እኔ ኦሮሞን የማውቀው … (አሌክስ አብርሃም)

107686169 10218054711381120 5999123358652919935 n‹‹የኦሮሞ ጥላቻ ›› የሚል ታፔላ በመለጠፍ ማንንም ማሸማቀቅ አይቻልም፡፡ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ህወሃትና ደጋፊዎቹ እንዲሁም የጥቅም ተጋሪዎቹ ሲነኩ ሲመከሩና ሲዘከሩ ነገሮችን በሰከነ መንገድ ቁመው ከማየት ይልቅ ዘለው ‹‹የትግሬ ጥላቻ›› እያሉ ህዝብ ውስጥ ለመደበቅና ስህተታቸውን በህዝብ ካባ ሲጠቀልሉ ይሄው የጊዜ ሰፌድ ራሱ እንደ ልቃሚ አንጓሎ ገለል አደረጋቸው ፡፡ ለህዝብ ምን ይዘውለት ሄዱ ተረትና ስጋት ፡፡
108082784 10218054711981135 1168980528802384204 nአሁንም በኦሮሚያ ህዝብ ራሱን ለመጠቅለል የሚፍገመገመው ዋናው ቄሮ ሳይሆን የድል አጥቢያ አርበኛውና እነጃዋር ጠፍጥፈው የሰሩት ቄሮ ይሄን አለም በሙሉ የሚፀየፈውን የሽብር ድርጊቱን‹‹ተው ›› ሲባል ‹‹የኦሮሞ ጥላቻ ›› እያለ የማያዛልቅ ለቅሶና ስም ልጠፋውን ተያይዞታል ፡፡ ‹‹ለኦርጅናሌዎቹ›› ያልበጀ ዘፈን ምን እንሁን ብላችሁ ነው የምታላዝኑት ? ‹‹ዋነው ያልበጀ ቅራሪው ሰው ፈጀ ›› !
ቆይ የምን ጥላቻ ነው የምታወሩት ?
እኔ ኦሮሞን የማውቀው… በባዶ እግሩ ሮጦ በአለም መድረክ ላይ ሲያስጠራን እንጅ …በባዶ ጭንቅላቱ ገጀራ ይዞ ሰው ሲያርድና ባዶ ሲያስቀር አይደለም ፡፡
107766599 10218054714381195 31405253843570084 n
እኔ ኦሮሞን የማውቀው …በነፋጡማ ሮባ በነሃይሌ ገብረስላሴ በነቀነኒሳ በነጡሩነሽ ዲባባና በሌሎቹም ጀግና ልጆቹ በኦሎምፒክ ትራኮች ላይ አረንኳዴ ጎርፍ ሁኖ በህብረት ሪከርድ ሲሰብር እንጅ በመንጋ ግር ብሎ የሰው ንብረትና ተስፋ ሲሰባብር አይደለም !
እኔ ኦሮሞን የማውቀው… በእርሃብና ድርቅ ስሟ የጠፋ አገሬን በስፖርት መድረኮች ላይ በፍቅር ባንዲራዋን ከፍ አድርጎ ከፍ ሲያደርገን እንጅ <<ዳውን ዳውን>> እያለ አገሩንም ራሱንም አውርዶ ባንዲራ ሲረጋግጥ አይደለም !
107845323 10218054713461172 1188998386449234385 n
እኔ ኦሮሞን የማውቀው … ገና በ15 ዓመት እድሚያቸው እምቢ ላገሬ ብለው አገራችንን ከወራሪ ፋሽስት በታደጉት ሌፍተናት ጄኔራል ጃገማ ኬሎ እና ቢጤዎቻቸው እንጅ …በየኩሽናው እየገባ አያቶቹ የሚሆኑ ባልቴትና ሽማግሌዎችን በግፍ ሲገድል አይደለም ፡፡
እኔ ኦሮሞን የማውቀው ወላጅ ያጡ ህፃናትን በጉዲፈቻ ወስዶ በፍቅር ሲያሳድግ እንጅ ያራሱን ልጆች በሃሳብ ልዩነት ሲበላ አይደልም !
እኔ ኦሮሞን የማውቀው… በብርቱ ክንድ ህዝቡን ከወራሪ ሲከላከል እንጅ ህፃናት ላይ ስለት ሲያነሳና ወላጆቻቸውን ጨፍጭፎ ካለወላጅ ሲያስቀር አይደለም ፡፡
107696392 10218054719541324 103247211212875029 n
እኔ ኦሮሞን የማውቀው… በአባ ገዳዎቹ አገርና ህዝብ የዱር እንስሳና አዝመራ ሳይቀር በመልካም ቃል ሲመርቅና ልዩነት አንተም ተው አንተም ተው ብሎ ሲያስታርቅ እንጅ በወጉ አፍ ያልፈቱ ህፃናትን የድምፅ ማጉሊያ አስይዞ የዘር ፍጅት ሲያሳውጅ አይደለም !
እኔ ኦሮሞን የማውቀው… ትርጉሙን እንኳን ሳናውቀው አይኖቻችን በሲቃ እንባ እስኪቋጥሩ በውብ ዘፈኖቹ ባስደመመንና እንኳን ሰውን የኦሮሚያ ጫካና ተራሮችን ‹‹ምነው ሂደን ባየናቸው›› ባስባለን አሊ ቢራ ዘፈኖች እንጅ ጩኸታቸውና ስድባቸው በሚቀፍ ምድሩ ላይ የሚኖሩ ዜጎች ላይ በዋለው ግፍ አገሩን በዋይታና ሰቆቃ ድምፅ ባስሞሉት ወመኔዎች አይደለም፡፡
107854057 10218054716301243 176351771873240359 n
እኔ ኦሮሞን የማውቀው …ወዳጅ ብቻ ሳይሆን አገራችንን የወረረ ጠላት መሪዎች እነ ጂዬቫኒ ቴዶን ለሰራዊታቸው መሸነፍ ቁልፉን ሚና የተጫወቱት የኦሮሞ ፈረሰኞች መሆናቸውን ሲመሰክሩላቸው እንዲሁም ‹‹የኦሮሞ ተዋጊ ፈረሰኞች ወደ ሸለቆው ሲወርዱ ድንገት የገነፈለ ጥቁር ባህር ይመስሉ ነበር›› ሲሉላቸውና ጠላት ገና ከሩቅ አይቷቸው ሲርድ እንጅ …ዱላና ስለት ይዘው ያውም ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ሲዘምቱና ህፃናትና ሴቶችን ሲያስለቅሱና ሲያስጨንቁ አይደልም!
107809500 10218054714741204 4576132181641641394 n
እኔ ኦሮሞን የማውቀው እንደዚህ ነው !! አገር ሲያረጅ ጃርት ያፈራል እንደሚባለው … የጥላቻ ንግግራቸው መርዛማ ላባ የሆነ ፣ በጥላቻ የተሞሉ፣ እንደጃርት የሰው ሰብልና ንብረት የሚያወድሙ …ነብሰ ገዳዮች ስለዚህ ከፍ ባለ ክብር ስለማውቀው ያገሬ ኦሮሞ ሊሰብኩኝም ሆነ ሊያስተምሩኝ ወኔውም እውቀቱም የላቸውም ፡፡
108225349 10218054712381145 1049282174155173880 n
አገሬው ስለጃርቶቹ ያውራ እንጅ ጃርቶቹ ስለአገሩ ሊያወሩ አፍ የላቸውም !! ባጭሩ አንተን ኦሮሞ ህዝብ መሃል የተደበከውን ነብሰገዳይ ጃርት እንኳን እኔ የሰው ልጅ በሙሉ ይጠለሃል !! ኦሮሞው ራሱ የውሸት እና ጥላቻ ስብከትህ እየገባው አንቅሮ እየተፋህ ነው ፡፡ ከህዝብ ማሳ ውስጥ የደረሱ ልጆቹን እያነክ የምትቀጥፈው ጃርት …ጥላቻህ አስጠልቶሃል፡፡ ህዝብ መስተዋት ነው…በዚህ መስተዋት እያየህ ያለኸው የራስህን የጥላቻ መልክ ነው ! ደግሞ መልኩ የራስህ አይደለም የሚነዱህ አጥፊዎች እንደሜካፕ ፊትህ ላይ የሳሉልህ ነው ፡፡ በአባቶችህ ፍቅር ፊትህን ታጠበው ያኔ ኩሩ ኦሮሞ መልክህ ይወጣል… መስተዋት ፊት ስትቆምም የምታየው ያንኑ ፍቅር ነው !!ከዚህ ውጭ ጠሉኝ እያልክ ስትጮህ ብትውል …የሚቀየር ነገር …..አበደን !!

5 Comments

 1. ወንድሜ ታላቅ አባባልና ሀቅም ነው ። ተባረክ በሕዝብ ስም እኩይ ተግባር የሚፈጽሙ ሁሉ ብዘገይ እንጂ ፍርዳቸውን ያገኛሉ ። ጫካውን መንጥረውና በሰደድ እሳት አጋይት መደበቂያ ሊያገኙም አይችሉም ። ለመምህሮቻቸው ያላዋጣውን ኃላ ቀር ሴራ ይዘው ያዝ ስሉት እንደ ውሻ ለመንከስ የሚቅነዘነዝ መንጋ ከዛ ደግ ሕዝብ ወጣ ብሎ ለማሰብ የሚከብድ ነው ።

 2. ልክ ብለሃል ግን ተማርን ከሚሉት እስከ ተከታይ ጭፍራችው አሁን የሚሉትና የሚያረጉት የድርቡሽ ሥራ ለመሆኑ ተግባራቸው ይናገራል። የአሁኑ ትውልድ ባለፈው የኦሮሞ ታሪክ አይመዘንም። በራሱ ሥራ እንጂ! አሁን ቆንጭራና ካራ ነዳጅና ጭድ ይዞ ቤት በሚያጋየውና አንጋሎ በሚያርደው የነጃዋር ቡድንና በሌሎች እይታ ነው መገምገም ያለበት። አዎን ጥቂቶች ናቸው ይህን እብደት የሚፈጽሙት ሲባል በተደጋጋሚ እንሰማለን። የክልሉ ፓሊስ ቆሞ እያየ፤ አሮሞ የሆኑት ቆመው እያዪ አይደል እንዴ ሰው ተገድሎ ተዘቅዝቆ የሚገደለውና ሬሳው የሚቃጠለው። የኦሮሞ ሙሁራንም ሆኑ የሙት ጥሪ ተከታዬች በሃገርና በውጭ ሃገር አብደዋል። ባስጠለላቸው ሃገር መንገድ የሚዘጉ፤ የቆመ ሃውልት የሚያፈርሱ፤ የሰውን ሰላም የሚነጥቁ የእብድ ጥርቅሞች ናቸው። በፓለቲካና በሃይማኖት ዙሪያ ራሳቸውን አስከልለው እናውቅልሃለን የሚሉ የዘመናት የፓለቲካ ተጧሪዎችና የአሁኑ ጭፍን ትውልድ አሸንክታቦች የኦሮሞን ህዝብ ሳያማቱት በፊት ሃገሩን የሚወድ፤ ሰው አክባሪና ያለውን የሚያካፍል ህዝብ እንደሆነ በመካከሉ ኖረን ያየነው እውነት ነው። የስማ በለው ነጋሪ አንፈልግም። እናውቀዋለን የኦሮሞን ህዝብ። ግን እነዚህ የፓለቲካ ተኩላዎች በውስጡ ከበቀሉ በህዋላ የተፈጠረውና በመፈጠር ላይ ያለው እጅግ ዘግናኝና ትውልድ የማይረሳው ነው።
  ታዲያ በየምክንያቱ እየተባረረ በሰው ሃገር የተሸጎጠው የተማረና ያልተማረ በጥምር ህብረተሰብ ውስጥ ራሱ አስጠግቶ በኦሮሞ ህዝብ ሲነግድና ሂድ በለው ሲል ማየት ያማል። ዳዎን ዳዎን ኢትዮጵያ፤ ዳዎን ዳዎን አብይ፤ ዳዎን ዳዎን ኤርትራ ማበድ ይሏቹሃል ይህ ነው። ኤርትራዊያን ደግሞ ምን አደረጉ? ዶ/ር አብይ ኦሮሞዎች በወለጋና በአዲስ አበባ በጃዋር የውሸት የኡኡታ ጥሪ ሰው ሲያልቅ ዝም ከማለቱ በስተቀር ምን አደረገ? ይህቺ ለዘመናት ሃበሳዋን የምታየው ሃገርና ህዝቦቿስ ምን አድርጋ ነው ዳዎን ዳዎን መባሏ። የጅምላ ፓለቲካ እንደዚህ ነው ለማሰብ ጊዜ አይሰጥም። ራሱ በድሎ ራሱ ያለቅሳል። አሁን የሚወጡ መረጃዎች በትክክል እንደሚያሳዬት በወያኔና በኦሮሞ ጠበንጃ አንጋቾች ተጠንሶ ነው ሃጫሉ የተገደለው። ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል ይሉሃል ይህ ነው። የጫቱ ዶ/ር ህዝቅያስ በወያኔና በኦ ኤም ኤን ላይ እንዲሁም በሌሎች የዜና አውታሮች የተናገረውን ላዳመጠ ይህ ሰው አብዷል እንጂ ጤነኛ አይደለም ማለት ይቻላል። በቀለ ገርባ እኔም ታስሬአለሁ ያለውን ሴል ሁሉ አንቀሳቅሱ ግደሉ፤ አስከሬኑም ከአዲስ አበባ እንዳይወጣ መንገድ ዝጉ ማለቱ የሚያሳየው ከታሰረ በህዋላም የኢሜል መለዋወጥ ተፈቅዶለት እንደነበረ ያሳያል። ሌሎች የሚለብሱትና የሚበሉት እንዳይገባላቸው ተከልክለው እሱና መሰሎቹ እንዲህ ያለ የእስር ቤት መንቀባረር የሚያሳየው የኦሮሞ ጽንፈኞች በእስራትም ቢሆን አድሎ እንደሚያደርጉ ነው።
  ዛሬ ከክልሌ ውጣልኝ፤ ሃገርህ አይደለም እያለ ሰውን እንደ እንስሳ አጋድሞ የሚያርደው የኦሮሞ ስብስብ ነገር እርስ በራሱ እንደሚጫረስ የታወቀ ነው። ፓለቲካ ሸፋፋ ነው። የትም ሃገር በየትም ሥፍራ የተቃና ጉዞ የለውም። ትላንት አብረው የመከሩ በማግስቱ ይተራረዳሉ። የሃበሻው ያለፈ የፓለቲካ ጥምረት የሚያሳየውም ይህኑ ነው። እኔ ኦፌኮን ብሆን ገዳም እገባለሁ። እንዴት ሰው የሚያስተራርዱ ሰዎችን በአባልነት የሚይዝ ድርጅት ለኦሮሞ ህዝብ ቆሜአለሁ ይላል? እንዴት እልፍ ያገራችን ልጆችን መቃብር ያወረደ የወያኔ መንጋ ጋር ሃገር ለማፍረስ ኦሮሞ ሆኖ ሰው ይዶልታል? በወያኔ የተገደሉ፤ አካላችው የጎደለ፤ ከሃገር ተሰደው በየምድረበዳውና በባህር የቀሩ የኦሮሞ ወጣቶች ደም አይፋረዳችሁም። በእሬቻ በዓል ላይ የደረሰው ግፍ የቅርብ ትዝታ አይሆናቹሁም? እናንተ አሁን ለኦሮሞ ህዝብ ቆመናል ትላላችሁ?
  መፍትሄው አንድና አንድ ነው። በውጭም ሆነ በሃገር ቤት የእነዚህ እውራኖችን ተግባር በመረጃ ለሃገራችን ህዝብ፤ ለውጭ መንግሥታት፤ የዘር ማጥፋት ግድያው እንዲፋፋም የሚገፉትን በሶሻል ሚዲያ ላይ የሚለጥፉትን፤ በመገናኛ አውታሮች የሚናገሩትን በማቀናጀት በውጭ ላሉ የዜና አውታሮች፤ የሃገር የደህንነት መ/ቤትች፤ የትምህርት ተቋማት በማስረዳት ከሥራቸው እንዲባረሩ፤ አልፎ ተርፎም ለኢትዮጵያ መንግሥት ታልፈው እንዲሰጡ ማድረግ ይቻላል። ለምሳሌ አንድ ሃኪም ነኝ የሚል ጠባሳ ጠባብ ብሄርተኛን ከስራው ለማገድ ታላቅ የመረጃ ማሰባሰብ ስራ ተጀምሯል። ከሚሰራበት መ/ቤት ብቻ ሳይሆን የእርሱ በሽተኞች የሆኑ ሁሉ ሰው እንዲገዳደል የለጠፈውንና የተናገረውን በመረጃ በማቅረብ ማንም ከእርሱ ዘንድ እንዳይታከም ለማድረግ በህቡዕ ተጀመሮ የዶክተርነት ላይሰንሱን ለሰጠው ክፍል በማቅረብ ውሳኔ እየተጠበቀ ነው። ከአሁን በህዋላ እዚህ የራሳቸውን ኑሮ በሰላም እየኖሩ ህዝባችን የሚያጨራሩሱትን ላፍታም ዝም አንላቸውም። ኦሮሞ ሆነ ትግሬ አማራ ሆነ ጉራጌ ሰው እያጫረሱ እፎይ ብሎ መኖር አይቻልም። ጠ/ሚሩ ቁርጥ እርምጃ ካልወሰድ የአሁኑ የእነ ጃዋር የመፈንቅለ መንግስት ሙከራና የኦሮሞ አመራሮችን የመግደል ድግስ ቤተ መንግሥት ድረስ በመግባት ጥፋት እንደሚያደርስ መገመት ይቻላል OMN የኦሮሞ ድምጽ ሣይሆን የኦሮምን ድምጽ አፋኝ ነው። የሃጫሉ ቃለ መጠየቅ ለሞቱ ለማመቻቸት የተደረገ፤ ቆርጦና ቀጥሎ የቀረበ ለመሆኑ አሁን እየገባን ነው። ከዚያ በፊት አንድ የኦሮሞ ጄኔራል ቃለ መጠይቃቸው ሙሉው እንዳልወጣ ሲናገሩ ተሰምተዋል። ይህ ነው ድርጅትና የሚዲያ አውታር ነው ለኦሮሞ ህዝብ ነጻነት የቆመው? ድንቄም የነጻነት ፋና! ዳግም ድምጸ ወያኔ! የሁለት የፓለቲካ ሙታኖች ድምጽ!

 3. የኢትዮጵያ ህዝብ ይህ ሁሉ ለምን ይሆናል ብሎ ከስር መሰረቱ ከመመርመር ይልቅ፣ ስልጣን የተቆጣጠረው አካል በሚያናፍሰው ሴራ ብቻ ይነዳል! እስቲ፣ ሃጫሉ ከተገደለ ከጥቂት ሰዐታት በኋላ፣ የተገደለበት ቦታ እንኳ በደንብ ሳይመረመር፣ ገዳዮቹ ግብጽ፣ ወያኔ እና “ሼኔ” ብሎ ሲያዉጅ፣ ኤረ እንዴት አወቃችሁ? ብሎ መጠየቅ ቀርቶ የጠረጠረ አለ??? መንጋ ማለት ያ ነው! ሃጫሉ የተገደለበት፣ ሬሳው የተጉላላበት፣ ከፌደራል ፖሊስ ሌላ ዘመዶችሁ እንኳ እንዳይቀብሩት፣ 2 ተጨማሪ ዘመዶቹን እስከመግደል የተሄደበት ርቀት፣ ያለምንም ማስረጃ እና የፍርድቤት ትዕዛዝ የOMN ስቱዲዮ ተወሮ፣ ንብረቱ የተዘረፈበት አካሄድ፣ የፖለቲካ ተቀናቃኞቹን ያሰረበት ፍጥነት ሁሉ ሲደማመር፣ ግድያው የብልጽግና ፓርቲ ጊዜ ወስዶ ያቀናበረው የፖለቲካ ሴራ መሆኑ፣ ጤነኛ አዕምሮ ላለው ሁሉ ግልጽ ነው። ግና በዚያች ሃገር ውስጥ ጤነኛ ዐእምሮ ያለው ሰው መኖሩን እጠራጠራለሁ። ጀዋርን፣ OMNን እና ነጻ የኦሮሞ ድርጅቶችን እስካጥንታችሁ ድረስ ስለሚትጠሉ፣ በለው! ከማለት ዉጪ፣ በዚያች የተረገመች ሃገር ሌላ አደገኛ አምባገነናዊ ስርዐት ስር እየሰደደ እንደሆነ እንኳ ማሰብ አልቻላችሁም!

  ኦሮሞን “ጀግና” ብላችሁ የሚታሞጋግሱት ስማችሁን እስካስጠራ፣ የናንተን ባህል፣ቋንቋ፣ እና አምልኮ ተቀብሎ ራሱን በናንተ አምሳል ስሲል እንጂ እኔ እኮ ኦሮሞም ነኝ ባለ ማግስት አንቅራችሁ የምትተፉት፣ ሲበዛም የምትገድሉ ናችሁ! ስንቱን እንቁ የሆኑ የኦሮሞ ልጆችን ገድላችሁ የአዞ እንባ እንደምታነቡ ቆጥረን አንጨርሰውም! ሃጫሉ አዲሱ እንጂ የመጀመሪያው የመጨረሻውም ሰለባችሁ እንደማይሆን ይታወቃል! በየዘመኑ ስንት እንቁ ኦሮሞዎችን እንዳስፈጃችሁ፣ ጎባና ዳጬ፣ ባልቻ አባነፍሶ ለምን እና እንዴት እንደሞቱ ጀምሩና እስከሃጫሉ ድረስ ቁጠሩ። እንኳን ለኦሮሞ ህዝባቸው ድምጻቸውን ያሰሙ የታወቁ እና ያልታወቁ ሺህ የኦሮሞ ጀግና ልጆች ቀርተው፣ ለሃበሻ መንግስታት በቅንነት ያገለገሉ ሺህዎች ያለርህራሄ ተፈጅተዋል! ጀነራል ታደሰ ብሩ፣ ሃይሌ ፍዳ፣ ጀነራሎች ራጋሳ ጅማ፣ ደምሴ ቡልቶ፣ ግ/ክርስቶስ ቡሊ፣ ወዘተ፣ የሃበሻ መንግስታትን በቅንነትና በትጋት ሲያገለግሉ ቆይተው አንዴ ብቻ ሳት ብሎአቸው የኦሮሞን መጨቆን ሲያነሱ በግፍ ተገድለዋል፣ ዶ/ር ናጋሶ ጊዳዳ ሜዳ ተጥለዋል! እነዚህን ለሃበሻ ያገለገሉትን ለምሳሌ አነሳሁ እንጂ የኦሮሞ ሰማዕታትን ከኦሮሞ ዉጪ እንኳን ልትዘክሯቸው፣ መኖራቸውንም አታውቁም፣ ቢታውቁም በጠላትነት በመፈረጅ ነው! አንድ ሚሊዮን ኦሮሞ ከሶማሌ ድንበር ሲፈናቀል፣ ኦሮሞዎች ሶማሌዎችን እና ሌሎችን ኦሮሞ ያልሆኑትን ገደሉ፣ ፈጁ፣ ብላችሁ ሌላ ጦርነት ስትቀሰቅሱበት ነበር። በጉጂ እና በገዴኦ ህዝቦች መካከል የመንግስት ጸጥታ አካላት በለኮሱት መገዳደል እና ስደት፣ የተገደለው እና የተሰደደው ዖሮሞ በቁጥር ከገዴኦው የሚልቅ የነበረ ቢሆንም፣ የገዴኦውን ብቻ አግዝፎ በማቅረብ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ተጨማሪ የስነልቦና ጦርነት ከፍታችሁበት ነበር። ዛሬም በሃጫሉ ሞት ሰበብ ከተገደሉት ውስጥ 80% ኦሮሞ ሆኖ፣ የዘር ፍጅት (ጀኖሳይድ) ብላችሁ ባላችሁ የሚዲያ ቀዳዳ ሁሉ ኦሮሞው ላይ እየዘመታችሁ አላችሁ። የኦሮሞ ህዝብ በጅምላ ተፈርጆ እንደጠላት መታየቱ ታሪክ መጻፍ ከጀመራችሁ ጀምሮ ያለ ትርክታችሁ ሆኖ የኖረ ቢሆንም ያሁኑ ከመጠን አለፈ!
  ነገር አበዛሁ፣ ላሳጥረውና ከ130አመታት በሁላ እንኳ ኦሮሞ በመንግስት ደረጃ እንደኢትዮጵያ ጠላት (ኢትዮጵያ ሲባል ሃበሻ ተብሎ ይነበብ) የሚታይ ስለሆነ፣ ከመለያየቱ ሌላ አማራጭ እንደሌለ አረጋግጦልናል። መገዳድሉ እና ጥላቻው ይብቃን፣ የመለያየቱን መንገድ የሰላም ያድርግልን! አሜን!

 4. ውድ አሌክስ አብርሃም፣
  የጠፋው እንዳንተ የሰከነ አመለካከት ያለው ዜጋ ነው። ሌሎች ብዙዎች ዝምታቸው አገራችንን ለጥቂት ጯኺዎች መፈንጫ አድርጓታል። እዚሁ ዘሃበሻና ሳተናው ላይ የሚሞነጫጨሩትን ብታይ አንድ ትርክት ላይ ብቻ አተኲረዋል። ይኸውም ቆንጨራ፣ ገጀራ፣ ዱላ የያዘ ዜጋ (ኦሮሞ ይኸ ነው ለማሰኘት) ዘመቻ ይዘዋል። እራሳቸው ችግር ፈጣሪ እንደ ሆኑ አልገባቸውም። የሚያሳዝነው፣ የህወሓትን ስውር ሥራ እየሠሩ መሆኑ ነው። ህወሓት ዓላማው አንድ ነው። ኦሮሞና አማራን ማጣላት ነው። ለጊዜው የተሳካለት ይመስላል። ዜጋ ቢነሳ ግ ን ይህን እኲይ እቅዱን ማምከን ይቻላል። አሁንም ጊዜው አላለፈምና በርታልን!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.