ኢትዩጵያ ሃገሬ…. የአዲስ አበባ ከንቲባ ታከለ ኡማ ውሳኔ – ቅድስት ግርማህ

ዛሬ በአዲስ አበባ ከንቲባ ታከለ ኡማ ውሳኔ ለአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ት/ቤት በስሙ እንደተሰየመለትና በመቀጠልም በሃይሌ ጋርመንት አካባቢ የሚገኘውን አደባባይ በሃጫሉ ስም ለመሰየም መርሃ ግብር መያዙ ሰማን። ለአርቲስቱ የሚመጥነዉ ማስታወሻ ማስቀመጥ ተገቢ እንደሆ ስላመንኩ እሰየው ብለናል።
ነገር ግን…
በነ አለምፀሃይ ወዳጆ አማካኝነት አዲስ አበባን የቆረቆረቻት የእቴጌ ጠሃይቱ መታሰብያ ሃውልት ለመስራት የተቀመጠን የመስራት ድንጋይ በቄሮ መንጋ ሲፈርስ ታከለ ኡማ መጀመሪያ የፈቀደውን ፕሮጀክት ከኔ እውቅና ውጭ የተሰራ ስራ ነው በማለትና ሸምጥጦ በመካድ ፕሮጀክቱ እንዲቆም ማድረጉን አስታውሶኝ ሁኔታው አግራሞትን ፈጥሮብኛል።
ሌላው ከዚህ ጋር በተያያዘ…
ሃገሩን በኢኮኖሚና በልማት ለማሳደግ የሙቀት መጠኑ ከ38-40 ዲግሪ ሳልሲየስ በሚደርስ ሃሩር በርሃ ላይ ለ7 አመታት እየተቃጠለ ሲሰራ የነበረው የልማት አርበኛ ኢንጂነር ስመኘው የግፍ ግድያና በመንግስታቸን የተሰጠው ምላሽ ትዝ አለኝና አንዳች ነገር ውስጤን ሰንጎ ያዘኝ።
109071727 1244251302583396 8982190867994442875 n
~~~~~
የ53 ዓመት ጎልማሳ የኢንጂነር ስመኘው ስም በህዝብ እውቅና እያገኘ የመጣው የአባይ ግድብ ፕሮጀክት ማኔጀር ሆኖ ሲሾም ይሁን እንጂ ስመኘው የግልግል ጊቤ አንድንና ሁለትን ግንባታዎችን በመገንባት በሃላፊነት የተወጣ መሪ መሃዲስ ነበር።
ኢንጂነሩ የጀመረውን ግድብ እውን ለማድረግ ትጋቱ ይገርመኝ ነበር። በግድቡላይ የነበረው መሻት የህዝብ ግንኙነት እስኪመስል ድረስ ሊጎበኙ ለሄዱ ሰዎች ስሜት ውስጥ ገብቶ ንግግር ሲያደርግ ምኞቱ ከፊቱ ይታይ ነበር።
~~~~
እንዲህ አይነቱ ከራሱና ከቤተሰቡ ሂዎት የሃገሩን ያስቀደመው ስመ ጥር መሪ መሃዲስ በአክራሪ ኦነጋዊያን በጭካኔ ሲገድል እንኳንስ አደባባይና ት/ቤት ሊሰየምለት ለረጅም ጊዜ ከመቃብሩ ላይ ድንጋይ የሚያስቀምጥለት አልነበረም። ጭካኔ ከተሞላበት አገዳደሉም በላይ የጠ/ሚንስትራችን “አንድ ኢንጂነር ስመኘው የሚባል ሰው ሞቶ ተገኝቷል” ብለው የተናገሩትን መስማት ቅስም ስባሪ ነበር።
ሃገራችን መቼ ይሆን በመርህ የምትመራው❓
ያሳዝናል!!

 

5 Comments

 1. You’re just ignorant. Can’t you have a day without criticizing someone? Let the country and the people have a day of peace at once.

 2. ቀንደኛው የዘር ፓለቲካ አቀንቃኝ ያሄው ከንቲባ ተብዬው ደላላ ነው፡፡ ደግሞ አያፍርም መድረክ ላይ ቆሞ ቀስቃሽ አዝማሪን ት/ቤት ይሰየምለት ሲል? በአገልግሎት ላይ ያለውን ት/ቤት በሳት እንዳያጋዩት ምክር መስጠት አይሻለውም? እፍረት ያጣ ነው፡፡
  ኢንጂነር ስመኘውን ሃውልት ቀርቶብን ገዳዮቹን በቅጡ ምርመራ አድረገው አሁን ለአዝማሪያቸው እንደሚራወጡት ምነው አልነገሩን? ከንቲባው ሃዘኑን በአማርኛ ሲናገር እንባው ያልመጣበት በኦሮምኝ መተርጎም ሲጅምር እንባውን ማበስ ጀመረ፡፡ ሰው ምን ይልናል የማይሉ ደንቆሮዎች ናቸው፡፡
  አብይ በጠረራ ፀሃይ የዘር ፓለቲካ የሚሰሩትን በተለይ እንደ ኡማ አይነቶች ብዙ ናቸው የመንግሥትን ተቋማት ጠለላ ለብሰው፡፡ አብይ እንደዚህ አይነቱን መንጥሮ ማውጣት የግድ ይለዋል፡፡

 3. ዛሬም ትናንትም ለኢንጂነር ስመኘው ከአማራው ህዝብ የበለጠ ልብሳቸውን ጥለው የሚያብዱለት ወያኔዎች ናቸው::እባቦች! ኢትዮጵያዊው ጅል ነው ይህ ሁሉ አይገባውም:: ሀጫሉ በሙዚቀኛነቱ አልተገደለም:: ሆን ብሎ አማራን አስጨፍጭፎ ኦሮሞንና አማራን በማጋጨት ለወያኔ ዘረፋ ስራ መመለሻ የደደብ ድራማ ናት:: ወያኔ 27 አመታት የቆየችው የአመራር ብቃት ኖሯት ሳይሆን አማራንና ኦሮሞን በተንኮል በመለያየት ነው:: ዛሬ ኢትዮጵይን ለማፈራረስ ጦርነት ከፍታለች እናንተ የወያኔ መንገድ ጠራጊዎች ህዝቡን መለያያ አጀንዳ እያመጣችሁ የሴራ ፖለቲካችሁን ታደነቁራላችሁ:: በቃ አማራው ጀላጅል ነው:: losers አሁን ወቅቱ ስለሀጫሉ ሀውልት ጉዳይ ነው?

 4. ETHIOPIA is a country of shameless people. Yesterday, the woyanes, and today, the yes men of yesteryears are doing it in a worse manner. They are totally inconsiderate and shameless. Their more shameless keens in the diaspora are even saying to the world that the bodies of poor non-oromo Ethiopians as if they were oromos.

  I feel sad for the untimely death of the singer but what about the more than 200 people who were killed in a very savage way for no reason other than being non-oromo. Waht about the thousands who are now sheltered at churches and police stations. The shamless guy who once said “We broke Neftegnas” and considered as “the leader “of the ruthless state did not care to visit these poor people.

  Ayi Ethiopia- bewnetu tasazegalesh

  • ምን አይንት ደንቆሮ ህዝብ እንዳጋጠምን እግዚአብሔር ይውቅው፡፡ ስንቱን ዘቅዝቀው ሰቅለው የእነሱ ደም እንኳን ምን ይላቸዋል? በገጀራ ለታረዱት ከመኖርያቸው ለትፈናቀሉት መታሰቢያቸው ምንድነው?? መንግሥት፤ ህግ ያልደረሰላቸው ወገኖች ምንደነው የሚድረግላቸው? ጃንሆይም እንኳን እንደዚህ ማእረግ አላገኙም አንድ አዝማሪ ያገኘውን ያህል፡፡ እነዚህ አኝ ቀቅለው የብሉ ናቸው፡፡ ከአጼ ሚኒሊክ ፈረስ ጎን ሃውልት ያቆሙለት ይሆናል፡፡ ማፈርያ ናቸው፡፡
   ጠ/ሚሩ እንደዚህ ማንም ክብት እየተነሳ የሚውስንውን እንዴት ነው ቁጭ ብሎ የሚያየው? ጀግና ጠፍቶባቸው መድረክ ላይ ቀስቃሽ አዝማሪን መላ ቅዱሱን አሳጡት፡፡ ደግሞ ጥሩ ምሳሌ እንዳለው ሰው? ሚስቱ ካልሆነች ሴትጋ አይደል እንዴ የሞተው? ለህጻናት ኦሮሞዎች እንኳን ምሳሌ እንዳይሆን፡፡ የክብት ጥርቅም ብቻ ነው፡፡
   በእርግጥ ለመለሰ ዜናዊም ብዙ ቃል ተገብቶ ነበር ወይ እንደዛ ይሄንን ሳኔ የሚቀለብስ ሌላ ተረኛው ይመጣ ይሆናል፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.