ይድረስ ለዖሮማራ አስተዳዳሪዎች አቶዎች  ሽመልስ አብዲሣና ተመስገን ጥሩነህ – ጥብቅ ማሳሰቢያ – ከአባዊርቱ

Achalu
ሀጫሉን ለመግደል የጨከነ ልብ ለታከለና ሽመልስ አይተኛም:: በሀጫሉ፣ ሺመልስና ታከለ ልዩነት አይታየኝምና። የተመሰገን ጥሩነህማ ግልጽና ግልጽ ነው። የዶር አቢይንም ፈጣሪ በቸርነቱ አልፎናል።
የዝብዝብ ጊዜ ሳይሆን ወቅቱ የሚጠይቀው መፍትሄን ስለሆነ እናት አገሩን የሚል  መፍትሄ ያለውን ሁሉ አምጦ ይውለድ። ቀጥታ ወደዛው እገባለሁ።
1). ሺመልስ አብዲሳ አክራሪ ሀይሎችን ቀን ቀን ብልፅግና ማታ የሸኔ አገልጋዮችን ከድርጅትህ አፅዳ።  አሉ በደንብ ተንሰራፍተው። በዚህ አጋጣሚ አምና ያዘንኩብህን ያህል መልሰህ ክሰኸናል። የኢትዮጵያዊነት መገለጫ ቡሉኮ ከጎጠኝነት ጥብቆ በመልክም፣ ይዘትም ፣ እድሜና ጥንካሬም አሳምሮ ይበልጣል። ለሀጫሉ የዘረገፍከው እምባ ልብ ይሰብራል። ውስጥህ የማውቀውና የተዋሃደኝ የንጹህ ዖሮሞነት ፍቅርና ቁጭት ለመሆኑ ያስከብርህ ይሆናል እንጅ አያስወቅስም። ያ ዶር ዳኛቸው እንዴት ደስ ይበለው? ተስፋ አልቆረጠብህም ነበር ሁላችን ስንወቅስህ። በርታ። ወጥረህ ያዝ። የዚህ ድንቅ ልጅ ደምማ ደመከልብ ሆኖ አይቀርም ።ያ ታዬ ደንደአንም በደንብ ጠብቁት። እርስ በርስ ተጠባበቁ። ከአማራ ወገኖቻችሁ ጋር በጥልቀት ተወያዩ፣ ተናበቡም።
2) አቶ ተመስገን ጥሩነህም ቀን ቀን ካንተ ጋ ብልፅግና ማታ ማታ ለህውሀት ደፋ ቀና የሚሉ የአማራውን ህዝብ ከሀዲዎች መንቅረህ አውጣልኝ። አሳምረው ተሰግስገውልሀል። ሁለታችሁም የአካባቢ ወንዝነት አያማላችሁ።  እነ አምባቸውን የበላ ጅብ ከአንድ ጎሬ  ብቻ እንደማይሆን እሙን ነውና። ልብ ያለው ልብ ይበል።
3.) ህውሀትና ሸኔ በቀጥታ ለመገናኘት አማራው ግዛት  ላይ ማለፍ አለባቸው:: በሩን በብረት አጥር ቀርቅራችሁ ዝጉባቸው
4.) የ100ና 50 ብር ኖቶችን ዐቢይ በአስቸኳይ ይለውጥ ዘንድ አሳምኑት:: የኢትዮጵያ እፍራሾች በጆንያ አጭቀው በየካዝናው በግመሎቻቸውና አህያ ነጋዴዎቻቸው ያጠራቀሙት አፈር ድሜ ይበላል በአንዲት ጀምበር።
5) አቶ ተመስገን የሀገር እፍራሹን ሀይል በሸረሪትና ድር ማመሳሰልህ ይደነቃል:: አሁን ድሩን በጣጥሰን ትኩረታችን ሸረሪትዋ ላይ ነው:: አዎ ሙያ በልብ ነው  አዋጅ አይስፈልገውም …. ደግሞ አድኖ ለመያዝ የአደባባይ መግለጫ ጋጋታ አያስፈልግም:: ድሯ ሲበጣጠስ ሸረሪትን ለመጨፍለቅ ብዙም ጉልበትና ዘዴ አይፈልግም:: የኢትትዮጵያዊነት ድር ላይ አበክራችሁ ስሩ! ድር ቢያብር እንኳንስ ኮሲና አመድ ስር የሚርመጠመጥ ጅብ ቀርቶ ታላቁንስ አንበሣ ያስር የለ?
6)ከዚህ ቀደም ደጋግሜ እንዳልኩት የአማራውና ዖሮሞው ህዝባዊ ሚሊሻ በአስቸኳይ የጋራ ኮማንድ ሴንተር አብጁለትና እየተናበበ ስራውን ይስራ። ሚሊሻው አለ የስምሪት መሪዎቹን አናቧቸው እንጅ (ታድያ ብቃትና ቁርጠኝነት እየተለካ)።
7) ዶክተር ዐቢይ ባንዳዎች የሚል ቃል ደጋግሞ ተጠቅሟል:: ይህ መረጃ በማስረጃ ተደግፎ ህዝብ በፍርድ ቤት ይየው። አዲሲቱ ጠ/አቃቤ ህግ እንደ ቀድመው ደከም ያለች  አትመስልም። የዚህች ግስላ እመቤት ዳኛ አያያዝ ተመችቶኛል። አቃቂር የምታወጡላት መጪው ቆራጥ አመራሯ ስላስፈራችሁም ይመስለኛል – እርማችሁን አውጡት። ስለሆነም “ባንዳዎች መሀላችን አሉ” ከሀሜት አልፎ እርግጠኝነት በአደባባይ መውጫው ዛሬ ነው። አለበለዚያ አገራችንን ለባንዳና ምንደኞች አስረክበን እጅ አጣጥፈን ልንቀመጥ ነው።  የህግ ጉዳይ ለህግ ቢተውም መሰረታዊ የእናት አገር ጉዳይ ከህጎች አናት በላይ ነው። መረጃው በይፋ በጋዜጣና ቲቪዎች ይውጣልን። ምን እስክንሆን ነው የሚጠበቀውስ? ሰዎቹ የሮኬት ወንጪፍ ካበሩብን ወራት ተቆጠሩ። የምንደኞች ሰልፈኞቻቸውን በአንዲት ጀምበር ድባቅ የሚመታ የኡትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆችን ማሰለፍ እየተቻለ በትእግስትና በማስፈራርያ አለቅን። ትእግስት አይምሮው ለሚሰራ ዜጋ እንጅ ለምንደኞች ጥርቅም ከቶ ሊሆን አይችልም – ሰርቶም አያውቅም ። እናም አጥብቀህ ወጥር ዶር አቢይና የለውጥ ሀይል። እንዳላችሁትም የትእግስት በርሜሎች ሞልተው አፍሰዋል።
8) የእስክንድር አቀጣጣይነት ለኢትዮጵያ ሀገር መፍረስ ይረዳል እንጂ የፖለቲካ ፋይዳ አይኖርም::የዘመነ ወያኔ ነብርነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በአቢይና ታከለ ላይ አድማ አይሉት መውረግረግ በውስኪ  ፍላት ለሚወራጩ ወያኔዎቹንና አክራሪዎቹን ያስፈግግ ይሆናል ለጊዜው። ምነው አስተዋይ ባለቤቱ እንኳ ብትነግረው? እኛስ መከረኛ ወገንተኛ ተብለን ተቸገርን  ። በበኩሌ የእስክንድር ጉዳይ ለፍርድ የማይመች ከባድ ነገር እየሆነብኝ ነው። አቶ ምናላቸው ስማቸው የተባለው የ 360 አውታር ቤተኛ በቅርቡ የጻፈው አይታችሁ ከሆነ ያስፈራል።  ሰውዬው ህሊናዬን ብሎ የዘረገፈውን ጉድ ሰው ሲነጋገርበት አላየሁም። ከድንጋጤ ይሁን ከምን እንደደሆነ ባይገባኝም አገር ወዳድ ተብዬው ዝም አለብኝ። ጭራሽ ደግሞ እነ አይጋ ፎረምና ልሣነ ዲጂታሎች ስለሱ መብት ሲቃጠሉ ሳየው የሆነ ነገር ወሮኛል። በበኩሌ በኢትዮጵያ ጉዳይ የጠላቴ ጠላትን ለፖለቲካ ፍጆታ ብዬ አብሬው አልቆምም። ሞት ምንድነው? ለምን አልሞተውም በክብር? ይህው ነው   አቶ ስማቸው በርግጥ “ኤርምያስንና አጃቢዎቹን” ነው እርቃን ያቆመው። አንድና አንድ ሁለት እንዲሉ በቅርብ እስክንድር ደግሞ በኤርምያስ ቡራኬ  ሸገር እንደገባ ሰምተናል። ምናልባት ተጠቅመውበትስ እንደሆነ ብዬም እሰጋለሁ ከልቤ።  እውነት አያርገው ብቻ። አቶ ስማቸውም ይቺን ተንፍሶ ዝም የለም። የሚያውቀውን መረጃ በሙሉ ለኢትዮጵያውያን አቅርቦ ኢትዮጵያን በጋራ እናድን ካላደረገ በስም ማጥፋት ሊያስከስስ ይችላል። ሌላው የአዲስ አበቤነት ትርጉም የለሽ ስብስብና ከታከለ ኡማ ጋር ግጭት አማራና ኦሮሞን ከመከፋፈል ውጪ ለኢትዮጵያ አንድነት የሚሰጠው ፋይዳ ሊታየኝ አይችልም።
9) Let’s close the Menelik chapter once  and for all : ከሸዋ ዖሮሞ የበለጠ ለምኒልክ የሚቀርብ አማራ አልነበረም:: ውሸት ነው?  ወጣቱ ምኒልክ በአፄ ቴዲ መቅደላ ታስሮ አፍትልኮ ሸዋ እንዲመለስ 12 ዖሮሞዎች ለምኒልክ ህይወታቸውን ገብረዋል:: ፀረ ኢትዮጵያ ወያኔ ፣ ሀገር አፍራሽና ዘራፊው ወያኔ፣  በ30 አመታት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ምኒልክን በማጠልሸቱ ዛሬ ወጣት ልጆቻችንን ክፉኛ በክሏል:: ይህ ያፈጠጠ ሀቅ ነው:: ስለሚኒልክ ምን ያልተባለስ አለ? እነዚህ ጨቅላዎችና ብሎም የአይምሮ የአዋቂ ጨቅላዎች ምኒሊክን ጠሉና ታሪካቸውን መለወጥ ከቶ አይችሉም ። በጥቁርነቱ የሚኮራ በምኒልክ ይደመማል። ካልወደዳቸው እንኳ ስለ እልፍ ጥቁር ህዝብ ክብር  ተብለው መከበር አለባቸው።  የሚያሳቅቀኝ ጥቁር አሜሪካዊ ባለበት ዩኒቨርሲቲ ሌክቸር እያደረክ አንዱ ወገን ጥቁር ስለ ምኒልክ ቆፍጣናነትና የአድዋ ድል ቢያቅራራ ምንሊክን ታሪክ አውቆአበድ አያውቄ ምን ጉድጓድ ልግባ አይል ይሆን በሀፍረት ወይስ የሀሰት ጡት ቆራጭነታቸውን ሊያስተምር ይሆን? ምናለ ተማሪው ሆኜ ጉዱን ሰምቼ አደባባይ ባወጣሁት ያስብላል። ግን እኮ ካልተከበሩም ግድ የለም ምግባራቸው ያስከብራቸዋል። በፈጣሪ አምሳል የተፈጠረን ሰው ግን “የምኒልክ ሰዎች” ናቸው ተብለው መግደልና ማዋከብ በጉርብትና አያኗንርም። ይህ የምኒልክ ጥላቻ ስር የሰደደው እነዚህ ወያኔዎች ብቅ ካሉ በሁዋላና ሆን ብለው እንዲጠሉ መርሀግብር ስለዘረጉ ብቻ ነው። እንዴት ነው? ዛሬ እኮ አይዶለም የተወለድነው። ብዙ የቋሚ ምስክሮች አለን በህይወት።የወያኔ ስነልቦና ምኒልክን ይጠላል:: ለምን? በአድዋ ጦርነት ብዙ ጀግኖች የነበሩንን ያህል አብዛኛው ባንዳ ሆኖ ከአካባቢያቸው  ስለተሰለፈ ይህ ብዙውን የህውሀት መሪዎችና ጀሌዎቻቸውን  የስነልቦና ቀውስ ፈጥሮባቸው ከኢትዮጵያዊነታቸው የበለጠ ወደ ንግድና ዘረፋ እዲገቡ ገፏፍቷቸው  ብዙ ችግር ፈጥረዋል በአገራችን: ዶላር ከተገኘ ኢትዮጵያ ብትቸበቸብ ደንታም የላቸውም:: ስንቱ ይሆን የሚያውቀው በሶማሊያ ጦርነት ጊዜ  ከጠላት ጋር እንዳበሩና ዛሬም ጥቅም ከተገኘ ኢትዮጵያን ለግብፅ ለመሸጥ ወደሗላ እንደማይሉ? እንናገረው እንጅ ወገኖች።
10) የብዙሀን ዝምታ ያስቆጫል። ህዝቡ በተለይም ወጣቱ በየመንደሩና ቀበሌው ከመንግስት ፖሊሶችና መከላከያ እየተቀናጀ ወላጆቹን፣ ደሀውን ሰፈርተኛና ጎረቤት አብሮ ይጠብቅ ። ማ ምን እንደሆነ ይታወቃል። እነ ጅቦቹ ባመጡት  የ 5  ለ  1 የክፉዎች ገመድ መልሶ እነሱኑ ወጥመድ መክተት። ፖሊሱ ካልታመነ መረጃና እርዳታ ስትሰጡ ፎቶና ቪዲዮ ማንሳት። ማ ማንን እንደሚከዳ መያዣ ይሆናል። በሀይማኖቱም ይሁን ፖለቲካው የምትወደውን የምትሳሳለትን ወገን ሊያጠፋ ሲመጣ ወይም በደሀ አቅም የተገነባን ተቋም ሊያጠፋልህ ሲመጣ አስቀድመህ ተዘጋጅተሀልና ፈጥነህ ከመከላከያና ፖሊስ ተቀናጅ። የየሰፈሩ ወጣት አቅራቢያው ካለው የመንግስት ሀይል በየተጠሪው ይተዋወቅ። ክፉ ወሬ እንኳ (፣የውሃ መመረዝን ልብ ይሏል) ሲሰማ በቅጽበት እነዛን መሰሪዎች መቀፍደድ ይቻላል። እንደው እቤት ተኝቶ መንግስትን ሳንረዳና ሁሉም የበኩሉን ሳይወጣ መንግስት በየስርቻው ሳቦታጁን ሁሉ እየበጣጠሰ ብቻውን ደሀውን ወገን ሊታደግ ከቶ አይችልም። ሁሉም ይተባበር ለማለት ነው። ለየልን እኮ ወገኖች። የሀጫሉ ህልፈት እንዲለይልን አደረገው። ይህ ብርቅዬ ወንዳታ በህልፈቱም ምናልባት ወጣቱን ያጀግንልን ይሆናል።
ማጠቃለያ!
የተከበራችሁ የዖሮማራ ክልል አስተዳዳሪዎች!
ዋናው መልእክቴ በዚህ ጀግና ወጣት፣ ገና ጨቅላ ህጻናቱንና አራስ ባለቤቱን አቅጣጫ ሳያስቀምጥላቸው በግፍ ለተገደለው ልጆችን የምትበቀሉለት በመናበብና አብሮ በመስራት ነው ለኢትዮጵያችን። የምትበቀሉት ደግሞ እንደ ምንደኞቹ ነፍስ በማጥፋት፣ ንብረታቸውን በማውደም፣ እሴቶቻቸውን በማጥፋት ሳይሆን የሁለቱን ታላላቅ ህዝቦች የጥንት አንድነትና እጅግ የተጠላለፈን ማንነት አደባባይ በማጉላትና የየቤቶቻችሁን ጣራና ግድግዳ በማጠባበቅ ነው። ፕሮፖጋንዳቸውን አትለፉ። በየቀኑ ካስፈለገም በየሰአቱ የሚያመክን ግብረሀል ከህዝቡ፣ አገር ወዳድ ምሁራን፣ አባቶችና እናቶች፣ እህቶችና ወንድሞች ማቋቋም። አቶ ንጉሱ ተመችቶኛል። ያቀናጀውና በስሩ ደጀን ይሁኑለት። ጥሎ የማይጥላት ፈጣሪ ኢትዮጵያ ከዚህ በአሸናፊነት ትወጣዋለች። የጥቂት ጊዜ ጉዳይ ነው። አባይ  ሲሞላ፣ ሁሉ ይረግባል (እስከ ዘፈኑስ አባዬ ሞላልሽ፣ ያሰብሺው ሆነልሽም አይደል?)። በነገራችን ላይ ያ በተለየ መንገድ አባይ ከሚለማ ሲናይ ትልማ ያለውን ክፉ አውሬ አደራ በእንክብካቤ ያዙት። አባይ ለከርሞ መብራት ሲያፈነጥቅ ጉሮሮውን ይዞ ሪቫን እንዲቆርጥ አድርጎ “ይህው እንዲህ ነን የኢትዮጵያ ልጆች” እንድንል ያብቃን። አሜን።
በመጨረሻም ማስጠንቀቅያ!
ካርታው ለጊዜው በአማራውና ዖሮሞው ስለከሸፈ፣ የትግራይ ብርቅዬ ተቃዋሚ ወጣቶችንም ይተናኮሉና “ይህው ጉደኛው መንግስት ለትግራዋይም አይመለስም ” ብለው የፈረደበትን ከ ሀምሳ አመት በላይ የሚያምሱትን “የራሳቸውን” ወገን ከመተናኮል አያርፉምና ጥበቃ አርጉላቸው። ይህው ነው። ስለ አነበባችሁኝ አስቀድሜ አመሰግናለሁ።
አባዊርቱ ነኝ
ከአገር ፍቅር አምባ

8 Comments

 1. Wirtu: If you really care about Ethiopia, you have to denounce the crimes Takele Uma commits on poor and helpless Addis Ababans. I believe this guy is a clandestine oneg/shene leader. Instead of calling a spade a spade, you are trying to blame Eskinder the great, an honest and God-fearing Ethiopian who always stands for Ethiopia and Ethiopians. However, you tried to relate Eskew to Anti-Ethiopians. What a crime!!!!! This is not Eskew`s personality.

 2. “ለሀጫሉ የዘረገፍከው እምባ ልብ ይሰብራል”!! ሃሃ!ሃሃ1ሃሃ! አይኑን በጨው ታጥቦ የአዞ እንባ እየፈሰሰ ፎቶ ሲነሳ እንኳ አይገባህም!! ዐእምሮ አይገዛ!!
  “ከአማራ ወገኖቻችሁ ጋር በጥልቀት ተወያዩ፣ ተናበቡም” / “የሸኔ አገልጋዮችን (ለኦሮሞ የሚቆረቆሩትን) ከድርጅትህ አፅዳ” > ገብቶናል! ወገንተኝነታችሁ ለማን እንደሆነ አሁን ግልጽ አደረከው!
  “ዶክተር ዐቢይ ባንዳዎች የሚል ቃል ደጋግሞ ተጠቅሟል” > የአምባገነኑ መንግስቱ ሃ/ማሪያምን “የአረብ ቅጥረኛ” የሚለውን ቃል ላለመጠቀም ብሎ ነው፣ ጊዜ ከሰጠነው ይጠቀምባታል! “ታላቁ መሪያችን” ካላንተ ኢትዮጵያ አትኖርም ብላችሁ ልትሰግዱለት ተዘጋጅታችኋል! አምባ ገነን የሚፈጠረው እንዲህ ነው። ጀሌው ግን እሱ የሚናገራቸውን ዝባዝንኬ እያስተጋባ እንደበግ መከተል ነው!
  “የእናት አገር ጉዳይ ከህጎች አናት በላይ ነው” > ህግ ከሌለ “እናት ሃገር” የምትላት እንደማትኖር ግን ሊገባህ አይችልም፣ በግ ነህና! ሃገሪቱን እዚህ ቅርቃር ዉስጥ የከተቷት ከህግ በላይ የሆኑ ነፍሰገዳዮች እንደሆኑ ሊታይህ አይችልም!
  አልቀጥልም ።
  እጅግ በጣም የሚያሳዝነው፣ የህግን ምንነት እና ህገመንግስታዊነት የማይገባቸው ጨቅላ ዐእምሮ የተሸከሙ አዛውንት፣ በስሜታዊነት ተነሳስተው የአምባገነኖችን ጭፍጨፋ እና ቅፍደዳ ሲያበረታቱ ማየትና መስማት ነው! ይህችን ጽሁፍህን ለታሪክ አስቀምጣለሁ። ኖረህ ላታየው ትችላለህ፣ ቀጣይ ትውልድ ካለ ምናልባት ትምህርት ያገኝበት ይሆናል።

  • እንዲሁ በቅዥት ትኖራለህ ክዚያም ትሞታለህ ኢትዮጵይ ፈርሳ ኦሮሚያ ሀገር እትሆንም:: እናንተ ንፁህ ኦሮሞዎች ግፋ ቢል 29% አትሆኑም:: የእናንተ ቦኮሀራም ጨፍጫፊዎች ማንነታችሁን አጋልጧል አማራውን ጉራጌውን ወዘተ ጭፍጭፋችሁ አትዘልቁትም:: ኢትዮጵይዊ ሁሉ ይፋረዳችሗል:: የንፁሀን ደም ከንቱ አይቀርም:: 40 አመታት ከማንም የታጠቀ ህይል ይላሸነፋችሁ እንዲት ኮረብታ ያልያዛችሁ ድኩማን አሸባርዎች:: እኔ አንተን ብሆን ኢትዮጵያ ሳይት መጥቼ ቅርሻቴን አልዘራም አሁንም ስልጣኔ እንደራቀህ ነው

   • በየአመቱ በአስር ሺህዎች በግፍ የሚጨፈጨፉት ኦሮሞዎች ንጹሃን / ኢትዮጵያውያን አይደሉም ማለትህ ነው?? ያስ ለምን እንዲህ አያስቆጭህም?? የቅማንት ቤተሰብን ከነቤቱ ሲታጋዩ ፣ የጉሙዝ ህጻናት እና አሮጊቶችን በጅምላ ስትቀሉ ቦኮሀራምነት አይደለም?? ሌላው ላይ ጣት ቀስረህ ሲትፎክር የሚያመልጥህን አታስተውል!! “እውነቱ” ይላል ደግሞ ስሙን፣ hypcrite!
    ኢትዮጵያ ፈርሳለች እኮ! በ130 አመታት *ሃገር* መሆን ያልቻለች፣ በጠብመንጃ ብቻ የሚትጠበቅ ግዛት ሃገር አይደለችም፣ እስር ቤት እንጂ፣ የብሄረሰቦች እስርቤት! ጠብመንጃው ዞር ሲል ወይም ሁሉም እኩል ሲታጠቅ፣ ያው ወደ ቅድመ ምንልክ እንመለሳለን! እናንተ ወደ ሽፍታ፣ እኛ ወደ Gadaa ባህል።

 3. @Meseret, don’t get me wrong, I am only deducing from ato Simachew’s allegations. I am not directly blaming him per se; I am only worried in the event “eskew” got unbecomingly entangled in some dubious anti-ethiopian web, albeit very unknowingly. Look, I have no doubt he is a great ethiopian who had been preoccupied with grand ethiopian projects and paid dearly in the process.  unfortunately at this time , he comes across as a confused person who is fighting for little condominiums while the mighty “Ethiopian chateau “ is on fire.  Trust me,  TPLF wants Eskinder at this time for their “Addis project” and  they can easily get into his very caring nature. That is why i am spooked following Simachew’s exposé against  gang of 360’s.  With regard to Takele’s fate,  let the people of Addis decide his future at the upcoming election. Short of that, Eskindir will unwillingly exacerbate divisions among the two massive nations and in that  process help weyane – I simply can’t accept and allow that. Not after Simachew’s exposé. 
    እኛ በኮንዶሚኒየም ስንጣላ ሀገር እያጣን ነው:: እስክንድር ከፈለገ ወደጋዜጠኝነቱ ይመለስ። የእሱ ግጭትና አቀጣጣይ ፖለቲካ ሀገርን አያድንም:: ወጣቱ ዖሮሞ አማራው ወገኑን  አጥብቆ እንዲጠላ አጀንዳ ተቀርጾ፣ በጀት ተመድቦለት 27 አመታት ተሰርቶበታል:: እንደ እስክንድር ያሉ  የዛሬውን ጀግና መባል የሚማርካቸው በጀብደኝነት ይህን ወያኔ የቀረፀውን የኦሮሞ ወጣት የባሰ እንዲቀጣጠል ቤንዚን ከማርከፍከፍ ይልቅ ረጋ ብለው  ውሀ ቢከልሱበት ለሀገር ግንባታ ይበጃል:: ሰደዱንም እሣት ያመክናል። አሁን ማን ይሙት ታከለ ኦሮሞ ባይሆንና አርከበ ተመልሶ ቢሆን አዳሜ ይንጫጫ ነበር? ምናለ ባንሞኛኝ። 

 4. ማሳሰቢያ ለኢትዮጵያውያን!

  ዖሮሞ መስለው፣ የዖሮሞን ጠረን ሸተው በስመዖሮሞ ወገኖቻችን እየጨረሱ ያሉት ህውሀትና የህውሀት ቅጥረኞች ghost oromos ናቸው። ለዚህ ማስረጃው ከታረዱት ውስጥ የሸዋ ክርስትያን ዖሮሞዎች አሉበትና እያስተዋላችሁ።

  @Abba Caala, አንተ የሰው ጭራቅ ምንደኛ ወያኔ አንድ ሰሞን ዖሮሞ መስለኸኝ ክፉኛ አጃጅለህኝ ነበር። ለነገሩ በአደባባይ የሚመጣውን እሣት መቀሌ ስታቦኩና ስትጋግሩ የሰነበታችሁትን እንደ ትንቢትም ከአመት በፊት ስትናገር ነበር። መች አመንህ እንጅ ። ወደሁዋላ ሄዶ ፋይልህን ላገላበጠ ብዙ ጉድ ይገኝበታል። ደግሞ የኔን ፋይል ለታሪክ ቢቀመጥ አልክ? የኔውስ ቅንጣት የሚያሳፍር የለብኝም። እንኳን በዚህ እድሜ በልጅነቴም አብሮነትን እንጅ መጠፋፋትን አልነበረም ከመልካም እርጎና ጨጨብሣ ጋር ተመግቤ ያደኩት። እንዳንተ እነ ቢስማርክንና ናፖሌዮን ቦናፓርትን ሳይሆን፣ የምኒልክንና እናንተ እንደውጋት የምትጠሏቸውን እነ ጎበናን፣ በኛው ዘመን ደግሞ ጃገማን እያደነቅን ነው የጎለመስነው። ያንተው ያበቃልኝ RIP ETHIOPIA ካልከኝ በሁዋላ ነው።  የናንተው ግብአተመሬት ይፈጸም እንደሆነ እንጅ ኢትዮጵያስ ገና ታብባለች በልጆቿ። ድንገት የዖሮሞ ደም ካለብህ (እንደሌለህ ልቤ ይነግረኛል አንት ምንደኛ ወያኔ)  ደግሞ እነአቢይ በጭንቅላት ስለበለጧችሁ ተቃጥላችሁ ልትሞቱ ነው ምድረ ማፈርያ ዶክተር ተብዬ ገልቱዎች። የተማረ ክቡር ገላን በልቶ አያቅራራም የአይሲስ (አልሲሲ) ውላጅ ካልተሆነ በቀር። ህጻናትን በገጀራ አስቆራርጦ አይደነፋም። ቦቅባቆች። ያውም በውድቅት። ፊትለፊት በቀን ብትመጡባቸው ባላቸው መሳርያ የማይከላከል ወላጅ አይኖርም ነበር። አዝናለሁ። ለመሆኑ እንበልና የሸኔና ዖነግን ደም ለመበቀል ከሆነ (አንድ የዞረበት አናንያ ሶሪ የሚሉት እንዳስቀመጠው) እንደው በፈጣሪ የአርሲ ይሁን ዝዋይ ድሃው “አበሻ” የምትሏቸው ዜጎች ምን በደሉ? ለምን የዖሮምያን ወይም ፌዴራል መከላከያውን ብቻ እየመረጣችሁ አትጨርሱም ነበር? ለምን መሰለህ? የመጨረሻ በጥራቆች ስለ ሆናችሁ ነው። ወንድ ልትሆኑ ነው በዚህ? ከእናንተ ተደምሬ ዖሮሞ ልሆን? ምን የሚሉት ፖለቲካዊ ሳይሆን አጋንንታዊ ስቴትመንት ነው ህጻናትን በማረድ እባክህ? ዖሮሞ ከሆንክ የጌቶችህን ወያኔዎች ጉዳይ ብቻ ነው ያስፈጸምከው። ይህው ነው። ለነገሩ ሃጫሉን ደፍታችሁ አበሻ ለምትሉት ምንስ ደንታ ይሰጣችሁዋል። ንቄ ትቼህ ነበር። የዚህ የሃጫሉ ጉዳይ ከሰየፋችሁት በሁዋላ እንቅልፍ ስለነሳኝ ነው። አንት ሟርተኛ ዖሮሞ “ሰፉ” ያውቃል። ጥጃ ስትሞት የሚያነባ ፍጥረት ነው። አንተና ህውሀቶች ምንደኞች ልጆቻችሁም ቢያልቁ በንዴት ወደመጠጥ/ጫት ቤት  ትሄዱ ይሆናል እንጅ ሀዘን ምን እንደሆነ ዬት ታውቁና? በሺመልስ እምባ የምታሾፍ ጉድ? ያውም ለጓደኛው ሀጫሉ? እረ የማውቃቸው አማራ ጎረቤቶቼ ከሺመልስ በላይ አምረው አልቅሰዋል ዖሮሚፋን ብትግታቸው የማያውቁት ዜጎች። አይ ጨካኝ! አይ አውሬ! እስቲ የሀጫሉ የግፍ አገዳደል እንደዛ አይነት ደፋርና ቆራጥ ወንዳታ መቀጠፍ እንደምን አይቆጭ ሰው ሆኖ ለተፈጠረ ፍጡር ። ለካ ያንተ አይነቱን ምንደኛ ነው Oromo ghost writers  ያለችው ክብርት አዳነች አቤቤ። ቀላል አቃቤህግ አይደለችም። ጉድ ልታፈላባችሁ ነው። ጥቂት ታገሳት ብቻ!!! 

 5. ምድረ ምንደኛ፣ ቅጥረኛ፣ ነፍሰገዳይ የአውሬ ውላጆች አሁን መልካም ዜና እናንተን ግን ሲያቃዥ ወደጫትና ሺሻ ቤት የሚሰዳችሁን ዜና ይዤላችሁ መጥቻለሁ። ይሰማል???

  የአባይ ሙሌት ተጀመረ!!!!!! እንኳን ደስ ያለን ወገኖች!! እንኳን አፈራችሁ ምንደኞች!

  አቢይ አህመድ የዋዛ መስሏችሁዋል እናንት በጥራቆች፣ ። እናንተ ጨለማን ተገን አርጋችሁ የህጻናትን አከላት ስትበልቱ የኢትዮጵያ ልጆች ወገባቸውን አጥብቀው ይቀዱት ጀመር! የኢትዮጵያ አምላክ አያሸልብም የሚባለው ለዚህ ነው። ሰማህ አንጋች አባ ጫላ? አቤት አልሲሲ ሲቆጣችሁ በደም ፍላት ስንቶች ትሆኑ ኪኒን ስትውጡ የምታድሩት!? አይ ኢትዮጵያ! ከዛሬ በሁዋላ ብንሞትም አይቆጭም። ይህው ነው ምድረ ባንዳ ሁላ!

  ወጥር አቢይ! ሽመልስ! ተመስገን!

  የፍርዱን ነገር ቶሎ ታድያ! የፍርድ ሠረገላ እስከወሰዳችሁ——-

  እመቤት አዳነች አቤቤ በርቺልን የኛ ጀግና!

  በሙሌቱ መጀመር ብንደሰትም ሸረሪቷ አሁንም አልተያዘችም። መዘናጋት እንዳይኖር አደራ!
  ሁሉም ጓሮውን ያጽዳ። በየቀኑ መረጃ አቀብሉ ለህዝባችን። ሀዘን ባይሆን የሙሌቱ ጉዳይ ያስፎክር ነበር። ይዘግይ ያልኩበትን ቀን ነው የቆጨኝ። ወገን የሆነ ሁሉ አይደለም እርስ በራስ ወንዞቻችንና ደኖቻችንን፣ የዱር እንስሳትን ሳይቀር በቁራኛ ይጠብቅ። አጥፍቶ ጠፊን ማመን ቀብሮ ነውና። ይህው ነው። በዚህ አጋጣሚ ያረፈባችሁን ስትሬስ ሁሉ ተቋቁማችሁ ለዚህ አባይ ጉዳይ መከራ ስትበሉ የሰነበታችሁ፣ በግልጽም በስውርም፣ ከውጭም ከውስጥም ከቴክኒክ ሙያተኞች እስከ ዳያስፖራ አማካሪዎች የኢትዮጵያ አምላክ ውለታችሁን ይክፈለው። ወያኔዎች በሽታው ሳይጨርሳችሁ በነፍስ አቆይቶ የአባይን ፍሬ ስንቃመስ በአይን ለማየት አብቅቷችሁ በነጋታው በብስጭት አይጨርሳችሁ (እንደናንተ ክፉ አልመኝም)።

 6. “አንድ ሰሞን ዖሮሞ መስለኸኝ ክፉኛ አጃጅለህኝ ነበር።” no! ሁሌም እንደተጃጃልክ ነህ!
  “የኔውስ ቅንጣት የሚያሳፍር የለብኝም።” ሰው ሃፍረት የሚኖረው እኮ ህሊና ሲኖረው አይደል?
  “ከመልካም እርጎና ጨጨብሣ ጋር ተመግቤ ያደኩት” > አዎ፣ ነፍጠኛ መቼም ለሆዱ ነው የሚሞተው!
  “እነ ቢስማርክንና ናፖሌዮን ቦናፓርትን” በስም መጥራት መቻልህም ትልቅ ነገር ነው። እንዳልከው የተማርከው ግን ከምንልክና ከጎበና ነው > ክህደት፣ ጭካኔን እና መግደልን።
  “እነአቢይ በጭንቅላት ስለበለጧችሁ …” ሃሃ!ሃሃ!ሃሃ! ያንተ ፌክ ዶክተር አቢይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደጅ እንኳ አልደረሰም! አልሰማህም እንዴ እንደሊስትሮ ዶክተር ፕሮፈሰሮችን ሲያንቋሽሽ? ይልቁንም እንዴት ኮሎኔል እንደተባለ ጠይቅ! ከተራ ወታደርነት ኮሎኔል ለመድረስ ስንት አመት ይፈጃል?
  “ድንገት የዖሮሞ ደም ካለብህ …” > ኦሮሞነት በድንገት አይደለም የሚመጣው! ከኦሮሞ አባት/እናት በመወለድ እንጂ!
  “ህጻናትን በገጀራ አስቆራርጦ …” እንደሚታደርጉት ጭንቅላታቸውን በስናይፐር መበተኑ ጨካኝ አያሰኝም ነው ነገሩ?
  “ዖሮሞ ጥጃ ስትሞት የሚያነባ ፍጥረት ነው።” > “ፍጥረት” አይደለም፣ የሰው ልጅ ነው! “ሰፉ” ያውቃል። “safuu” ነሳችሁት እናንተ!
  “እረ የማውቃቸው አማራ ጎረቤቶቼ ከሺመልስ በላይ አምረው አልቅሰዋል”። የእነርሱ እውነተኛ እንባ ከዐዞ እንባ የተሻለ ስለሆነ እኮ ነው! እነርሱ አልገደሉት!
  “ከእናንተ ተደምሬ ዖሮሞ ልሆን?” > ነፍጠኛነት አይበቃህም? ኦሮሞ ለመሆን ግን 9 የትውልድ ሃረግ ከዬት አምጥተህ ትቆጥራለህ? *abbaa koo’yyuu hin beeku, akaakayyuu na qorattaa? jette qamaleen*. ወይስ ኦሮሞን ለመጨረስ እየዛትክ “moggaasaa” ዉሰዱኝ ልትል ነው?
  “የአባይ ሙሌት ተጀመረ!!!!!!” እንኳን ደስ ያለህ! ግና ለምኑ? ባለሃብትነቱ እኮ የአረቦች ነው፣ ተሽጦ ያለቀውን?

  “ክብርት አዳነች አቤቤ ቀላል አቃቤህግ አይደለችም። ጉድ ልታፈላባችሁ ነው!” ጉዳችን! ግና ህግ ሳታውቅ እንዴት አቃቤህግ ሆነች? Oh sorry! በአናንተ ፒፒ ቤት እውቀት በወረቀት ላይ እንጂ አንጎል ዉስጥ የለም!! Nagaa hin qabduu, Nagaatti!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.