አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ ! – ያሬድ በላይነህ

የሰሞኑ የሃጫሉ ሞት ያስከተለው የሰው ህይወትና የንብረት ጥፋት የመንግስት ልፍስፍስነት ውጤት ነው።ሃገር ለማፍረስ ሆን ተብሎ በወያኔ በጉልበት የተጫነ የጉልበት ሰነድ ህገመንግስት ብለህ ይዘህ ሃገር ለዘለቄታው በሰላም ውላ ታድራለች ማለት ዘበት ነው።ድሮም ወያኔ በጉልበት ጨፍልቆ እየገደለና እስርቤት እያጎረ እያኮላሸና ጥፍርን እየነቀለ በፍርሃት አርዶ ገዛ እንጂ ህግ ተከብሮና ፍትህ ሰፍኖ አልነበረም።
ዛሬ ላይ ለውጥ አመጣለሁ ያለው የዶ/ር አብይ መንግስት የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት የተሻለ ቢሰራም በብብቱ አቅፎ የያዛቸው ተሻጋሪ ችግሮች ቀፍደው ይዘው ወደፊት እንዳይራመድ ጉልበቱን አርደውታል።
Bekaበተለይም ኦነግን የመሰለ ከነሻጋታ ዘረኛ አስተሳሰቡ ያረጀ ዘረኛና ከፋፋይ ድርጅት በሰላም ሃገር ጦር ሲያዘምት በወገነተኝነት ስሜት በጊዜ አለማረሙ ዋጋ አስከፍሎታል። እንደጃዋር አይነቱን ጽንፈኛ ሚዲያ አስታጥቆ እነዳሻው የዘረኝነት ትፋቱን በህዝብ ላይ እንዲተፋ መፍቀዱ የዛሬውን መንገድ ድጥና ጨለማ አድርጎበታል።
ትናንት ንፁሃን በዘራቸው እየተለቀሙ ሲቀሉና ንብረታቸው ወድሞ ሃገር የፍትህ ያለ ስትል ለወንጀለኞች ሽፋን በመስጠት ፍትህ በአደባባይ እንድትረገጥ በዝምታ የፈቀደው መንግስት በሌላው ደም ግብር በቸልታው ተንከባክቦ ያሳደጋቸው እፉኝቶች ዛሬ ላይ ከዘንዶ ገዝፈው አንገቱ ላይ ተጠምጥመው ትንፋሽ እየነሱት ነው።”እባብን ለመደ ብለህ በኪስህ አትይዘውም”እንደሚባል በዘር ሃብሾ ተለክፎ ያበደንም ዘረኛ አባብለህና በነፃነት ስም ተማጽነህ መረዙን አታስተፋውም።
የንፁሃንን ደም እየገበሩ በፖለቲካ አገም ጠቀም የዘር ከረጢት ውስጥ ሆኖ ዘረኛን ወገኔ ዘመዴ እያሉ እያስታመሙ መበልፀግም ሆነ መሻገር የሚባል ፌዝ የለም መንግስት ያለምንም ማድበስበስ የዘር ጥቃትን በፊትለፊት ተቃውሞ ከፍትህ ጋር መቆም አለበት።እሳቱ ወደራሱ ስለመጣ ሳይሆን የአንድ ዜጋም ቢሆን ደም በከንቱ ሲፈስ ሬሳ መቁጠር ሳይሆን ወንንጀለኞችን በፍርድ አደባባይ አቅርቦ ቀጥቶ ሌላውን ማስተማር ማስጠንቀቅ አለበት።ይህ ካልሆነ ደም በከንቱ ፈሶ አይቀርም ፍርድ ያመጣል ያ ፍርድ ደሞ ደም አፍሳሹን ብቻ ሳይሆን በዝምታው ለወንጀለኛው ሽፋን የሰጠውንም ጊዜውን ጠብቆ ይቀስፋል።መንግስት ከዚህ የንፁሃን ደም ፍርድ ለማምለጥና ተቀስፎ ላለመሞት ዛሬም የሚገባውን የማይገባውንም እስርቤት ከቶ አባይ ሚዛኑን እየወዘወዝ እንደተለመደው በዘረኞች እግር ስር መውተፍተፉን ትቶ ጨክኖ ህግን ማስከበር ይጠበቅበታል።ይህ ካልሆነ እነደብሂሉ”አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ”እንደሚባለው ይሆንና የጥፋት አዙሪቱ ቀጥሎ ዳፋው ራሱንም ይዞት ገደል ይገባል።ይህ ሳይሆን የንፁሃን ደም በአደባባይ ፍትህ ያግኝ መንግስትም ቤተመንግስቱን ብቻ ሳይሆን ህዝቡንም ከጥፋት ይጠብቅ።\
እግዚአብሔር ሃገራችንን በምህረቱ ያስባት!
ያሬድ በላይነህ

1 Comment

  1. There are no human beings in Ethiopia who support the current constitution more than Prosperity Party. TPLF just wants article 39 to remain , besides that the other parts in the constitution about justice and crimes or ethnic divisions , TPLF does not want it. TPLF knows Fenkil will not let it remain to own Tigrai that is why TPLF wants to make s comeback to Addis Ababa with a new national party under a new constitution , just to look after it’s investments in Ethiopia.

    Even TPLF doesn’t care about the constitution as Prosperity Party does. Keeping the current ethnic constitution to continue shows the strength of the current government , not it’s weakness.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.