ኢትዮጵያን ብሎ አብይን ጥሎ? – ዶ/ር ዘላለም እሸቴ

Abiy 8በፊታችን ያለው መንታ መንገድ፥ አንዱ መንገድ ዶ/ር አብይን እየደገፍን ኢትዮጵያን ለማስቀጠል የምንሄድበት መንገድ ነው፥ ሌላኛው ኢትዮጵያን ለመበተን ሌሎች የሚሄዱበት መንገድ ነው። ከዚህ ውጭ ሦስተኛ መንገድ ሊኖር አይችልም። የውስጥ ልዩነታችንን በምርጫና ምርጫ ብቻ እንዳኘዋለን። ከዚያ ባለፈ ራሱን ዶ/ር አብይን እንሞግተዋለን እንጂ በስመ ኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ አንጮህም። ምክንያቱም ሦስተኛው መንገድ አንድነት እንዳይኖር ውዥንብር የሚፈጥር ነውና አይጠቅመንም። ወደምንናፍቀው ከፍታ ኢትዮጵያን በቤተሰብነት አውድና ብልፅግና ውስጥ ሊያስገባት የሚያስቸለው መንገድ ራሱ ዶ/ር አብይ ባይሆን እንኳን ለዚያ በሚያበቃ ቁመና እንድንደርስ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ወደ ምርጫ ያደርሰናል።

ዶ/ር አብይን ዛሬ ዛሬ የሚደግፈው ሰው አማራን ይበልጥ የሚወድ፥ ወይም ኦሮሞን ይበልጥ የሚወድ፥ ወይም ሌላ የራሱን ብሔር አብልጦ የሚወድ ወይም ኢትዮጵያን የሚወድ ሊሆን አይችልም። ታዲያ ማን ሊሆን ይችላል? ብንል ከአጀማመሩ እንመልከት። የዶ/ር አብይን ንግግር ሰምቶ ያልወደደው ፍጡር የለም ማለት ማጋነን አይደለም። ንግግሩ ከስብዕናው የወጣና ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ራዕይ ሰንቆ፥ አርቆ በማየት ምን ማድረግና ምን መሆን እንደምንችል ፍንትው አድርጎ ሲተርክልን ያልተማረከ አልነበረም። ሃይማኖት ሳይለይ ሁሉንም አስታርቆ፥ ዲሞክራሲን ላዋልድ ብሎ በጎነቱ ድክመቱ ቢሆንበትም ቅንነቱ ታይቶ፥ ተረት ተረት የሚመስለው የኤርትራ ዕርቅ እውን ሆኖ የኖቤል ሰላም ሽልማት አስጨብጦት፥ ጉድ ድንቅ እየተባለ ሳለ፥ ግና ተራ በተራ በየፌርማታው ወራጅ አለ እየተባለ ዛሬ መንታ መንገድ ላይ ደረስን።

በመጀመሪያ በእርቅና መግባባት ፍቅር ማውረድ ሲቻል ሆን ተብሎ የታሪክ ዕዳ በጥላቻ ማወራረድ ተመረጠ። ሲቀጥል በሕወሃት ሃያ ሰባት ዓመታት አብሮነታችንን የሚሸረሽር መሠሪ ትርክት በትውልድ ላይ ተቆመረ። ይህ ሳያንስ በየተለያየ አቅጣጫ ሁሉም በየብሔሩ ጎራ ተሰልፎ ዶ/ር አብይን ወዲያና ወዲህ ይጎትታል። ያም ሆኖ ዶ/ር አብይ ሁሉንም ያመረቀነውን ራዕይ ወደ ተግባር ለመቀየር በሚሄድበት አዲስ ጎዳና በትልቅ ትዕግስት፥ ከስህተቱም እየተማረ እየነጎደ ይገኛል።

ለምሳሌ ያህል፥ አንድ ሰሞን አዲስ አበባ የማን ናት ተባለና ተባላን። ጠቅላዮ ጭቅጭቁን ለእኛ ትቶ አዲስ አበባን ማስዋብ ጀመረ። አብሮነታችንን፥ ታሪካችንን፥ የተፈጥሮ ፀጋችንን በአማከለ ሁኔታ ምን ልንሆን እንደምንችል በአዲስ አበባ ከተማ ዘወትር በሥራ እየታተረ ይገኛል። በጊዜ ሂደት ልብ እንደምንገዛና አብሮነታችንን እንደምናገዝፍ በራዕዩ ሃይል የታመነ ይመስላል። ዶ/ር አብይ የኦሮሞን ጥያቄ አልመለሰም ብለው የኦሮሞ ሊሂቃን ይዋጉታል። ሌሎችም በብሔራቸው ቆመው እንደዚሁ ያደርጋሉ። የሚገርመው የዶ/ር አብይ አካሄድ የዛሬን ጥያቄ መመለስ ብቻ ሳይሆን፥ የነገን ጥያቄ በመመለስ ሂደት ላይ ጭምር ነው። ተላለፍን።

እኛ ተፈትነን ስናንገራግር፥ የኢትዮጵያ አምላክ ዶ/ር አብይን እስካሁን ረድሔቱን አልሰሰተበትም። ወደቀ ስንል እየተነሳ፥ ኢትዮጵያ ጠፋች ስንል እያመለጠች፥ አባይም እየተሞላ፥ ወደፊት እየተባለ ነው። አሁን ላይ ግን ዶ/ር አብይን ለመውደድ፥ አብሮነታችንን መውደድ ብቻ እንደሚጠይቅ አያጠራጥርም። መንገዱ ተራራና ሸለቆ የሞላበት ነው። ተራራው ላይ ስንደሰት፥ ሸለቆ ውስጥ ስናዝን፥ መሄዳችን አሁንም አይቀርም። ግን ዶ/ር አብይን ለመደገፍ መንገዱን ሳይሆን አድራሻችንን (ራዕዩን) ማየት አለብን።

በደመና ላይ ያንሳፈፈን ራዕይ፥ መሬት ሲወርድ ውጣ ውረድ አለው። በዚህ ላይ ሰው ነውና የዶ/ር አብይ ድክመት ተጨምሮ፥ ብዙ ፈተና አለው። በተጨማሪ ይህ ጉዞ ብዙ ጠላቶች መንገድ ላይ ሊያስቀሩን ምሽግ ይዘው የሚዋጉን ጭምር በመሆኑ እጅግ አድካሚ መሆኑ የታወቀ ነው። ታዲያ መዳረሻችን የሆነው ራዕይ ለሁላችንም የምትበቃ ብቻ ሳይሆን፥ ለአፍሪካና ለዓለም የምትተርፍ ኢትዮጵያን ለማየት ዶ/ር አብይን መደገፍ ኢትዮጵያዊነት ነው። ምርጫችን አብሮነታችን ይሁን። የአብሮነታችን መንገድ ደግሞ ዶ/ር አብይ ነው። ስለዚህ ያለምንም ማመንታት መደገፍ ይሁንልን። ስናመነታ እንዳንመታ። ፈጣሪ እንደሆነ ለኢትዮጵያ መድረሱን ቸል ብሎ አያውቅም። ድርሻችንን እንወጣ።

8 Comments

 1. Weird you do not get it. Either you do not want to get it, ethnic cleansing is OK as long as amhara disappears from Earth or you hope to get a cushy job with him or you are ignorant when it comes to human rights etc, etc. If u are for Ethiopia with out Amhara you should keep ur head in the sand and keep it there. Sad to see Education does not make the mind broad in ur case.

 2. Well, it is good to express what we feel and what we think about the situation in our country regardless of who agrees or disagrees with us . It is from this perspective I want to see the above piece . However, the way the writer sees and understands the Prime Minister’s political personality which cannot be seen out of the very context of the criminal ruling circle or system EPRDF/Prosperity is highly. Simplified .

 3. ዶ/ር አብይን መደገፍ ኢትዮጵያዊነት አይደለም። የኢትዮጵያን ውድቀት ማፋጠን ነው። ኢትዮጵያዊም ዴሞክራሲያዊም የሆነ መሪ ሶስተኛ አማራጫችን ነው። እኔን የሚገርመኝ እንደ ዘላለም እሸቴ አይነት ምሁር ተብየዎች ናቸው የአምባገነን መሪዎች መፍለቂያ ። አብይን ለሁለት አመት ተኩል አይተነዋል። በተጎዱ ሰዎች ጫማ ውስጥ ሆነን አብይን እንየው። ያማል የተፈፀመው ግፍ።

 4. Zelalem Eshete,

  You probably have MD or PhD degree, but at this forum, you acted like a typical cadre. Who the hell are you to say there are only two options, either to support Abiy Ahmed and be Ethiopian or not support Abiy and be anti-Ethiopian. What about opposing the fake Abiy and still remain ETHIOPIAN? I am in the third group as I belieive that Abiy Ahmed is a very superficial guy and full of pretension. What did he say about the terrorist Jooowar Mohamed in Diredawa a few days after 86 Ethiopians were killed by Joowar and the wild animals by the name kero?

  What did Abiy Ahmed say when Ethnic southerners in the environs of Addis were killed by the terrorist wild animals in the nam of kero?

  What did Abiy Ahmed say when hundreds of people from the Gedeo ethnic group were killed by fascist Oromos?

  Of course the answer for all three questions is: nothing

  What did the great Eskinder Nega did to serve prison together with oromo terrorists? Nothing but simply because Takele goma is scared of Eskinder Nega, a very innocent and trustworthy person who unlike many Ezema politicians always stands for the rights and well being of ordinary Ethiopians .

  FREE THE GREAT ESKINDER NEGA AND CO.

 5. D/r. Zelealem
  shame on you, you said only two alternatives but we Ethiopians have many alternatives. we saw D/r. Abiyu for the last two years he did nothing rather than he wanted in genocide.

 6. በኢትዮጵያ ልኡላዊነት የማያምኑ ኢትዮጵያዊነትን የማይቀበሉ ድርጅቶችንና ግለሰቦችን በጉያው አቅፎ : እነዚሁ ቡድኖችና ግለሰቦች በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው ህጋዊነት አግኝተው ህዝብ እንዲጨርሱ የጥላቻ አክታቸውን እንዲተፉ ማድረግ ለኢትዮጵያ ቆመናል ለሚል መንግስት ማድረግ የሚገባ ነገር ነውን? እባካችሁ ህሊናችሁን መርምሩ።

 7. Down with Marionetten………………….!

  Down with Aanarchism…..!

  Unity in Diversity………………!

  ኢትዮጵያ በተባበሩ የልጆችዋ እጆች ተከብራ ትኖራለች………..!

 8. አንተ ሁለት ያልካቸው ሁለቱም አንድ ናቸው። ሁለቱም ሕገመንግስቱ እና በክልል አወቃቀሩ ያምናሉ። ሁለቱም ፀረ አማራ ናቸው። በዜጋ ፖሐቲካ ሁለቱም አያምኑም። ሁለቱ ልዩ የሚመስሉት የስልጣን ፉክክር ስለሚያደርጉ ብቻ ነው። እኔ ልግዛ ልግዛ ብቻ ነው። ስለዚህ አማራጩ ትግል ብቻ ነው።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.