ከሃውልቱ ጀርባ ያለውን ድንቅ ኢትዮጵያዊ ታሪክ እና ክቡር ኢትዮጵያዊነት ግን በፍጹም ማፍረስ አይቻልም – ቴዎድሮስ አበበ ዋሽንግተን ዲሲ

ቴዎድሮስ አበበ
ዋሽንግተን ዲሲ
232

የወንድማችንን የሀጫሉ ሁንዴሳን ነፍስ ቸሩ አምላክ ይማርልን። ለቤተሰቦቹና ለወዳጆቹም መጽናናትን ይስጥልን። ለክቡሩ የሰው ልጅ ሕይወት ክብር የማይሰጠው ክፋት፣ ጭካኔና ዘረኝነት ከአገራችን ይጥፋልን። ሰላም፣ ፍቅር፣ መተሳሰብ፣ አንድነት ይብዛልን…

106422112 304423320936512 8748718416384155087 o
ሃውልት ማፍረስና ታሪክ ማበላሸት መፍትሔም፣ አዋቂነትም አይደለም። ለዚህ ሁሉ ችግርና የሰው ሕይወት መጥፋት ምክንያት የሆነውን ዘረኝነትን ነው ማስወገድ ያለብን
106505012 304847760894068 3779597107497286497 nኢትዮጵያዊነት በጭፍን ጥላቻ የሚመራ የዘረኞች መጫወቻ አይደለም። ኢትዮጵያዊነት የሰው ሕይወት በማጥፋት፣ ቤተ ክርስቲያን በማቃጠል፣ ንጹሓንን በማሳደድ የሚያምን የመንጋ አስተሳሰብ አይደለም። ኢትዮጵያዊነት የኢትዮጵያ ባለውለታ ለሆኑ ታላላቅ ሰዎች ክብር ይሰጣል እንጂ ከባህልም ሆነ ከሰብአዊነት ውጪ የሆነ የጥላቻ ሃውልት አይገነባም።
ስለሆነም የዛሬው ኢትዮጵያዊ ትውልድ በዘረኝነት ከተመረዙ፣ በጥላቻ ከሚጋልቡ ግለሰቦች ራሱን መጠበቅ ይኖርበታል። በኢትዮጵያና በህዝቧ አንድነት የምናምን ልጆቿ በሙሉ አሁንም ዘረኝነትን አጥብቀን እንቃወማለን፤ ለኢትዮጵያ አንድነትና ታሪክ በጽናት እንቆማለን። እውነታው ይኸው ነው።
107372467 306849744027203 197355819733385851 n“. . . በየጊዜው የሚደርሰውን ችግር በመታገስና ተስፋ ባለመቁረጥ፡ ይልቁንም በእግዚአብሔርና በትክክለኛ ፍርድ ላይ ያለንን እምነት መሠረት በማድረግ እስከ መጨረሻው ድረስ በቁርጠኛ አሳብ ጸንተን የፈጸምነው ትግል ፍሬ አፍርቶ ድልን ለመጐናጸፍ በቃን። ይህ ድል በትምክህትና በትዕቢት ሳይሆን በአምላካዊ ረድኤት መሆኑን ከማመን ሕሊናችን ምንጊዜም ተዛብቶ አያውቅም።”
— ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ
ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ
“ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ”
ኢትዮጵያዊ ፈሪሀ እግዚአብሔር ያለው፣ ደግነት የተቸረው፣ መተሳሰብንና ጥሩ ጉርብትናን የሚያውቅ የአንዲት ታሪካዊ አገር አንድ ሕዝብ ነው። ይህ ማንነታችን “ነበር” ሆኖ እንዳይቀር ጥቂቶች ለማሰራጨት የሚሞክሩትን የዘረኝነትና የጥላቻ መርዝ አንድ ላይ ሆነን “አይሆንም! በቃ!” እንበላቸው። ኢትዮጵያዊው አቋማችንና የሰላም ድምጻችን የክፉዎችንና የከፋፋዮችን ከንቱ ሙከራ በእርግጠኝነት ያሸንፋል። የኢትዮጵያና የህዝቧ አንድነትም ለዘለዓለም ይኖራል። እንበርታ!
የሰሞኑ የአገራችን ሁኔታ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈ ቃል አስታወሰኝ . . . “ጻድቅ የድሆችን ፍርድ ይመለከታል፤ ኅጥእ ግን እውቀትን አያስተውልም። ፌዘኞች ከተማቸውን ያቃጥላሉ፤ ጠቢባን ግን ቁጣን ይመልሳሉ . . .” (መጽሐፈ ምሳሌ ፳፱:፯-፰)
እንደ ቀድሞዎቹ ጠቢባን እንሁን።
ለዛሬዎቹ . . . (ከዓመታት በፊት የተጻፈ)
10693877

እንደ መጻሕፍት የፖስታ ቴምብሮችም የማይጠፋውን የኢትዮጵያ ታሪክ ያስታውሱናል። ለምሳሌ ያህል (from my stamp collection album)…

 

83341335 309077830471061 55819887270201070 n

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.