በምእራብ አርሲ የደረሰው ዉድመት በአቡነ ሊቀ ሄኖክ ገለጻ

አደባባይ ሚዲያ እንደዘገበው የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ሞት ተከትሎ በተፈፀመ ጥቃት በምእራብ አርሲ ሀገረስብከት ብቻ የደረሰ ውድመት ከፍተኛ እንደሆነ ብፅዕ አቡነ ሄኖክ የምእራብ አርሲ ሀገረ ስብከት  ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቨዥን ገልጸዋል፡፡
19 ምእመናን በግፍና በጭካኔ እንደተገደሉ የገለጹት አቡነ ሄኖክ፣ 934 ድርጅቶች፣ 493 መኖሪያ ቤቶችና አንድ ቤተ ክርስቲያን መውደማቸውን፣ 4 ትምህርት ቤቶች፣ 72 ተሽከርካሪዎችና አንድ ቤተክርስቲያን  መቃጠላቸውን ነበር ያሳወቁት፡፡
3362 ምእመናን በአሁኑ ጊዜ በቤተክርስቲያማት ተጠልለው እንደሚገኙም ሳይጠቅሱ አላለፉ፡፡
እነዚህ ጥፋቶች የተፈጸሙት ከውጭ አገር በመጡ ወራሪዎች ወይንም ጦርነቶች ሳይሆን፣ መንግስት አለ በሚባልበት አገር ውስጥ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ጥቃቶቹ በተፈጸሙ ወረዳዎቹ፣ ከተሞችና ዞኖች ያሉ  የመንግስት ሃላፊዎች አስፈላጊዉን ጥበቃ አለማድረጋቸው፣ አንዳንድ ቦታም መመሪያ አልደረሰንም ብለው ዝምታን መምረጣቸው  ብዙዎችን ማሳዘን ብቻ ሳይሆን እያስቆጣ እንዳለም እየተሰማ ነው፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.