ኦነግ እና ኦፌኮ አመራሮቻችንና አባላቶቻችን በጅምላ እየታሰሩ ነዉ አሉ

ሺ የሚቆጠሩ አባላቶቻችንን እና አመራሮቻችንን ማሰሩን ቀጥሏል ሲሉ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር  (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) ገለጹ። የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ በበኩሉ በቁጥጥር ስር የዋሉት ሁሉ በወንጀል ተጠርጥረው ብሎአል።

oromoየድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያን ተከትሎ መንግስት በሺ የሚቆጠሩ አባላቶቻችንን እና አመራሮቻችንን ማሰሩን ቀጥሏል ሲሉ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር  (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) ገለጹ። ቀደም ሲል የሁለቱ ፓርቲዎች ዋነኞቹ ፖለቲከኞች አቶ ጀዋር መሀመድ ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣አቶ ሽጉጥ ገለታ እና ሚካኤል ቦረንን ጨምሮ በርካታ የየፓርቲዎቹ አመራሮች እና አባላት በቁጥጥር ስር ውለው ነበር። የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ በበኩሉ ነውጡን ተከትሎ በቁጥጥር ስር የዋሉት ሁሉ በወንጀል ተጠርጥረው እንጂ የፖለቲካ አመለካከት በማራመዳቸው አይደለም ሲል ክሱን አጣጥሏል። ስዩም ጌቱ ከየፓርቲዎቹ ያገኘዉን መረጃ አካፍሎናል።

 

ስዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ
ነጋሽ መሐመድ

6 Comments

 1. ምንም ሳያጠፉ ባላወቁት ጉዳይና ሁኔታ ያስጨፈጨፏችሗቸው ንፁሀን ወገኖች ደም በእጃችሁ አለ:: በአለም ፍርድ ቤት በዘር ማፅዳት ወንጀል ያስጠይቃችሗል:: የንፁሀን ደም ይጮሀል:: ህዝብን የፈጀ ወንጀለኛ በህግ ይጠየቃል:: በማስፈራራት አይለቀቅም

 2. ይገርማል እናንተው ትእዛዝ በተወካዮቻችሁ አማካኝነት ሰጥታችሁ ጯሂም እናንተ ሆናችሁ? ሲጀመር ዋና መታሰር የነበራችሁ እናንተ ነበራችሁ ዳሩ ምን ያደርጋል

 3. አይ መራራ ጉዲና መለስ በጣም ተነፈስክ ብሎ ሲገላምጥህ እንዴት መግቢያ እንደሚጠፋህ ረሳኸው መሰል? ተው ማፍቀር እንጅ መጨከን አይከብድም አብይ እጅ ከገባህ የሚያስጥልህ የለም ሌሎቻችሁም በተመሳሳይ ሁኔታ ከኢትዮጵያ እንዴት እንደወጣችሁ ሳትረሱት አልቀራችሁም። አብይ ጥቅማችሁን ቀንሶ ከቤት አስወጥቶ ሰርተህ ብላ ቢልህ አደብ ትገዛ ነበር። ዳር አብይ የህዝብ ንብረት እንዲያባክን ማንዴት ስለሌለው ለተቃዋሚ ፓርቲ የሚሰጠው ማንኛውም ድጋፍ ሊቆም ይገባል።

  • ሁሌም ቢሆን ኢትዮጵያዊነትን መስበክ ይሻላል።
   ለነገሩ ዘረፉ እንጂ ያመጡት ለውጥ የለም
   ሁልሽም ለራስሽ ጥቅም ነው እየተዋጋሽ ያለሽው እንጂ ለህዝብ ወፍ የለም

 4. የዘመናችን ከሀዲዎች፣ ሀገር ኣፍራሾች፣ የሰገራ ( ጥንብ ) ፖለቲካ ኣራማጆች። የንጹሃን ሞት ነጋዴዎች።
  ታሪክ ከዚህ በተሻለ ኣያስታውሳች ሁም !

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.