ይድረስ ለዘሓበሻ ለጥያቄየ መልስ ካገኛችሁ? ለምን ይህ ሁሉ ጭቃኔ ለሻሸመኔ !!!

ይድረስ ለዘሓበሻ ለጥያቄየ መልስ ካገኛችሁ?
ለምን ይህ ሁሉ ጭቃኔ ለሻሸመኔ !!!
1658 scaled

1 Comment

 1. እኔ ከዘ-ሐበሻ ዝግጅት ክፍል ጋር የሚያነካካኝ አንድም ነገር የለም።
  ግን እንደ አንድ ወገን ለጥያቄህ ምላሽ ይሆናል ያልኩትን እንሆ። ችግሩ የተፈጠረው ዛሬ አይደለም። ወያኔ የሃገር አለቃ ከሆነ ጀምሮ ሰዎች በዘራቸውና በቋንቋቸው ጥቃት እንደደረሰባቸውና እየደረሰባቸውን እንደሆነ ያለፈውን መለስ ብሎ አሁን ከምናየው ግፍ ጋር መመልከት ይረዳል። በመሰረቱ ዘርና በቋንቋን ተገን አርጎ በክልል የተከፋፈለ ሃገር የሰው መኖሪያ ሊሆን አይችልም። ከለለ ማለት አጥር አበጀ፡ የእኔ ነው አለ ማለት ነው። ሰካራሙ የሃገራችን ፓለቲካ ወንድምና እህቱን ገድሎ የሚፎክር ነው። አሁን ለሚሆነውና ቀደም ብሎ በወያኔ በኩል ለሆነው መሰረቱ የፈጠራ ታሪክና ጥላቻ ነው። በዚህም የተነሳ ወያኔና ወልጋዳ የኦሮሞ ፓለቲካ አቀንቃኞች ዛሬም የሰው ደም ያፈሳሉ። በሌለ ነገር ላይ ኡኡታ ያሰማሉ። የሚከተሉትን ነጥቦች እንመልከት።

  1. የችግራቸው ሁሉ መንስኤ ነፍጠኛ ነው ብለው ያምናሉ 2. አማራንና የኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያንን አንድ አርገው ያያሉ 3. የዛሬ ምዕተ ዓመት እንዲህ ጉዳት ደርሶብናልና አሁን እንበቀል ብለውም ያምናሉ። ለዚህ ፕ/ህዝቅየል ጋቢሳ፤ ዶ/መራራ፤ ጃዋር እና ቆንጨራ ይዘው የሰው ዓይን እያወጡ እሳት የሚለኩሱትን እብዶች ድርጊት መረጃ አርጎ ማቅረብ በቂ ነው። 4. ሰው ባጭሩ የጅምላ ሃሳቢና ተሰላፊ በመሆኑ በራሱ አስቦ መቆም አይችልም። በዚህ ዙሪያ እውቁ ጀርመን አሜሪካዊ ገጣሚ Charles Bukowski – The Genius of the Crowed ማንበቡ ጠቃሚ ይመስለኛል። አንተ ከባህር ማዶ ሆነህ የምትስላት የድሮዋ ሻሸመኔ እና ሌሎችም ከተሞች ዛሬ ሰው በዘሩ የሚሳደድባት የእብድ መንጋ ሰውን እንደ እንስሳ አርዶ አስከሬኑ እንዳይታወቅ ነዳጅ አርከፍክፎ የሚያቃጥል በአልኮልና በጫት እንዲሁም በአደንዛዥ እጽ የደነዘዙ በዘራቸውና በቋንቋቸው ዙሪያ የሚንጋጉበት ስፍራ ነው። አረብና ሻቢያ ጋግሮ ለወያኔና ለኦሮሞ ጭፍን ፓለቲከኞች ያከፋፈለው ይህ የዘር፤ የቋንቋ የክልል ፓለቲካ ገና ብዙ ገመና በህዝባችን ላይ ያመጣል። አትራፊ ግን አይኖርም። ጭፍኖቹ ቄሮዎች መስሏቸው ነው እንጂ የጠሉትን ሁሉ ገድለው ሲጨርሱ እርስ በርሳቸው እንደሚተራረዱ ግልጽ ነው። ፓለቲካ ለዛውም የዘር እሳት ተጨምሮበት ማቆሚያ የለውም። ሁሉን ይለበልባል። በቅርብ ጊዜ በተለያዬ የኦሮሚያ ከተሞች ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች እኮ ሃገር ሰላም ነው ብለው እያሉ ነው በተቀናጀና በተጠና መልኩ የሞቱት፤ ቤታቸው የተቃጠለው፤ የተዘረፉት፤ የንግድና የመማሪያ ተቋሞች የጋዪት በዝርዝር በተያዘ አሰራር ነው። እንዲሁ በነሲብ ግር ብሎ በግብታዊነት እንደ ተፈጸመ አድርገው የሚናገሩ ሁሉ ሴራው ያልገባቸው ተላሎች ወይም ወሬን በማማታት እውነትን ለመደበቅ የሚሹ ብቻ ናቸው።
  አሁን 220 ሺህ ወታደር አለኝ ኑ ግጠሙኝ የሚለው ወያኔ እነርሱ ሊሞቱ ሳይሆን ያው እንዳለፈው ሁሉ የድሃ ልጅን ለመማገድ ነው። ግን የዶ/ር አብይ መንግሥት ልፍስፍስ ነው። የዘረፉትን ሃብት መቀማት፤ በወጀላቸው መጠየቅ ሲኖርባቸው ትግራይ ላይ መሽገው የትግራይን ህዝብ በማፈን ለጥፋት ስራቸው እየተጠቀሙበት ነው። የከያኔ ሃጫሉ ግድያም በወያኔና በኦሮሞ ሃይሎች ተቀነባብሮ በኦሮሞዎች የተፈጸመ እንጂ ሌላ ሚስጢር የለውም። ስለሆነም አንተ ከሩቅ ሆነህ ስለ ሻሸመኔ Nostalgic መሆንህ በሻሸመኔ የተፈጸመውን ግፍና መከራ ከሂሳብ አላስገባም። ስንቶች በእሳት ነደድ፤ ስንቶች አንገታቸው በስለት ተቆረጠ፤ ስንቶች በድናቸው ተጎተተ። አንድ የኢንተርኔት አገልግሎት የተዘጋበት ዋናው ምክንያት ሲገድሉ ፊልምና ቪዲዪ እያነሱ ስለነበር የክፋት ስራቸውን ሌሎች አይተው የብቀላ ሥራ እንዳይፈጽሙ ነው። ችግሩ በሃርር፤ በባሌ፤ በአርሲ በሽዋና በአዲስ አበባ እንዲሁም በሌሎችም የኦሮሚያ ክልልች የተፈጸመ እንጂ ሻሸመኔ ላይ ብቻ የሆነ አይደለም። ፓሊሱ ቆሞ እያየ ሰው ተዘቅዝቆ በሚሰቀልባት ሃገር፤ የክልል ልዪ ሃይል የሚባለው አብሮ ተሰልፎ አይዞአቹሁ በሚልባት የሙታን ምድር ሰው በሰውነቱ ተከብሮ ይኖራል ብሎ መገመት እብድ መሆን ነው። አላማው ሚስጢራዊና የውጭ እጅ ያለበት ጭምር እንጂ እንዲሁ በሰፈር ልጆች ጥል የተነሳ ችግር አይደለም። ስለሆነም የአንተም እይታ ከሻሸመኔ ባለፈ መልኩ ዘር፤ ቋንቋ፤ ሃይማኖትና ክልል ሳታበጅ ለሰው ልጆች ሁሉ ነገር ሰላም እንዲሆን በመስራት የምትችለውን አስተዋጾ አድርግ። ሌላው ሁሉ ውሃ ወቀጣ ነው። የሃገራችን ፓለቲካ ሰው በላና ደም ጠጪ ነው።
  ስንቶችን አፈር መልሷል። ግን ማብቂያው መቼ ይሆን? ያ ቀን ናፈቀኝ።
  በቃኝ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.