ከውጭ የሚመጣ መንገደኛ በ72 ሰዓታት የሚጠበቅበት የኮሮናቫይረስ ምርመራ ማረጋገጫ ወደ አምስት ቀን ከፍ ተደረገ

108593396 1306699169505074 4325387186452706636 nከውጭ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣ መንገደኛ በ72 ሰዓታት ውስጥ ተመርምሮ ‘‘ከኮሮናቫይረስ ነፃ’’ የሚል ማረጋገጫ እንዲያመጣ የሚያስገድደው መመሪያ ወደ አምስት ቀናት ከፍ መደረጉን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የሚኒስትሮች ኮሚቴ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅታዊ ሁኔታና ቀጣይ አዝማሚያ፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም እንዲሁም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ዛሬ ተወያይቷል።
ከዚህ ቀደም ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣ ማንኛውም ዜጋ በ72 ሰዓት ጊዜ ውስጥ ተመርምሮ ከቫይረሱ ነፃ የሚል ማረጋገጫ ሲኖረው ወደ መግባት እንደሚችል ነገር ግን በቤቱ ለ14 ቀናት እንደሚቆይ የሚደነግግ መመሪያ ወጥቶ ነበር።
ከውጪ የሚመጡ ዜጎች የምርመራ ውጤት ካልያዙ ለሰባት ቀን ወደ ለይቶ ማቆያ እንደሚገቡም ይታወቃል።
ዛሬ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳስታወቁት በበርካታ አገራት ምርመራው ጊዜ የሚወስድ እና መንገደኞችም በቶሎ ምርመራውን አድርገው ውጤቱን ይዘው መምጣት እንዲችሉ እና መንገዱ የሚፈጀው ጊዜ ታሳቢ ተደርጎ መሻሻል እንዳለበት አንስተዋል።
ባለቡት አገር ተመርምረው ኢትዮጵያ እስከሚገቡ ከሦስት ቀናት በላይ ይወስድብናል የሚል ቅሬታ ከተለያዩ መንገደኞች በመምጣቱ ነው ማሻሻያው የተደረገው።
ውጤቱ በጣም ከቆየ ያንን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እና የመከላከል ሥራውን በማያደናቅፍ ሁኔታ ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱንም አመልክተዋል።
ይህ በመሆኑ ከቴክኒክ ቡድን እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ተደርጎ 72 ሰዓታት ተብሎ የተቀመጠው ወደ አምስት ቀን እንዲሻሻል ተደርጓል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ይህ በመሆኑ በአምስት ቀናት ውስጥ የተደረገ የምርመራ ውጤት ይዘው የሚመጡ መንገደኞችን አየር መንገድ ሲደርሱ ናሙና እየተወሰደ የ14 ቀናት የቆይታ ጊዜያቸውን በቤታቸው እንዲቆዩ መደረጉ የተሻለ መሆኑን ነው የገለጹት።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ ሐምሌ 09/2012 ዓ.ም (አብመድ)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.