የኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፍ በጄኔቫ

22

ይህንኑ ጥሪያቸውን የገለጹባቸውን ደብዳቤዎችም ለተመ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና ለሌሎችም የተመድ ተቋማት አስገብተዋል።ሰልፈኖቹ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓቢይ አህመድም ደብዳቤ ልከዋል። በደብዳቤው መንግሥት ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ የደረሰውን ጥፋት ለማስቆም ፈጣን እርምጃ ባለመውሰዱ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

ስዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ዛሬ ጄኔቭ በሚገኘዉ የተባበሩት መንግሥታት ጽፈት ቤት እንዲሁም በሰብዓዊ መብቶች ተቋማት ፊት ለፊት ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ  ኢትዮጵያ ዉስጥ በአርቲስት ሃጫሉ ግድያ ሰበብ በግፍ ግድያ የፈፀሙ እና ንብረት ያወደሙ ግለሰቦች ለፍርድ እንዲቀርቡ ፤ ተጎጅዎችም ፍትህ እንዲያገኙ ጠየቁ። ዶቼቬለ ያነጋገራቸው ሰልፉ አዘጋጆች ፣የሃይማኖት እና የዘር ጥላቻን  የማያካሂዱ ተቋማትም ሆነ ግለሰቦች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጥሪ አስተላልፈዋል። ይህንኑ ጥሪያቸውን የገለጹባቸውን ደብዳቤዎችም ለተመ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና ለሌሎችም የተመድ ተቋማት አስገብተዋል።ሰልፈኖቹ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓቢይ አህመድም ደብዳቤ ልከዋል። በደብዳቤው መንግሥት ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ የደረሰውን ጥፋት ለማስቆም ፈጣን እርምጃ ባለመውሰዱ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።።መንግሥት ቸልተኝነቱን አቁሞ አሁን በጀመረው መንገድ ወንጀለኞችን ለፍርድ ማቅረቡን እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

https://www.dw.com/am/%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB%E1%8B%8D%E1%8B%AB%E1%8A%95-%E1%88%B0%E1%88%8B%E1%88%9B%E1%8B%8A-%E1%88%B0%E1%88%8D%E1%8D%8D-%E1%89%A0%E1%8C%84%E1%8A%94%E1%89%AB/a-54206373?maca=amh-Facebook-dw

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.