የኦሮሞ ፓለቲከኞች እርስ በእርስ መገዳደል ከባሮ ቱምሳ እስከ ሓጫሉ ሁንዴሳ-አማራ እንዴት ተጠያቂ ይሆናል!? – በአቻምየለህ ታምሩ

ኦነግ ኦሮሞን በገደለ ቁጥር በአማራ እየተመካኘ በአማራ ላይ ሲካሄድ የኖረው የዘር ፍጅት…

hachalu baro 1 1

የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ ሐጫሉ ሁንዴሳን የገደሉት በኦነግ ታጣቂ ቡድን ተልዕኮ የተሰጣቸው የኦሮሞ ተወላጆች መሆናቸውን በአቃቢ ሕጓ በወይዘሮ አዳነች አበቤ አማካኝነት በዛሬው እለት ከአዲስ አበባ በሰበር ዜና ነግሮናል። የሐጫሉን ግድያ ብቻ ሳይሆን አማራ በኦሮሞ ላይ አደረገ እየተባለ ሲነተርክ የኖረውንና የኦሮሞ ልጆች ሲጋቱት የኖሩትን የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ሁሉ የፈጸሙት ኦነግ አልያም የኦሮሞ ተወላጆች ናቸው።

ኦነጋውያን የትግል አባት አድርገው የሚቆጥሩትን ባሮ ቱምሳን የገደለው አብዱል ከሪም ኢብራሂም አሚድ ወይም በጫካ ስሙ ጃራ አባገዳ በመባል የሚታወቀው የእስላማዊ ኦሮሚያ ሪፐብሊክ ግንባር መሪ የነበረው ጨካኝ አውሬ ነው። “ኦሮሞ ከፖለቲካ ስልጣን ተገልሏል” ብሎ ኢስላማዊ ኦሮምያን ለመፍጠር ጫካ የገባው ጃራ አባገዳ ወይም አብዱል ከሪም ኢብራሂም አሚድ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዋና ዳኛና ሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት ገዢ የነበሩት የፊታውራሪ ኢብራሂም ሀሚድ ልጅ ነው።

ባሮ ቱምሳን ጃራ አባገዳ እንደገደለው ታሪኩን የነገረን የኦሮሞ ብሔርተኛው መረራ ጉዲና ነው። መረራ ጉዲና ይህን ታሪክ የነገረን በጦብያ መጽሔት በጥር 1988 ዓ.ም. «በመስታወት ቤት ውስጥ የሚኖር በሌሎች ላይ የመጀመሪያውን ድንጋይ ወርዋሪ አይሆንም» በሚል ርዕስ ባሳተመው ሁለት ክፍል ጽሑፉ ነው።

ፕሮፈሰር መሐመድ ሐሰን የኦሮሞ ብሔርተኛት አባት የሚለው ዳኛ አሰፋ ዱላ ኢትዮጵያ ሆቴል ውስጥ የተገደለው በኦሮሞው በጃራ መስፍን በጥይት ተጠዛጥዘው ሲሆን ርስ በርሳቸው ተገዳደሉበት የጠባቸው ምክንያትም በመካከላቸው የተፈጠረው ቁርሾ ነው። ኦነጋውያን ግን ለኦሮሞ ወጣቶች ያስተማሩት ዳኛ አሰፋ ዱላን አማራ እንደገደለው አድረገው ነው።

ኦነግ የኦሮሞ ትግል አባት ያደረገውን ጀኔራል ታደሰ ብሩን የመሬት ላራሹን አዋጅ ተቃወመ ብለው የገደሉትም ኦሮሞዎች ናቸው። መጋቢት 5 ቀን 1967 ዓ.ም. አዲስ ዘመን ጋዜጣ ካወጣው ሪፖርት ማንበብ እንደሚቻለው ጀኔራል ታደሰ ብሩ ከነ ጭስኞቻቸውና ከኮሎኔል ኃይሉ ረጋሳ ጋር ከሸፈቱበት አስሶ የያዛቸው የኦሮሞ ነገድ ተወላጁ ሻለቃ ተስፋዬ ገብረ ኪዳን ነው። ሻለቃ ተስፋዬ [ኋላ ሌተናት ጀኔራል] የኢትዮጵያ 11ኛው መከላከያ ሚንስትር ሲሆን ከመንግሥቱ ኃይለ ማርያም በኋላ ደግሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ነበር።

ስለ ሻለቃ ተስፋዬ ገብረ ኪዳን ሲከነክነኝ የሚኖረውን አንድ ነገር ዛሬ ልተንፍሰው። ሻለቃ ተስፋዬ ታህሣሥ 20 ቀን 1971 ዓ.ም. የብርጋዴር ጀኔራልነት ሹመት ያገኘው ከሌተናት ኮሎኔልነት ተነስቶ ማዕረግ ሁለት በመዝለል ነው። የሻለቃ ተስፋዬ ማዕረግ መዝለል በዚህ አላበቃም። የመከላከያ ሚኒስቴር በሆነ ባመቱ በአንድም የጦር ሜዳ ሳይውል የጦር ሜዳ ሜዳይ አንደኛ ደረጃ ተሸላሚ ሆነ። ሁለት ዓመት ቆይቶ ደግሞ በየካቲት ወር 1974 ዓ.ም. ማዕረግ የመዝለል ታሪኩን በመድገም ከብርጋዴር ጀኔራል ማዕረግ በቀጥታ የሌተናት ጀኔራል ማዕረግ ሹመት ተሰጠው። ይህ ሁሉ ሲሆን ሰጪውም አላፈረም ተሸካሚው ሻለቃ ተስፋዬም ከሻለቃነት ተነስቶ የሌተናት ጀኔራልነት ማዕረግ ሲሰጠው ሳይከብደው ተቀበለው።

በኢትዮጵያ ሠራዊት ታሪክ [የወያኔን ጦር እንደ ኢትዮጵያ ሠራዊት አልቆጥረውም] እንዲህ አይነት የማዕረግ እድገት ያገኘው የኢትዮጵያ ጀኔራል ተስፋዬ ገብረ ኪዳን ብቻ ነው። ማዕረግና እድገት ዋጋው ከፍ ያለ በነበረበት በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ቢሆን ኖሮ ግን ከሌተናት ኮሎኔልነት ወደ ብርጋዴር ጀኔራልነት ለማደግ ቢያንስ የ15 ዓመታት፤ ከብርጋዴር ጀኔራልነት ወደ ሌፍተናት ጀኔራልነት ለማደግ ደግሞ ቢያንስ 10 ተጨማሪ የአገልግሎት ዘመን ይጠይቅ ነበር። ሻለቃ ተስፋዬ ሌፍተናት ጀኔራል የሆነው በእሱ የሞያ አግባብ ቢያንስ 25 ዓመታት ተጨማሪ የአገልግሎትና የትምህርት ጊዜ የሚጠበቅበትን በመዝለል ነው። ወያኔዎች ደርግ የገደላቸው የሳንሲየርና የሳንድረስት ምሩቃን ጀኔራሎች የነበሩትን የኢትዮጵያን ጦር አሸነፍን የሚሉት እንደዚህ አይነት ከሻለቃ በላይ ጦር መርተው የማያውቁ የመንግሥቱ ኃይለ ማርያም መደዴዎችን ማሸነፋቸውን እንደ ድል እየቆጠሩነው።

ወደ ጀኔራል ታደሰ ብሩ ታሪክ ስንመለስ ጀኔራሉ እንደሸፈቱ እጃቸው እንዲያዙ አልያም እምቢ ካሉ እንዲደመሰሱ ትዕዛዝ የሰጠው የደርጉ ደኅንነት ኃላፊ የነበሩት የወለጋው ኦሮሞ ኮሎኔል ተካ ቱሉ ነበሩ። ጀኔራል ታደሰ ተይዘው ልዩ የጦር ፍርድ በቀረቡ ጊዜ የልዩ የጦር ፍድር ቤቱ አቃቢ ሕግ ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ የነበሩ ሲሆኑ ዳኛው ደግሞ ኦሮሞው ሻለቃ በቀለ ነዲ ነበሩ። መረራ ጉዲናም ቀደም ሲል በጠቀስሁት ጽሑፉ ጀኔራል ታደሰ ብሩ በኦሮሞ እንደተገደሉና ጀኔራሉ እንዲገደሉ ሴራውን ያቀነባበረው ባሮ ቱምሳ እንደሆነ ጽፏል። ኃይሌ ፊዳ የሚመራው መኢሶንም ጀኔራል ታደሰ ብሩ ሲገደሉ ፊውዳሉ ታደሰ ብሩ እንደተገደለና የተወሰደውን አብዮታዊ እርምጃም እንደሚደግፍ በልሳኑ መግለጫ አውጥቷል።

በሌላ አነጋገር ጀኔራል ታደሰ ብሩ የተረሸኑት ከሸፈቱበት ተይዘው እንዲመቱ ወይም እንዲረሸኑ ኦሮሞው ኮሎኔል ተካ ቱሉ በሰጡት ትዕዛዝ መሰረት ኦሮሞው ጀኔራል ተስፋዬ ገብረ ኪዳን ባካሄዱት ኦፕሬሽን ሲሆን፤ ጦር ፍርድ ቤት የቀረቡትና የሞት ቅጣት የተፈረደባቸው ደግሞ ኦሮሞው ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ አቃቢ ሕግ በነበሩበትና ኦሮሞው ሻለቃ በቀለ ዳኛ ሆነው በተሰየሙበት የልዩ ጦር ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት ነው። ይህን በጀኔራል ታደሰ ብሩ ላይ የተላለፈው የግፍ ፍርድ በኦሮሞው በኃይሌ ፊዳ ድርጅት በመኢሶን ተደግፎ ነበር። ኦነጋውያን እንደ ትግል ጀማሪያቸው የሚያዩትን የመኢሶኑን ኃይሌ ፊዳንም አብዮታዊ እርምጃ እንዲወሰድበት የወሰኑትም [የወሰኑበት ሰነድ በእጄ ገብቷል] ኦሮሞዎቹ መንግሥቱ ኃይለ ማርያም፣ ተስፋዬ ገብረ ኪዳን፣ ደበላ ዲንሳና ተካ ቱሉ ናቸው።

ይህ ብቻ ሳይሆን ሐውልት የቆመለትን የጡት ቆረጣ ታሪክ ሳይቀር በኦሮሞ ላይ የፈጸመው ኦነግ እንጂ አማራ አይደለም። ይህን ታሪክ ኦሕዴዶችም፣ ኦነጎችም፣ ወያኔዎችም ያውቃሉ። የኦሮሞን ጡት የቆረጠው ኦነግ መሆኑን የማይሞተውን የታሪክ ምስክርነት የሰጠን የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት የነበረው ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ነው። ነጋሶ ጊዳዳ “ዳንዲ የነጋሶ መንገድ” በሚል በተረከውና የሕይዎት ታሪኩን ባቀረበበት መጽሐፉ ገጽ 50 ላይ ኦነግ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ሴት ወታደሮችን ማለትም የሴት ኦሮሞ ወታደሮች ጡት ይቆርጥ እንደነበር ባይኑ ያየውን ታሪክ ነግሮናል። ነጋሶ ኦነግ የኦሮሞ ሴቶችን ጡት የቆረጠበትን ታሪክ የኦነግ አምበል የነበረው አባ ቢያ አባ ጆቢር አባ ጅፋር ሳይቀር በሽግግር መንግሥት ተብዮው ምክር ቤት ፊት ቀርቦ እንዳረጋገጠና የሰጠውም ምስክርነት በምክር ቤቱ ላይበራሪ ውስጥ በምስልና በድምጽ ተመርጆ እንደሚገኝ ነግሮናል።

ለኦሮሞ ወጣቶች ግን እየተነገራቸው ያደጉት ቀደም ሲል የቀረቡትን ኦሮሞዎች ሁሉ የገደላቸውና የኦሮሞን ጡት የቆረጠው አማራ እንደሆነ ተደርገው ነው። ይህም በመሆኑ ኦነጋውያን ለፖለቲካቸው መሳከት ኦሮሞን የመስዕዋት በግ እያደረጉ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ሲፈጽሙ የኖሩትን ግፍ ግን በአማራ የተፈጸመ እያስመሰሉ ያስተማሩትና አማራን እንዲያጠቃ እያሰለጠኑ ያሳደጉት አንድ ትውልድ አንድ ፖለቲካውን አማራን መፍጀትንና የአማራ የመሰለውን ሁሉ ማውደም አድርጎታል።

ታዋቂ ኦሮሞዎች የሚባሉትን ሁሉ የገደላቸውና የኦሮሞን ጡት የቆረጠው አማራ እንደሆነ ሲነገረው ያደገው የኦሮሞ ወጣት ባለፈው ሳምንት በኦሮሞዎቹ በጥላሁን ያሚ፣ አብዲ አለማየሁና ከበደ ገመቹ የተገደለውን ሐጫሉ ሁንዴሳን ሞት ለመበቀል በገደለ የዘር ፍጅት ሲያካሂድ የሰነበተው ምንም በማያውቁ ምስኪን አማራዎች ላይ ነው። የዘር ፍጅቱ የተካሄደው ኦሮምያ በሚባለው ክልል ልዩ ኃይል የሚደገፉት በሁለተኛ መንግሥት [ማለትም በጃዋር መሐመድ በሚመራው መንግሥት] የዘር ፍጅት እንዲያካሂዱ የተደራጁ ቄሮዎች ቢሆኑም የዘር ፍጅት ለማካሄድ የሰለጠኑት የጃዋር መሐመድ ቄሮዎች ፍጅቱን በአማራዎች ላይ እንዲጀምሩ ኦሮሞዎች የገደሉትን ሐጫሉን አማራ እንደገደለው አድርገው የቀሰቀሱት ዋና ዋናዎቹ ግን ብርሃነ መስቀል አበበ ሰኚ፣ ጸጋዬ አራርሳ፣ ሕዝቃኤል ጋቢሳ፣ ሄኖክ ጋቢሳ፣ ኢታና ሐብቴና የኦ.ኤም.ኤን ቴሌቭዥን ናቸው።

ከነዚህ ሁሉ የፍጅት ጠማቂዎች የሚገርመኝ ብርሀነ መስቀል የሚባለው ጉድ ነው። አሜሪካን አገር ሲሰራ የኖረበትን የጥብቅና ፈቃድ ከተቀማ በኋላ ለአገዛዙ አድሮ አምባሳደር ለመሆን የበቃው ብርሃነመስቀል አበበ “ፊንፊኔ ለሁለት ሺህ ዓመታት የኦሮሞያ ዋና ከተማ ነበረች” ፤ “ዐፄ ምኒልክ የኦሮሞህ ሕዝብ በባዮሎጂካል ኬሚካል ፈጀተዋል፤ ወዘተ እያለ ሲቀሰቅስ የሚውል ይውል የነበረ ፕሮፓጋንዲስት ነው።
ብርሀነመስቀል አበበ አምባሰደርነት ለመሾም ጭራውን ይቆላ በነበረበት ወቅት የዐቢይ አሕመድ አገዛዝ በኦነግ ታጣቂ ቡድን ላይ እርምጃ እንዲወስድ ይመክር ነበር። በመካከላቸው በተፈጠረ የጥቅም ግጭት የተባረረበት ወቅትና አምነስቲ ከአንድ ዓመት በፊት በወለጋ በአግዛዙ ኃይሎች ተወሰደ ያለውን የኃይል እርምጃ ይፋ ያደረገበት ወቅት ስለገጠለት ዐይኑን በጨው አጥቦ አምነስቲ ያወጣውን ሪፖርት <<በካፒታልዝም ስም የጭሰኛውን ስርዓት መልሰው በሕዝባችን ላይ ሊጭኑ የሚቋምጡት አሃዳዊያን>> የፈጠሩት አድርጎ አቀረበው።

ብርሀነመስቀል ከተባረረ በኋላ ወለጋ የሆነውን <በካፒታልዝም ስም የጭሰኛውን ስርዓት መልሰው በሕዝባችን ላይ ሊጭኑ የሚቋምጡት አሃዳዊያን>> ሲል ያቀረበው ከዐቢይ አሕመድ ጋር ተደምሮ ሽር ብትን ይል በነበረበት ጊዜ ኦሮምያ በሚባለው ክልል በተለይም ወለጋ ውስጥ ይካሄድ የነበረውን <<ጌታቸው አስፋ በኦሮሞ ስም ያደራጃቸው ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የከፈቱት የውክልና ጦርነት>> ፤ << በሕወሓት የሚታገዝ የኦሮሞ ካባ የለበሰ ጸረ ኦሮሞ አጀንዳ [አራማጆች] >> ፤ <<[የኦሮሞ ካባ የለበሱ] ጃንጃዊዶች ሽብር>> በማለት ይገልጠም የነበረውንና << ጌታቸው አስፋ በኦሮሞ ስም ያደራጃቸው ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች>> ፤ << በሕወሓት የሚታገዝ የኦሮሞ ካባ የለበሰ ጸረ ኦሮሞ. . . >> ፤ <<ጃንጃዊድ>> ሲል በገለጻቸውና ወለጋ ውስጥ ኦሮሞን አሸበሩ ባላቸው ሸኔዎች ላይ መንግሥት ትዕግስቱ አብቅቶ እርምጃ ሊወስድባቸው ይገባል እያለ በመከረው መሰረት የተወሰደውን የኃይል እርምጃ ነው። ብርሀነመስቀል ከውስጥ አዋቂዎቹ የሐጫሉን መገደል እንደሰማ “ኢትዮጵያ ኦሮሞን ገደለች” ብሎ ጻፈ። ቀጠለና ሐጫሉን ነፍጠኞች[ አማሮች ማለቱ ነው] እንደገደሉት ጻፈ። በአማሮች ላይ ያ ሁሉ ፍጅት የተካሄደው ይህንን መሰሉን የጥላቻ ዘመቻ ተከትሎ ነው።

የፍጅት ጠማቂዎቹ ወደፊት ለሚመጣው የኦሮሞ ትውልድም ርስ በርሳቸው እየተገዳደሉ አማራ ኦሮሞን ገደለው እያሉ ማመካኘታቸው ይቀጥላሉ። ነገ በሚጽፉት ታሪክም ዛሬ በኦሮሞዎቹ በጥላሁን ያሚ፣ አብዲ አለማየሁና ከበደ ገመቹ እንደተገደለ የተነገረውን ሐጫሉ ሁንዴሳን አማራ እንደገደለው አድርገው ማስተማራቸውን አይተውትም። ባለፉት ስድስት ዓመታት ውስጥ በበነራቸው የማኅበራዊ ሜዲያ ተሳትፎ ለማሰብ ፍቃደኛ ላልሆነው ወጣት ሲነግሩ የቆዩት ይህንን አይነት በፈጠራ ታሪክ ላይ የተመሰረተ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳቸውን ነው።

ባጭሩ እነዚህ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ እያመረቱ ለኦሮሞን ወጣት አማራ የኦሮሞን መሬት ቀምቶ እንደሰፈረ፣ አማራ ኦሮሞን እንደጨፈጨፈና ጡት እንደቆረጠ ሲያስተምሩ የከረሙ፣ ለበቀልና ለዘፍ ፍጅት ሲያሰለጥኑ የባጁ የኢትዮጵያ ጁቪን ሃብሪማናዎች ናቸው። በጃዋር መሐመድ የሚመራውና የዘር ፍጅቱን ያካሄደው ቄሮም የተደራጀው ሩዋንዳ የተካሄደውን የዘር ፍጅት ያካሄዱትና በቱትሲዎች ጥላቻ የሰከሩ ወጣቶች ኅብረት የነበረው የኢንተርሐሞይ ትጥቅና ዝግጅት እንዲኖረው ተደርጎ ነው።
ይቀጥላል…

12 Comments

 1. “ፕሮፈሰር መሐመድ ሐሰን የኦሮሞ ብሔርተኛት አባት የሚለው ዳኛ አሰፋ ዱላ ኢትዮጵያ ሆቴል ውስጥ የተገደለው በኦሮሞው በጃራ መስፍን በጥይት ተጠዛጥዘው ሲሆን ርስ በርሳቸው ተገዳደሉበት የጠባቸው ምክንያትም በመካከላቸው የተፈጠረው ቁርሾ ነው። ኦነጋውያን ግን ለኦሮሞ ወጣቶች ያስተማሩት ዳኛ አሰፋ ዱላን አማራ እንደገደለው አድረገው ነው።”
  በግል ፀብ ሁለት ኢትዮጵያውያን ተገዳደሉ: ሆቴሉ ደግሞ ዋቢሸበሌ ነበር::ጃራ መስፍን የራስ መስፍን ስለሺ የሸዋ ቆፍጣና የአማራ ልጅ ነው:: በእናት የወለጋ ኦሮሞ ነው::አንተ የዘር ትውልድ መዘርዘር ስለምትወድ:: በጊዜውም ግድያው ምንም ፖለቲካ ይዘት ያልበረው ነው::
  የአሁኑ ወቅታዊ ጥያቄ ወያኔ ከተላላኪው ኦነግ ሸኔ ጋር ኢትዮጵያን ለመበታተን ጦርነት ከፍታለች:: ይንተ ችግር ከኦሮሞ ልሂቃን ጋር ሂሳብ ማወራረድና ብሽሽቅ ነው:: ይህ ብሽሽቅ ደግሞ በኦሮሚያ ተበትኖ የሚኖረውን አማራ በአረመኔዎች ከማስጨፍጨፍ ውጪ የሚጨምረው አይኖርም:: ላንተ ብዙ ጀሌዎችን ሊኮለኩልልህ ይችላል:: በኢትዮጵያ ውሁድ ማንነት ያለው በብዛት አማራ ነው:: እንደ ሀገር ኢትዮጵያም ለዚህ የደረሰቸው አማራው ከኦሮሞ ወገኖቹ ተጋብቶና ተቀላቅሎ ስለኖረ ነው:: ዛሬም ኢትዮጵያ የምትረጋጋው ኦሮሞንና አማራውን ህዝብ በማቀራረብ ነው:: ከዚያ ውጪ የወያኔ መንገድ ጠራጊ መሆን ነው::

 2. ይህ ትንተናህ አገር ከዳነች በሁዋላ በሆነና እንዴት ቀልቤን  በሳበውና በተማማርንበት (ምንም እንኳ አንዳንድ ኢምቤልሽ ያረካቸው ቢኖሩም)። ቆይ ግን ትላንት በቪኦኤ  ስሰማ ነበር የወገንን ሲቃ። ፖሊስ ጣቢያ ተጠልለው የሚላስ የሚቀመስ አጥተው ፣ ቅሪታቸው አልቆ የሰው ያለህ የሚሉ። ምናለ ይህን ብእርህን እነሱን አይነት ለመታደግ ለህብረት ጥሪ በሆነና ደስ ባለኝ። እስቲ ዶር አክሎግን እያቸው እንዴት አድርገን በህብረት እንታደግ እንደሚሉ። አቢይን አፓርታይድ አድርገህ ዬትኛው መንግስት ለነዛ ምስኪኖች ሊደርስላቸው ነው በዛሬው ቀን? አገር በቋፍ እንዲህ ተይዛ ዖሮሞ ሲጠፋፋ እዚህ እንደደረሰ ብትነግረኝ ሀዘኔን ያበዛውና ልቤን ይሰብረው እንደሆነ እንጅ ዛሬን ላይ ሆነው የሰው ያለ፣ ያገር ያለ ለሚሉት ምን ይፈይድ ይሆን? እውነቱን እንነጋገር እስቲ ። እንደው ጥቅሙ ምንድነው? ምን ጠብ ይልላቸዋል? ሰምተሀል መቼስ  ጃንጃዊድ የምትላቸው  ለሸዋውም ዖሮሞ አልተመለሱም። ይህ ልጅ ከተሰየፈ ወዲህ ግልጽ የወጣ ጠላት፣ ከገዳይ ጀርባም ያለ እየተነገረ፣ እርምጃም እየተወሰደ  ስለ አቢይ “የሁለት አመት አፓርታይዳዊ” ስርአትና ስለ ዖሮሞ እርስ በርስ እየተጨራረሰ እዚህ መድረስ ብትነግረን በተጻራሪ የቆመው ሌላው ወገን ደግሞ ይመጣልህና “ለመጨራረሱ ደግሞ፣ ለመከዳዳቱ ደግሞ፣ ማ ማንን ያስተምራል – በናንተ አይብስ? ” ቢልህ እናንተ እርስ በርስ በየሚዲያው በምሁራዊ ቋንቋችሁ  ስትሞላቀቁ የእነዛ በቀደም ቤተስብ በግፍ ያለቁባቸውና ለመከራ  “የተረፉት”  ዜጎች ከሲሚንቶ ላይ መተኛት ወደ ክረምት ጭቃ መወርወራቸውም አይደል? ኸረ በኢትዮጵያ አምላክ እየተስተዋለ? በአንድነቱ ላይ ጉልበት ማባከኑ አይሻልም ብለህ ነው? አንዱ ያንተ አድናቂ የብእር ወንድሜ “ምናለ ከነ አቻሜ፣ የተከበሩ አቶ ሰርጸ” ብትማር ይለኛል። የተጠማሁት ምሬትንና ወይም ወቀሳን ሳይሆን አብሮነትንና ወቅታዊ አገር አድን የጋራ አጀንዳን ነው። ባልማረው ይቅርብኝ። ከአክብሮት ጋር።

 3. አቻምየለህ ታምሩ ቤተ ሰቦችህ እንዴት የወደፊቱን ቢገነዘቡ ነዉ ይህን ስም የሰጡህ?
  ተቺዎቹ አቻምየለህ ቄሮ ጫት ጠግቦ በተገዳደለ ቁጥር አማራና ኦርቶዶክስን ሂሳብ ማወራረጃ ማድረጉ ይቁም ነዉ ያለዉ። ጎበዝ ሰብአዊነት ካለ በዘር ልክፍ ካልተለከፋችሁ ይህን ሰዉ ልትደግፉት በተገባ ነበር። ያም ሆነ ይህ ግለሰቡ በእዉቀት ተመርኩዞ ሰነድ አገላብጦ ግፍና እልቂቱ እንዲቀር ማሳሰቡ ስህተቱ ምኑ ላይ ነዉ? የተናገርከዉ ስህተት ነዉ ከተባለ ማስረጃ አለኝ አንድ ነገር ነዉ:: እንዲህ አይነቱ አተካራና ሞራል መጣል የተመደብኩበት ስራ ስለሆነ መልስ መስጠት አለብኝ ካላችሁ ስራችሁ ነዉ ብለን እንቀበለዉ። በተረፈ ለማስተማሪያነት የሚያገለግል የነጠረ እዉቀትን በነጻ ለሚሰጥ ዜጋ ምስጋናዉ ቢቀር ዝምታም አንድ ነገር ነበር። እሱን እንደሆነ አሸማቆ ወደ ምሽጉ ማስገባት የማይሞከር ነዉ አታዉቁትም እንደዉም ያበረታዋል።

 4. ቆይ ሌላ ልጨምርልህና የመረጥከው አርስት እራሱ ለራስህ መልሶ ጥያቄ ይገባልሀል። ለመሆኑ የአቢይ መንግስት ነው እንዴ የሀጫሉን ግድያ በአማራ ያላከከው?ጽንፈኞቹ (ሁሉም አውሬዎች) መስለውኝ። እና የጻፍከው ማመልከቻ ለጽንፈኞቹ ነው? ካልሆነ በአማራ ያሳበበው ጽንፈኛ በየሚዲያው መስኮቱ እየፈነጨብህ “አፓርታይዳዊ” የምትለውን መንግስት መውቀሱ ለዛሬው መከራ ምን ጥቅም አለው? ይልቅ ምሁራን የምትባሉ ሰብሰብ ብላችሁ ሁሉን አካታችሁ መላ መፈለጉ አይሻልም? ሌላው ቢቀር እነዚህ የሚላስ ያጡትን ወገኖች ለመታደግ ያንን መከረኛ ታማኝን ተማጽነን ገንዘብ ሰብስብልንና እንርዳ ማለቱ አይቀልም? እኔ በበኩሌ የሰውን ልጅ የምለካው በደረደረው የዲግሪ ዶቃ ወይም አካዳሚክ ክህሎቱ ሳይሆን በሰው ሰውኛው ነው። ቅንነትን ላልተላበስ ምሁርነት ክብር የለኝም – ጨርሻለሁ።

 5. አባ ዊርቱ ብዙዎች ፅሁፋዎችን አስተይየርቶችህን ለንፅፅር ይረዳ ዝንድ አነባቸዋለሁ;;ሁሉም እውንት እንደ ኮሶ የሚመርህ ነገሮችን እንደ ዘሙድህ ማስመስል የምትወድ አስመሳ ብተለይም የቆሮ እጅግ አረመኔነት ያደረስው በደል እዲሽፋፈን የምትወድ ስው መሆንክ እርዳለሁ::ከይቅርታ ጋር አንትም በኦሮሙማ ፅንፈኝነት ገመድ ውስጥ ያጠለቅ መሆንክን አስተያየትህ ያሳብቃል::
  አንድ ነገር ልጠይቅህ መቼም ሀኪምም ባትሆን አንድ ቀን ታመህ ወይም ዘመድ ይዘህ ሄደህ እንደሆነ እገምታለሁ::አዎ ህመምህን ለሀኪም ስትገልፅ የሚስማህን የህመም ስሜት ምልክቶችና ያስከተለብህን ጉዳት በጭንቀት ታስረዳለህ::እዚህ ጋ የሀኪም ጥበብ ይህን ስሜት እንዲፈጠር ያደረገውን መንስኤ መመርመር ይሆናል;;ብነገርከው ምልክት ብቻ ተነስቶ መድህኒት የሚያዝልህ ከሆነ በግምት ይህ ይሆናል መንስኤው ብሎ በከሆነ ከህመም መዳህ ግማሽ ብግማሽ አልፎም ህመህን ወደማባባሱ ይዘላል;:;:ሆኖም ብልሁ ሀኪም በነገርከው ህመም ስሜት ተንስቶ በእምተ ላይ ምርመራ ይጀምራል ከዛም ለተጨማሪም የበሽታህ መንስኤ የሆነውን ንገር ለሜጤን ወደ ከፍተኛየተለያየ ምርመራ ይክህል::ከዚያም ከምርመራው በተገኘው ውጤት መድሃኒት ወደ መምርጥና ማዘዝ ይሽጋገራል::ይህ ህመምትኛውን በግዜ ልታድነው የምትችለው ይህ መንገድ ብቻ ነው:: ይህን ያነሳሁብህ አንተ እንዲንገር የምትፈልገው የበሽታው መንስኤ ባስከተለው ምልክትን ብቻ ተንስተው በዛ ላይ ተረባርበን ዝንተአለም የስው ህይወት ዘወትር እየቀጠፈ የህመም ማስታገሻ እየስጠን እንቀጥል የምትል በማር የተለውሰ መርዝ ለደሁው እየተስጠ እንዲቀጥል የምትፈልግ በአፍቅሮተ አብይ የስከርክ ወይም አንተም የኦሮሙማ እቀንቃኝ ድብቅ መስሪነትህን ከመመስከር በስተቀር መፍትሄ አያመጣም::
  አባዊርቱ ; አቶ አቻሜለህ አቶ ስርፅ እየተናገሩ ይሉት ይህን እስከዛሬ ድረስ ያስከተሉውን ይዘር ጥላችና አርመኔአዊ እልቂት መንስኤው ላይ ነው::ይህ በደንብ ተረግጦ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ስው ንኝ ያለ ሁሉ በችግሩ መንስኤ ላይ በግልፅነት ህዝብና መንግስት መወያየት ሲችሉና አስትማሜኝ የማያዳግም በመርህና በግዜ ላይ በጋራ ተነስተው መፍትሄ ሲያመጡ ብቻ ነው;;ይህ ደግሞ ወቅቱ አሁን ነው::እስከ መቼ እራሱ ኦሮሞ በፈጠረው የሀስት ትርክትና ጥላቻ በተለይም አማራ በአረመኔአዊ ጭካኔ በገጀራ እየገደላችሁ ሬሳ ስታቃጥሉ ንብረት ስታወድሙ ስታስለቅሱ ትኖራላችሁ?ፍላጎትህ ቄሮ አትበሉ አሁን ጥቃት የደረሰባቸውን አስታሙ !አብይንም አትናገሩ ስትል ጭራሽ አእምሮህ እረፍትያገኛልን?ለዛች አገር መፍትሄው ሁሉም ያገባኛል የሚል ቡድን ህዝብ መንግስት በመንስኤው ላይ ተነጋግሮ መድሃኒት ማግኘት ሲችል ብቻ ነው::
  ወንድሜ አባዊርቱ ,እስቲ በቅን ልቡና ተመከተው?የተከበሩ አቶ አቻሜለህ ግዜውን ውስዶ የትደበቀ ውንእያወጣ ያጋራናል::ጥንትም ዛሬም ድረስ ኦሮሞ ሞተው በራሱ ኦሮሞ ነው::ወንድማችን የሞተው በራሱ ኦሮሞ ነው ሌላ የለበትም እያለ ማስረጃ እያሳየን ነው ስውመሆን ከቻልን::በዚህ መረጃን በደንብ ፈትሽን እየተስራበት ያለውን የሀስት ጥላቻ ቅስቀሳ ማስቆምና ትውልድን ማስተማር ለሁሉም ኢትዮጵያ በእኩል የሚያገለግል ህገመንግስት ማውጣት ስንችል በዛች ምድርን ስላምን ብልፅግና ማምጣት እንችላለን ;:ወንድም አልም እውነት መቼም ቢሆን እንዲነገር አትጥላ!!ወንድሜ ሀስት በጣም አደገኝ ናት ጌታችንን እየሱስ ክርስቶስ ይስቀለች ለማንም የማትመለስ ቀን ቆጥራ ለበቀል የምታነሳሳ ክፉ መርዝ ነች ይህን አትጥላ!!ችግሩን እስከመቼ ተሽክመን እንኖራልን?እየሱስ ክርስቶስ ያስተማረን እውነት እውነት ሀስትን ሀስት እንድንል የሚያስተውል ክፉን ከደጉ እንድንለይ እንድንችል አእምሮአበጅቶልን ነው
  አባዊርቱ !እስቲ አስተውል እነአብይ እየስሩት ያሉበት አንድ መንገድ ኦሮሙማን ለመጥቀም ኦሮሞ ፈርስት በሚያስኝ መንገድ::የአንድ አጫሉን ሞታ ብቻ እንጅ ከፍታ የስጡት ለሌላው 259 ምንም ግዴታ እንዳልተስጣቸው እያስተዋልን ነው::እስቲ ብሄሪዊ የሀዘን ቀን ብሎ ማወጅ ማንይጎዳል? በህይወት ለተረፉት ፈጣን እርዳታ መንፈግስ?ወይስ አዲስ አበባ ላይ ትምህርት ቤት በአጫሉ መስየም በራሱ ኦሮሞ ተገድሎ?ስማእታቱስ 259 በምን ታስቡ?እንዴ እነእንጅነር ስመኝ ሲገደል ምን መታስብያ ተደረገለት?እነአብይ በእኩል እያስተዳደሩን ነው ለማለት እንደፍርም!እነ እስክንድር ወጣቱን ራስህን ከጥቃት ተከላከል ማለት እንዴት ተደርጎ ወንጀል ይሆናል?ለምንስ ይደበደባል?ጁሀር ሳይደበደብ!እንጅነር ይልቃል ተድብድቦ ለምን ይታስራል?
  አሁን ወሮ አዳነች አቤቤ ለዚሁ ለomn ገቢዎች አስተዳደር በነበርችበት ወቅት 45 ሚልየን የሀገሪቱን ገንዘን አውጥታ ስትስጥ ይህን ጥፋት ይበልጥ ርእንዲስሩበት አይደለምን?ሹመትስ ቢሆን አብይ የሚስጣቸው ሹመቶች ቅድምያ ምርጥ ምርጡን ለኦሮሙማ ኡይደለምን?ይህ ህውሀት ቀደም ሲል ሲያደርገው የነበረውን አይነት አይደለምን?
  አባዊርቱ እውነት እንዲነገር እንደማትወድ አውቃለሁ::እግዚአብሔር ሁላችንንም ማስተዋል ስጥቶናልና እውነት ከመናገር አንቆጠብም!ማስመስልንም እንጠየፋለን!ብዙ ብዙ ማለት ይቻላል!ግንአንድ ነገር ማወቅ ያለብህ ፍጥረትሁሉ ምድሪቱ ሁሉ የእግዚአብሔር ሀብት ነው::የተስጠችንም በፈቃደ እግዚአብሔር በፍቅር በስላም በእንድነት የእርሱን ፈጣሪ ህግና ትእዛዝ ተቀብለን እየፈፀምን እይመስገን እንድንኖር ያው ለግዚያዊ ህይወት ነው:;:ነገ በየትኛው ስእት በምን መንገድ እንደሚመጣ የማናውቅ ስው በፍቅር መኖር ትልቅነት ነው::እነዚህ በአይሲስ መንገድ የሚሄዱ አረመኔ ቄሬዎች በኦሮምያ ምድር መብቀላቸው ባዝንም ቤተስብ እምነት የሌለው አምላኩን ፈጣሪውን ከረሳ ርንዲመለሱም ካላስተማረ ክፉ ቤተስብ መፈጠራቸው ነው::ታሪክም እንደ ግራኝ አህመድ እንደሂትለር እነደ አይሲስ ታሪክ ይዘክራቸዋል?እግዚአብሔርም በራሱ አምሳል አምሳል በዚህ መልኩ በጭካኔ አየገደሉ ሲጨፍሩ ዝም አይልም!ዕድሜ ይስጠን ሁሉንም እናያለን!
  እግዚአብሔር ልቡና ይስጠን!
  ወንድምህ!
  እናንተም ትውልድ እንዲማር እንዲድን ከፍተኛ ስራ የምትስሩ የዘሀበሻ ድህረ ገፅ ባለቤቶች እግዚአብሔር ስራችሁን ይባርክ!እደጉ!ተመንደጉ!ብዙ ተባዙም!!!

 6. “አማራ እንዴት ተጠያቂ ይሆናል!?”
  ልክ አንተ ዛሬ እንደሚታደርገው፣ የአማራ መንግስት ራሱ ገድሎ፣ መልሶ የተበዳዩን ወገኖች ለወንጀሉ ተጠያቂ አድርጎ የልብወለድ ታሪክ በመጻፍ!
  አንድ ሰው በአማራ የገዢ መደብ በዉሸት ተመስክሮበት፣ አይኑን በጨፈነ የአማራ ዳኛ ሞት ተፈርዶበት ቢሰቀል፣ ፍርዱን ያስፈጸመው/ የሰቀለው ድሃ ፖሊስ ኦሮሞ ቢሆን ኦሮሞ ገደለው ልትለን ነው (ለምሳሌ መ/አ ማሞ መዘምር) !
  ሰውን ለማደናገር ከመጣር ይልቅ መጀመሪያ በአንድ የፖለቲካ ስርዐት (political system) እና በግለሰብ ወይም የግለሰቦች ስብስብ መሃከል ያለውን ልዩነት ተረዳ! አንድ ባለፋብሪካ ሺህ ሰራተኞችን ቀጥሮ ቢያሰራ፣ እሱ አንድ ብቻ ስለሆነ ፋብሪካው የሰራተኞቹ ነው፣ ነው ያንተ ሎጂክ! ላለፉት የኢትዮጵያ መንግስታት ተቀጥረው የሰሩ (በተለይ በዉትርድናው መስክ) ብዙ ኦሮሞዎች ቢኖሩም፣ የሰለሞናዊውን ስርወ መንግስት የኦሮሞ ሊያሰኘው አይችልም። ስርወ መንግስቱ፣ የርዕዮተ አለም፣ የዘር፣ የባህል፣ የሃይማኖት፣ የቋንቋ፣ የመሳሰሉ ዋና ዋና መለኪያዎች ነበሩት፣ ዛሬም ከነዚህ ብዙዎቹ አልተለወጡም! በነዚያ መለኪያዎች እስከዛሬ ያለው የኢትዮጵያ መንግስት የሃበሻ (ባብዛኛው የአማራ) መንግስት ነው! ያንተ የተጣመመ የታሪክ አረዳድ፣ ነገሮችን በቁንጽል ወይም ከcontext ዉጪ አጣሞ በመተርጎም “የታሪክ ማስረጃ” ለማቅረብ የምትሄደው መንገድ ሰውን ያሰለቸ፣ ከደነቆረ ጋር መጯጯህ ስለሆነ መሙዋገት ዋጋ አይኖረውም።

 7. “ሐውልት የቆመለትን የጡት ቆረጣ ታሪክ ሳይቀር በኦሮሞ ላይ የፈጸመው ኦነግ እንጂ አማራ አይደለም።” ይለናል አቻምየለህ አይኑን ሳያሽ! “ኦነግ” የተቋቋመው በ1974 (GC) ሲሆን፣ ጡት ቆራጩ ምንልክ የኖረው እስከ1913 ይመስለኛል። በዖሮሞ ጥላቻ በመናወዝህ ምክንያት ትንሽ አልተምታታብህም?? ነጋሶ “ነገረኝ” ብሎ የታሪክ ማስረጃ የለም፣ ነጋሶም ሞቶዐል!
  ለነገሩ፣ ሃበሻ ብሎ ምሁር እንደሌለ እየገባኝ ነው። ከናንተ ጋር መዳረቅ ድንጋይን እንደመቀቀል ነው፣ ላይበስል! “Retarded” ናችሁ ብላ የለ ሚሚ ስብሃቱ!?

 8. ጉዱካሣ ሆይ፣ እንደው ወደ ሌላ ሳልሄድ እስቲ ከሀኪሙ ተምሳሌትህ ተነስቼ ይህን ልበል። ምናልባት የችግሩን ጥልቀት ትረዳልኝ ይሆናል። ምን ሲደላ ነው ይላሉ አማሮቹ። የምትለኝ ያለው “እስቲ ረጋ በል፣ መጀመርያ ሀኪሙ የደረስክበትን በሽታ በጥሞና ይመርምረውና ይድረስበት፣ አለበለዚያ ያልሆነ መድኃኒት ይታዘዝልህና ከበሽታው አትፈወስም” አይደል የምትለኝ? ይሁን። እኔ የምለውን ደግሞ ተረዳልኝ እንዲህ። how about በሽታው ER ከቶኝ  ሀኪሙ ገና ጊዜ ወስዶ እንኳን ሊያጠናውና ሊታደገኝ ቀርቶ ነፍሴ ድንገት ልትወጣ ቀርቦ ኖሮ ባካበተው ክህሎትና በጥቅሉ ከነገርኩት በመነሳት ለግዜው የሜዲካል ኮሚኒቲውና ያጠናው ትምህርት ያስታግሰዋል ብሎ ያመነበትን ማስታገሻ ከሰጠኝ በሁዋላ ለዋናው ፈዋሽ መድሀኒት በቀጠሮ መለያየት አይሻልም ብለህ ነው?  እንደውም በሽታዬን የማስረዳበቱ አንደበት ሁሉ ታስሮ በቃሬዛስ እንደሆነ ሀኪም ቤት ደጃፍ የተጣልኩት?  እና ” ቆይ ላንቃው እስኪከፈትና በሽታውን እስኪያስረዳኝ ልጠብቅ ይላል ወይስ እስፔሻሊስቶቹን ሁሉ ሰብስቦ በአይናቸው ከሚያዩትና አከላቴን በመመርመር ጊዜያዊም ቢሆን በኦክሲጂንና በመሳሰሉት ሊታደጉኝ medical ethics ግድ ይላቸዋል? እኛ እኮ ያለነው በዚህ ER ሁኔታ ላይ መሰለኝ። እና የአንተና መሰል ወንድሞቼ አይደለም ከቅድመ ሀጫሉ እልፈት  የትላንትናውን የመንግስት ጉድፍ ለቀማ ዛሬ ላይ ለሞቱት ይሁን በቁም ለሞቱት ወገኖቻችን ምን አይነት መፍትሄ ይሆናል? እስካሁን የምከትባቸውን ያየ ወገንተኛ አለመሆኔን ቢረዳም “የስውር የዖሮሙማ አቀንቃኝ  ካባ” ካጠለክልኝም መቼስ የመጻፍ መብትህ ነው – እኔነቴን አውቀዋለሁና። አሁን ጉዳዩ ስለኔና አንተ፣ ስለ አቻሜና አቶ ሰርጸ አልነበረም ብንታደለው ኖሮ። ስለአገርና ወንበዴዎች ብቻ መሆን ነበረበት። አንተው የኔን ዖሮሙማ አቀንቃኝነት የተጠራጠርከውን ያህል አንተን ሆነ አቶ ሰመረን “አይ ጉዳችን ፣ እነዚህ ይሆኑ እንዴ ghost amaras ” ብዬ እንደሆነ በምን አውቀህ? እኔ እንኳ አቢይ ወደመድረክ ከመጣ ጀምሮ ቅንነቱን አይቼ ፣ በስሩ ያሉት ከሀዲዎች ሆነውበት እንጅ ስንት ቁምነገር ለአገር በሰራ ” በሚለው ለ ሁለት አመት ዝንፍ ሳልል እናንተ ግን እንዳስተዋልኩት ከ ሀጫሉ እልፈት በሁዋላ አስተዋይነታችሁ ቀርቶ ሳታስቡት የተከናነባችሁት፣ እኔም ከልቤ አምኜ ተቀብዬው የነበረው የእትዮጵያዊ መልካሙን ካባ አውልቃችሁብኝ ጠርጥሬስ ቢሆንና አይ ይቺ አገር አላልኩም ብለህ ነው? ወደሁዋላ እየሄዱ ፋይል ማገላበጥ የአሣውን ጎርጔሪ ነገር አያመጣ ብለህ? እስቲ በሚያስማሙን እንስማማ።

  1) ወገኖቻችን የተጨፈጨፉት አዎ በአክራሪ ዖሮሞ ደመነፍሶች ነው – ለኔ ሰዎች አይደሉም – በተለይም ደግሞ በሰለጠነው አለም እየኖሩ “በሏቸው” የሚሉ
  2) እነዚህን ደመነፍሶችን የሚዘውረው ህውሀት ተብዬ የአመዳም ጅቦች ጥርቅም ነው
  3) መንግስት ባለፉት አመታት ብዙ ስህተት ሰርቷል። እርምጃ አለመውሰዱን ልክ እንደጠረጠርኩት ዛሬ አቶ ታዬ ደንደአ ዘርግፎታል -ፈልገህ አድምጠው

  እንግዲህ የኔ አቶ አቻምየለህን ሆነ የአንተን ወንድሜን ትችት ዛሬ ለሚሆነው መንግስትን ተጠያቂ ማድረግ ችግሩን ያቀለዋል ወይስ ያብሰዋል? መፍትሄ ለመፈለግ ከሆነ ከላይ የጠቀስኩልህ የኢመርጀንሲ ሩም ምሳሌዬ መልስ ካልሆነ የምትለኝን ለመቀበል እቸገራለሁ። እውነት ስውር ተልእኮ ከሌላችሁ ይህን ለመረዳት ቀላል ነው። በርግጠኝነት የምነግርህ የአቢይን ሀጢያት ሀምሳ ሉክ ብጽፈው ዛሬ በጣር ላሉ ወገኖቻችን ቅንጣት የሚተርፋቸው አይኖርም። ግን አክራሪን ወይም ይህን መስማት ለሚፈልግ ዜጋ ብዬ ጉልበቴን በወቀሣ ላይ አላባክንም።  ለዛሬ ፣ ለነገና ተነገ ወዲያ ለሚሆነው የሁላችን ኢትዮጵያ ፖዚቲቭ በሆኑ ነገሮች ላይ ከመጠመድ ግን አልታክትም። ይህንንም የምለው እንደው የተሳሳተ ግንዛቤ ስለያዝክብኝ እንጅ እሰጥአገባውን ወድጄው አልነበረም። 
  በዚህ ልሰናበትህ
  ወያኔ ኢትዮጵያዊነትን እንዲጠላ 30 አመታት ኮትኩቶ አርሞና ጎልጉሎ ያሳደገው ትውልድ አለ።  ታዲያ ይህን ወያኔ ቢላሽ ያረግብንን  ትውልድ  ሲሆን እንደማንቃት እንደ አቻሜለህ ያሉ (ብዙ ህዝብን የሚያቅራርቡ ሀሳቦች እያሉ) አበጣባጭ የሆኑ hot button issues ማቀጣጠል ለታዳጊ  ዖሮሞው ይሁን  እሱ ለሚቆጭለት አማራና ኢትዮጵያ አይጠቅምም ብዬ በጽኑ አምናለሁ።አስራስምንት ነጥብ እስከሰረዙ። ይህው ነው።

  • አባውሪቱ ህመምዎትን ማንም መረዳት ይችላል እውነት ነው፡፡ የአቢይ አስተዳደር ውስጥ የሚሰማዎት ጆሮ ካለ መለዕክት ላኩለት፡፡ አብይ የልምምድ ጎማውን ማውለቂያውን ግዜ ተላልፎታል፡፡ 3 ዓመት ያየነው ሰቆቃዊ የዘር ማጥፋት ዘመቻ የውጪ ወራሪ ጣሊያንም ካደረገው ጦርነት ሊትካክል ትንሽ ነው የቀረው፡፡ አራዊቶችን ሥጋ በማሳየት እድሜ ሊስጡ ይችላል ነገር ግን እዛው አጥር ውስጥ አስገብቶ ማግለል ተፈጥሯዊ ገዴታ ነው፡፡ ይሻላቸው ይሆናል እያለ የትዕግስት ዝምታው የባሰ አገር እያጠፋ ነው፡፡ በጭነት መኪና እይተዘውዋወሩ የኪላ ይለፍ እየተሰጣቸው ህዝብን በገጀራ ማረድ ሁለት መንግሥት ያለበት አግር ንው የሚያሳየው፡፡ አስተዳደሩን ክላይ እስከታች አብይ ማጽዳት የግድ ይለዋል፡፡ የታጠቁትን ወያኒን እና ኦነግን ትጥቅ ማስፈታት አለበት፡፡ ትጥቅ ስንል አጣና ላይ ሚስማር ሰክቶ የሚቅበዘበዝውን አራዊቶች ጨምሮ;

 9. በ21ኛው ክፍለዘመን ወንድሙን ዘቅዝቆ የሚሰቅል ፤ በቆንጨራ የሚያርደ ፤ ዱላ ላይ ሚስማር ቸንክሮ ወገኑን የሚገል ፤ መማሪያ የትምህርት ተቋሙን ፤ የዜጋው የእለት ጉርስ ማግኛ ተቋማትን ፣ የጤና ጣቢያዎችን የሚያወድም ነው “Retarded” ውይንስ በእውቀትና በመረጃ የሚያስተምርህ አቻምየለህ ታምሩ ?

 10. Jara Mesfin illegally grabbed the ancestoral land of Assefa Dula, bringing this feud between the two which resulted in they shooting and killing each other at Ethiopia Hotel. This incident brought the end of sharp shooting culture in Ethiopia, thus DERG military was able to overthrow Hailesselasie with little resistance from the students or from the public because the military had all the sharp shooters. Finally after so many years EPRDF replaced DERG because EPRDF fighters practiced sharp shooting .

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.