«የሃጫሉ ግድያ አማራና ኦሮሞን በማጫረስ ኢትዮጵያን የማፍረስ ዓላማ ነበረው» አቶ ንጉሱ ጥላሁን የጠቅላይ ሚኒስትር ፕሬስ ሴክሬቴሪያት

Nigusu
ንጉሱ ጥላሁን

አዲስ አበባ፦ የታዋቂው የኦሮሚኛ ሙዚቀኛና የነጻነትና እኩልነት ታጋይ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ አማራና ኦሮሞን በማጫረስ ኢትዮጵያን የማፍረስ ዓላማ እንደነበረው አቶ ንጉሱ ጥላሁን የጠቅላይ ሚኒስትር ፕሬስ ሴክሬቴሪያት አስታወቁ። የትግራይ ህዝብ አገር እንድትበጠበጥ፣ እንድትፈርስና ለባዕድ ጥቅም ተላልፋእንድትሰጥ እንደማይፈቅድም አመለከቱ።

አቶ ንጉሱ ጥላሁን በተለይም ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፣ ነፍጠኝነት በሁሉም ብሄር ያለ ቢሆንም፣ ሁሉም የኢትዮጵያ ብሄሮች የራሳቸው ነፍጥ ያዥና ጀግና ቢኖራቸውም ፣ ህወሃት ሆን ብሎ በአማራ ህዝብ ላይ ይሄን ታርጋ በመለጠፍ ድሃው የአማራ አርሶ አደርና ህዝብ አብሮት ከሚኖረው፣ ከተጋባውና ከተዋለደው ወንድሞቹ እንዲገፋ እንዲጣላና ጥቃት እንዲደርስበት አድርጓል፤ እያደረ ገም ነው ብለዋል።
አርቲስት ሃጫሉ ከመገደሉ ቀደም ብሎ ከኦ ኤም ኤን ቴሌቪዥን ጋር በነበረው ቃለመጠይቅ ሆነ ተብሎ የተሰራው ስራ የትኞቹን ብሄረሰቦች ሊያጋጭ እንደሚችል ለማንም ግልጽ እንደሆነ አመልክተዋል። በስመ ነፍጠኛ የአማራ ህዝብ ገዳይ ተደርጎ እንዲወሰድና ተገደለብኝ ብሎ የሚያስበውም የኦሮሞ ህዝብ ብቻ እንደሆነ በማስመሰል አማራንና ኦሮሞን የማቃቃር፣ የማጠፋፋት በዚህም ኢትዮጵያን የማፍረስ ተልእኮ እንደነበረው ጠቁመዋል። በጉጉት የሚጠበቀውን የህዳሴ ግድብን የማደናቀፍ ተጨማሪ ግብ እንደነበረው ጠቁመዋል።
ለዚህም ማሳያው ገና ግድያው በተፈጸመ ሌሊት ገዳይ እገሌ ነው ብሎ የማወጅና ህዝብን ክህዘብ የሚያጋጩ መልዕክቶች በኦ ኤም ኤን ቴሌቪዥን ሲተላለፍ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ንጉሱ፣ ይሄው ሚዲያ ሲያስተላልፋቸው በነበሩ ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶች ምክንያት ሲዘጋም የትግራይ ቴሌቪዥን ተቀብሎ ማሰራጨት መጀመሩ ከዚህ ትብብር ጀርባ የሆነ ነገር አለ እንድንል ያደርጋል ብለዋል።
“የአማራና ኦሮሞ ህዝቦች እሳትና ጭድ ናቸው” በሚል ደካማ አመለካከትና እነዚህን ትልልቅ ህዝቦች በማጋጨት አገርን ማዳከም ይቻላል በሚል እሳቤ ጥገኛውና ዘራፊው የህወሃት ቡድን ከዚህ ቀደም የተለያዩ ሴራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ያስታወሱት አቶ ንጉሱ፤ የህወሃት ነባር አመራር የሆኑት አቦይ ስብሃት ነጋ አባገዳዎችና የሁለቱ ብሄሮች ታላላቅ ሰዎች ሳይቀር ተሳትፈው የመሰረቱትን የኦሮ-ማራን ጥምረት “የዱርዬዎች ስብስብ ነው” በማለት በአደባባይ እስከመዝለፍ መድረሳቸውን አስታውሰዋል።
“ለውጡ እንዲመጣ ግንባራቸውን ሳያጥፉ የታገሉ ጥርስ ተነክሶባቸው እንደሚሳደዱ እናው ቃለን። ጥርስ ከተነከሰባቸው ፈርጥ የኦሮሞ ልጆች መካከል ደግሞ አንዱ ሃጫሉ ነው። ስለዚህም ለውጡን መቀልበስና አገር ማተራመስ ከተፈለገ እንደ ሃጫሉ ያሉ ሰዎች ላይ እርምጃ መውሰድና በዚህም ቁጣ በማስነሳት ጎረቤት በጎረቤቱ፤ ብሄርን ብሄር ላይ በማስነሳት በዚህ ፈተናና ክረምት ውስጥ ንጹሃን እንዲገደሉ አካላቸው እንዲጎድልና ከቤታቸው እንዲፈናቀሉ ተደርጓልም “ብለዋል።
በጥላቻ ፖለቲካ የሰከሩና ያረጁ ሰዎችን ያሰባሰበውና አዲስ አበባ ላይ ጀምረን አዲስ አበባ ላይ እንጨርሳለን ሲል በአደባባይ የጦር ቀጠሮ ሲያሲዝ የነበረው የጥፋት ቡድን፣ በሃጫሉ ሞት ተደስቶ ድምር ውጤት ለማምጣት እየተረባረበ መሆኑ አመልክተዋል ፣ አሁንም የሚዲያ ሽፋን በመስጠት በጥፋቱ እንደቀጠለበት ጠቁመዋል። የትግራይ ህዝብ ግን አገር እንድትበጠበጥ፣ እንድትፈርስና ለባዕድ ጥቅም ተላልፋ እንድትሰጥ እንደማይፈቅድም አስታውቀዋል።
አዲስ ዘመን ሐምሌ 9/2012
በጋዜጣው ሪፖርተር

2 Comments

  1. The Oromo and Tigray fascists are cooperating to cause mayhem in Ethiopia by triggering civil war between the Amharas and Oromos. The brain and center of coordination for this evil plan is Makelle where the TPLF leaders are plotting and financing the violence from. Out of weakness or tolerance, the Abiy Ahmed government has not moved against the TPLF. The TPLF leaders though they use the Oromo fascists to instigate violence and genocide, have a deep seated contempt towards the Oromos. They see these Oromo fascists as simple tools to be used against the Amharas and destabilize the country.

  2. What got Hachalu killed is nothing but his own attitude towards all Oromos. All fanatic ethnic supporters should learn from Hachalu’s mistakes, his mistake was trying to appease all competitor Oromo politicians and also by appeasing all “ethnic Oromo competitor violent systemic business people capitalists”. In Ethiopia there are more business owners who evaluate their success by counting how many similar businesses went out of business than by their own internal successes . Many make it their mission to monopolize the trade they are in, they don’t think they are successful unless they achieve absolute monopoly of the market. Same as one ruling party (EPRDF) monopolized the government and all the amenities for long.

    He was literally caught up in the middle of the Oromos shootout when Burayu Police Commissioner, Solomon Tadesse was shot and killed by OLF Shane in 02/2020 .

    OLF Shane wanted to kill Commissioner Solomon Tadesse because OLF Shane wanted the investigation on the Burayu Massacre to die down. During the Burayu Massacre many Oromo muslims were killed also which is the main reason OLF did not want to be outed as the perpetrator of the Burayu massacre.
    Until his death Hachalu tried to side with anyone who is an Oromo, many different Oromo groups ( OPDO , OLF , OFC , OMN …) all used Hachalu as a spy . Hachalu unknowingly was going back and forth among these different Oromo groups competing each other, he was leaking ones secret to the other, before he realized what he was doing he was in too deep in the espionage game which the Oromo groups were playing.

    When OLF picked up arms military style , when Jawar’s Querro picked up macchettes Jihadist style , when OPDO start being busy about national issues by letting only Takele Uma accommodate Oromo’s issues with federal concentrating on national issues , when the original Querro who fought TPLF went back to its hungry lifestyle Hachalu was not able to appease all anymore so he was lost not wanting to take sides or not wanting to believe there were serious fractures amongst Promos , the more he tried to bring understanding and the more he tried to play a diplomat the more secrets he leaked about one another which got him killed.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.