አዳነች አቤቤ ሕዝብ ራሱን ለመከላከል ያደረገውን ጥረት “ኦሮሞ አይገዛንም እያሉ፣ ገጀራ ይዘው ሁከት ፈጥረዋል” በማለት የህዝብ መብቱን መጠቀሙን ወንጀል አድርጋዋለች

abbeበአዲስ አበባ በርካታ ቦታ ላይ አሸባሪዎች ቤተክርስቲያንን ለማቃጠል ከበባ ሲያደርጉ ሕዝብ ተጠራርቶ የመጣዉን ሀይል አስቁሞታል። ሆኖም መንግስት ቤተክርስቲያናትን የተከላከሉትን አስሯል።
ቃሊቲ አካባቢ በአሸባሪዎች ቤቱ ሊቃጠልበት የነበረ አንድ ግለሰብ በተኩስ አሸባሪዎቹን ለማባረር ችሎ ነበር። ሆኖም ፖሊሶች ወደ ግለሰቡ ቤት በመግባት መሳሪያዉን በመንጠቅ ግለሰቡን ለመንጋው አሳልፈዉ ሰተዋል። መንጋውም ሰዉዬዉን ደብድቦ በመግደል እሬሳዉን ጎትቷል።
የአዲስ አበባ ህዝብ ቤቱ በአሸባሪው ሀይል በድንጋይ ሲደበደብ፣ የንግድ ተቋማቱ ሲወድም፣ በጎዳና የተገኘዉ ሲደበደብ ፖሊሶች በአላዬሁም ሽፋን እየሰጡ አልፈዋል።
የአዲስ አበባ ህዝብ እና ወጣት እራሱን ለመከላከል ጥረት በሚያደርግ ሰዓት ፖሊሶች በህዝብ ላይ ተኩሰዋል፣ አስለቃሽ ጭስ ለቀዋል።
አዳነች አቤቤ ሕዝብ ራሱን ለመከላከል ያደረገውን ጥረት “ኦሮሞ አይገዛንም እያሉ፣ ገጀራ ይዘው ሁከት ፈጥረዋል” በማለት የህዝብ መብቱን መጠቀሙን ወንጀል አድርጋዋለች።
———————————–
እኔ ደግሚ ትንሽ ላክልበት።፡ባልደራስ ሲመሰረት ያነገባቸው ጥያቄዎች አሉ። ከነዚህ መካከል አንዱ የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ በመረጠው ከንቲባ ይተዳደር ፣ አሁን ያለው ከንቲባ በሕዝብ ያልተመረጠ ሰለሆነ፣ ምርጫ እስኪደረግ ድረስ ጊዚያዊ የማስተዳደር ስራዎችን ከመስራት ውጭ መሰረታዊ በከተማዋ ጉዳዮች ዙሪያ መወሰን የለበትም የሚል ነው።
በአዲስ አበባ መስተዳደር፣ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ በብዙ ክፍለ ከተሞች የተሾሙት ሃላፊዎች በዋናነት የተሾሙት በአቶ ለማ መገርሳ ነው። ዶር አብይ ኢንጂነር ታከለን ሳይሆን ሟቹ ዶር አምባቸውን ነበር ለመሾም የፈለገው። ሆኖ አቶ ለማ በመቃወማቸው፣ አቶ ለማን በኦህዴድ ውስጥ ዋናው ሰው ስነበሩ፣ ዶር አብይን በድርጅታዊ አሰራር አስገድደው ነው ታከለ ኡማ የተሾመው።
እነ አቶ ለማ የነርሱን ሰው በአዲስ አበባ ማስቀመጣቸው ምክንያቱ የፊንፊኔ ፕሮጀክት የሚሉትን ተግባራዊ ለማድረግ ነበር። አቶ ታከለ ለምን እንደተሾመም ራሳቸው አሁን የብልጽግና አመራር የሆኑት አቶ አዲሱ የተናገሩት ነገር ነው።
አቶ አዲሱ ስለ ኢንጂነር ታከለ ኡማ
“እነ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ጠዋትም ማታም ሻይ አብረን ስንጠጣ፣ የኦሮሞን ጥቅም አዲስ አበባ ውስጥ ለማስጠበቅ፣ በተለይም ካሁን ቀደም ተገፍቶ ከአዲስ አበባ ሲወጣ የነበረውን አርሶ አደርና፣ ኦሮሞነት ከከተማ ውጭ እንዳይሆን ከፍተኛ ስራ እየሰሩ ነው፡፡ ስራው የሚያስገኘውን ውጤት አብረን በጋራ የምናየው ነው የሚሆነው፡፡ ማድረግ ያለብን መርዳት ነው፤ ከጎናቸው መቆም ነው….…በአዲስ አበባ መንግስት ካቢኔ ውሳኔ የኦሮሞን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚቻልበትን መንገድ ለመፈለግ፣ ካሁን ቀደም የተሰሩትን ስህተቶች ማረም የምንችልበትን መንገድ ለማግኘት እንዲቻል አስበው ሌት ተቀን እየሰሩ ነው ያሉት፤ የአዲስ አበባ መሪዎች፡፡ ይህንንም ሁሉን ነገር በሚዲያ መናገር አስቸጋሪ ነው፡” ነበር ያለው።
ይሄንን አይነት ንግግሮችና ፖለቲካዎችን ነው ባልደራስ የሚቃወመው።ባልደራሶች
1) ሕብረ ብሄራዊ በሆነ ከተማ የአንድ ጎሳ ጥቅም ብቻ ማስጠበቅ አፓርታይዳዊ አሰርር ነው በሚል ነው ተቃውሞ ያቀረቡት። “ኦሮሞ ለምን ገዛን፣ ኦሮሞ ለምን ተጠቀመ ?” አላሉም። የአዲስ አበባን ሕዝብ እኩል እስካገለገለ ድረስ ኦሮሞ ሆነ ማንም ቢገዛ ችግር የለውም። ወ/ሮ አበበች በቴሌቪዥን ያቀረበችው ክስ ውሸት ብቻ ሳይሆን አሳፋሪም ነው።
2) ማንም ይግዛን ማንም፣ ፍትሃዊነት በሰፈነበትና ሁሉንም እኩል ተጠቃሚ ባደረገ መልክ የሚያስተዳደር፣ የሕዝብ አዎንታ ያለውን በሕዝብ የተመረጠ፣ ለአንድ ጎሳ ብቻ ሳይሆን ለሁሉን አዲስ አበባ ነዋሪዎች ጥቅም የቆመ መስተዳደር መኖር አለበት ብለው ነው የሚከራከሩት።
3) በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ የሚወስኑት፣ ከወለጋና አርሲ፣ ከቦረናና ጉጂ የመጡ የኦሮሞ ክልል መንግስት ሃላፊዎች ሳይሆን ፣ ኦሮሞ ይሁኑ አማራ፣ ትግሬ ይሁኑ ጉራጌ፣ ወላይታ ይሁኑ ውህድ ፣ ሙስሊም ይሁኑ ክርስቲያን ፥የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ብቻ ናቸው የሚል አቋም ነው ያላቸው።
4) የሚያደረጉትን እንቅስቃሴዎች የሚያደረጉት ፍጹም ሰላማዊን ሕጋዊ በሆነ መንገድ ነው። አንድ በባልደራስ ስብሰባዎች ሆነ ሰለፎች እንኳን ገጀራና ጩቤ ተይዚ ሊወጣ ጠጠር አልተወረወረችም።
አንዳንድ ጽንፈኞች ፣ መንግስትም ያምነው የሽብር ተግባራትን ለመፈጸም በተንቀሳቀሱበት ጊዜ የአዲስ አበባ ወጣቶች ተደርጅተው ራሳቸውና ሰፈራቸው መክተዋል። እነዚህ አሸባሪዎች መከላከል ከሆነ እነ ወ/ሮ አዳነች በኦሮሞ ላይ መነሳት አድርገው የወሰዱት፣ አንደኛዉኑ ዝም በሉና ታረዱ፣ ተገደሉ ብለው ለሕዝቡ ይንገሩት።
Tona Ethio

 

1 Comment

  1. በዚህ ወቅት ጉንጭ አልፋ ክርክር የሚጠቅመው ባንዳው ወያኔና ተላላኪው ኦነግ ሸኔ ነው:: በዚህ ወቅት በተለይ አማራው የፖለቲካ ኳስ ጫወታ ሳይሆን ሰብሰብ ብሎ እንደ ኢትዮጵያዊ የውድ ሀገራችንን ማፍረስ የወገኖቻችንን በግፍ መገደል ለማቆም በአንድነት መቆም አለበት ብዬ አምናለሁ:: ጎራው ለይቷል:: የታከለ ኡማ ከንቲባነት አንገብጋቢ ጉዳይ አይደለም እንደ ሻሸመኔ ያሉ ቦታዎች እየተቃጠሉ:: ባልደራስ በዚህ ወቅት ለወያኔ መንገድ አመቻች እንጂ ብዙም ቁምነገር አላይበትም:: አዲስ አበቤዎች ማን ናቸው:: ይህ ወያኔ ያመጣው የጎጥ ስሜታዊ ጣጣ ነው::
    ለእኔ አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን የጋራ ከተማ ናት::ምርጫው ሲመጣ ነዋሪዎቿ መሪዎቻቸውን ይመርጣሉ:: ባልደራስና አዲስ አበቤዎች ሳይፈልጉ የወያኔ አጫፋሪዎች እንዳይሆኑ እሰጋለሁ:: ዛሬ ወያኔ እስክንድርን ይፈልገዋል:;

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.