በኢትዮጵያ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 166 መድረሱን የኦሮሚያ ፖሊስ አረጋገጠ

የድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳን ሞት ተከትሎ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ እና ኹከት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 156 መድረሱን የኦሮሚያ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ገላን ትናንት ምሽት አረጋግጠዋል። ከእነዚህ ውስጥ 145 ሰላማዊ ሰዎች እና 11 የጸጥታ አስከባሪዎች ናቸው። የታሰሩ ሰዎች ቁጥር 1084 ደርሷል

oromo 1ድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ከተገደለ ወዲህ በኢትዮጵያ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 156 መድረሱን ፖሊስ አረጋግጧል። የኦሮሚያ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ገላን ትናንት ማምሻውን በሰጡት መግለጫ እንዳሉት 145 ሰላማዊ ሰዎች እና 11 የጸጥታ አስከባሪዎች መገደላቸውን ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የጸጥታ አስከባሪዎችን ጨምሮ 165 ሰዎች  ጉዳት ደርሶባቸዋል። 1084 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ገላን አረጋግጠዋል።

ስዩም ጌቱ

እሸቴ በቀለ

3 Comments

 1. መንግሥት እነዚህን በምስሉ የሚታዩትን ወጣቶች አጣና ይዘው ሽብር የሚፈጥሩ መንጋዎች ላይ ለምን ገደብ አያደርግም? የያዙት አጣና ብዙ ምርምር ሳያስፈልገው የህዝብንሰነልቦና ሰላም የሚነሱ አሸባሪ መንጋዎች ናቸው፡፡ ካመቻቸው ለመጠቀም እንደማይመለሱ በተግባርም እያሳዩም ነው፡፡ ያለው መንግሥት ህግ እና ደንብን እንደሚመቸው ነው እየቆነጠረ የሚያሳየን፡፡ አገራችን ህዝቡ ስላም እንዲያገኝ እንግዲህ የመንግሥት ግልበጣ ሴራ ብቻ አይደለም የሚያስፈልገው፡፡ ጀዋርና ጀሌዎቹ ይሄው አመታት አስቆጠሩ በአገራችን እንኳን በውን በህልምም ታይቶ የማይታወቅ አጸያፊ ከዱር አራዊት የሚጠበቅ ተግባራትን ሲይሳዩን አመት አለፈን፡፡የእምነት ተቋማት ቤተ ክርስቲያን ሲያቃጥሉ፡ ተቋማትን ሲያፈርሱ ሲያነዱ ወዘተ ይሄ ሁሉ ሲሆን የመንግሥት ቸልተኝነት አስደንጋጭ ነበር፡፡

  መንግሥት መሰረታዊ የህዝብን መብቶች የማስጠበቅ መብትና ግዴታ ይጠበቅበታል፡፡ እንደዜግ ነታችን መንግሥትን መጠየቅ ያለብን አጣና እየያዙ በመንጋ መንደራችንን ቂያችንን ሰላም የሚያደፈርሱ ህግ ፊት እንዲያቀርብስን ነው፡፡ ከሁለት ሰው በስተቀር በመንጋ በየቦታው በየመንደሩ ማንዣበብን ማስቆም አለበት፡፡ የመንግሥቱን ሓይለማሪያምን አረመኔ አስተዳደር ለማሞገስ አልነበርም ነገር ግ ን እንደዚህ በጅምላ ያሚንቀሳቀስን ወሮበላ እየቆፈደደ ነበር እሥር ቤት የሚያገባቸው፡፡ ለነገሩ እንታፈሳለን ሲሉም በድፍረት እይጋለጡም ነበር፡፡ ለአሁኑ እነዚህ ጨቅላ ወጣቶች ለሚያስዩን ተግባር መሰረታዊ እርምጃ የግድ ነው፡፡ ከወጣቶቹም አልፎ ወላጆች ካሏቸው እነሱም ተጠያቂ እንዲሆኑና ለሚያደርጉት አጸያፊ ተግባር ሃላፊነት እንዲወስዱ መጠየቅ አለብን፡፡

  • Kuni

   Soon you will see Abiy’s , Lemma Megersa’s & so on’s own children joining Querro at these type of actions and events. Abiy’s Government is sponsoring and encouraging these በምስሉ የሚታዩትን ወጣቶች to act the way they act. The only reason Abiy is not openly encouraging them is because he is afraid of foreign aid getting cut off, but it is known these ወጣቶች act the way they act with Abiy’s blessing and with the government’s soldiers protection.

   • ገብቶኛል አባባልህ፡፡ የጠ/ሚሩ ዝምታ ባለፉት 3 አመታት ለተፈጸሙት አሰቃቂ የነፍስ ማጥፋት ዘመቻ ለሰሚው ግራ ያጋባል፡፡ በዘር በሃይማኖት በቋንቋ የስንት ሰው ነፍስ አጣን! በእድሚአችን አይተን ሰምተን የማናውቀውን ነው ለመመልከትና ለመስማት የተዳረኘው፡፡ በእርግጥም በአገሩ መንግሥትም መኖሩን ያጠራጥራል፡፡አሁን ግን አማራጭ ስለሌለን በዘር ተመርኩዞ የአገራችንን ህልውና የሚያቃውሱትን መንጥሮ እንዲያወጣ መርዳት አለብን፡፡ ለነገሩ አሁን የሥልጣኑን ህልውና እየተፈታተኑት ስለሆነ ምን አልባት እሱም ዝምታው አንደማያዋጣው ተረድቶ ለመከላክል እርምጃ መውሰድ ይጀምር ይሆናል፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.