ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዛሬ በለንደን ከተማ ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ

109578999 10217865726215881 3058099329890923188 n መንግሥት በወንጀለኞች ላይ ተገቢ እርምጃ እንዲወስድ ተጠየቀ

መንግሥት የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ሞት ተከትሎ በኢትዮጵያ በግፍ ግድያ የፈፀሙ እና ንብረት ያወደሙ ግለሰቦችን ለፍርድ እንዲያቀርብ ተጠየቀ። ተጎጅዎችም ፍትህ እንዲያገኙ ተብሎአል። በብሪታንያ መዲና ለንደን ላይ የተደረገዉን ሰልፍ የጠራዉ የኢትዮጵያዉያን ትብብር በብሪታንያ በሚል የተደራጀ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ አአካል ነዉ

በብሪታንያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዛሬ በለንደን ከተማ ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ በድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ሰበብ ሰዎችን በገደሉ ንብረት ባወደሙና በዘረፉ ዜጎችንም ባፈናቀሉ ላይ መንግሥት ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ጠይቁ።መንግሥት ለተጎጂዎች አስፈላጊውን እርዳታ እንዲያደርግም ጥሬ አቅርበዋል። መሰል ድርጊቶች ወደፊት እንዳይፈጸሙም መንግሥት የዜጎችን ደህንነት በአግባቡ እንዲጠብቅም ጠይቀዋል።መንግሥት ይወስዳል ያሉትን ሕጋዊ እርምጃ እንደሚፈግፉም ሰልፈኞቹ አስታወቀዋል። ጥሪዎቻቸውን የያዘ ደብዳቤ በኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ጽህፈት ቤት መላካቸውንም ለዶቼቬለ ተናግረዋል። የለንደኑ ወኪላችን ዝርዝሩን ልኮልናል።

London 1

ድልነሳ ጌታነህ

54222807 303

ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ/ DW

1 Comment

  1. ያሳዝናል ሰልፉ ከ get together ያለፈ ፖለቲካዊ ፋይዳ የለውም። 300 ዜጋ ታርዶ ስፍር ቁጥር የላለው ንብረት ወድሞ ስለ ጄኖሳይድ አታብሰፕ ስለ እስክንድር ስንታየሁቸኮል አታንሱ ስለ ቤተ ክርስቲያን ቃጠሎ አታንሱ ማለት ትርጉም አይሰጥም። አላማ የሌለው ዳንኪራ ብዬ አስበዋለሁ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.