድም። ያፈሰስከው ደም፤ ያቃጠልከው ቤ/ክርስቲያንና የንግድ ተቋማት፤ ገለህ የቆራረጥከው የሰው ልጅ ደምና በመኪና የጎተትከው አስከሬን የሚፈረድለት ቀን ይመጣል። ያኔ ምን ሊውጥህ ነው። አሁን በኮቪድ የሚያልቀው ህዝብ ያንተን ቤት አንኳኩቶ እምሽክ ቢያረግህ በማን ልታመካኝ ነው? እንደ ጉንዳን ሰው ለመግደል አንድ ላይ ሆ እያልክ ስትተም ብትያዝ? እብድ ብቻ ነው ሃገሩን በእሳት የሚለኩስ። የኦሮሞ ብሄርተኞች እብዶች ናቸው። ለነገሩ የማንኝውም ዘር ቢሆን የክልል ፓለቲካን ድጋፍ አድርጎ ሌላው ወገኑን የሚጠላና የሚያሳድድ ሁሉ ሙት ነው! መኖር በህብረት ሲሆን ሞታችንም ያምራል። አይ ፓለቲካ ድንቄም ፓለቲካ ዝንተ አለም መዘናጠል። ሁሌ ቆንጨራና ቢለዋ ጠበንጃና የሚስማር ጣውላ ይዞ እንዘጥ እንዘጥ ማለት። ስንት በህይወት የሚሰራና የምንማረው መልካም ነገር እያለ በሃበሻ ፓለቲካ ጢምቢራን ማዞር። የዶ/ር አብይ ጠላቱ ራሱ ነው። ገና ከጅምሩ የጃዋርን የውሸት የድረሱልኝ ጥሪና ሞት መፍትሄ ቢሰጥ ኑሮ ዛሬ ለደረሰው አስከፊ ድርጊት ባልበቃን ነበር። ያው የዘር ፓለቲካ ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ሆነና ገና አያሌ መከራዎች እናያለን። በየመድረኩ ሲያቀነቅኑ የነበሩት አቶ ለማ መገርሳ ዛሬ ብቅ ብለው ምንም ነገር አለማለታቸው “በዘሩና በቋንቋው የተለከፈ ትውልድ መዳኛ እንደሌለው ያመላክታል”. በአማራ ስም ለዘመናት የነገድት የአማራ አመራሮች ሰው እንዲህ ሲያልቅ አብረው ዘጥ ዘጥ ማለታቸው የፓለቲካን ጊዜአዊ ፍጆታ ያሳያል። የትግራዪ ወያኔ “የትግራይ ህዝብ ተከበሃል፤ ታጠቅ፤ ተሰማራ” የሚለው የዛሬ 45 አመት በተገጠመለት ጭንቅላት በማሰብና በዚያው ሳንባ በመተንፈስ ነው። የትግራይ ህዝብ ነቅቷል። አዲስ አበባ በሃገሪቱ መንበር ላይ እያለ ያላቋጠረውን የትግራይ ህዝብ አሁን እንደገና ለተጨማሪ እልቂት እንዲዘጋጅ መገፋፋቱ ወያኔ ለትግራይ ልጆች ደም እንደማይገደው ያሳያል። እናንተ የቀበራችሁት ደባ አይደል እንዴ አሁን ሃገሪቱን የሚያተራምሳት? እናተ አይደል እንዴ በአረብና በሌሎች ሃይሎች እየተረዳችሁ ድልድይና የሃይል ማመንጫ አውታሮችን እያፈረሳቹሁ ከሻቢያ ጋር በማበር ሃገርን የሸጣቹሁት? ምን ለማለት ነው ህገ መንግሥቱ አልተጠበቀም ማለት? ግን ፓለቲካ ወልጋዳ ነው። የትም ይሁን የትም ተንሻፎ እንጂ አምሮበት ታይቶ አያውቅም። ወያኔዎች እባካቹሁ ህዝባችን የእሳት ማገዶ አታድርጉት። የኦሮሞው እሳት ለዚያውም በእናንተ መሪነትና እርዳታ የተለኮሰው ይብቃ። ባጭሩ የጠቅላይ አቃቢዋ ቃል ከእውነት የራቀ የጃዋርና የእስክንድርን የፓለቲካ እይታና አሰላለፍ ያልተረዳ የትየ ለሌ የሆነ ንግግር ነው። ከህጻን ልጇ ተለይታ የDHL ፓስታ መቶልሻል ተብላ ስለተያዘችው ሴት አቃቢዋ የሚሉት ይኖር ይሆን? ግን የለም። አይጣል። እንዲህም ብሎ ነጻነት የለም። በቃኝ!

  • ተሥፋ! ይህ አስተያየትህ እኮ ራሱን ችሎ አንድ መጣጥፍ የሚሆንና በየድረገፆች ተልኮ ሊነበብ የሚችል ነው። ታዲያ ለምን አሥተካክለህ አትልከውምና ለበርካታ አንባቢዎች ተደራሽ አታደርገውም?
   ሥላገርህ ያለህን ‘ተንጫጭሮት’ እንደሁሌው ሁሉ ዛሬም አደንቅሃለሁ። እንዲህ እንደተንጨረጨርንም አንቀርም፤ ሀገርን መምራት ዱባና ድንች እንደመግመጥ የሚመሥላቸው ዋልጌ ዘረኞች እሳቱን እንዲቀምሱትና በዚያውም በእግረ መንገድ እኛም ትዛዛቱን ስለመተላለፋችን ሊቀጣ አምላክ ሽቶ እንጂ ወደ መልካም እጆች መግባታችን የጊዜ ጉዳይ ነው። ጠባቧ ቀን ስታልፍ የሚደርሥ ይደርሥባታል፤ ለዚያች ቀን ለመድረሥ ግን የእውነትን ዘገር መጨበጥ ይገባናል። በዘረኝነት ልምሻ ተኮድኩደን ወገቡን እንደተመታ እባብ ወዲያና ወዲህ ውልሚጥ ውልሚጥ ማለት የለብንም። ዘር ከልጓም መሣቡን disprove ማድረግ ይጠበቅብናል።

 2. ድብብቆሽ የሌለበት ጥሬ ሃቅ! በውነት ግሩም ትንታኔ ነው አቢያውያንን ማሥቆጣቱ የሚጠበቅ ቢሆንም።

 3. በቄሮ የታረዱት :ሬሳቸው በመንገድ የተጎተተው ንፁሀን ዜጓች ደማቸው ይጮሀል። ፍትህ እንሻለን። የፍትህ ያለህ!!! መንግስት በኦነግና ወያኔ ቅንብር ለተገደለው ዘፋኝ ሀጫሉ ሀውልት ሲያሰራ በግፍ ለተጨፈጨፉተት 300 ዜጎች ሀውልት ቢቀር መዘከር እንዴት ተሳነው?

 4. “ከእንግዲህ አቢይ ኢትዮጵያን ወደ ወርቃማ ጊዜዋ ያሻግራታል ብሎ ራስን ማታለል ሲበዛ የዋህነት ነው”

  እኛ የዋሆችና ሞኝሞኞች አይደለንም:: ዛሬ ላንቃው እስክሚሰነጠቅ ለእስክንድር የሚጮኸው ወያኔ ነው:: ኢትዮጵያን የማፈራረስ ጦርነት በባንዳው ወያኔና ተላላኪዎቹ ተጀምሯል:: ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው አንድነት ከዐቢይ መንግስት ጋር ይቆማሉ:: ኢትዮጵያውያን ደግሞ ባንዳውን ድባቅ ይከታሉ::

 5. የአቢይ መንግስት ከፍተኛ ውጥረት በህውሀት ማምጣቱን በግልጽ የምናይበት መድረሳችንን ሳስበው ለፈጣሪ ምን ይሳነዋል ያስብላል። so much so በርግጠኝነት ኢትዮጵያዊያን ናቸው ብዬ ስጃጃል የነበሩት ሁሉ ghost amaras ሆነውብኝ ዳግም ሊያጃጅሉኝ ሲሞክሩ ማየት ያማል። ይህ መጣጥፍ አረጋገጠልኝ። አቃቢት ጄኔራል “እስክንድርና ጁዋር ተናበው ነው የሚሰሩት” ማለቷ how about መረጃና ማስረጃውን ካቀረበች? መጠበቁ አይሻልም የአቢይን መንግስት ወደ ሲዖል እየወሰደን ነው ከማለት?

  እሺ ወንድም ጉዱ ካሣ! ምን የቀረህ አለህ? በግልጽ እኮ “ይህ እራሱ ከሀዲ የሆነ መንግስት ነው፣ መጪው ዘመን ብሩህ እንዲሆንላችሁ የብዙ ሺህ ዘመን ያላት ኡትዮጵያ በትግራይ ሪፐብሉክ ፕሮቴክቶሬትነት ስር ገብሩና የየራሳችሁን ሪፐብሊክ ፍጠሩና ተመልሰን እናስተዳድራችሁ፣ ላሁን ግን አርማጌደኑን እንድንታደጋችሁ እኛኑ መልሱን እናንት ንኡሳን የማትረቡ አለኛ አይናችሁ የጨለመ ደመነፍሶች” እያልከን እንደሆነ ልብ ብለሀል? “ወይ-ለከ”አለ አንድ ለአገሩ የሚንጨረጨር ቶለሣ ኢብሳ የሚሉት ልጅ። ምነው ጭምብልህን እንደለበስከው በቀረህውና ጽሁፍህን እንደወትሮዬ እያነበብኩ ብትከዝብት ኖሮ። ደሞ “ወልፈካቲን ወልበርባዲ ” ብለኸኛል ለካ። ለኔ የተመኘኸው መስታወትስ ለአንተው አይሻል ብለህ!? እዛው እራስህን ስታይ የምትውልበት? እስቲ እንጠብቅ ማ ደሞ እንዳንተው ጭምብሉን የሚያወልቅ ለያውም በዚህ የከፋ ኮረና ዘመን ። ወደው አይስቁ አሉ። ፈጣሪ እናንተንም በህይወት አቆይቶ ይህ እንዲህ የናቃችሁት ፍጹም ኢትዮጵያዊ የሆነው አቢይ አገራችንን በሰላም አሻግሮ ለማየትና ለመጸጸት ያብቃችሁ – መቼስ አንድ ሰው ይጠፋል የሚጸጸት? ሰላም ሁን ጉዱካሣ! አይቀናችሁም ግን። ገና ብዙ ህይወትና ንብረት ሊወድም ይችላል ሆኖም በመጨረሻም አይሳካም። ለምን? እውነቱ እናንተ ዘንድ አይደለምና። በዛ ላይ የፈጣሪንም ቁጣ አትዘንጋ። ትንሽ ብትታገስ ኖሮ በተሻለ። ምን የሚያስቸኩል መጣ ግን? አሃ! ለካ አቢይ ወጥሮ ይዟል በአራቱም ማእዘን። በርታ ወንድም አለም!!

  • እ? አባዊርቱ? ምን አልከኝ? ጆሮየን ተጠራጠርኩት ልበል?
   “በቅሎ አባትሽ ማን ነው ብትባል እናቴ ፈረሥ ነች” አለች ይባላል። አንተ ኦሮሞ እንደሆንክ ትናገራለህ፤ ጥሩ ነው። ለኢትዮጵያም መጥፎ ሃሣብና የጥፋት ድግሥ እንደሌለህ ከጽሑፎችህ መረዳት ይቻላል። ይህም በጣም ጥሩ ነው። እናም እንዳንተ ያሉ በአብሮነት ባህል የታሹ ኢትዮጵያውያን ኦሮሞዎች አሁን ቢገዙ ሀገራችን አሁን ካለው የአንተን ጎሣዊ ቡራኬና ድጋፍ ካገኘው የዐውሬ ቄሮዎች መንግሥት በተሻለ የዘረኝነት ቅኝት ማስተዳደር እንደሚችሉ እገምታለሁ።
   በተረፈ የለጠፍክብኝ የዘር ታርጋ ትውውቃችንን ይበልጥ ፍንትው አድርጎ ከማሣየቱ በሥተቀር ከሥሜት የተወለደ የሃሰት ግንዛቤ ለመሆኑ አንባብያን ብቻ ሣይሆኑ የወቅቱ የሀገራችን ሁኔታ አፍ አውጥቶ የሚናገረው ነው። ሰውን መወንጀል የመጨረሻው ቀላል ነገር መሆኑን አውቃለሁ – መፈረጅም።
   እኔም እንዳንተው ስጃጃል መኖሬን ተረዳሁ – “ይህ ሰው የተሻለ ‘ኦሮሞ’ ሣይሆን አይቀርም” እል ነበር – አልጸጸትም፤ ጊዜ አለን ብዬ አምናለሁና። ዘረኝነት የፍየል ሥጋ ነው። ገና ብዙ ያሥወጣል።
   ግን ግን አማራ ይግዛ የሚል እንኳንስ በጽሑፌ በአእምሮ ጓዳየም የለም። በዚህ መጣጥፍ ዜጎች ከተኩላና ከቀበሮ ራሣቸውን እንዲከላከሉ ከመምከር ውጪ አማራ ሥልጣን ይያዝ ያልኩበት አንድም ሐረግ የለም። አሥፈላጊ ቢሆን ኖሮ ማን ሥልጣን ቢይዝ ሀገር ልትረጋጋና እንደሀገርም ልትቀጥል እንደምትችል መጠቄም እችል ነበር – ከጥቆማየ ውሥጥ ጄ. መርዳሣ ሌሊሣ፣ ጄ. ካሣየ ጨመዳ፣ ፕሮ. ፍቅሬ ቶሎሣ፣ አቢ ሳኖ … ከመጀመሪያው ተርታ የሚካተቱ ናቸው። ዘረኝነት ይገማል፥ይጠነባል። እውነትን ይጋርድና በምናባዊ የወገንተኝነት ጭምብል ኅሊናን ጋርዶ በደሥታ ያሥቦርቃል። እንጂ አሁን የአቢይ መንግሥት በምኑ እንዲህ በፍቅር ሊያማልል ይችላልና ነው እንታገሰው እንጠብቀው የሚያሥብል? ያለፉት 3 ዓመታት ለኢትዮጵያ የኬክ ቆረሳና የሻምፓኝ እርጨታ ነበሩ ለማለት ነው? ቄሮ አማራን አላረደም? ቄሮ አዲስ አበባን አልተቃረጠም? ምን ማለት ነው “ብሶትን አትናገሩ፤ ዝም ብላችሁም ሙቱ” ብሎ ፍርደ ገምድል መሆን? ዘረኝነትም ልክ ሊኖረው ይገባል፤ ጭፍን ዘረኝነት ያሥተዛዝባል።
   አባዊርቱየዋ! በሠላም ያገናኘን። የወሎ ኦሮሞ ነኝ። ኦሮሞነትና አማራነት ማንም በማንኪያ እየለካና ከድብኝት ወይ ከማሰረ እየጨለፈ የሚሰጠው የገዳም መቁነን ሣይሆን ኢትዮጵያ ውሥጥ በመኖርና ኢትዮጵያዊ በመሆን የሚገኝ ፀጋ ነው። በደልን መናገርና በዳይን ማጋለጥ፣ የተበደለንም መደገፍ ተፈጥሯዊ ግዴታ እንጅ ዘረኝነት አይደለም…
   እግዚአብሔር በምሕረቱ ይጎብኝህ፤ እውነቱንም ይግለጥልህ ወንድማለም ፤ “ሣንተዋወቅ ተጋባን፥ ሥንተዋወቅ ተፋታን” አለ አንድ ነገረኛ የቀድሞ ባል።

  • “አባዊርቱ”
   ጉዱ ካሳ ቀበሮ እንደሆነ እንዴት እስካሁን አልለየኸውም? እስቲ አባባሎቹን ደግመህ አጢናቸው። “ይህ ሰው የተሻለ ‘ኦሮሞ’ ሣይሆን አይቀርም እል ነበር” ይልሃል። ራሱን መዛኝና ሿሚ ሲያደርግ እንኳ አያፍርም? እሱ ከማን ተሽሎ ነው? በርሱ እይታ “ኢትዮጵያዊ” የሚኾነው የርሱና የመሰሎቹን አጀንዳ በመፈጸም ብቻ ነው! አይገርምም? እንዲህ ዓይነት ሰዎች በ21ኛው ክፍለ ዘመን መገኘታቸው?

 6. እግዜር ይስጥልን፥ጽሑፉ እውነተኛ ኢትዮጵያውያንን የሚያስማማ ግሩም ጽሑፍ ነው።ባጭሩ ለማከል ያኽል፤
  ሆደ ሰፊ ኾነን ታግሰናል ሲል የምንግሥቱ ቃል አቀባይ የጭፍጨፏው ግብረ ዐበር መኾኑን አረጋግጧል። ስው ሆደ ሰፊ የሚኾነው ራሱ ሲጠቃና ግድ የለም ብሎ ችሎ ጠቃቱን ሳይመልስ ሲቀር ነው። ሌላ ሰው ሲጠቃ ዐልፎ መኼድ ወይም ዳር ቆሞ ማየት ሆደ ሰፊነትም ታጋሽነትም አይዶለም። ሲኾን ጥል አልገባም በሎ ራስን ማግለል፥ ወይም ለራስ ፈርቶ እንዳላየ ኾኖ የተጠቃውን ሰው ትቶ ዘወር ማለት አለዚያም ተጠቂው እንኳን ተጠቃ እሰየው ብሎ ማለፍ ወይም ቆሞ ማየት ነው።
  መንግሥት፥ የህዝብን ድኅንነት መጠበቅ ዋና ተግባሩ ሳለ፥ ሰላማዊ ዜጋ ሲጨፈጨፍ ታገስኩ ካለ፥ ቆሜ አይቻለኹ። ህዝብን የመጠበቅ፥ ወንጀለኛን የመያዝ ግዴታዬን አልተወጣኹም ብሎ አመነ ማለት ነው። ይህ የሚያሳየው መንግሥት ነኝ ባዩ በራሱ ላይ የመሰከረ የህዝብ ጠላት መኾኑን ነው።
  ለኢትዮጵያ ህዝብ፤ ሳይመርጠው፥ ሳይሰይመው ራሱ ላይ ቁጭ ብሎ የሚጫወትበትን ባእድ አካል አውርዶ፥ ራሱ ባረቀቀው ሥርዓተ መንግሥት መሠረት መሪውን መርጦ ራሱን በራሱ ከማስተዳደር በቀር ሌላ ማማረጫ ፈፅሞ የለውም።
  ፈቃደ።

 7. አይዞን አይዞን! ወደድንም ጠላን ያልበሰለ ጠ/ሚር አለን እሱኑ እንዲበስል lመነዝነዝ ነው የሚያዋጣው፡፡ ጠ/ሚሩ ያሉት አማራጮች እየጠበቡ ስለሆነ የአሻንጉሊት መንግሥት ሆኖ በሥም መኖር አይችልም፡፡ መንግሥታዊ ተግባራቶችን ለሕብረተሰቡ በማያዳላ መንገድ መተግበር ይጠበቅበታል፡፡ አሁን ለእኛ ብሎ ሳይሆን ለእራሱም ህልውና ሲል እስክዛሬ ያላገጠውን ያህል እንደማያዛልቀው ተገንዝቦ የመሪነት ተግባሩን ያሳየን ይሆናል፡፡
  ኢትዮጵያ ከዓለም ሁለተኛ ነች በኦርቶዶክስ ተከታይ እምነት ቁጥር ብዛት፤ ከዓለም!! ለመጀመሪያ ግዜ በኢትዮጵያ 3ሺ ዘመን በዚሁ ጠ/ሚር ዘመን ነው የሌላ እምነት ተከታይ ጋር ሲኖድ ቁጭ ብሎ የሚባረክበት ዘመን የደረሰነው፡፡ ክርስቲያኑ እየታረደ ያለው የአስላም አክራሪ የኦሮሞ ጅዋር ቡችላ ፔገንስ እንደሆኑም የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ እየሄድን ያለነው ወደመጥፎ አቅጣጫ እረኛ እንደሌለው መንጋ ነው፡፡ ይኅውም መሪ አለመኖሩን ነው የሚያሳየው፡፡
  መጀመሪያ ግን ያለውን መሪ ህዝቡም እንዲተባበረው መጀመሪያ እራሱ ጠላቱን እና ወዳጁን መለየት ያስፈልገዋል፡፡ አክራሪ ኦሮሞዎችን እየለቀመ ማጽዳት እና የኦሮሚያ ሀገር ግንባታ የቀን ቅዥታቸውን እወነት እንደማይሆን ደጋግሞ ለአመራራቸው፤ ለብጤዎቹም ቁልጭ አድርጎ ማስረዳት አለበት፡፡ ከዚህ በኋላ እያደባበሰ ማወናበዱን አቁሞ ጥርት ያለ መልእክት መስጠት ግዴታው ነው፡፡
  በእርግጥ እስከአሁን የተረዳነው የአብይ አስተዳደር በጉልቻነት የተቀመጠ መንግሥት እንጂ ምንም ኃይል እና ስልጣን እንደሌለው ነው የሚያስረዳው፡፡ እስከአሁን ያየነው በቀበሌው ሁሉም መንግሥት እንደሆነ ነው፡፡
  የአስከአሁንን ጥፋት ወደጎን እናድርግ እና ከዚህ በኋላ ዕቅድ አለው ወይ? ኃይሉንስ እንደገና መመለስ ይችላል ? ነው ጥያቄው፡፡ ወያኔ እና ጀዋር ሳይፈነግሉት ከቀልቡ ተመልሶ እንደ መሪ ቢያስብ እና ቢተገብር ይሻላል፡፡

 8. በውስጤ ያለውን እየተንቀለቀለ መኝታ አልጋዬን እያጣበበ እንቅልፍ የነሳ ረመጥ ስሜት ከመስል ጎደኞችና ሳወራና ሳነብ ትንሽ እረፍት ብጤ እንቅልፍ ብጤ ቢጠልኝም ከቅዥት ጋር ነው::
  አስመሳዩን አብይ እንደዛሬው ሳይሆን ከጅምሩ የወይኔን ስቆቃ ግፍ አገዛዝ እንደዛሬው ሳይብስ 14 ስዕት ይለድካም ከጎደኞቼ ገር ነድተን ከስባት ስዕት በላይ ስልፍ ወደ አዳራሹ ለመግባት ተስልፈን ነበር እውነት መስሎን በዚህም ላይ የአመት መዋጮ ገንዘብ ሳናመነታ ስጥተን ነበር::ግና ተስፋችን ድካማችን ዛሬ ከንቱ ሆኖ ሀገሬ ወይም በእለም ታሪክ ስው በራሱ አምሳል ዛሬ ቄሮ ብሎ በሚጠራው አውሬ መንጋ ቡድን በስው ላይ ይህን አይነት ጭካኔ ይፈፅማል ብሎ የማይታስብ ተፈፅሞ ስናይ ስንስማ ያማል;::ቄሮ የራሱን አብሮ የኖርውን ወገኑን በገጀራ ሲገድል : አይን በሹል ብረት እየጎለጎለ ሲያወጣ እጅ ጡት ሲቆርጥ ቤተስብ ፊት ተራ በተራ እያወጣ አንገት ሲቀላ ሬሳ ሲደፍር ሬሳ ሲያቃጥል ቤት ውስጥ ገድሎ አንዳንዴም በላያቸው ላይ ቆልፎ ሲያቃጥል በዚህ ሁለት ዓመት በአብይ መስተዳድር በኦሮሞ ወጣቶች መፈፀሙ ምናልባት ምናልባት መለስ ዜናዊ በህይወት ኖሮ ቢሆን እየጠላሁትም ቢሆን የዚህ ሁሉ ምንጭ መሆኑን ባስብም ይህ የዛሬው በአብይ ዘመን አይነት እልቂት አናይም ነበር::የኦነግ የበደኖ የጎለልቻ አማራን ግድያ በዛም ዘመን መሳርያ በአነገቡ የኦነግ ወጣቶች ነበር ይፈፀም የነበረው::ግና አልቀጠለም ኦነግ ተስናበተ::
  አብይ እራሱ እንደሚነግረን በ14 ዓመቱ በህውሀት ቅስቀሳ ኦሮሞ በነፍጠኛው አማራ ተበድሎል በሚል ለትግል መውጣቱን አብስሮናል::በስራውም ህውሃት ታማኝነት ከሲቭል ስርቪስ አስተምረው ድግሪውን ሽምተውለት በተለያየ የስልጣን እርክን አብቅተውታል::አሁን ለአለበት ስልጣን የህውሃት ምንጭ ነው;:መርሳት የሌለብን የርሳቸው ወይም ይድርጅታቸው ከህውሃት ጋር ልዩነታቸው በስልጣን እንጅ በመርህ ደረጃ አንድ ናችው:;:ሁለቱም የፅንፈኛ ብሄር አራማጆች አማራን ጠላት ያደረገ ቢሆንም እንደ አብይ ድርጅት የወረደ ፅንፈኝነት የሀገር ጠላት አለ ብዬ አላስብም;;
  አብይ እጅግ አደገኛ አስመሳይ ውሽታም ስው ነው::ከእነጁሀርም ጋርም አንድ ናቸው::በአፈፃፀም ደረጃ ነገሮች ቀስ በቀስ የኦሮሞን ፅንፈኝነት የሚያራምድ ነው::እስቲ እውነት እንደ አፉ የሚለው ኢትዮጵያዊነት ስሜት ቢኖረው ኖሮ እስክንድርን እነክርስትያንን አብን እነ ኢንጅነር ይልቃል ከኢትዮጵያ ምድር ለማጥፋት የተንኮል ድሩን አይዘረጋም ነበር::አለማስተዋሉና ስልጣን እውር እንዳደረገው ና ሌላው ይረዳዋል ብሎ አለማስቡ ነው::
  እስቲ አስቡት በኦሮምያ ክልል የራሱን ስራዊት እየገነባ ነው::ለምን አስፈለገ የፌደራል ስራዊት እያለ?ልቡ አድርጉ የሚወጣውን ወጪ::
  ያም ብቻ አይደለም የክልሉ የሌላ ብሄር ተወላጅ ራሱን ከጥቃት እንዳይከላከል እያደረጉት አልፎም አሁን ለተፈጠረው ጥቃት አሳልፈው ስጥተውታል:: ይህን ለየት ያለ መልክ በኦሮምያ የሚስለጥነው ስራዊት እመኑኝ ክልሉን የሚያጠፋ ወደለየለት የብሄር ጦርነት መንስኤ እንደሚሆን ይታየኛል::
  ውሽታሙና አስመሳዩ አብይ በዙርያው ቁልፍ ቁልፍ የፌደራል ስልጣን እንደወያኔ ይዞል:አዲስ አበባ ላይ ታከለነ ጨምሮ:::እንደ ህውሃት ሁሉ በራሱ ትርክትና ተውኔት እየፈጠረ የአብይን አካሄድ አስቀድመው የነቁ ቆራጥ ለጥቅም የማይገዙ ትን እንደ የአብን ክርስትያንን የባለደራሱን እስክንድርን አማራጭ ሀይሉን እንጅነር ይልቃልን እንደፈለገው ያስራል ይፈርጃል!ራሱ ከሳሽ ራሱ ፈራጅ ሆኖ::ይወንድማችን አጫሉ ሞት አንድ ድራማ ያለበት ለመሆኑ ጥርጥር የለውም::ከህውሀት የሚለዩት ዝቅተኛ ክህነቶቻቸው ስለሆነ በቶሎ እንነቃለን:;: በመሆኑም በምንም ተአምር ገዳዩም የደረስው በደልም በገለልተኛ እንዲጣራ አይፈፋጉም ለምን የሚደግፉት እጃቸውም ስለአለበት;;አብይ ኮ ገዳዩን ዶር ወርቅነህ ገበየሁን ያሽሽ ነው::ለምን ብትሉ እርሱም በይንዳዱ ጉዳይ ስላለበት!
  እመኑኝ አብይ ሀገሪቱን ወደተሻለ መረጋጋት ያመጣል ብሎ ማስብ ህልምወይም ቅዥት ነው::አሁን ኦሮሞ ብልፅግና በስልጣን ስክሮል ፅንፈኝነቱ ተደባልቆ አእምሮው ነትቦል:አገሪቱ ይህን በታሪኩ አይታውቅ ጥፋትና ከመፍረስ የትድነው ሁሉም ክልሎችበአገሪቱ ጉዳይ ላይ አስገዳጅ ውይይትና ስምምነት ሲደርሱኑ ሙሉ በሙሉ በሚያስችል ደረጃ በፅንፈኛ ኦሮሞ የተያዘው በሌላውሲይዝ ነው::ህውሀት ወደ ህሊናው ተመልሶ ወንጀለኞችን ለህዝብ ፍርድ አሳልፎ በመስጠት ህዝባዊ እርቅ በመፍጠር ወደጣምራ ሀይል መምጣት አለበት:;:በተለይም ከአማራ ክልል ጋር የተወስዱትን ወረዳዎች በመመለስ ህዝቡ በራሱ በመረጠው እንዲተዳደርና ከአማራ ጋር አንድ ሀይል ሆኖ መውጣት አለበት;::ይህም ቢሆን ከፍተኛ ስራን ይጠይቃል ;:ለምን አስመሳዩ አብይ የሚከውነው ተውኔትና ደባ ቀላል ስላልሆነ::ምስማር ሲመቱት ይጠብቃል እንዲሉ እየደረስብን ያለው ይበልጥ በቶሎ እንድንነቃ አድርጎናል;;እስክንድር ከፍ እንዲል!አብይ መስሪነቱ ግልፅ እንዲወጣ!ቄሮና ኦነግ በአለም አቻ የሌላቸው አሽባሪዎችና ጨካኞች እነደሆኖ!ወራዳዋ አዳነች አቤቤ ተተኪዋ ገነት ዘውዴ እንደሆነች አውቅን!
  ወንድም አለም ተባረክልኝ!ሀገሬ ብርቅዬ ልጆች አሉዋት!!

  • በናትህ አብንን አውጣ አታውቃቸውም:: ከወያኔ የሀገር ማፍረስ የረቀቀ ድራማችሁ ውስጥ የሉም:: የመስከረም 30 ልጆች::

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.