በአርቲስት ሃጫሉ ሞት ሳቢያ እየተካሄደ ያለው የዘር ማጥፋት የሀብት ውድመት አረመኔያዊ ተግባር በእጅጉ አሳስቦናል – የዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት 

Amhara**የዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት ወቅታዊ መግለጫ**

በዚህ ታሪካዊ ወቅት በአገራችን በኢትዮጵያ በየቦታው በዘርና በሃይማት ማንነት ላይ ያነጣጠሩ፣ ሕይወት በመቅጠፍ፣ አንጡራ ንብረታቸውንና የእምነት ተቋማትን በማውደም እየተካሄዱ ያሉትን እጅግ ዘግናኝ ጥፋቶች በከፋ ሀዘንና በተሰበረ ልብ እንዲሁም በጥልቅ ወገናዊነት ቁጭት በቅርብ እየተከታተልነው እንገኛለን። ይህ በከፍተኛ ወንድማዊ ፍቅር የምንመካበትን የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን በመሰሪዎች ሴራ መገደልን ተከትሎ በተቀነባበረ መንገድ እየትካሄደ ያለው ወገንን ከወገን በማጨፋጨፍ ሕዝብና ሀገርን የመበታተን ሴራ፣ በሀገራችን ታሪካዊ የውጭ ጠላቶችና በምንደኛ የውስጥ ጉዳይ አስፈጻሚዎች መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው። በየአካባቢው የስም ዝርዝር በመያዝ በአብዛኛው በማንነታቸው ምክንያት ብቻ ሕይወታቸውን እየቀጠፉ ንብረቶቻቸውን ያወደሙት እኩያን ሀገሪቱን በመዝረፍ፣ ሕዝብን በግፍ ዘር በማጥፍት፣ ለስደትና ለሞት ሲዳርጉ የቆዩና በተለይም በአማራ ላይ ያነጣጠረ የጥፋት ተለእኮ በስፋትና በጥልቀት ለዘመናት ሲሸርቡ የቆዩ የአገርና የወገን ጠላቶች እንደሆኑ ለሁሉም ወገን ግልጽ ሊሆን ይገባል። ከዚህ የተቀነባበረ የጥፋት ሴራ የመንግስትን መዋቅር በኃላፊነት የሚመሩ ባለሥልጣናት እንዳልተሳተፉበት ለማመን እንደማይቻል በጥብቅ ለማስገንዘብ እንወዳለን። በዚህም ምክንያት እነዚህ የሽብርና የጥፋት ወገኖች ወደፊት ለሚደቅኑት ምልባትም የባሰ የጥፋት ተግባር ላነጣጠሩበት አደጋ የሚጠብቀው ማን ሊሆን እንደሚችል እንቆቅልሽ መሆኑን መላው ሕዝብና ገዢው መንግስት በውል ማወቅ አለባቸው። ከአሁን ቀደም በተመሳሳይ በዘር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የፈጸሙ ወገኖች በአስቸኳይ ለሕግ ቀርበው ተመጣጣኝ ቅጣት እንዲያገኙ ጉዳዩ በእጅጉ ያሳሰባቸው ወገኖች መንግስትንና ባለድርሻ አካላትን ወይም የሚመለከታቸውን ሁሉ ሲማጸኑ መሰንበታቸው ግልጽ ነው። በአጥፊዎቹም ላይ አፋጣኝ ምርመራ ተካሂዶ ተመጣጣኝ ሕጋዊ እርምጃ ሳይወሰድ ሲድበሰበስ መቆየቱ ለነዚህ እኩያን የበለጠ መጠናከር እንደጠቀማቸው እሙን ነው። በታሪክ አማራው እንደዚህ በገሃድ አለም እያየ በሁለተኛው አለም ጦርነት ጁዎቹ የደረስባቸው የዘር ማጥፍት ወንጀል አይነት   ዛሬም በአማራው ወገኖቻችን ላይ በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልል ውስጥ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ ዘግናኝ የሆነ የዘር ፍጅት ተፈፅማል ይህም የኦሮሚያ ፓሊስ የክልሉ ሃይሎች ቄሮ ነን ብለው ራሳቸውን ለዘር ማጥፍት ወንጀል ካደራጁ አካላት  ጋር አብሮ በመሆን ከፍተኛ እልቂት የፈፅሙ መሆናቸውን በመረጃ የተደገፈ ስለሆነ ስለዚህ መንግስት በነፃ እና በገለልተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው አፍጣኝ ውሳኔ እንዲስጣቸው አለም አቀፍ የአማራ ህብረት ይጠይቃል። የድምፃዊ አጫሉ ግድያ ጋር ተያይዞ ምንም ግንኙነት የሌለውን የባልድራስ ለኢትዮጵያ ፕሬዘዳንትን አቶ እስክንድር ነጋን ለብዙ አማሮች ህይወት  መጥፍት ምክንያት የሆኑትን እን ጅሃርና በቀለ ገርባ ስለታስሩ ብቻ ንፁህና በስላማዊ መንገድ ብቻ ለውጥ ይመጣል ብሎ የሚታገለውን እስክንድርን ማስረ እጅግ ፍትህ የጎደለውና ምናልባት ከዚህ በፊት ጠ/ሚንስትሩ ከባላደራው ጋር ጦርነት እንገባለን ባሉት መስረት  በግል ቂም ላይ ተመረኮዞ የተወስደ እርምጃ መሆኑ አገር ያወቀው ፅሃይ የሞቀው ሃቅ ስለሆነ ምንም ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት የሌላቸውን አቶ እስክንድርን ጨምሮ ኢንጅነር ይልቃል እና አቶ ልደቱ አያሌው በአስቸካይ ተፈተው ከቤተስቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ የአለም ዓቀፍ አማራ ህብረት ጥያቄውን ያቀርባል።ሚዲያንም በተመለከት የአማራን ብሶትና እየደረስበት ያለው የተቀነባበረ ሴራን በማጋለጥ እውነቱን እየተከታተለ የሚዘግበውን የአማራን ድምፅ የአስራት ሚዲያን  የዘር እልቂትና ፍጅት በግንባር ቀደምትነት ከሚቀስቅስው የኦኤም ሬዲዮ ጣቢያ ስለተዘጋ ብቻ ያለምንም ፍትሃዊነትና የህግ አግባብ አስራት ሚዲያም ይዘጋ ብሎ መወስን እጅግ አድሎዊ የሆነና ኢፍታሂ በመሆኑ በአስቸካይ የአስራት ሚዲያ የተጣለበት እግድ ተነስቶ ወደ ስራ እንዲመለስ አለም አቀፍ የ አማራ ህብረት ያሳስባል።

በእርግጥም በዋናነት መንግስት እንዲሁም የሚመለከታቸው ወገኖች የተቀላጠፈ እርምጃ ለመውሰድ እያቅማሙ ደንታቢስነታቸው እየተባባሰ ሄዶ ጽንፈኛ አሸባሪዎቹ በማን አለብኝነት የጥፋት ተልእኳቸውን በሰፊው ቀጥለውበታል። በመሆኑም፦

 1. በተለያዩ አካባቢዎች በእምነታቸውና በማንነታቸው ላይ ባነጣጠረ መልኩ መስዋእትነት እየክፈሉ ከመሆኑም በላይ አሁንም የዜጎችን ሕይወትና ሰላም የመጠበቅ ኃላፊነትና አደራ የተሸከመው መንግሥት በአፋጣኝ ተንቀሳቅሶ ጥበቃ እንዲያደርግላቸው፣ ሕዝቡም እየተደራጀ ራሱንና አካባቢውን እንዲጠብቅ መንግሥት ግልጽ መመሪያ እንዲሰጥ፦
 2. የአርቲስት ሃጫሉን ሞት ተክትሎ በተቀነባበረ መልኩ የታሰበበት የጥፋት ዘመቻ ፈጻሚና አስፈጻሚዎች እየታደኑ አስቸኳይ ሕጋዊ ርምጃ እንዲወሰድ በጥብቅ እንጠይቃለን። በዚህ ዘግናኝ  ድርጊት ክፍተኛ ሀዘንና ብስጭት ያደረበት መላው ተጠቂ ወገን እያቀረበ ያለው የአስቸኳይ ፍትህ ጥያቄ አሁንም በቸልታ የሚታለፍ ከሆነ የሚያስከትለው መዘዝ እጅግ የሚያሳስበን መሆኑን በአጽንኦት እናስገነዝባለን።
 3. መደበኛ ያልሆኑና የዘር ጭፍጨፋን ለማካሄድ ተድራጅተው የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች በመንግሥት የጸጥታም ሆነ የአክባቢው ባለሥልጣናት ሆን ተብለው የተተውና ይህንን የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲያካሂዱ የተለየ ድጋፍና ከለላ እየተሰጣቸው በመሆኑ ጉዳዩ በአስቸኳይ እንዲታርምና በተለይ ለተጠቂው የአማራ ሕዝብ በግልጽ ለሚሟገቱና ለሚታገሉ የአንድነት ወገኖች ጥበቃና ከለላ እንዲደረግላቸው እናሳስባለን።
 4. “እኔ ከሞትሁ ሰርዶ አይብቀል” እንዳለችው እንስሳ ሁሉ በተገኘ አጋጣሚ ብቻም ሳይሆን የተለመደ የዘር ጭቆናና ጭፍጨፋቸው እንዲቀጥል የምህንድስና ሥራቸውን ከፍርፋሪ አቅራቢዎቻቸው የውጭ አሸባሪ ኃይሎች ጋር እየሠሩ መሆኑ ታውቆ መንግሥት በእነዚህ ባንዳዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ በይፋ ለሕዝብ የገባውን ቃል በተግባር እንዲተረጉም በአንክሮ እየጠየቅን መላው የሰላምና የአንድነት ወዳድ ወገናችን ሁሉ ለዚህ ስኬት እንዲረባረብ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
 5. አገራችን በተለያዩ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች በውጥረት ባለችበት በዚህ ወቅት እርስ በርስ በማጨራረስ ኢትዮጵያን ለመበታተን በውጭም ሆነ በውስጥ የእልቂት ነጋሪት የሚጎስሙ አረመኔዎችን በጋራ ኃይላችንን አስተባብረን ከወገናችን ጎን እንድንቆም በውጭ ሀገራት ለምትኖሩ ወገኖቻችን ጥሪ እናስተላልፋለን።
 6. እንደሩዋንዳ የኢንተር ሃሞይን የማጨራረስ የቅስቀሳ ስልት በመከትል ወገንን ከወገኑ ጋር ለማጠፋፋት ይቀሰቅሱና እየቀሰቀሱ ያሉ ሚዲያዎች እንዲዘጉ እየተወሰደ ያለው ሕጋዊ እርምጃ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እናስገነዝባለን።

የዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት  ሰኔ 29 ቀን 2012 ዓ.ም

ዋሽንግተን ዲ ሲ

 

2 Comments

 1. በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው የሰው ነብስ እና ንብረት ማጥፋት በፋሺስት እና በናዚዎች ግዜ የቀረ መስሎኝ ነበር ። ተንኳሾቹ እና ክብሪት ጫሪዎቹ ከተያዙ ዕግ ፊት ቀርበው እንዲፈረድባቸው እና እንዲቀጡ ያስፈልጋል ። ማንም ከዕግ በላይ ሊሆን አይችልም ። ኦሮሞ ነው ፥ አማራ ነው ፥ ትግሬ ነው ፥ ጉራጌ ነው ፥ እያልን ከመከፋፈል ይልቅ የግል ንብረታችንን ኢትዮጵያን ለማፍረሥ የሚጥሩትን ዕግ ፊት ማቅረብና መቅጣት የያንዳዳችን ተግባር መሆን አለበት ።
  በኦሮሞም ሆነ በሌላ ግለሰብ ሥም ሀገሬን ኢትዮጵያን ሲነኩብኝ አልወድም ።
  ኦሮሞን ነኝ ፥ ከዛም በላይ ኢትዮጵያዊ ነኝ ።

  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !

 2. @የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን በመሰሪዎች ሴራ መገደልን ተከትሎ…@ ስለደረሰው የንብረት ዉድመት እንጂ፣ የሃጫሉን በግፍ መገደል በአንድ አረፍተነገር እንኳ አላነሳችሁም! That tells volumes!! Galatoomaa!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.