የአርቲስት ሃጫሉን አሰቃቂ ግድያ ተከትሎ አገራችን በድጋሚ አደገኛ የሆነ ፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ ትገኛለች

Achaluበርግጥም ይሄንን ሰብአዊ ርህራሄ የጎደለው ወንጀል ያቀዱና የፈጸሙ ግለሰቦችም ይሁኑ ቡድኖች ለማሳካት ያለሙለት ከዚህም የከፋ ዘር ተኮር እልቂትና መጨራረስ እንዲሁም አገራችንን መበታተንና ማውደም እንደ ነበር ግልጽ ነው።
መንግስት ህግና ስርአት የማስከበር አገርና ህዝብን ከህልውና አደጋ የመታደግ ሃላፊነት ያለበት ቢሆንም የተፈጠረው ፖለቱካዊ ቀውስና ግርግር ተባብሶ ለኢትዮጵያ ህዝብ የውስጥና የውጭ ታሪካዊ ጠላቶች ምቹ የሆነ አጋጣሚ እንዳይፈጠር ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባዋል። መንግስት በተለይ በአንዳንድ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የዘር ጥቃት እየተፈጸመባቸው የሚገደሉ፣ የአካልና ስነልቦናዊ ጉዳት እየደረሰባቸውና ንብረታቸው እየወደመባቸው ያሉ ዜጎቻችንን ለመታደግ ፈጥኖ መንቀሳቀስና ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር ህገወጦችን በህግ እንዲዳኙ ማድረግ ይገባዋል።
ይሁንና የኢትዮጵያ ህዝብ ታግሎ ወዳስወገደው አይነት ስርአት እንዳንመለስ የጅምላ እስርና ወከባ በአስቸኳይ እንድዲቆም ማድረግ ይገባዋል። ሰሞኑን የታሰሩ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ መሪዎችና አክቲቪስቶች ጉዳያቸው እየተጣራ በወንጀልና ሁከት ተሳትፎ የሌላቸውን ንጹሃን ዜጎች ሁሉ ባስቸኳይ ይፈቱ።
በዚህም አጋጣሚ የተፈጠረውን ፖለቲካዊ ቀውስ በመጠቀም ሃላፊነትና ሰብአዊነት የጎደለው የዘር ፍጅት ቅስቀሳና የጥላቻ ስብከት ከተለያዩ አገራት በማህበራዊ ሚድያና በመገናኛ ብዙሃን ወደ ኢትዮጵያ ጥሪ የሚያስተላልፉ ሰብአዊነት የጎደላቸውን ግለሰቦች በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ ለማጋለጥና ለፍትህ አካላት በመጠቆም ሃላፊነት የሚሰማው ዜጋ ሁሉ በተለያዩ የአለማችን ከተሞች በተቀናጀ መልኩ እንስቃሴ ማድረግ ከምን ጊዜውም በላይ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው።
በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ለኢትዮጵያ ህዝብ ታሪካዊ ጠላት ለሆነው ለወኔ ድንጋይ የሚያቀብሉም ነገሮችን ከማጋጋል ይልቅ የተፈጠረውን ችግር ለማርገብ እንድተተጉ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
ቸሩና ሃያሉ ፈጣሪ ኢትዮጵያና ህዝቦቿን በቸርነቱ ይጠብቅልን!
ተጨማሪ ያንብቡ:  ከዓመት በዓሉ ጋር ተያይዞ የሸቀጦች ዋጋ እየናረ ነው

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.