ኦኤምኤን አርቲስት ሃጫሉን እንግዳ ለማድረግ ቀደም ሲል የነበረውን ፕሮግራም ስያሜና ቅርጽ ሆን ብሎ ለውጧል

107869302 1696916467126361 9201809239380574015 nኦኤምኤን የተባለው ሚዲያ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን እንግዳ አድርጎ ለማቅረብ ሆን ብሎ የፕሮግራሙን የይዘትና የስያሜ ለውጥ ሳይቀር ማድረጉን አስታውቋል።
ኦኤምኤን ቀደም ሲል እንግዳ የተባለውን የፕሮግራሙን ስያሜና የይዘት ለውጥ ማድረጉን የገለጸው የፕሮግራሙ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጉዮ ዋሪዮ የተባለው የፕሮግራሙ አዘጋጅ ፤ “ዛሬ አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሊመረመር እንግዳችን አድርገነዋል” በማለትም ኦኤምኤን ለምን ሃጫሉን እንግዳ እናደደረገው ቆርጦ ባስቀረው የአርቲስቱ ኢንተርቪው ላይ ተገልጿል።
“የእንግዳ ፕሮግራማችን መቅረብ ከጀመረበትና ኦኤምኤን ከተመሰረተበት ከአምስት ዓመት በፊት ጀምሮ መንግስት ባለስልጣናትን ፣ አባ ገዳዎችን ፖሌቲከኖችንና ሌሎች ለኦሮሞ ህዝብ ትልቅ ስራ የሰሩትን ወደ ፕሮግራሙ በማምጣት አቅርበናል” ያለው የፕሮግራሙ አዘጋጅ፤ አርቲስቱ እንግዳ በሆነበት እለት ለምን የፕሮግራሙን ቅርጽ ለመለወጥ እንደፈለጉ ግን ያለው ነገር የለም።
አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ በኦነግ ሸኔ በተጠነሰሰ ሴራ ከተገደለ በሁዋላ ኦኤምኤን የተባለው የቴሌቪዥን ጣቢያ አዲስ አበባ ከሚገኘው ቢሮው በቀጥታ ስርጭት ብሄርን ከብሄር የሚያጋጭ ዘገባዎችንና ቅስቀሳዎችን ሲያስተላለፍ እንደነበር ይታወሳል።
ኢ ፕ ድ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.