“ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን ይልቀቁ” – ሄኖክ ገቢሳ

abiy 5 “ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን ይልቀቁ”  ሄኖክ ገቢሳ

የኦሮሞ ተቃውሞ አራማጆች የድምፃዊ ሐጫሉ ሑንዴሳ ግድያ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ፣ ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአፋጣኝ ሥልጣን እንዲለቁ እንዲሁም የታሰሩ ፖለቲከኞች እንዲፈቱ ግፊት እያደረጉ ነው። በማኅበራዊ ድረ ገፆች የቀረቡት ሰባት ጥያቄዎች ናቸው። መልስ ካልተሰጠ በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ይሻሉ

ድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ተገድሎ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባን ጨምሮ 35 ሰዎች ከታሰሩ በኋላ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የተቃውሞ ዘመቻ በመካሔድ ላይ ይገኛል። ፌስቡክ እና ትዊተርን በመሳሰሉ ማኅበራዊ ድረ ገፆች በሚካሔደው ዘመቻ ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል የድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ፣ ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአፋጣኝ ሥልጣን እንዲለቁ፣ የዘፈቀደ ግድያዎች ይቁሙ የሚሉት ይገኙበታል።

ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፤ በሚቀጥሉት አምስት ወራት ነጻ እና ፍትኃዊ ምርጫ እንዲካሔድ፤ የተቋረጠ የኢንተርኔት እና የመደበኛ ስልክ አገልግሎት ወደ ሥራ እንዲመለስ የሚሉ ጥያቄዎችም ቀርበዋል።

እነዚህ ጉዳዮች መልስ ካልተሰጣቸው በጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ላይ ዓለም አቀፍ ማዕቀብ እንዲጣልም ግፊት ያደርጋል። እሸቴ በቀለ ተቃውሞውን የሚያስተባብሩትን ዶክተር ሔኖክ ገቢሳን በስልክ አነጋግሯቸዋል።

እሸቴ በቀለ

ኂሩት መለሰ / DW

ሄኖክ ገቢሳ እና አባሮቹ

8 Comments

 1. በመጀመሪያ እነዚህ ገዳዮችና አስገዳዮች ተለቃቅመው ለፍርድ መቅረብ ይገባቸዋል:: ምንም የፖለቲካ ተሳትፎ የሌላቸውን በኦሮሚያ ኦሮሞ ያልሆኑ ወገኖችን ያስጨፈጨፉ በእነሱ ብሶም በኢትዮጵያ ላይ ተፅእኖ እንዲኖር ይጠይቃሉ:: losers!
  በሰለጠነው ሀገር እየኖሩ ስልጣኔ የራቃቸው የበታችነት ስሜት ያጠቃቸው መንጋዎች!

 2. መማር የሚያሳፍር ፣ ርካሽ፣ የገለሞታ ስራ ፣ ክብር የለሽ መሆኑን በጋቢሳ ትውልዶች ደጋግሜ ማየቴ ስለ ነሱ ተሸማቀኩ።
  ኣቀራረብህን እንኩዋን ለየት ለማረግ ያልቻልክ የጌታቸው ረዳ ቱልቱላ መሆንህ የበለጠ ናቁህ።
  ደግሞስ የኦሮሞን ህዝብ ንቀታችሁ ?? የእምዬን ወደ ኣብዬ ! Vulgar, barbarian.
  የናንተን ቅስቀሳ ሰምተው ለወያኔ ስናይፐር ሰለባ የሆኑት የኦሮሞ ወጣቶች እናቶች የደም ለቅሶ ይፋረዳችሁ።
  የታረዱ የንጹሃን ደም ይጮሀል፣ የቃዬልን ኑሮ ይስጣችሁ.
  ማፈሪያ።

 3. ጎበዝ ጊዜ አታባክኑ። ሃገር የለንም። የኦሮሞ የፓለቲካ እብዶች ልክ በ 60ዎቹ እንዳበድ ዛሬም ልብሳቸውን አለበሱም። ይገርማል። ሰው በዘሩ እየተለየ ቤቱ ንብረቱ የሚቃጠልባት ኦሮሚያ ክልል ነው ስለ ሰው ልጆች ነጻነት የሚታገለው? ዶ/ር አብይ ይውረድ የሚሉት ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ልክ እንደ ወያኔና ሻቢያ ስለሚጠሉ ብቻ ነው። ዶ/ር አብይን እኔ አላውቀውም። ግን በሃገሪቱ ታሪክ ውስጥ እስረኞችን የፈታ፤ በውጭና በውስጥ የተበተኑ ወገኖችን ለማስታረቅና ለማሰባሰብ ሙከራ ያደረገ ከዶ/ር አብይ በፊት ማንም አልነበረም። ሰው በዘሩና በሚናገረው ቋንቋ ሳይሆን በሥራው ብቻ የሚመዘንባት ያቺ ሃገር ትናፍቀኛለች። የክልል ፓለቲካን የተቃመሱት እነዚህ የንጉሱና የደርግ ያለዚያም የወያኔ ትራፊዎች ከሃገር ውጭ በየስርቻው ተሰግስገው ሃገርን ማተራመስና የድሃ ህዝባችን ደም ማፍሰስ የለመድት የፓለቲካ ዘዴ ነው። የኦሮሞ ህዝብ ስንት የፓለቲካ ድርጅት ነው ነጻ እናወጣሃለን የሚለው? ራሱ በድሎ ራሱ አለቀሰ እንዲሉ ሃጫሉን የገደለው ማን ነው? አምቦ ቀብሩ ላይ አጎቱንና ሌሎችን የገደሉት ራሳቸው በኦሮሞ ስም የሚንቀሳቀሱት አይደሉም እንዴ?
  ይብቃ የዘር ግጭት፤ እባካቹሁ አርፋቹሁ ተቀመጡና አንገታችሁ ሲቀላና ቤት ንብረታቹሁ ሲቃጥል ዝም በሉ የሚል የውስልትና ፓለቲካ ሊቆም ይገባል። በሃሳብ የሚስማሙ ሁሉ ራሳቸውን አድራጅተው ያልሞት ባይ ተጋዳይ በመሆን ንብረታቸውና ራሳቸውን መከላከል አለባቸው። በዘር በተሰመረ ሃገር ላይ የፌዴራልም ሆነ የክልል ፓሊስ ከዘሩና ከቋንቋው ዝንባሌ ውጭ ሆኖ ሰውን በስብዕና ዓይን በማየት በኩልነት አገልግሎት ይሰጣል ብሎ ማመን ሞኝነት ነው። ደም አፍሳሾች እንደ ተኩላ ብሄር ተኮር ጥቃት የሚያደርሱት ሆን ተብሎ በተጠና መልኩ እንጂ እንዲሁ በነሲብ አይደለም። ወስላታው የኦሮሞ ፓለቲከኛ ከሃገር ውጭ ራሱን እና ቤተሰቡን አስጠልሎ ” ኦሮሞ ለኦሮሞዎች ይሉናል” እውር ፓለቲካ። ዶ/ር አብይን ለማውረድ የሚደረገውም ጥረት ኦሮሚያን እንደ ሃገር ከመመስረትጋር ከተያያዘ የጭፍኖች እይታ የመነጨ ነው። በየስማቸው ጥግ ዶ/ር፤ ፕሮፌሰር/እንጂኒየር፤ ገለ መሌ በማለት እናውቅላችሁሃለን የሚሉን ተምረው የደነቆሩ ምንም ቢለፉ ምንም ህዝባችን ለይቶ አውቋቸዋል። እኔ የሚገርመኝ የኦሮሞ ህዝብ ሰላም ወዳድ ነው ይሉናል። ሰላም ከወደደ ሰው በጥይት ሲረሽን፤ ቤት ንብረቱ ሲቃጠልና ሲዘረፍ ምነው አንድ ላይ ግር ብሎ በመውጣት እንዲህ ያለ ነገር አንቀበልም አላለም? የጅምላ ፓለቲካ ውጤት ይህ ነው። በራስ አስቦ መኖርን ይቀማል። አሜሪካና አውሮፓ ተቀምጠው ያለምንም መረጃ ሃጫሉን የገደሉት አማራና ትግሬዎች ናቸው በተገኙበት ግደሏችው የሚሉ እብዶች በስሜት እንጂ በእውነት የማይመሩ ደመነፍሳዊ ጥርቅሞች ናቸው። ግን ገዳይም ተገዳይም ኦሮሞዎች ናቸው። የዶ/ር አብይ መንግሥት የሰራቸው ስህተቶች ብዙ ቢሆንም ጃዋር ተከብቤአለሁ በማለት 87 ሰዎችን እንዲገደሉ ካደረገ በህዋላ እርምጃ አለመወሰድ የልቡን መደንደን ጣራ ላይ አድርሶታል። የፓለቲካ ሳይንስ ተምሬአለሁ በማለት ለዘሩ የሚያቀነቅነው ይህ ደም አፍሳሽ ምንም ዓይነት የፓለቲካ ሳይንስ አብሮ በህብረት መኖርን የማያስተምር የለም። ግን መማር በዘሩና በቋንቋው መነጸር ብቻ ዓለምን ለሚመለከት እይታው እዚያው አፍንጫው ሥር ነው።
  በመጨረሻም በዘርና በቋንቋ እንዲሁም በሃይማኖት ዙሪያ ልዪነት ሳናበጅ በሰሜን አሜሪካ በአውሮፓ፤ በአውስትራሊያ፤ በአረብ ሃገራት በጥቅሉ በዓለም ዙሪያ ያለን ሁሉ እነዚህን ከፋፋዪች በመረጃ ክስ መመስረት አለብን። እዚህ ተሸጉጠው ሰውን እንዲያጫርሱ መፍቀድ የለብንም። ለሚሰሩበት መ/ቤት፤ ለሚያስተምሩበት ተቋም፤ ለሚኖርበት ክፍለ ከተማ ሰው ደብዳቤ በመጻፍና በመረጃ በተደገፈ ክስ በመሰረት ከሚኖሩበት ሃገር ሁሉ እንዲባረሩ ማድረግ እንደሚቻል የአንዳንድ ሃገሮች ህገ መንግሥት ይጠቁማል። ህዝባችን መቀለጃ መሆኑ ያብቃ። የዘር ፓለቲከኞ ምትሃታዊ ትዕይንት ያብቃ!

 4. ጠ/ሚኒስተሩ ከስራ ይልቀቁ የሚለዉ ከኦዲፓ ነዉ ወይስ ከጠ/ሚኒስተርነታቸዉ ከጠ/ሚኒስተራነታቸዉ ከሆነ እሱ ኢትዮጵያዊ ስላልሆነ አያገባዉም የድር ገጾችም ጽሁፉ ኢትዮጵያዊ መንፈስ ስለሌለዉ ለእይታ ባያበቁት መልካም ነበር።

 5. ውድ ዘሐበሻ፣
  “ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን ይልቀቁ” ያለው ዶ/ር ሄኖክ ገቢሳ ነው። “የኦሮሞ ተቃውሞ አራማጆች” ብላችሁ መዘገባችሁ አሳፋሪ ብቻ ሳይሆን የጋዜጠኛነትን ሙያና ስነምግባር እንደ ዘነጋችሁ ያስረዳል። የገጻችሁን ክብር ለመጠበቅ ካሰባችሁ አንሱት!

  • ትክክል ወንድሜ ለፅንፈኞች አቀጣጣይ ፈንጂ እያቀበሉ በአማራና ኦሮሞ መካከል ግጭትን ይፈጥራሉ::

 6. ምን ያህሉ ኦሮሞ ሰሞኑን የተካሄደውን የ ብሄር ጭፍጨፋ እንደሚቃወም ባላውቅም ፣ ተማርኩ ከሚሉት ኦሮሞች ግን ብዙ እንዳልሆኑ እርግጠኛ ነኝ። በቅርብ ከማውቃቸውምም አይቼዋለሁና። ይህን ስብዕና የጎደለውን ተግባር የማይቃወም ሰው፣ ሰው ነው ማለት አልችልም፤ እንስሳ እንጂ። እንስሳ እንኳን የሚገድለው ሊመገበው ነው እንጂ እንዲሁ ለመግደል ብሎ አይደለም። የግድያም አይነት አለው። በዱላ ጨፍጭፎ መግደል፣ በድንጋይ ወግሮ መግደል፣ ማረድ እና ከዚያም ሬሳ መጎተት ምን ይባላል? ይህ ከሰው ፍጡር በፍጡር የሚደረግ ተግባር አይደለም። እጅግ በጣም ያሳፍራል።
  ምንም ያላደረገ ሰላማዊ ህዝብ በአሰቃቂ ሁኔታ ሲጨፈጨፍ እርዳታ ያላደረጉ የ ኦሮምያ ፖሊሶች ተባባሪ ለመሆናቸው ሌላ ማስረጃ አያስፈልግም። ከእንግዲህ ወዲህ ኦሮሞ ያልሆኑ ህዝቦች ለህልውናቸው ያሏቸው አማራጮች ሁለት ናቸው።
  1) ከተቻለ በህብረት ሆነው ቄሮን እና ፖሊስን መቋቋም፣
  2) አካባቢያቸውን ለቅቆ ወደ ሰላማዊ ቦታ መሄድ ናቸው።
  እግዚአብሄር ልቦና ለሌላቸው ልቦና ይስጣቸው። አገራችንን ሰላሙን ይስጣት።

 7. ወንድሞቼ በኦሮሚያ ብዙ ቁጭትና ንዴት አለ:: ኦሮሞን ስታሳንሱ ህዝብን ታስቀይማላችሁ:: ወንጀለኛ ብሄር የለውም:: በዝዋይና አርሲ ሻሸመኔ ያለው የአያቶላ ጃዋር ኦሮሞ ስልጣኔ የራቀው ጭካኔ የተላበሰ የሸዋ ክርስቲያን ኦሮሞን ከአማራ ለይቶ የማያይ ለፅንፈኝነት ተጋላጭ ነው:: የኢትዮጵያ ቦኮሀራም ማለቱ ይቀላል:: ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ:: ህዝብ ግን በጅምላ አይሰደብ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.