የሚሊዮን ጉንዳን ሸክም – ከአባዊርቱ

Gundanበቅርቡ ዶር አቢይ በፓርላማ እንዲህ ብሎ ነበር
” አሁን ባለው ሁኔታ ኢትዮጵያን መምራት አንድ ሚሊዮን ጉንዳን ተሸክሞ መሄድ ነው እንጂ ትርፍ አይደለም”
ጦርነቱ ጦፏል። ወገን መለየት ይኖርበታል። ወይ ከሚገድሉን በግልጽ መደመር (ከህውሀትና ነፍሰ ገዳይ ጸረ ኢትዮጵያ ነፍሳቶች) ወይም ከመንግስት ጋር ቆሞ ዶር አቢይን ለወረረው የጉንዳን ሠራዊት መላ መፈለግ።  ግልጽና ግልጽ ነው።
ይህን አባባል ለምን መጠቀም ፈለገ ዶር አቢይ  ብዬ አሰብኩና  በገሀድ ፊታችን ፈጦ ያለውን ሀቅ እንድጎበኘው ሆነ። ኢትዮጵያ እንኳን ነገሮች እንዲህ ተዘበራርቆ ቀርቶ በንጉሱ ጊዜም አገሪቱን ለማስተዳደር ከባድ ብልሀትና ጥንቃቄን የምትፈልግ ሀገር ናት። አንድ ሚሊዮን ሳይሆን አንድ ቢሊዮን በሰራ አከላት ጠቅጥቆ እንደመሄድ አስቸጋሪና ውስብስብ ሀገር ነው ያለን። እስቲ የአቢይን የገደምዳሜ ጉንዳን እንደ አንድዜጋ በዶር አቢይ ጫማ ገብተን እንቃኘው።
ቅድመ ብልጽግና ኢሀዴግ
የዛሬ ሁለት/ሶስት አመት የኢትዮጵያ ጓዳ ምናልባት ከማማሰያ በቀር ከጭልፋ አቅም እንኳ ሳያስተርፉልን ብዙም ሳይቆዩ ወደመቀሌያቸው ሲፈረጥጡ ለ አንድ አመት ያህል ዶር አቢይ ከየሀገራቱ እየቀፈለ ከውጭ ምንም ቅሪት ሳይዙ የተመለሱትን ምድረ ነጻአውጪና ፖለቲከኛ ተብዬዎች  ጨምሮ አስቤዛና የአልጋ እየከፈለ አስተናግዷል። ህዝባችንንም ታግዷል። እንግዲህ በብዙ ምርቶች እጥረት የሚሰቃየውን ደሀውን ወገናችንን ከጀርባው አዝሎ ማለት ነው። የትምህርት ፍኖተ ካርታ ጥናት ላይ እያለ፣ ሁሉ በፍቅርና ተስፋ እንደተሳከረ ብዙም ሳይቆይ ውስጡን ጉንዳኖቹ ቢዚ ሆነው ነበር። መፈናቀሉና መግደሉ ተጀመረ። ከዚያም ለጠቀ። ጁዋርና ቡችሎቹ ባስነሱት አቧራ ከ 80 በላይ ንጹሀን ጭዳ ሆኑ። በወቅቱ ከጥቂት የታዬ ደንደአ አይነት በቀር ህሊና ቢስ ሁሉ ዝም አሉ። ነገሮችን ከመሰረቱ እንየው ብዬ እንጂ አንባብያን ይህን ሳታውቁት ቀርታችሁ አይደለም። አንድ የሚገርመኝ ነገር አለ። የዖሮምያ ሆነ የፌዴራል መከላከያው እያለ እንደምን አቢይ አላስጣላቸውም አይደል ወቀሳው? ታስታውሳላችሁ የ ኦቦ ዳውድን በቪኦኤ ፉከራ? ለምን ይሆን ብሎ የጠየቀ አለ? ወገን የሚያየው በአካል መከላከያና ፖሊስ መኖሩን እንጅ ምንኛ በዘር ልክፍት የታጀለ፣ በጥቂት የህውሀትና አክራሪ ሲምፐታይዘርስ ስምሪት ስር ለመሆኑ እያደር ነበር የተገለጸው። በዛን ጊዜ ጁዋር ላይ እርምጃ ቢወሰድበት ኖሮ የሰሞኑን እልቂት child play ነበር የሚያደርገው። አንድ የብእር ወዳጄ የሙስጠፌው ሶማሌ እንደምን የተሳካለትን አቢይ ጉልበቴን አለ ለማለትም ደፍሯል። ሲጀመር የሱማሌን አረም ሱባኤ ገብቶበት ነቃቅሎና መሬቱን አለስልሶ ለሙስጠፌ ያስረከበው አቢይ ነበር። ፈጣሪንም እያሰብን እንጅ ። ለ 27 አመታት የአንድ ሰንበቴ ልጆች አገሪቱን በሁሉም መስክ ቀፍድደው ይዘው ፣ የኢትዮጵያዊነት ጠረን በተለይም ከዖሮሞ ልጆቻችን ርቆና ባእድ ሆኖ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በስም ብቻ እንደቀረች ነገር ደብዛዋ ጠፍቶብን ይህ ሰውዬ በጀርባው ይህን ሁላ ዳውላ ጉንዳን ተሸክሞ በፈገግታ ደፋ ቀና ሲል በምእራቡ አለም ያለነው በአብዛኛው ይህ ሰው መላ ይፈልግ ይሆን? እንደምን እንርዳው ? ምን አይነት መፍትሄ ብናፈልቅ ይቺን መከረኛ አገር ይታደጋታል ከማለት አቢይ እንዲህ አልሆነም፣ እንድያ አላደረገም ስድብና ዛቻ አገር ይገነባ ይመስል ቁምስቅሉን ማሳየቱን ተያያዘው። እስቲ አብዛኛው ወገን እኔኑ ጨምሮ ምን የረዳነው ነገር አለ ህዝባችንን? ያቺ የቡና መግዣዋን እንኳ በቁጥር የኛን ሲሶ የማይሞሉት ኤርትራውያን በሁለት ሳምንታት ብቻ ተወጠውቷል። ሳጠቃልለው በቅድመ ብልጽግና ኢትዮጵያ የጀመረ መከራ እስከዛሬም ቀጥሎ ሞላና ተደፋ። እኔ የዚህ ሰውዬ ሸክም እጅግ ስለከበደኝ ለመፍረድ እቸገራለሁ። ከድህረ ኢሀዴግም በሁዋላም ያለው የከፋ ነው።
ዘመነ ብልጽግናና ጉንዳኖቹ!
ኢሀዴግ ማለትም በጎሳ የተዋቀረ ስብስብ ብልጽግናን ተላብሶ፣ መደመርን አንግቦ ባለው አቅም አገሪቱን ለማሻገር ቃልኪዳን ሲገባ ቀንደኛውን አውሬ አስከፍቶ ኖሮ ጫናው እንደተፈጠረ አየለበት። ይህ አውሬ ሲፈልገው ለማዳ የቤት እንሰሳ ይሆንና አብረን እንበልጽግ ይላል ፣ አላማው ለአገር ብልጽግና ሳይሆን ለራሱ ገናናነትና ስልጣን በመሆኑ ብዙም ሳይቆይ ለይቶለት ወደሚመቸው ጎሬ ገባ። ከጎሬው ነገር መጎልጎልና የተቀሩትን አቅጣጫ ማሳት ስለነበረ አላማው በተንኮልና ሴራ አገራችንን ያምስ ገባ። ጥንት ልባቸውን የማረካቸው በራሳቸው እግር መቆም የማይችሉትን ነውጠኞች እያማለለ በስመ ፌዴራሌ ሸንጎ እየጠራ፣ በዘረፈን ገንዘብ ፍቅር እየገዛ፣ ከውስጥም ከውጭም የአቢይን አስተዳደር መገዝገዝ ጀመረ። የምታውቁትን ግን የዛሬው መሪር እልቂት ስሜታዊ አርጓችሁ የረሳችሁትን ደባ ነው እየነገርኳችሁ ያለሁት። አቢይ ላይ የሰፈሩት ጉንዳኖች እያደር እየበዙበት፣ ክፉኛ እየቆጠቆጡትም ዝንፍ ሳይል ትግሉን ተያያዘው። በግልጽ እንነጋገርው እስቲ ። አንድን የአገር አላማ ወይም መርሀግብር ለመተግበር በአላማም፣ በትልምም አብረው የሚቆሙ የመልካም ምግባር አርበኞች ያስፈልጋሉ። እኔ ከርቀት እታዘብ የነበረው ከአቢይና ጥቂት ሰዎች በቀር አብዛኛው አጀንዳው የተሰወረ ይመስለኛል። በየእለታዊ ስብሰባው አብረው ይመክሩና በነጋታው አብዛኛው አፈንግጦ ባይሆን እንደ ሰውዬው አጀማመር ብዙ ታሪክ በሰራ ነበር። ለዚህ ትልቁ ምሳሌ ኦቦ ለማን መጥቀስ ይቻላል። በቅድመ ብልጽግና ያላደረገውን ከመሸ በሁዋላ አልተደመርኩምን ከመንትያ ያህል ወንድምህ ስትሰማ ያውም በአደባባይ የጉንዳኑን ጭነት ያከብደው ይመስለኛል። ብዙ ዝብዝብ ሳልገባ ምን ይሻለናል ለሚለው ዛሬን ላይ ቆሜ ፣ በዚህ ውድመትና እልቂት ማግስት ለአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እንዲህ ልበል:።
1)  ወደድነው ተከፋንበት እስከማውቀው  ያለን አንድ መንግስት ነው። ይህ መንግስት የሁላችንን እርዳታ ይፈልጋል ። ያለፈውን የመንግስት ሀጢያት ብንዘረዝረው ከ ሶስት አመት ወዲህ ያለቁትን ወገኖች አይተካልንም።
2) መንግስት ሳምንት በማይሞላ ጊዜ እየቀፈደደ ነው። በየቀኑም አፕዴት እያረገን ነው።
3) በብልጽግና ውስጥ ተንሰራፍተው መሰሪ ደባ የሚፈጽሙትን ለማጋለጥም ይሁን ለመመከት መንግስት ብቻውን ሸክሙን አይችለውም – እንተባበረው።
4) የኢትዮጵያ ጠላት ዛሬም ትላንትም ቲፒሌፍና አክራሪ ሀይላት ናቸው ( ቄሮ የሚለውን የወል ስም በፈጣሪ አትጠቀሙ)። ያ ከንቱ ጁዋር እራሳቸውን የማያውቁ፣ ማደርያ ቄያቸውን የማይለዩ የፌስ ቡክ ህጻናትን ሰብስቦ ከመልካሙ እውነተኛው የቄሮ ስም አሳክሮ ለግል አጀንዳው መጠቀምያ በማድረጉ የሱኑ ማስተጋባት እሱኑ መሆን ነው። የዶር አቢይንም ጭነት ካበዛው አንዱ ይህው ነው። ለምት የማይመች ስም። ጁዋርም ይቺን አውቆ የተከፋው ወገን ወደተባበሩት መንግስታት አቤቱታ ድረስ እንዲኬድበት ሆን ተብሎ የቀመረው ደባ ነው። መቼስ አንድ  ቀን እውነቱ ይወጣል።
5) ወገኖቻችን በግፍ ታርደዋል። አማራ ይሁን ጉራጌ ሁሉም ወገናችን ነው። ያለቁት ደግሞ በተለይ በዖሮሞ ወገኖቻችን ሲሆን ከአብራኩ የወጣነውን ማህበረሰብ የማይወክሉም በመሆናቸው እንደ ሀጫሉ ሞት ሁላችንም ደጋግመን ሞተናል። አንገታችንንም ደፍተናል። ሁሉም አንገቱን ይደፋል ብዬ አስባለሁ።  እንደ ኢትዮጵያዊነቴም ድርብ ውርደትና ኪሳራ ነው። መስሏቸው እንጅ ገዳዮችም በቁም ሞተዋል። አገራችን በእድሜዬ እንዲህ አይነት አሰቃቂ ነገር ባለማየቴም እንደ አገር ሞተናል ብዬም አስባለሁ። ታድያ የሰሞኑን ሀዘን ሳንወጣ ጣት እርስ በራስ የተረፍነው መቀሳሰሩም የሞት ሞት ነው። ምን ሊፈይድ ነው ከወራት በፊት መንግስት በመዘናጋቱ ሀጢያቱን የምናበዛው? ነፍስ ሊመልስ ወይስ ንብረት? እያስተዋልን እላለሁ።
6) እያንዳንዱ ዜጋ አንዱ ለሌላው ዘብ ይቁም። በየሰፈሩ እየተደራጅ ከፖሊስ ትብብሩን ያሳልጥ። ከሰሞኑ መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ ማበረታታት። በጎደለው እየሞላን በህብረት መጓዝ። ነጻና አገራዊ ራእይ ባላቸው ሚዲያ ይሁን በአካል እየሄዱ መንግስትን መደገፍ። አቶ ተመስገን ጨርሰውታል። ሸረሪቱ ገና አልተያዘችም፣ አደኑ ግን በኦፊሴል ተጀምሯል።
ማጠቃለያ!
ጦርነቱ ጦፏል። ወገን መለየት ይኖርበታል። ወይ ከሚገድሉን በግልጽ መደመር (ከህውሀትና ነፍሰ ገዳይ ጸረ ኢትዮጵያ ነፍሳቶች) ወይም ከመንግስት ጋር ቆሞ ህዝባችንና አገራችንን መታደግ። ከመንግስት ጋር ከሆንክ/ሽ የተቻለህን እርዳ/ጅ።  ሰዋች እውነት አገራችሁን የምትወዱ ከሆነ ዛሬን ላይ ቆሞ መንግስትን የሚያብጠለጥል ከጸረ ኢትዮጵያ ሀይላት ጋር የቆመና ህውሀት ተመልሶ እንዲመጣለት የሚፈልግ ብቻ ነው። ከዚህ  በቀር ምን ማለት ይቻላል?? ካለ ደግሞ የሆነ ተስፋ ስጡን እንጅ ወገን እንዲህ እየተበለተ ዛሬም እንደ ትላንቱ ያውም በፌስቡክና ነጻ የውጭ ሚዲያ ቁጭ ተብሎ አቃቂርና ለምን አቢይ ይህን፣ ያን አላደረገም ማለት ወገንን አይታደግም።  እያለቁ ወገኖቻችን እኛ እዚህ በቃላት እንሰነጣጠቃለን? ምን ሊፈይድ ነው? ወይም አንደኛውን ሰዎቹ ይመለሱና ይግዙ በሉንና አርፈን እንቀመጥ። እየጠየኩ ያለሁት አገርና ወገን የሚገዳችሁን እንጅ ጨርሷቸው የሚሉትን አይደለም። ቅን ወገን ከሆናችሁ ግን ሚሊዮን ጊዜ እራሳችሁን ጠይቁና ፍረዱ። የናንተ ውጭ ሆኖ አቢይን ስለ ባለፈው  መውገር ደሀውን ይታደጋል ወይስ ገደል ይከታል? አንዳንዶች “የአቢይን ስህተት አትንገር ነው ወይ?”_ከሆነ አዎ፣መንገሩ ነው ወይስ መደገፉ ነው ዛሬ ጉልበት ሆኖት ፣ ደጀን ሆኖት ህዝባችንን የሚታደግልን?  እጅግ የሚደንቀኝ ይህን አስቸጋሪ ህዝብ ለመምራት የሚመኘውን ተስፈኛ ፖለቲከኛ ነው። አበቃሁ። ፈጣሪ ምህረቱን ያምጣልን። እንዲህም ባላ መንገድ ላይ ኢትዮጵያ ተቀምጣ አንብቤም፣ ሰምቼም ባላውቅ ከዚህ ሁሉ መከራ በአሸናፊነት እንደምትወጣ ግን  ይታየኛል።
በመጨረሻም  ለአቢይ መንግስት ብርታትን፣ በማያውቀው ለሚሞተው ደሀው ህዝባችን ጽናትንና የፈጣሪን እርዳታ እጠይቃለሁ። ህዝባችን እንዲህ በግልጽ ከውጭ ሳይቀር አሰቃቂ  የሞት ፍርድ ተበይኖበት የአቢይን ቅድመ ሰሞነኛ ሀጢያት መዘርዘር እነዚኑ የኢትዮጵያ ጠላቶች መርዳት ይሆን እንደሆን እንጅ ቅንጣት የሚያስገኝልን ትርፍ አይኖርም። አመሰግናለሁ።
ተጨማሪ ያንብቡ:  ለኢህአዴግ ግዜ ምኑ ነው? - ከተማ ዋቅጅራ

6 Comments

 1. ሀገራችንን ለማፈራረስ እየተዶለተ እና በተጨባጭ ሙከራ እየተደረገ ባለበት በኣሁኑጊዜ ሀገርን የመከላከል ሃላፊነት ለመንግስት ብቻ መስጠት ተገቢ ኣይደለም።
  ስለሆነም ሰፊ ኣገር ኣድን / National Salvation Front /ን ህበረት ፈጥሮ ባንድ እጁ የውስጥ ቅጥረኞችን ምህረት የለሽ ቅጣት እየሰጠ የውጭ ሃይልን በህብረት ተደራጅቶ ሀገራችንን መመከት የግድ ይላል።
  ህብረ ብሄር ድርጅቶች እና የኢትዮጵያን እንደ ሀገር እንድትቀጥል የምትፈልጉ ሃይላት ሁሉ ለፖለቲካ ትርፍ ሲባል በጥቃቅን ጉዳይ መተቻቸቱን ኣቁሞ ለመንግስት ተጨባጭ ድጋፍ ለመስጠት መቀሳቀስ ይኖርባችሁዋል።
  የሀገር ካሃዲዎች፣ ባንዳዎች፣ የጥንብ ፓለቲካ ኣራምጆችን ከነሰኮፋቸው ነቅሎ መጣያው ጊዜ ኣሁን ነው ።
  በሳል ፖለቲከኞች ዶ/ር ብርሃኑ፣ ዶ/ር ኣረጋዊ፣ /ር በየነ፣ ኦባንግ ሜቶ፣ ዶ/ር ሙሳ፣ ኣብረሃ ደስታ፣ ኣንዱኣለም …etc ሌሎችም ምሁራን ከዳር ወደ መሃል ገብታችሁ ህዝብ ኣስተምሩ ፣ ኣስተባብሩ፣ ኣደራጁ ከመንግስት ጋር ጊዜያም ቢሆን ህብረት ፈጥራች ሁ ሃገራችንን ኣድኑ።
  መጀመሪያ ሀገራችንን ጠብቁ፣ ሌላው ሁለተኛ ደረጃ የሚቀመጥ ነው ።
  መጀመሪያ መሶቡን ጠብቁ ፣ ውስጡ ያለውን ከመቀራመት በፊት።
  ከኣደራ ጋር !
  God bless Ethiopia !

 2. ወንድሜ አዊርቱ የሀገሪቱን ችግር ለመፍታት አሁን በደምሳሳው ዶር አብይ በሚከተለው መንገድ መደገፍ ዘላቂ መፍትሄ ለዛች ሀገር አያመጣም::አባቶች አለባብስው ቢያርሱ በአርም ይመለሱ ይላል የሀገሬ ገበሬ::ለዚህ ትልቁ ዋናው የበሽታው መንስኤ በህውሀትና በኦነግ የተቀረፀው ብሄርን ማዕከል ያደረገ ህገመንግስት አማራን ጨቆኝ ነፍጠኛ አድርጎ በመሳል በማግለል ነበር::ይህ ወያኔ የፈጠረው ዘረኛ ክልላዊ በጥላቻ ላይ የተመስረተ መንግስት እነ አብይን ወልዶ ለዚህ አብቅቶል::በህውሀትና በእነ አብይ መሀከል ልዩነቱ የአላማ ሳይሆን የእስትራተጅ እንደሆነ አብይ ወደስልጣን ሲመጣ ህውህት ይዞብን የመጣውን የዘር ፓለቲካና ሁብት ይግልፅ የአደባባይ ዘረፋ ቆሞ ስው የተፈጥሮ ስብአዊ መብቱ ተከብሮ በፈለገበት የሀግሪቱ ክልል የመኖር መብትና ዋስትና ያገኛል በሚል ህሳቤ አብይ በመልካም ምላሱ ሙሴን አድርገን ስለን ገንዘባችንን እውቀታችንን ልምዳችንን በማካፈል በትእግስት እምነታችንን ጥለን ከዛሬ ነገ መልካም ነገር ይመጣል ብለን ጠብቀን ነበር::ብዙ ቃል እንደገባ አንተም ታውቃለህ የባስ እንጅ የተሻለ ነገር አልመጣ አለ;;:
  ብዙ ደካማና ስህተቶች አንዳንዴም ፍፁም ትስፋ አስቆራጭ ክስትቶች የወይኔ ግልባጭ ሁሉም ትላልቅ ሹመቶች እውቀትን ሳያገናዝብ የሚስጣቸው ሹሙቶች እርስዎም ይሞክሩት ይዘረፉት አይነት ሲትይ በአስችኮይ ይትረም ዘንድ ገንቢ አስቱይይት ሲስጥ በአፍራሽነት እንጅ የሚቀብል ሳይሆን በእልህ የነታከለ ኡማ የጠይባ ሀስን የእነ ብርህኑ ጁላ ሹሙት ሌሎችም ሁሉንም ስልጣን እንደ ወያኔ በስግብግብነት ቃሉን አጥፎ ሜስይዝና እስተያየቶችን በፀሉምትኝነት ስሜት አሁን እየተባባስ እንዲመጣ እድርጎታል:: እንጅ እንድ ወያኔ ብቻ ብሎ መፈረጅ የአሁንን ችግር ከመደረትና ድሪቶ ከመፍጠር ይዘለለ ዘላቂ መፍትሄ አያመጣም:;
  በማስር መፍትሄ ማምጣት አይቻልም::አብይ አሁንም ዝም በጥላቻ ዝም ብሎ በደፈናው በሃስት እንደ አይሁድ ክህናት ክርስቶስን በሃስት እንደሚከሱት ሁሉ እነ እስክንድርን እነ ኢንጀነር ይልቃን ማስር ህዝብ ጆሮ ስጥቶ የሜያደምጣቸውን ከነጁህር ጋርቀላቅሎ ሲያስር ቀደም ሲል አብይ በእስክንድር ላያ ያለውን ጥላቻ ብቻ ሳይሆን የአዲስ እበባ ህዝብ በራሱ በሚመርጠው ስው መተዳደርን መቃወም ህዝብን በወያኔአዊ ፍልስፍና ሁሉንም በኦሮሙማ በህዝብ ላይ አብይ የፈለገው ስልጣን እየጫነ መግዛት እብደት አስመሳይ አባዜ ነው:: በአዲስ አበባ አሁን የታስሩት ራሳቸው ከጥቃት ለመልከል የሞከሩትን እንጅ አጥቂዎችን አይደለም::
  አባዊርቱ ! ሁለት አመቱን ክህዋት ነፃ አድርገው ሙሉ በሙሉ ኦሮምያን እየመሩ ያሉት ኦሮሞዎች ብቻ ናቸው:;: ይህም ብቻ መላው ሀግሪርቱ የምትመራው አሁን በኦሮሞዎች ነው የሀገሪቱ እጣ ፋንታ በጃቸው ገብቶል;;ቢያንስ በእጃችው የገባውን ኦሮምያን ከአመፅ ነፃ በማድረግ በክልሉ የሚኖረውን ህዝብ ስለም መጠበቅና ማልማት ቅድምያ ስራቸው ነው;በነገራችን ላይ የሱማሌው ክልል አቶ ሙስጠፊ በእራሳቸው ያመጡት እንጅ አብይ እንዳልስራላቸው በአለማወቅ በድፍረት ስለተናገርከው ይቅርታ ጠይቅ;(አብይ የራሱ የሚመራውን የኦሮሞ ብልፅግና መምራት ያልቻለ ሱማሌ እንዳልተሽገረ እሙን ነው
  እናም በዚህ ሁለት አመት የህብረተስቡን በተለይም የወጣቱን በማንቃት በማደራጀት አእምሮውን በማፅዳት እንዳስራ ይልቁንም እንደሚፈልገው አብይ እራሱ አንዳንዴ እነክርስትያንን እነ እስክድርን በንቀትና ሲወርፍ ይስተዋላል:: እነጅዋር ብዙዎች ምድያ እየጮሁ ጁሀርን እዚህ ደረጃ ያደረስው አብይ ነው:;: ወሮ አዳነች አቤቤ የጉምሩክ ሃላፊ በነበርችበት ወቅት ለOMN ሬድዬ ጣብያ 30 ሚልየን የህዝብ ገንዘብ ስትስጥ አብይ አዙዋት ነበር::
  አሁንም አብይን እንርዳው ስንል ከአነድሪቶው እየጣፍን ከሆነ ነግ ተመልስን እናለቅሳሉን ::በፍፁም ዋስትና የለንም;መሆን የአለብት አብይ ይከተል የነበረውን አሁንም ስህተት የሚስራውን አቁሞ ወደ ቀደሞው ህዝባዊ ኢትዮጽያዊነት አመልካከቱ ማስመስሉን ቶቶ የእነእስክንድርን ጥያቄ በእርጋታ ቁጭ ብሎ ወደህዝቡ ወርዶ እነርሱን ፈትቶ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉትን ሁሉ ወያኔንም ጨምሮ ከህዝብ ጋር መወያየት እንጅ አሁን በያዙት መንገድ ጦርነትን እየናፈቁ መሆን የለበትም;;ኮነሬር መንግስቱ ህዝብና አማካሪያቸውን ባለመስማት ሀገሪቱን ጥልው ሊጠፉ ትርፍ የሌለው ጦርነት ዳርገውን የህውሀት መጫወቻ እንድንሆን አድርገውናል ስንት አኩሪና መተኪያ የሌልቸውን እየተሳለቁ በመግደል;;ዶር አብይ ይህን ማስተዋል በልህ ጦርነት የሚሞተው የራስችን ዜጋ በራሳችን ሀብት ነው የምናተትፈው ድህነትና ህብታምአገሮችን መሳርያበብድርበመግዛት ውድቀት ነው:::ስከን ብሎ ሁሉንም ወያኔ ላይ ከመቀስረ ኦሮምያ ሹማምንቶች ህውሃት ዘረኝነትና ጥላቻ በህሊናቸው ረመጥ ሆኖ እየቆስቆሱ ራሳቸው ይመጡት ያባባሱት ነው::ይህን ቁጭ ብለው መጀመርያ ራሳቸውን ማፅዳት:የራሳቸው ልጆች ከትምህርት ቤት ጀምሮ ነፍጠኛ አማራ ቴሌሽዥኑ ሚድያው የራሳቸውን መፈተሽ አለባቸው;(በክልላቸው የሚኖረው ውክልና ማግኘት በመስተዳድሩ ውስጥ ከቀበሌ አመራር ጀምሮ እንዲገባ መፍቀድ አለባቸው::በፍርድ ቤት በቀበሌ በቆንቆው መዳኘት መፍቀድ አለባቸው በፍፁም መገለል የለባቸው;;ወጣቱ የሌላ ብሄር በክልሉ ሙገለሉን እያስተዋለ አያስተማርነውም ነው ባእድ ተደርጎ!የተከበሩ ርአቶ ሙስጠፌ ያደረጉት ትልቅ ነገር በህዝቡ መሀከል እኩልነትን ማምጣታቸው ነው;(
  ብዙ አወራሁ መስለኝ

  ወንድም አለም ለሁላችንም ምህረቱ ወስን የሎለው እግዚኡብሔር ቅን ልቦና ስጥቶ በቃችሁ ብሎ ምህረቱን ያውርድልን!አሜን

  • ብዙ ነጥቦችህ እውነትነት አለው፡፡ ለንገሩ እኔ መቺም ተውጦልኝ አያውቅም የዶ/ርነቱም የጠ/ሚኒስትርነቱም ነገር፡፡ በአገራችን ላይ ህግ መንግሥት መኖሩን እስኪያስጠረጥር ድረስ የሚሰራው ሥራ ጠ/ሚ ተብዬው አረንጓዴ ምልክት እየሰጠ ነው እዚህ ያደረሰን የሚመስለው፡፡ ከዳር እስከዳር የሰራ መስኩ ሙያና እውቀት በሌላቸው በኦሮሞ ሲጥለቀልቅ ጠ/ሚሩ የዘር ፖለቲካ እየመራ መሆኑ ክርክር ውስጥ አያስገባንም፡፡ የመኪና አደጋውን ስትትስቲክ አይቶ ማን መኪና ያለ ህጋዊ መንጃ ፍቃድ እንደሚነዳ እና እያደረሱ ያለውን እልቂት በጥቁቱ ማየት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ቲይትር ነው የሚታየው፡፡ ይሄ ሁሉ የአስተዳደሩ ጀዋር እና ብጤዎቹን ላለማስቀየም የሚያደርገው የጥፋት ውጤት ነው፡፡
   ኧረ! አረቦቹ የእስልምናን ተጸእኖ የእንዲያደርጉ በሩን እየጠረገ ቀይ ምንጣፍ የሚዘረግላቸውን ጥፋት እያስተዋል ነው፡፡ አማርኛና እና አማራን መስማትም ማየትም የማይፈልጉት የኦርሞ አክራሪዎች አበአጣና እና በገጀራ አማራን ሲያቃጥሉና ሲገሉ መንግሥታዊ ተግባራቸውን እንኳን አላሳዩንም፡ የጥበቃ ሃይል ተብየው የህዝብ ደሞዝ እየበሉ ምንም አይነት እርዳታ ሳያደርጉ ይሄው 3 ዓመት አለፈን!!
   ሆኖም ይሄ ሁሉ ሆኖ ለሥራው ብቃት የሌለውን ጠ/ሚኒስትራችንን ወደንንም ጠላንም በትእግስት ማየት ነው፡፡ ይሄው 3 ዓመት ሙሉ ኦሮሞ ያልሆነውን በገጀራ እያሳረደ ነው በእሳት እያጋየ ነው፡፡ አሁን ምን አልባት የሰላም ሽልማቱ በዓለም ፊት እያሳፈረው የአራት ኪሎ ወንበሩን ብቻ መጠበቁን ትቶ አገር ማስተዳደር ይጀምር ይሆናል፡ ለማንኛውም እስቲ አሁን ሆዳችንን በወሬ መንፋቱን ትቶ እግዚአብሔር አገሩን ለማረጋጋትና ለፍትህ መሪነት ጥበቡን እንዲያስመለክተው መጸለይም መርዳት ከቻልም መርዳት ነው፡፡

 3. “የሚሊዮን ጉንዳን ሸክም” ያለው ጭንቅላቱ ውስጥ ነው! ዕብደት ሲመጣ፣ የጭንቅላት ነርቮች ውጥንቅጥ ስለሚያጋጥማቸው፣ ሚሊዮን ጉንዳኖች ጭንቅላትን እንደሚነክሱ ሆኖ ይሰማል። ስለሆነም፣ ሰውዬው አብጃለሁና ድረሱልኝ እያለ ነው፣ እርዱት!!

 4. ጸሐፍው ሰው ባቀረበው አስተያዬትም ሆነ ራሱ በሚጽፈው ዶክተር አብይን አትንኩት ባይ መሆኑን ተገንዝቤአለሁ ። እንዲህ አይነቱ ምክንያት አልቦ ጭፍን ድጋፍ ለጠቅላይ ምንስቴራችን ለራሳቸው ጠቃሚ አይደለም ። መልካም ሲያደርጉ መደገፍ ሲሳሳቱ በምክንያት መተቸት ይጠቅማቸዋል እንጂ አይጎዳቸውም ። የዶክተር አብይ መንግሥት ህግና ስርአትን አያስከብርም ብሎ መተቸት ነውሩ ምን ላይ ነው ? ውሸት ነው እንዳትል ሌላውን ትተን በኦሮሚያ ብቻ ለናሙና ከ23 በላይ ባንኮች ተዘርፈው ማን ለፍርድ ቀረበ ? የኦሮሚያ ባለስልጣናት ተረሽነው ማን ተይዞ ለፍርድ ቀረበ ? ተማሪዎች ታፍነው ይሙቱ ይኑሩ የሚያውቅ የለም ። የሀገር መከላከያን የሚያክል ሰው ተገድሎ ጉዳዩ እየተድበሰበሰ ነው ፣ በራሳቸው ላይ ተሞከረ የተባለው ግዲያ ከምን ደረሰ ? የኢንጂነር ስመኘሁ ግዲያ ጉዳይ ምን ደረሰና ወዘተ ጉዳዮችን የሚከታትል ምክንያታዊ ትችት ቢያቀርብ እንደነውር የታየው ለምንድን ነው ? በእነ እምነት ስንደግፍም ሆነ ስንተች ምክንያታዊ ብንሆን መልካም ነው ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.