የኦሮሞ እስላማዊ ቡድንና ሌሎች ጉዳዮች – ሰርፀ ደስታ

ሰሞኑን እየሆነ ያለውን ነገር ስላላስተዋልንው እንጂ ብዙ ሲሰራበት የኖረና ታቅዶ የተሰራ ነው፡፡ ዛሬ ሁሉም በደንብ እንዲያስተውል የምፈልጋቸው ነጥቦች አሉ፡፡

4544

የኦሮሞ እስላማዊ የሽበር ቡድን፡- ኢትዮጵያ ከጅምሩ ሦስት የአብርሀማዊ እምነት የሚባሉት የጂው፣ የክርስትናና የእስልምና አገር ስትሆን ከሌሎች አገራት በተለየ የእነዚህ እምነቶች ወደ አገራችን የመጡበት ሂደት በጦርነት ሳይሆን ፈጹም ሠላማዊ በሆነ ይልቁንም ሌላ ቦታ ሲደርስባቸው የነበረውን ግፍ ሸሽተው ለመጠለል ነው፡፡ ለዚህ አይነተኛ ምሳሌ የእስልምና እምነት ቢሆንም በክርስትናውም ብዙዎች ከሌሎች አገራት ኢትዮጵያን መርጠው መጥተውባታል፡፡ የዘጠኙ ቅዱሳንን አመጣጥ ያስተውሉ፡፡ የአይሁድ እምነት ቀደም ብሎም የነበረ ስለነበር መቼ እንደመጣ አላውቅም፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንረዳው ግን ምን አልባትም ይህ እምነት ከእስራኤሎችም በፊት እንደነበር እናስባለን፡፡ የሙሴ አማት የሆነው ዮቶር ራሱ ካህን እንደነበር፡፡ እንዲሁመ ገና እስራኤል ወደግብጽ ከመምጣቱ በፊት በግብጽ የነበረው የዩሴፍ አማችም ካህን እንደነበር እናነባለን፡፡ የእስራኤላውያን ክህነት ከአሮን እንደሚጀምር ከፍ ካለውም በዘሩ ምክነያት ከሌዊ እንደሚጀምር እናነባለን፡፡ እንግዲህ ኢትዮጵያ የእነዚህ እምነቶች ከጅምሩ ጀምሮ ቤት ሆና ኖራለች፡፡  ሆኖም ሁሉም እምነቶች ሲጀምሩ በሰላም የመጡ ቢሆንም አልፎ አልፎ ሐይማኖታዊ ጦርነቶች ነበሩ፡፡

ከብዙ ዘመን ጀምሮ በኢትዮጵያ ብዙዎች የማይረዱት  የኦሮሞ እስላማዊ አክራሪ ቡድን አለ፡፡ ይሄ ቡድን በተለያየ ጊዜ ብዙ ሙከራ አድርጓል፡፡ በአገኘው አጋጣሚ ሁሉ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚሰራ ነው፡፡ ዛሬ የምታዩት በአርሲ፣ ሐረርና ባሌ የተከሰተው አረመኔያዊ ድርጊት የዘመናት ጥረት አንድ ምዕራፍ ነው፡፡ ባለፈው ጥቅምት ላይ በተመሳሳይ እንደነበር አስታውሱ፡፡ ይሄ ቡድን እነ አልቃኢዳ ከመፈጣራቸው ብዙ ዘመን ይቀድማል፡፡ ዛሬ የህ ቡድን በኦሮሞ የዘረኝነትና ጥላቻ ፖለቲካ ታጅቦ ጥሩ አጋጣሚ ሆኖለታል፡፡ በኢትዮጵያ የመንግስት መዋቅርም ሰርጎ ለመግባት ችሏል፡፡ የሱልልታና ለገጣፎ ከንቲባ ከአርሲ ሲመደበት የዳንኤል ክብረት የሆነ ቦታ መመደብ የለበትም ብሎ አብድ ሲሆን ያያችሁት የዚህ ቡድን አካል እንደሆነ አስተውሉ፡፡  በዚህ እጅግ አደገኛ በሆነ ወቅት በኢትዮጵያ የዲፕሎማቲክ ቦታ ተቀምጦ የኢሚሬት አምበሳደሩ በቅረቡ በፊስቡኩ የለቀቀውን አስተውሉ፡፡ መለስ ከሞተ በኋላ የኦሮሚያ ፕሬዘዳንት በነበረው ሙክታር በሚባለው ሰው የቆመውን የጥላቻ ሐውልት አስተውሉ፡፡ በጁኔዲን ሳዶ በሚባለው ሰው ሲደረግ የነበረውን አስተውሉ፡፡ በመጨረሻም ከሱማሌ ክልል ድንበር በጦርነት መፈናቀል ሳቢያ በአዲስ አበባና በናዝሬት/አዳማ እንዲሰፍር የተደረገውን ሰፋሪ አስተውሉ፡፡ ጀዋር መሐመድ የዚህ ቡድን የሽበር ጥቃት አዋጅ የሚሰጥ እንደሆነ አስተውሉ፡፡  ሰሞኑን ሐጫሉን በጠላትነት ገድሎ እንደገና ለዓቀደው ዓላማ እንዴት እንደተጠቀመበት በደንብ አስተውሉ፡፡ ሐጫሉ እንደሚሞት ቀድሞ የተነገረውና የሽብር ኃይሉን እንዲያዘጋጅ የተደረገ ቡድን እንዳነበር ሁሉ እናስባለን፡፡ የምናየው ሁሉ በሐጫሉ ሞት በመቆጨት ለማሰመሰል ብዙ ተሞክሯል፡፡ አብዛኛው ሌላው ኦሮሞ ግን አልገባውም፡፡ አሁንም አልገባውም

ከዚህ ጋር በተያያዘ በአርሲ ባሌና ሐረር ቤተሰቦቻቸው የሚኖሩ ኦሮሞ ነን የሚሉ በኦሮሞ የጥላቻና ዘረኝነት ፖለቲካ (ተስፋዬ ገብረዓብ የፈጠራቸው) የተጠመቁ ምሁር ነን ብለው የሚያስቡ ብዙዎች ለዚሁ የሽብር ወንጀል ተባባሪ ሲሆኑ አይተናል፡፡ ከእነዚህ አንዱ ብርሀነመስቀል አበበ ሰኚ የተባለ ግለሰብ ነው፡፡ ይህ ግለሰብ የመጀመሪያው የሽብር እለት ኦኤምኤን በተባለው የእስላማዊ ሽብር ቡድኑ (አውቃለሁ ጸረ-ኢትዮጵያ የሆኑ ሌሎች አብረውት አሉ) ሚዲያ ለረጅም ሰዓት በንጹሀን ላይ ፍጅት እንዲፈጸም በኦሮምኛ ሲቀሰቅስ ነበር፡፡ ይህ ግለሰብ የሕግ ሰው ነው ሲባል ይሰማል፡፡ ሆኖም አሜሪካ ውስጥ ተቀምጦ ነው ንጹሀን እንዲታረዱ ሲቀሰቅስ የነበረው፡፡ ይህ ግለሰብ ቤተሰቦቹ አርሲ አካባቢ እንደሚኖሩ ይነገራል፡፡ ምን አልባት ለአሁኑ ተባባሪያቸው ስለሆነ የእሱን ቤተሰብ አይነኩ ይሆናል፡፡ ሆኖም የቆየውንም ቢቆዩ አርሲ እስከኖሩ ድረስ ወደፊት በእስላማዊው አረመኔ ቡድነ መታረድ ይቀርላቸዋል ብሎ አስቦ ከሆነ አላውቅም፡፡ በተመሳሳይ ብዙዎች የእሱን አይነት ሆነው አግኝቻቸዋለሁ፡፡  እንግዲህ በምድረ አሜሪካ የምትኖሩ ይሄን ግለሰብ ብዙዎች ለታረዱበት የአረሜኔያዊ ድርጊት ቀስቃሸነቱ በሕግ ሊጠየቅ እንደሚገባው ቢሰራ እላለሁ፡፡ ሌሎች አሉ፡፡

እዚህ ጋር የእስላማዊ ቡድን የሚባለው ሁሉም አርሲ እስላም ነው የሚል ግምት እንዳይወሰድ እፈልጋለሁ፡፡ ንጹሐንን ከአረመኔዎች ለመታደገ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ አሉና፡፡ ከኢትዮጵያዊ እስላማዊነት ጋርም እንዳይገናኝ አፈልጋለሁ፡፡ ዛሬ ላይ ቀድመው አረብኛ በማወቃቸው ስለአገራቸው በዋናነት ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረጉ ያሉት እንደነ ኡስታዝ ጀማልና መሐመድ አል አሩሲ አሉና፡፡ እንደውም መሐመድ አል አልሩሲ የአርሲ ተዋላጅ መሆኑም መዘንጋት የለበትም እና፡፡ ሲጀምር ከግብጽ ይቅርና እስላም ሁሉ ከሚመካባት መካ ኢትዮጵያ የእስልምናም እምነት ባለውለታ እንደሆነች ሳይማር ያደገ የእምነቱ ተከታይ ያለ አይመስለኝም፡፡ ችግሩ በክፉ አስተሳሰብ ባርነት መውደቅ ላይ የሚያመጣብን በሽታ እንጂ፡፡

የኢሳት የአማራ ክልል የተደገሰለት ሽብር ሴራ ሰበር ዜና፡- ጥሩ ነው ግን ማን ነገረህ፡፡ ቀድሞ ያሶሩና ችግሩ ሲፈጠር አከሌ ፈጠረው ለማለት እንዳይሆን ሰው ያስተውል፡፡ እኔ በባለፈው በአማራ ክልል የሆነውን አሁን መንግስት ነኝ ከሚለው አካል ውጭ ሌላ አካል ካለም በተባባሪነት ሊሆን ይችላል ባይ ነኝ፡፡ ዛሬም የማናየውን አረመኔያዊ ድርጊት መንግስት ነኝ የሚለው አካል እኔ የለሁበትም በሚል አዳኝና ፈጥኖ ደራሽ ሆኖ እያወራልን ያለውንም ዝም ብሎ መጋት ትክክል አደለም፡፡ ለአጥፊዎች በኦሮሞነት እየተሰጠ ያለ እድል አለ፡፡ አሁንም ብዙ ሰው ግር ያለው ይመስላል፡፡ ምን እየተደገሰ እንድሆነ ማስተዋል አልቻለም፡፡ አብይ አህመድ በቴልቪዥን ወጥቶ ስለሚናገረው ነገር እያደነቀ የሚያወራው ብዙ ነው፡፡ እንዲህ በቀላሉ የምንዘወር እንደሆነ ስላወቁ ብዙ ጊዜ ሲሸውዱን ሁሌም እዛው ነን፡፡  የሰሩት ሰርቶ እንደገና አዛኝና ሞግዚት ሆኖ መቅረብ የተለመደ ጫወታ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ አብይ አህመድ የአገሪቱን ዋና ዋና የመንግሰት መዋቅሮች በኦሮሞ ማስያዙ ብቻም ሳይሆን በተለይ ደግሞ አማራ(ነፍጠኛ) በተለይ ኦርቶዶክስ እምነት ያለው ወደ ስልጣን እንዳይመጣ በጣም ተጠንቅቆ ነው የሚሰራው፡፡

ነፍጠኛ ፡ ዛሬ በኦሮሞ ነፍጠኛ እያለ የሚዛትበትና የጅምላ ግድያ እየታወጀበት ያለው በዋናነት አማራ፣ ከዛ ጉራጌ ፣ ኦርቶዶክስ እንደሆነ ላፍታም ቢሆን ሊዘነጋ አያስፈልግም፡፡ በአባይ ሚዲያ ስለ ነፍጣና ማንነት ትላንት በፈይሳ ሮቢና በአናንያ ሶሪ በተደረገ ንትርክ አናንያ ተደብቆበት ከነበረው የኢትዮጵያዊነት ካባ ዛሬ ጊዜው የእኔ ነው በሚል ይሁን ወይም ጊዜውን ተነጠኩ (ከወያኔ ጋር በነበረ ስውር ውል) ባላውቅም ራሱን አስነብቦናል፡፡ ለነገሩ ብዙም አልገረመኝም፡፡ እሱን እኔ አላውቀውምና፡፡ በደንብ አውቃቸዋለሁ ብዬ ያልኳቸው ለዘመናት እንዴት ሲያሴሩ እንደነበር በዚህ ሳምንት የብዙ የቅርብ የምላቸው ጓደኞቼን ማንነትም አይቻለሁና፡፡

የሆነ ሆኖ አናንያ ዛሬም ነፍጠኛ ነፍጥ የያዘ ነው ሲል ሊያጃጅለን ሞክሯል፡፡ ዛሬ በየአደባባዩና በይፋ ኦሮሞ ሁሉ እንደ ጠላት የሚጠቅሰው ነፍጠኛ በእርግጥም አማራነት እንጂ አንዳች ከነፍጥ ጋር ግንኙነት የለውም፡፡ በአሜሪካና አውሮፓ በይፋ አደባባይ ወጥተው ነፍጠኛን እናጠፋለን ሲሉ የነበሩ በቀጥታ አማራ ማለታቸው እንደሆነ ማንም ሊያጃጅለን አንፈልግም፡፡ በግልጽ ነፍጠኘ እየተባለ ለዘመናት ሲታረድና ሲሳደድ የነበረው በዘሩ አማራ የሆነ ምስኪን እንጂ ነፍጥ አንጋች እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡፡ ይሄን ጉዳይ ከአይሁድ የሆሊኮስት ፍጅት አሳንሶ መታየት ያለበት እንዳልሆነ ከወዲሁ ታስቦበት በዓለም አቅፍ ደረጃ እርምጃ የሚያስወስድ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደሆነ በደንብ ሊታወቅና ሊመዘብ ይገባል፡፡ አማራ ከሌላ የአማራ ወዳጅ ተብሎ የታሰበ ጉራጌ ወይም ሌላው በነፍጠኛ ሥም ይገደላል፡፡ ይህም ባይሆን አሁንም ከአማራ ጋር ቅርበት አለው የተባለ ኦሮቶዶክስ ኦሮሞ ይገደላል፡፡ ይሄን ትርጉም ለማለባበስና ለወንጀለኞች ዛሬም አማራ ማለታችን አደለም እያሉ ተመልሰው የሚያጃጅሉንን አረመኔዎች ሌላ እድል ለመስጠት ይመስላል እንደገና እንዳልገባን ነፍጠኛ ማለትን ትረጉም ማብራራትን የምንጠይቀው፡፡ የአባይ ሚዲያ በዚህ በአለማወቅም ቢሆን የሌለ ማሳከር እንደፈጸመ አውቆ ሊታረም ይገባል፡፡ በቃ ነፍጠኛ ማለት አማራ ማለት እንጂ ነፍጥ ያነገተ አደለም፡፡ ይሄን ቃል እነሱ በሚግባቡበት የዘር ማጥፋት ቅስቀሳ  እያደረጉበት ተመልሰው አማራ ማለታችን አደለም ሊሉን የፈልጋሉ፡፡ የኦሮሞ የዘረኝነትና ጥላቻ ፖለቲካ የተለከፈው ብዙ ሕዝብ ልጁን ከልጅነት ጀምሮ ይሄንኑ ሲሰብክ ነው የሚያሳድገው፡፡  የኦሮሞ ፕሬዘዳንት ራሱ እኮ ሳይቀር ነበር በሕዝብ ላይ የዘር ጥላቻ ሲቀሰቅስ የነበረው፡፡  ነፍጠኛን ግድል እየተባለ ዛሬ በየተቃውሞ ሰልፍ ሳይቀር እየታወጀበት ያለው ማን ነው? ነፍጡማ ያለው ገዳዮች እጅ ነው፡፡ ይመለከተኛል የሚል ሁሉ ይሄን ቃል በመናገር ሕዝብን የሚቀሰቅስ ማንኛው ፖለቲከኛ ይሁን ግለሰብ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ሳይቀር በወንጀል የሚጠየቅበትን አሰራር ከወዲሁ እንዲያስበበት አላለሁ፡፡ ነፍጠኛ ማለት አማራ ማለት ነው ከዛ ካለፈ ኦሮሞ ያልሆነ ከዛ ካለፈ ኦሮሞ ኦርቶዶክስ ነው! በአጠቃላይ ነፍጠኛ የሚለው ምንነትን እንጂ ነፍጥን ለመግለጽ አደለም፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠበቅ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

 

3 Comments

  1. It is time that Ethiopian Orthodox church and her followers must find their place in Ethiopia. It is the time. Majority of Ethiopians are Orthodox Christians, but they are pushed from leadership since the revolution time by communists, then by Satanists, and then by two protestant leaders. Orthodox Christians must wake up and stand up. When we stand firm, our enemy will stand down. Otherwise these genocides will multiply like a wildfire. Orthodox church is losing ground to a systematic onslaught on many directions not because our enemies are strong, but We are too cowardly to stand up together. Orthodox Christians must defend themselves, their church, and their Country. We must stand together regardless of the language we speak as our destiny is one and the same. Most of the orthodox church teachers now are busy doing business on you tube while our brothers are being beheaded. Enough is enough, we should not wait any longer for protection from somebody else. Our forefather passed our church and our country to us not by giving their necks to be slaughtered like a sheep but by standing up like a lion to defend their families, their church, their country. Stand up! Enough is enough. Enough is Enough.

    • Majority of Ethiopians are Orthodox Christians, but they are pushed from leadership since the revolution time by communists, then by Satanists, and then by two protestant leaders. Orthodox Christians must wake up and stand up.

  2. ዛሬ ደግሞ በሃይማኖት መጣህ?? 45% የኢትዮጵያ ህዝብ እስላም በሆነበት ሃገር “እስላማዊ አክራሪነት” ብለህ የሃይማኖት ጦርነት በመቀስቀስ እሳቱን ለመሞቅ፣ ብሎም ያተርፍልኛል ብለህ ተነሳስተሃል! ሞጣ ለተፈጸመው መስጊዶችን የማቃጠልና የእስላሞችን ንብረት የማውደም የጅምላ ወንጀል በነማን ቀስቃሽነት እና አደራጅነት እንደተፈጸመ ቆይተህም ቢሆን ፍንጭ እየሰጠህ ነው። ለነገስ ዬት ጋ ደግሳችኋል?
    ነፍጠኛን እና አምሃራን አንድ አድርጋችሁ በማቅረብ፣ ዛሬም የአምሃራን ህዝብ የመሰሪ ሸራችሁ መያዣ (hostage) እና የስልጣን መወጣጫ አድርጋችሁ ትማግዱታላችሁ። ህዝብን ከህዝብ፣ እምነትን ከሌላው እምነት ጋር በማጋጨት የፖለቲካ ስልጣን ላይ የተጣበቃችሁት፣ ለአማራው ምንም የማትፈይዱ፣ አልፎም እማያገባው ጦርነት ውስጥ የምትማግዱት፣ በጠብመንጃ ሃይል የደቡቡን ህዝብ ባሪያና ገባር በማድረግ ደሙን የመጠጡ ጠብመንጃ አምላኪዎች እና እናንት የዛሬ ልጆቻቸው ናችሁ!! በተዘዋዋሪ፣ ነፍጠኛ ነፍጥ እንጂ ዘር የለውም ትላላችሁ፣ ድንገት እውነት ሲያመልጣችሁ!
    ባጭሩ፣ ከአማራውም ጫንቃ ላይ ዉረዱ! አገር ገደል የምትከቱት እናንተው ብቻ ናችሁ!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.