«የኦሮሞ ሕዝብ ነፃ ወጥቷል አሁን የሚያስፈልገው ልማት ነው» – ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ

abiy «የኦሮሞ ሕዝብ ነፃ ወጥቷል አሁን የሚያስፈልገው ልማት ነው»  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድአዲስ አበባ:- የኦሮሞ ሕዝብ ባለፉት መቶ ዓመታት ታግሎ አሁን ላይ ነፃ የወጣ በመሆኑ የትጥቅ ትግል ሳይሆን የሚያስፈልገው ልማት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ገለጹ። የህዳሴ ግድቡ ከነበረበት ውስብስብ ችግር ጠንከር ባለ አመራር እና ድጋፍ ወጥቶ አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስ ትልቅ ሥራ መሰራቱንም አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት ከሕዝብ ተወካዮች ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ወቅት እንደገለጹት፤ የኦሮሞ ሕዝብ ባለፉት መቶ ዓመታት ታግሎ አሁን ላይ ነፃ የወጣ በመሆኑ የሚያስፈልገው የትጥቅ ትግል ሳይሆን ከሌሎች ወንድም ሕዝቦች ጋር ተባብሮና ተጋግዞ መልማት ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዕድሜያቸውን ሙሉ ለኦሮሞ ሕዝብ ትግል የታገሉ መሆናቸውን ጠቁመው፤ የኦሮሞን ጉዳይ ሳይሸሹ ፊት ለፊት በመታገል የኦሮሞ ሕዝብ የሚያሸንፍበትን አቅጣጫ በማስቀመጥና እስትራቴጂ በመንደፍ አሁን ላይ አሸናፊ መሆን ተችሏል ብለዋል።
አንዳንዶች ኦሮሞ አገር መምራት አይችልም ይሉ የነበረውን ታሪክ ለመቀየር መቻሉን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በሰላማዊ መንገድ በምርጫ ሀሳብን ሽጦ አሸናፊ መሆን ሲቻል በአንድ እግር ሰላም በአንድ እግር ጦርነት የማይቻል መሆኑ በመንግሥት በኩል በነበረው ዝግጁነት በተደጋጋሚ መገለጹን ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ የኦሮሞ ሕዝብ ነፃና እኩል እንዲሆን ወጥቶ ሰርቶ እኩል እንዲጠቀም አምነው መታገላቸውን ገልጸው፤ ነገርግን የኦሮሞ ሕዝብ ሌላውን እንዲጎዳና እንዲጫን አስበውና አልመው እንደማያውቁ፤ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር በጋራ ሆኖ ኢትዮጵያን መቀየር ይችላል የሚል ሙሉ እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል።
በሃሜት የኦሮሞን ሕዝብ ድል ወደ ኋላ ለመመለስ የሚደረገው ጥረት የኦሮሞን ሕዝብ ጥቅም የሚጎዳ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለኦሮሞ የሚታገል ማንኛውም ኃይል በሰላማዊ መንገድ ሃሳብ ሽጦ ኦሮሞን አሳምኖ በምርጫ ለመምጣት መድረኩ ክፍት ነው፤ በቅናት መቃጠልና መስከር ጥሩ አይደለም። ይሄም ከኦሮሞ ባህል ውጪ ነው ብለዋል።
የኦሮሞ ሕዝብ አሁን ላይ ያገኘውን ድል ለማግኘት መቶ ዓመት ታግሏል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የኦሮሞ ሕዝብም ሆነ ሌላው በሰከነ መንገድ የፈለገውን በምርጫ መምረጥ እየቻለ እኔ ካልሆንኩ በሚል ቅናት ሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት አፍርሶ የኦሮሞ ሕዝብ ሥልጣን ለማግኘት ሌላ መቶ ዓመት መቆየት እንደማይገባው አስታውቀዋል።
እኛ ሥልጣን ላይ ተቀምጠን ኢትዮጵያን ማፍረስ ለማንም የማይፈቀድ መሆኑን በደንብ መገንዘብ ያስፈልጋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በቅናት ላይ በተመሰረተ ፖለቲካ ኢትዮጵያን የሚከፋፍል ፖለቲካ አይጠቅምም። ኦሮሞ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር በአንድነት ኢትዮጵያን ይገነባል። መከፋፈል ለጠላት እንጂ ለአገር አይበጅም ብለዋል።
ሁሉም ማሸነፍ የሚችለው በሰላም መንገድ መሆኑን አውቆ በሰላማዊ መንገድ እንዲራመድ፤ ከዚያ ውጪ ግን በጦርነት ሀገር ማፍረስ ይቻል ይሆናል እንጂ አሸናፊ መሆን እንደማይቻል፤ መንግሥት የጀመረውን ሕግና ሰላም የማስከበር ሥራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመልክተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ በአገሪቱ የፖለቲካ ነፃነት መጥቷል ነገር ግን ኢኮኖሚያዊ ለውጥና ብልጽግና ካልመጣ፣ ወጣት ከስደት ካልወጣ፤ አርሶ አደሩ በሚደክመው ልክ ምርት አግኝቶ ሕይወቱ ካልዘመነና ካልተቀየረ ትርጉም ስለሌለው መንግሥት ዴሞክራሲና ልማትን ለማምጣት ከሕዝብ ጎን በመሰለፍ የሚቻለውን ሁሉ ያደርጋል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የታላቁ ህዳሴ ግድብን በሚመለከት መንግሥት የሚከተለው አካሄድ ሦስት መሆኑን ጠቅሰው፤ የመጀመሪያው ግድቡን በጥራት ማጠናቀቅ፣ በዚህ ጉዳይ ላይ በተሰራው ሥራ ልክ ብዙ ማለት ባይቻልም ብዙ ሥራችንን ስንጨርስ እንደማንኩራራው ሁሉ አልተኩራራንበትም እንጂ እንዳሰብነው መፈጸም ችለናል ብለዋል።
ግድቡ ከነበረበት ውስብስብ ችግር ጠንከር ባለ አመራር እና ድጋፍ አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስ ትልቅ ሥራ ሰርተናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የግድቡን ግንባታ ከፍታ ከ25 ሜትር ወደ 60 አድርሰናል። ይህ ግድቡ ከነበረበት ውስብስብ ችግር አንጻር በቀላሉ የመጣ እንዳልሆነ አመልክተዋል።
እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ፤ ሁለተኛው ከተፋሰሱ አገራት ጋር የተደረገው ውይይት መወያየት ሲሆን፤ ወንድም ሕዝቦች ስለሆኑና ውይይት ስለሚያስፈልግ ከዚህ አንጻር ሰፊ ውይይቶች ተካሂደዋል። አንዳንዶች ለምን እዚያ ተካሄደ እና መሰል ጥያቄዎች ያነሳሉ፤ ጊዜው ሲያልፍ ለምን እዚያ ሄድን? ምን አተረፍን የሚለውን ወደፊት የምንገልጸው ቢሆንም ትልቁ ነገር ትርፍ ያገኘንበት ነው፤ ውይይቱ ወደ አፍሪካ ህብረት መምጣቱም ትልቅ ድል እንደሆነ ይታወቃል። ሦስተኛው ደግሞ ትንኮሳዎችን መከላከል ነው፡፡ ትንኮሳዎቹ የኢትዮጵያ መንግሥት ከግድቡ ግንባታ ዓይኑን እንዲያነሳ የሚደረግ ጥረት አካል ናቸው።
ሶሎሞን በየነ

2 Comments

 1. In my understanding “Limat” means development. Limatawi EPRDF or developmental EPRDF had been talking about limat for decades. Now the question is what kind of development are we talking about? Most of the Oromo society including the PM himself while in bed thinks development means or translates to having as much babies as possible. Whoever is giving birth the most amount of children is considered as the most developed by most Oromos or by almost all other ethnic groups of Ethiopia.

  Then when we step into the house of federation the EPRDF PP take measures for development by counting double digits economic growth , dollars borrowed from worldbank or by number of high rise buildings it built, not by the number of children got born as the society while in bed does measure development.

  The society gets married some muslims marrying ten wives at the same time and having babies non stop because that is what development translates to the people eventhough raising children is becoming extremely difficult for parents because both parents work many hours to feed their children, the children are left to grow up without proper role model guiding them as they grow up.

  When children go to schools colleges you find Professors such as Merira Gudina or Bekele Gerba teaching the children or until two decades ago people were being thought in schools by shabiya agents teaching students to Down Down Ethiopia formally in Ethiopian schools ,back then when children complain about their “down down Ethiopia” Shabiya teachers then the children get expelled from school by the shabiya teachers , with the students geting kicked out put out of school for resisting down down Ethiopia teachings and most of the time end up disowned by their family wrongly being accusung their children of being a lazy backward undeveloped student because at the time no parent believed there are teachers intentionally teaching their students to down down Ethiopia in Ethiopian schools , most parents thought they have a liar child who defames the teachers but the truth was Shabiya thought in schools within Ethiopia for the students to act savagely against each other, shabiya tried to convince students that down downing each other in a society means hard working society, means development or means competitive capitalism , those students who let down down Ethiopia to marinate in their brains believing that is what competitive capitalism development is all about graduated from schools with distinctions then went to be leaders and became teachers themselves holding key positions in EPRDF. Those who opposed such teachings are labeled lazy damn and had been ridiculed by the limatawi EPRDF most ended up in jails or in exiles with no contact from their parents or family members for being lazy backward damn who joined wants to listen to what they got to say.

  Building high rise buildings and borrowing billions of dollars from the west should not have been the only measure of development or having as many kids should not have been the measure of development, what development translates to is being able to understand communicate build thrust each other within a family or within a society which Ethiopia is least developed in this measure of development.

  Just having gangs of kids each year new baby being born only for some parents not even remembering their own children names is what is bringing the disaster we are experiencing.Even those who know their children names don’t know anything about the child they brought into this world meaning there is a loose cannon society of ethnic groups which tries to go on as a country without knowing what is in the minds of each other.

 2. TPLF has already told us through its lackeys collectively called OPDO that the Oromo people are liberated already in 1991. Now, that same OPDO, rebranding itself as PP, is retelling the same thing. What does freedom mean for OPDO aka PP? Filling your potbelly or bringing some psycopathic anti-Oromo to power? Does freedom mean the death of more than 60 thousand Oromos and the eviction of millions from their ancestral homesteads to make rooms for neo-colonizers? Does freedom mean death and destruction, what you openly vowed to bring upon the Oromo and Oromoness?! Most of all, who should tell if one is free? Don’t you see, The Qeerro are showing you the middle finger!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.