በፊንላንድ ከምንኖር ኢትዮጵያዉያንና ትውልደ ኢትዬጵያዊያን የተሰጠ ማሳሰቢያ

በቅድምያ በቅርብ ጊዚ ሕይውቱን በነፍስ ገዳዮች ባጣው አርትሲት አጫሉ ሁኔዲሳ ሞት የተስማን ሀዝን አየገለፅን፥ አሱን ተከትሎ በኑፁሃን ኢትዮጱያዊያን ላይ ጭካኔ የተሞላበት ግድያ፥ ሞት፣ ዝርፍያ የሀብት ውድመት በጣሙን አሳዝኖናል።

እንደሚታወቀው በአዲስ አበባ የድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳን መገደል ሰበብ በማድረግ በሀገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ብሔር ተኮር የሆነ ጥቃት ተፈፅሟል። ጥቃቱ የተፈፀመው ከጉድዩ ጋር ምንም ግንኙነት በሌላቸው ንፁሃን ዜጎች ላይ መሆኑ ጉዳዩን እጅግ በጣም አዛዛኝ ያደርገዋል።

ጥቃት የፈፀሙትን አካላት መንግሥት ክትትል በማድረግ ተጎጅዎች ፍትህ እንዲያገኙ በምንጠይቅበት ወቅት እዚህ ፊንላንድ ውስጥ የምትኖሩና ገዳዮችን የምታበረታቱ፤ ተመሳሳይ ጥቃት በሌሎች አካባቢዎች በተለይም በአዲስ አበባ እንዲስፋፋ በፌስ ቡክ የጥላቻ ፅሁፎችንና አስተያየቶችን የምትሰጡ ግለሰቦች እንዳላችሁ ለማወቅ ችለናል።

ቀደም ባሉት ቀናት ብሔርን ከብሔር ለማጫረስ የፃፋችሁትን ፖስትና አስተያየት ስክሩን ሾት እያደረግን ለማስረጃ አስቀምጠነዋል።

ይህንንም ተከትሎ  በስባአዊ መብት ዙርያ የሚስሩ የህግ ባለሞያዎች አማከረን ክስ ለመምስረት የሚይስችል ጥስት አንዳለ ነግረውናል።

አሁን ከጥፋታችሁ ታቅባችሁ ማንኝውንም ብሔርን ከብሔር የሚያጋጭ ፅሁፋችሁን ማውጣት እንድታቆሙ በአፅንዖት እየጠይቅን። ይህ ካልሆነ ግን የፊንላንድ ህግ የጥላቻ ፅሁፎችንና ንግግሮችን በሚመለከትበት ያለውን የህግ አንቀጽ ጠቅሰን  ወደ ክስ የምንገባ መሆኑን  እንድትገነዘቡ እናሳስባለን።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ያልተቀደሰው ጋብቻ (ኢህአዴግ፣ ፋና፣ ኢብኮ፣ ምርጫ ቦርድ) -ጌታቸው ሺፈራው

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share