የትግራይ ቴሌቪዥን እና ድምጸ ወያኔ ስርጭታቸው ተቋርጧል

51755462 303የትግራይ ክልላዊ መንግስት ይገለገልባቸው የነበሩ የትግራይ ቴሌቪዥን እና ድምጸ ወያኔ ስርጭታቸው ተቋርጧል። ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ብሔርን ከብሔር ለማጋጨት እያገለገሉ ነው ባላቸው ሶስት የቴሌቪዥን ጣብያዎች ላይ ምርመራ መጀመሩን አስታውቆ ነበር።

የትግራይ ክልላዊ መንግስት ይገለገልባቸው የነበሩ የትግራይ ቴሌቪዥን እና ድምጸ ወያኔ ሙሉ በሙሉ  ከስርጭት መውጣታቸውን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን  ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር አሁን ወደ ስርጭት ከመግባታችን በፊት ነግሮናል ። ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ብሔርን ከብሔር ለማጋጨት እያገለገሉ ነው ባላቸው ሶስት የቴሌቪዥን ጣብያዎች ላይ ምርመራ መጀመሩን አስታውቆ ነበር። እነዚህም የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ኦ ኤም ኤን ፣ አስራት ቴሌቪዥን እና ድምጸ ወያኔ ነበሩ። የአሁኑ የትግራይ ቴሌቪዥንን ጨምሮ የድምጸ ወያኔ ከስርጭት መውጣት ቀደም ሲል ከተሰጠው ማስጠንቀቂያ ጋር የተያያዘ ይሁን አይሁን ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

አዜብ ታደሰ

DW

https://www.facebook.com/AdebabayMedia/videos/725213601383603

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.