የታላቁ ሕዳሴ ግድብን አስመልክቶ የሚደረጉ ድርድሮች እንደሚቀጥሉ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ

106345633 1681765631974778 5283093066410245533 o e1593360637746
የታላቁ ሕዳሴ ግድብን አስመልክቶ የሚደረጉ ድርድሮች የኢትዮጵያን ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ እንደሚቀጥል የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ የምታደርገው ድርድር የአሁኑን ትውልድ ብቻ ሳይሆን የመጪውን ትውልድ ጥቅም በሚያስጠብቅ መልክ የሚደረግ እንደሆነም ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ጨምረው ገልፀዋል።
ዘግይቶ የነበረው የግድቡ የብረት ሥራ እና የጄኔሬተር ተከላ አሁን ላይ ተሠርቶ አልቋል ያሉት ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፣ በዘንድሮው ዓመት የግድቡን ከፍታ ከ525 ወደ 560 ማምጣት መቻሉን ጠቁመዋል።
ባለፈው ዓመት ውኃው ያልፍ የነበረው በ525 ከፍታ ላይ እንደነበር፣ አሁን ግን 560 ከፍታ ላይ ከደረሰ በኋላ የሚያልፍ መሆኑን ተናግረዋል። ይህም ከ560 ከፍታ በታች ያለው ውኃ ግድቡ ውስጥ የሚቀር እንደሆነ እና ሙሌቱም ከግንባታው ሂደት ጋር የማይነጣጠል እንደሆነ ገልጸዋል።
በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽን ጨምሮ ከኬንያ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ማሊ፣ ማዳጋስካር እና ደቡብ አፍሪካ የተውጣጡ 11 ባለሙያዎች የተሳተፉበት ውይይት ተካሂዷል።
ሚኒስትሩ በውይይቱ በተወሰኑ ነጥቦች ላይ መግባባት ላይ መደረሱንም አስረድተዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.