መንግስት ሆይ አታድበስብስ! አታሳክር! ! – ሰርፀ ደስታ

abiy 5 መንግስት ሆይ አታድበስብስ! አታሳክር! !  ሰርፀ ደስታዛሬ ያለንበት ችግር በዋናነት ራሱን መንግሰት የሚለው አካል ችግር ሆኖ ነው እኔን የሚሰማኝ፡፡ ለውጥ የተባለው እንዲመጣ ትግል በነበረበት ጊዜና በለውጡም ብዙ መልካም የሆኑ ሁኔታዎች ተፈጥረው ነበር፡፡  ራሳቸውን የለውጥ አራማጅ ያሉት ግን ከለመዱት የማሰመሰልና ሴራ መሸረብ ነጻ መሆን ስላልቻሉ ወደበለጠ የከፋ ነገር ገባን፡፡ ያኔ የኦሮሞ ደም የእኔ ደም በተባለበት ወቅት ለውጡን ጥሩ ሲመሩ ነበር ያልናቸው ዛሬ የዘሬን ብተው ይመንዝረኝ አይነት ሆነውብናል፡፡ ግን እስከ መቼ፡፡ ወዴትስ እያመራን እንደሆነ ይገባቸው ይሆን? በኢትዮጵያዊነት ታጅቦ ሌላውን ማጥቃትና የንግድ ዕቃ ማድረግ በኦሮሞነት ታጅቦ ትልልቅ አገር አፍራሽ ሴራን ማሴር ግን መጨረሻውን ምን እንደሚሆን ይረዱት ይሆን? 27 ዓመት ወያኔ የሸረበችውን ሴራ በጣጥሶ ከተለወጣችሁ ብሎ አምኖ የተቀበላቸው አንድም ቀን አላደሩ ነበር ከአሳዳጊያቸው የተማሩትን የዘረኝነት ስልት በተግባር ሲያውሉት፡፡ አዝናለሁ፡፡ ችግሩ ከጅምሩም በዘፈቀደና በአጋጣሚ የመቱ እንጂ አገርና ሕዝብ ማለት ምን ማለት እንደሆነ የማይረዱ በመሆኑ ይሄው ወጣንው ያልነበት አረንቋ ተመልሰን ጭራሽ በከፍጸኛ ፍጥነት እየዘቀጥን ነው፡፡

ጀዋር መሀመድና ቡድኑን ከመጀመሪያውም አገር ለማፍረስ እንደነበር አጥተውት አደለም፡፡ ሆኖም ብዙዎች የእሱ ፍላጎት ተጋሪዎችና ሌሎች ደግሞ በአላወቁት ነገር በኦሮሞነት አጃቢ በመሆን እስከ አምልኮት ደረስ ተከተሉት፡፡ ሲመኘው የነበረውን የሕዝብን ከሕዝብ አጫርሶ አገር የማፈረስን ሙከራ አንዴ ሳይሆን ሁለቴ በአዋጅ በአዲስ አበባ ውስጥ ተቀምጦ አወጀ፡፡ በመጀመሪየው አዋጁ ያ ሁሉ ሰው አልቆ እሱን ማን አባቱ ነው የሚነካህ በሚል ጭራሽ ሲያባብሉት ተመለከትን፡፡ በጣም የተማመንባቸው ብዙዎች ሳይቀሩ በሚያሳዝን ሁኔታ ለአገር ጠላት ሆነው በከፍተኛ ሥልጣን ላይ ተቀምጠው አስተዋልን፡፡ አገር በራሷ ጠላቶች እጅ እንደወደቀች ታዘብን፡፡ ኦሮሞነት ብዙዎችን እንዳያስተውሉ አወራቸው፡፡ ለዘመናት የገነቡትን የጥላቻና ዘረኝነት ጥማቸውን በተግባር ለመፈጸም እጅግ ተጣደፉ፡፡ ነፍጠኛ ነፍጠኛ ነፍጠኛ ብለው ምርር ብለው ጮኹ፡፡ የጥላቻቸውን ልክ አግጦ ወጣ፡፡ በዚህ ሁሉ ባላወቀውና ባልተረዳው ነገር በአጃቢነት የሚተምላቸው በዛ፡፡ እግዚአብሔር ግን ያያል፡፡ ማንንም አይምረውም፡፡ አንዳች የማያውቁ ሚስኪኖች ላይ አዋጅ ታወጀ፡፡ ለአንዳነዶቻችን ይሄ ለሶስተኛ ጊዜ ያየነው ሙከራ ነው፡፡ አንደ በደርግ፣ ሌላው ወያኔ የገባ ጊዜ ዛሬ ደግሞ ኦሮሞ ስልጣን ይዟልና አሁን ከየትኛውም ጊዜ ተመቻችቶልናል ብለው በአሰቡበት ጊዜ ነው፡፡ በመሀል የኖርንባቸውን ክስተቶች እዚህ ጋር መጠቆም አልፈልግም፡፡ እነዚህ ሶስቱ ዋና ምሰሶ ናቸው፡፡ ደርግ እንዳይነሳ አድርጎ ሰብሮት ነበር፡፡ ወያኔ ጠገገነቸው ዛሬ ደግሞ ራሱን ኦፒዲ የሚለው ቡድን አወፈረው፡፡ እርግጥ ነው በተለይ መለስ ከሞተ ጀምሮ በከፍተኛ ፍጥነት ይሄ ቡድን ወደ ላይ እየመጣ ነበር፡፡ በፍጥነት ነበር አኖሌ የሚባል የበቀል ሐውልት አቁሞ ኦሮሞን ሁሉ በጥላቻ ሲያጠምቅ የቆየው፡፡ የኦሮሞ እስላማዊ ቡድን ሴራ፡፡

አሁንም መንግስት ነኝ የሚለው አካል እያምታታን ነው፡፡ እኔን እስሚገባኝ መነግስት የሚያደርጋቸው ደድርጊቶች የጉዳዩን አንኳር መራከስና ማደበስበስ ነው፡፡ አያውቀውም የሚል እምነት ግን የለኝም፡፡ አጋጣሚውን ሌሎችን ለማጥቃትም እየተጠቀመበት ይመስለኛል፡፡ አሁን የተከሰተው ድርጊት ግልጽ የሆነ ባለቤት እያለው ከጉዳዩ ጋር የማይገናኙ ግለሰቦችንና ቡድኖች በዚህ ጉዳይ አባል ማድረግ እጅግ አደገኛ የሆነ አሁን አድበስብሶ የማለፍ አዝማሚያ እያየን ነው፡፡ ሌላው ሰዎች ጭንቅላት ውስጥ በሰፊው የሰረጹ ጉዳዮችን ለዚሁ ማደበስበሻ ሲጠቀምበት እናያለን፡፡  ግለሰቦችም ይሁኑ ቡድኖች ሌላ ከዚህ ጉዳይ ያልተያያዘ ሊጠየቁበት የሚችል ወንጀል ወይም የፍትሕ ጉዳይ ሊኖር ይችላል፡፡ የሐጫሉ ግድያና ግድያውን ተከትሎ ሕዝብን ከሕዝብ ለማጫረስ አገርን ለማፍረስ የተደረገው ሙከራ ግን ግልጽ የሆነ ባለቤት አለው፡፡ የእነጀዋርንና እስክንድርን ፖሊስና አቃቢ ሕጓ ተብዬዎች ይናበቡ ነበር ሲሉን አእምሮ እንዳለን እንኳን ትንሽ ሊቆጥሩን አለፈለጉም፡፡ ሌላው ሁል ጊዜ ኦሮሚያ ውስጥ አንድ ችግር ተከሰተ በተባለ ቁጥር በምክነያትነት እንደማምለጫ የሚደረገው ሸኔ ኦነግ የተባ ቡድን ነው ከዚሁ እነዚሁ የመንግስት የተባለው አካላት ሲጠቅሱት የሰማሁት፡፡ አዝናለሁ አሁን ነገሮችን በውል እያስተዋለን ነው፡፡ ሸኔ ኦነግ ሌላ ቦታ ጥፋት አድርሶ ሊሆን ይችላል፡፡ በምናያቸው ማንነትን ኢላማ አድርገው በተነሱ አደጋዎች ግን አንዳቸውም ጋር የሸኔ ኦነግ የተባለው ቡድን ለመኖሩ ምልክት የለንም፡፡ እንደተለመደው በሸኔ ኦነግ አሳቦ ሁኔታዎችን ለማድበስበስ እንጂ፡፡ በሌሎች ቦታዎች የሆነውን ሁሉ አሁን እያየን ነው፡፡ የሚገርምና የሚያሳዝነው ግን በአምቦ የሐጫሉ የቀብር ስነስርዓት እንዳይከናወንም የዚሁ የፈረደበት ሸኔ የችግር ፈጣሪ በሚል ሲወነጅል ነበር፡፡ እውነቱ ግን አሁንም አስከሬንኑን ተከትለው የሄዱ የአሸባሪው የወያኔና የጀዋር ቅጥረኞች እንደነበሩ ብዙም አጠያያቂ አደለም፡፡ እርግጥ ነው በአላወቀው ነገር ምንም የማያውቁ ወጣቶችን ለመጠቀም ችሏል፡፡ ሸኔ ኦነግ ያላችሁን ቡድን ግን በዚህ ክስተት ለመኖሩ አንድም የምናየው ምልክት የለም፡፡ የሚገርመው ከዩኒቨርሲትም ታፍነው የተወሰዱ ተማሪዎች እንዲሁ በሸኔ ኦነግ ተሳቦ እንዲቀር ተፈልጓል፡፡ የዛ ጉዳይ ወንጀል ሰሪና የሐጫሉ ገዳይ ግን የተለያዩ አይመስሉኝም፡፡ በግለሰብ ደረጃ ሳይሆን በመዋቅርና በቡድን ማለቴ ነው፡፡ እንግዲህ ከጀዋርና አጋሮቹ ጋር በአይናችን የምናየው ኦፌኮ የተባለ ቡድን እንጂ ሸኔ ኦነግ የተባለው አይደለም፡፡ እኔ የሸኔ ኦነግ ጠበቃ ሆኜ አደለም ግን በዚህ ቡድን እየተሳበበ የሚደረገው ሴራ ስለታዘብኩ እንጂ፡፡ እንዲህ ያለ ማምታታት ቆይቶ ለራስ አደጋ እንደሆነ ማሰብ ቢቻል ጥሩ ነው እላለሁ፡፡

እኔ ለዚህ ክስተት የመጀመሪያ ተጠያቂ የማደርገው መንግሰት የተባለውንና በውስጡ ከእነጀዋር ጋር የሚሰሩትን ነው፡፡ ምንም ሌላ ሌላ ጋር መቧጠጥ አያስፈልግም፡፡ መንግስት የሚባለው ከጅምሩ ለዚህ ወሮበላ የሚሰጠው ከለላ ለብዙ ወነጀሎች ተባባሪው እንደነበር እናስታውሳለን፡፡ የኮንደሚኒየም ቤት አይሰጥም ባለ ጊዜ መንግስት ተብዬው ፖሊስ መድቦለት ነበር፡፡ በአለፈው ያ ሁሉ ዜጋ የሞተበት ክስተት እንዲሁ መንግሰት ተባባሪው ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ዜግነት ሳይኖረው የፓርቲ አባል ሲደረግ ተባባሪው አሁንም መንግሰት ነኝ የሚለው ራሱን በኢትዮጵያዊነት ሳይሆን በኦሮሞነት የሚመዝን ነው፡፡ ኦሮሞ ከሆነ የትኛውንም ወንጀል ቢሰራ ተቀባይነት ስላለው፡፡ ሌሎች ብዙ ያየናቸው ችግሮችም አሉ ለምልክት እነዚህ ጠቀስኩ እንጂ፡፡ በኦሮሞነት እየታጀበ ብዙ ጥፋት ጠፍቷል፡፡ በኦሮሞነት እየታጀበ ብዙ ኦሮሞ ከቤት ንብረቱ አፈናቅሎ ቦታውን ነጥቆ ለሌሎች ቸርችሮት መልሶ ኦሮሞን ከቦታው አፈናቅለው እያለ ሌላ የጥላቻ መርዙን ይረጭበታል፡፡ ኦሮሞም ሆንክ ሌላው በደንብ አስተውል፡፡ የአዲስ አበባም ሆነ በዙሪያዋ ያሉ ቦታዎችን ሲቸረችር የነበረው ወያኔ ሳይሆን በዋናነት ኦሮሞ ነበር፡፡ እያፈናቀለ የነበረው የሸዋ ኦሮሞንና ሌሎችን ነበር፡፡ እስኪ ብዙ ገበሬ የተፈናቀለው በአዲስ አበባ ነው ወይስ በቡራዩ፣ በገላን፣ ዱከም፣ አለምገና በሱሉልታ ሳይቀር? መቼም በእነዚህ ከተሞች ኦሮሞ ነበር ከንቲባ ተብሎ ሲነግድ የቆየው፡፡ ችራሽ ሱሉልታና ለገጣፎ አርሲ ነበር የመሬት ነጋዴዎችና የሕዝብ ጠላቶች የተመደቡት፡፡ በኦሮሞነት እየታጀበ ብዙ ነገር እየጠፋ ነው፡፡ ዛሬ በኦሮሞነት ታጅቦ ነበር ሐጫሉን መግደል ነፍጠኛንና ኦሮሚያ ውስጥ የሚኖርን ሁሉ ለመጨረስ ጥሩ ምክነያት አድርገው ያሰሉት፡፡ ሐጫሉ በሐሳብ ስላልመሰላቸው እንደጠላት ሕዝብን ከሕዝብ ማባላትና አገር ለማፍረስ ደግሞ እንደጥሩ ኢላማ አስበውታል፡፡ ይሄ ሆኗል፡፡ ዛሬም ልታምታቱን አትሞክሩ፡፡ ኦኤም ኤን ለሐጫሉ ያደረገለት  ቃለመጠይቅ  ብዙ ነገር ነግሮናል፡፡ አዝናለሁ!

ቅዱስ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! አሜን!

 

9 Comments

 1. ሰርፀ
  የዶ/ር አብይ አገሪቱን ለማረጋጋት እየተሰራ ያልውን ስራ የማይደግፍ ካለ አገሪቱ እንዳትርጋጋ የሚፈልግ ብቻ ነው::”
  መንግስትን ማጠናከር እንጂ መተቸት ወቅቱም አይደለም:: ዛሬ ሀገር የማፍረስ ጦርነት ታውጃል:: ለማዳን ከመንግስት ጋር ቆሞ የኢትዮጵያውያንን ህይወት ማዳን አማራጭ የለውም:: በሻሸመኔ የተካሄደው ፀረ ህዝብ ጥፋት ለሁሉም ነገ በእኔ ብሎ ያስብበት:: ፖለቲካውን ሌላ ጊዜ

  • ውድ ተሰማ፣
   ሰርፀ የሚጽፋቸውን ወደ ኋላ ሄጄ ስመለከት ነበር። አንድም ቀን ተሳስቶ ጥሩ ነው ያለበትን እስካሁን አላየሁም። እርሱና አቻምየለህ፣ ወዘተ፣ መንቀፍን ቋሚ ሙያ አድርገውታል። ጊዜ ካገኘህ ጥቂቱን ጽሑፎቻቸውን አንብብ። እግረ መንገድ የሚያሞግሱትን ታሪክ ልብ በል።

 2. We are learning new information that Hachalu Hundessa didn’t die instantly after he was shot. In fact he was failed by doctors in Addis Ababa and the entire hospital and the federal police prevented people from helping Hachalu Hundessa. Such savagery is new to Addis Ababa.
  The man bled for 3 damn hours.

  How come they didn’t rush him to surgery?
  How come they didn’t stop the bleeding?
  How come security guards held him in his car to try to prolong his bleeding?

 3. Mulu Abebe
  What a perfect tplf analysis.? መንግስት ገደለው ብላችሁ ልታደንቁሩን እኛም ጅሎች የእናንተን ድራማ ልናራግብ ? What a low life !

 4. YES THE COVER UP HAS BEEN GOING UNTIL THE SERIOUSNESS KNOCKS THE DOORS OF THE PM, TAKELE UMMA, SHIMELESE AND OTHER HIGH OFFICIALS IF THEY AGAIN SNOOZE THEY WILL DEFENITLY LOOSE THEIR LIVES WITH NO DOUGHT. WE SHALL SEE IF THE DRAMA CONTINUES OR THE ACTION IS NO JOKE i CAN NOT IMAGINE HOW THESE CANCEROUS DIVISION SPREADS TO THE WEST AND THE EVIL Oromo ELITES ARE LAUGHING WHEN LIVES ARE LOST. WHEN I HEARD SLOGANS SAYING”DOWN DOWN HABESHA, DOWN DOWN AMARA AND DOWN DOWN ABYI AND ABYI IS REPRESENTING NOW ETHIOPIA”.
  THE MESSAGE WAS DISGRACEFUL AND SHAMEFUL NOT EXPECTED FROM PROTESTERS WHO DENY THEIR MOTHERLAND AND THEIR ROOTS.
  if IT WAS NOT FOR THE ALMIGHTY GOD WHO PROTECT AND DEFEND ETHIOPIA THE DAMAGE WOULD HAVE BEEN UNIMAGINABLE. GOD ALWAYS BLESS AND WILL PROTECT THE CHILDEREN OF MOSES FROM THE EVIL TYRANY OF THE PHARAOES AND THEIR MESSENGERS.
  MUCHFUN
  CANADA.

 5. ከታች ልጀምርልህ ከጸሎትህ። ልኡል እግዚአብሄር አንተኑ ማስተዋሉን ይስጥህ። በዛሬው ቀን ኢትዮጵያ እንዲህ እሳት እየነደደባት፣ የአባይ ሙሌት በእንጥልጥል እያለ፣ በየአቅጣጫው የወገን ድረሱልኝ ሮሮ በነ ቪኦኤ እየሰማን፣ ማንም ምን ይሁን ወያኔ የሚሉት የአውሬዎች ስብስብ በህይወት እያለ ሌላው ቢቀር በየክፍለሀገሩ ስላለቁት ነፍሳት እንኳን ብለህ ሰልስታቸው ሳይወጣ አንድ ሀይ ለማለት ቆርጦን የተነሳን በስልጣን ያለን መንግስት ፣ ለመተቸት የድሎት ዌስተርን ስታይል ፖለቲካ ላይ ነን አቶ ሰርጸ? በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ ያለን ኦፌኮ ከሸኔ ጋር ልታማታ ነው ወይስ ጁዋርን መታሁ ብለህ ነው? ምን ባለፈው ለጁዋር ተገን ቢሆኑ ዛሬ ጁዋር እኮ ተቀፈደደ፣ ሌሎችም እየተያዙ ነው እኮ። በርቱ ከጎናችሁ ነን፣ መቀሌ የመሸጉትንም ሰላቢዎች አትልቀቋቸው፣ በየሰፈሩና ገጠራገጠሩ በመሳቀቅ ላይ ያሉትን ወገኖች ለመታደግ አንድ ላይ መላ እንፍጠር የምትል ዜጋ ትመስለኝ ነበር። መንግስትን ሳይኮአናሊስስ ውስጥ የገባህው በዛሬው ቀን ማንን ለመጥቀም ነው? እነዛን ተሳቀው ያሉትን ወገን ይመስለሀል?” እምቦጭን ብጠየቅ ማጥፍያ ዘዴው አለኝ” ከሚል ወገን አልጠበኩም ነበር። ” መንግስትን አታሳክር? ቢሳከርበት እንኳ እንዴት ቀጥተኛ መንገድ እንደሚገባ በአደባባይ ኮምፓሱን እንዲያስተካክል ይመከራል እንጅ እነሱም እንዳሉትም ሸረሪቷን አደን ላይ ያለን መንግስት ጭራሽ አቅጣጫውን ስቶ ገደል እንዲገባ ይወገራል? ለመሆኑ ከዚህ ትችትህ ማ ይሆን የሚጠቀመው? መቼስ የዜጎችን ህብረት የሚፈልገው መንግስት አይሆንም ከዚህ የሚያተርፈው። ስሜታዊ እንሁን ካልን እኮ ብዙ ማለት ይቻላል። በበኩሌ ስሜታዊ ሆኜ ጽፌ እንኳ ሳተናዎችና የዘሀበሻን ቤተሰብ ከላኩኝ በሁዋላ “የላኩትን አታውጡት፣ ጣሉት” ያልኩባቸው ቀናት አሉ። ይመስክሩብኝ። ሀዘን ሲበዛ እንዲህ ያሳስታል እንጅ ሚዛናዊ እንኳ ነበርክ። እኔም ልጨርሰው በማሳረግያህ። አዎ፣ ፈጣሪ ሁላችንንም ማስተዋሉን ይስጠን። በዛሬው ቀን በተለየ የምጸልየው በሰቀቀን ላይ ላለው ወገናችንና እነሱኑ ለመታደግ ላይ ታች እያለ የወገንን ህብረት እየጠየቀ ያለውን መንግስት ነው። መንግስትን ዛሬ ላይ ሆኖ ማብጠልጠል ግን የሚዛናዊነት ምልክት ከቶ ሊሆን አይችልም። በጭራሽ!!! ኢትዮጵያ ብንታደለው ኖሮ ህውሀትንም ትፈልግ ነበር ግብጽ እንዲህ እየተጸዳዳችብን (ክፋቱ የግብጽ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነውብን አረፉት እንጅ) ። አበቃሁ።

 6. ጽሁፍህ ላይ ያስቀመጥካቸው ነጥቦች የአገራችንን አንደነት ፈላጊ ዜጋ ሁሉ ቁስል ነው የቀሰቀስው፡፡ ጨው ለራስህ ብለህ ጣፍጥ አለበለዚያ ድንጋይ ነው ብለው ይጥሉሃል ይላል ተረቱ፡፡ ፕ/ሚሩ ወደድም ጠላም በዘር ሥር እጉያው ተሰግስገው የአገራችንን ህልውና ለማጥፋት የሚፈራገጡትን ማጽዳት ግዴታው ነው፡፡ በአገራችን ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ አረመኔነት ያየነው በዚሁ ፕ/ሚር አስተዳደር ነው፡፡ እንደ ጃዋር ያለ ጫታም አገር ሲያሳምስ እያየ ዝም ብሏል ለ3 ዓመት አሁንም ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ማድረጉን ትቶ አስፈላጊውን እርምጃ ጅዋርና የመሳሰሉትን በአዲስ አበባ አስተዳደር ውስጥ ከንቲባው እያደረግ ያለውን የዘር አጀንዳን ጨምሮ ማጽዳት አለበት፡፡
  እስከዛሬ ባሳየው መሪነት አሁን የእራሱን ብርኩማ ብቻ ሳይሆን የአገራችንን ህልውና ሊያስጠፋ ስለሆን ከዚህ በኋላ ጠንከር ያለ እርምጃ ቢወስድ ግድ ነው፡፡ ጃዋርና አጣና ተሽካሚዎቹንም ህዝብን ማሸበር እንዲያቆሙ ጠንከር ያለ እርምጃ ማድረግ የግድ ይለዋል፡፡

 7. Thanks Tserse for identifing who, what, when, how, where of the current situation. Hopefully it opens the minds of our brothers who are under delusion.

 8. አባ ዊርቱ !መቆጣትህ ግልነትህ እና ማንነትህ ላይ እንድጠራጠር አድርጎኛል! ጎባጣን ጎባጣ ማለት ስው የመሆን ህሳቤ ነው::ጎባጣነቱ ለማስተካከል መስራት ብልህነት ነው አዋቂነት ነው::ደብቀህ መዋሽት ግን አጥፊ እንዳይስተካክል ማድረግ ነው;;
  ኡባዊርቱ እስቲ ልጠይቅህ በኦሮምያ ክልል በቀጥታው አማራ ወይም ነፍጠኛ እየተባሉ አንገት መቅላት ተባብሶ የቀጠለው ዶር አብይ ሀገሪትዋን በለውጥ ህሳቤ እየመሩዋት ባሉበት ግዜ ነው? ታድያ ልምን እየተባብስ ቀጠለ? አሁንም የስልጣን ባለቤት ተሁኖ ወያኔና ሽኔ ላይ መለጠፍ አይቻልም!! ለማንፃፅርያ የትከብሩ አቶ ሙስጠፋ የሱማሌ ክልል ያንን ትልቅ ቀውስ የተፈጠርበትን ቦታ ዛሬ ለሁሉምክልል ምሳሌ የሚሆን ስራ ህብረተስቡን በስላም በመቻቻል እያስተደደሩት ነው;;እርሳቸው ይህን ሰላም እንዴት አመጡት?
  አባዊርቱ !ዶር አብይ አብይ አሁንም በማስመስል ችግሩን ዉደ ሌላ አካል አንተም ጭምር ስትግፉት ሌላው ከእናንት በተሻለ የሜረዳ መትሄም መስጠት የሚችል እንደሌለ በየዋህነት ስትቀባጥሩ ሳይ ባፍርባችሁም ለመማርና ለመታረም እለመቻል ድንቁርና ነው;;የተከበሩ አቶ ስርፀ አቶ ግርማ አቶ አቻሜለህ የስጡትን አስያየት ማጤን ብህነት ነው::ችግሩ እየተባባስ ያለው ክልሉን የሚመራው ድርጊትን በከፊል እንደሚደግፈው ችግሩ የተፈጠረበት ቦታ በህዝብ ገንዘብ የሚከፈለው ችግሩ ሲፈጠር ተመልካች እንደሆነ አንዳንዴም እሪሱን ከጥቃት ይሚከላከለውን ሲያጠቃ ና ለአጥቂው ቄሮ እሳልፎ እየስጠ ነው;;: እራሳቸው ዶር አብይ ይህን ያህል በጅምላ በቄሮ በጭካኔ ሲያልቅ ብሄራዊ የሀዘን ቀን አላደረጉም!ብቀጥታ ቄሮ ; ጁሀር ወይምኦፍኮ እራሱ ብፅግና ውስጥ በአመራር ላይ ተጠያቂ ከማድረግ ይልቅ ወደሌላ ሲያመሩ ህዝቡን መናቅቸውን ታየለህ;: ይህን አስቀድሞ መከላከል ሁሉም የስልጣን ቦታ በኦሮሞ ብልፅግና ተሞልቶ መረጃ ፍንጭ ሳያገኙ ደረስ ማለት አይቻልም;;አፍንጫቸው ጁሀር እንደልቡሲናገር ኮነደሚንየም ወጥቶ በድንፋታ ሲናገር ጥበቃ ወታደር ነበር መንግስት የመደበለት;በአንፃሩ እነ እስንድር እነ ክርስትይን ለመስብስብ እንኮን ተነፍጉአቸው ከፍ ሲልም እራሱ ዶር አብይ ጦርነት እንከፍታለን የሚል ድንፋታ በአደባባይ ያስማሉ;;;
  አባዊርቱ ! አሁንም የእነእስክንድር የእነ እንጅነር ይልቃል ቤተስብ መጠየቅ አልቻልንም ልዩነት ይደረግብናል እያሉ ነው;;ዋናው ነገር ታይቶ በማይታውቅ በኢትዮጵያ ታርክ በመንግስት ችላ ባይነትና አድሎዊነት ይህ እልቂት ተፈፅሞል::መንግስት ራሱን እንዲፈትሽ በወቅቱ መግለፅ ትልቅ አስተዋይነት; ነው;;ይህ መጥፎ ታሪክ ይፃፋል ማንም የማይክደው በምስል እየተቀረፀ ስለሆነ!በጣም የማዝነው ኦሮምያ በጭካኔ በግጀራ አየገደለ ሬሳ እያቃጠለ የሚጨፍር ትውልድ ማፍራትዋና ወጣቱን ከጥፋት የሚያድን አካል ወይም ቤተእምነት መጥፋቱ ነው!!! አንተ አባዊርቱ እራስ ወጣቴን ከዚህ ድርጊት እንዲቆጠብ ምንአድርግሃል? እግዚአብሔር ቅን ልቦና ይስጥህ ወንድምህ!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.