አቃቤ ሕግ ሆይ የሐጫሉ ገዳይ ማን ነው? ነው ጥያቄው! አታምታታ! – ሰርፀ ደስታ

abebeከሐጫሉ ግድያ በኋላ የተፈጠሩት ሁሉ ከጅምሩ ለሐጫሉ መገደል ታሳቢ የተደረጉ እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ የሐጫሉ ገዳይና የተገደለበት ምክነያት ሲታወቅ ብዙ ሌሎች ወንጀሎች ሌላ ምስክር ሳያስፈልጋቸው ይዳኛሉ፡፡ መሠረቱ የሐጫሉ ገዳይ ማን ነውና ለምን የሚለው ነው፡፡ እሰካሁን አንድም ከሐጫሉ ግድያ ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪ ወንጀለኛ ፍርድ ቤት ቀርቦ አላየንም፡፡ ፖሊስ ከጅምሩ ባልታወቁ ሰዎች ተገደለ አሉን እስካሁንም እነማን እንደሆኑ አልተናገረም፡፡ አቃቤ ሕግ የሚነግረን ክስ እሰካሁን ከሐጫሉ ግድያ ጋር አይገናኝም፡፡ እያቀረበ ያለው ክስ ከሐጫሉ ግድያ ጋር አለመገናኘቱ ብቻም ሳይሆን የሐጫሉን ግድያ ለማደበሰበስ ቅድመ ዝግጅት እሆነ እንዳይሆን ስጋቴ ነው፡፡ የሚገርመው ግን ይሄም አቃቤ ሕግ ክስ ብሎ የሚያቀርባቸው ያው ከዚህ በፊት ሰው  በሰፊው ሲያወራ የነበረውን እንጂ ሌሎች ብዙ ወሳኝ ወንጀሎች ሰው ብዙም የማያውቃቸውን አላነሳም፡፡ ለመሳሌ ጀዋር የተባለው ሰው በባሌ፣ በአሶሳ፣ በሐረርና በመሳሰሉት ሁሉ በሚችለው ሁሉ ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት ሊያውም ብዙ ሕዝብ እየሰበሰበ ሲሰብክ ነበር፡፡ ያው መንግስት ተብዬውም አቃቤ ሕጉም የሕዝብን ቀልብ ይስባሉ የሚላቸውን ጉዳዮች እንጂ ሌሎችን ጉዳዮች ማንሳት አይፈልግም፡፡ በጉልህ ከሚታወቁት በላይ ከፍተኛ አደጋ ሊኖራቸው የሚችሉ ብዙ ቅስቀሳዎችን አድርጓል፡፡ የገረመኝ የሲዳማን ሕዝብ ቀስቅሷልም፣ ለ86 ሰዎችት መሞት አመጽ አነሳስቷል የሚሉት ናቸው፡፡ ለመሆኑ ሕግ ማት ምን ማለት ነው አቃቤ ሕግ፡፡ ይሄን ጉዳይ ተቀባይነትም አገኛ አላገኘምም በወቅቱ ለፍርድ ቤት የሕግ ባለሙያ ነበር? እንግዲህ ሕግ ማለት እኛን እስካልነካ ድረስ የፈለገ ወንጀል ቢሰራ አያገባንም ነው? ይሄ ነው ሕግ? የአሁንም ክስ ቢሆን ዋናውን ጉዳይ የሐጫሉ ግድያን ጋር በተያያዘ ሳይሆን ከዛ ወዲህ ስለተደገረገ የአስከሬን ማንገላታት ከእሱ ጋር ተያይዞ ሁከትና ሞት መድረስን ነው፡፡ ለመሆኑ ይሄው 48 ሰዓት ሳይሆን ቀናት እየተቆጠሩ ነው፡፡ እስካሁን በሐጫሉ ግድያ ፍርድ ቤት የቀረበ ማን ነው?

ተጨማሪ ያንብቡ:  የከተሞቻችን ፅዳት እንዲህ ከሆነ መሰልጠን መገለጫው ምን ይሆን? - ሙሉጌታ ገዛኸኝ

ሌላው ነገሮችን አሁንም ለመበረዝና ለማምታት እስክንድርና ሌላም ሰው ሁከት ሕዝብን ለአመጥ በማነሳሳት በሚል ታስተዋል፡፡ እሺ ለመሆኑ እነእስክንድር ሕዝብን ከሕዝብ አነሳስተው ምን ተፈጠረ? ምልክት እንኳን ነበር? እንግዲህ ስነትና ስነት አደጋ የፈጠረውን የወንጀለኞች ተግባርን ለመበረዝና ለማደበስበስ አሁን ሌላ ትኩረትና ንትርክ የሚፈጥር ነገርን እንደተለመደው እስክንድር እንደጠላት ስለሚታይም እግረመንገድም ለመበቀልም ጆሮና ናላን ጭው የደረገው የወንጀል ድርጊት ትኩረት ለመቀነስ ሆን ተብሎ እንደሆነ እየታዘብን ነው፡፡ ትንሽ ቆይቶ እስክንድር ነው ገዳይም የሚል ክስ ሊመጣ እንደሚችል እናስባለን፡፡

ሐጫሉን ጀዋርና ቡድኑ ምን ያህል ሲደባበት እንደነበርና ምን እሱንም በመግደል ለተቀጠረበት የግብጽና ወያኔ ተልዕኮ ሕዝብን ከሕዝብ ለማጨራረስ ሆነኛ  ኢላማ እንደነበር ታዝበናል፡፡ ሐጫሉ በኦኤም ኤን የተደረገለትን ቃለ መጠይቅ ደግሜ ልሰማው ሞክሬ ነበር፡፡ ባለፈው ገንዘብ የሰጠውን ሰው መጠርጠር አለበት የሚል ግምት ነበርኝ፡፡ አሁን ደግሜ እንደሰማሁት ግን ገንዘብ የሰጠው ሰው ምን የምርም የሐጫሉ አድናቂ እንደሆነ ተገነዘብኩ፡፡ የኦኤም ኤኑ ጠያቂ ከሐጫሉ ጋር የጦርነት ያህል ነበር፡፡ ሐጫሉን ለማሳሳት፡፡ የማይሆን ንግግር እንዲናገር፡፡ ሌላ ቀርቶ ስለሚኒሊክ ሐጫሉ አነበብኩ ያለውን ከተናገረ በኋላ  ሐውልቱ መፍረስ አለበት ሲል ሐጫሉ ሐውልቱ እንዲፈርስ አልፈልግም ይላል፡፡ የሐውልቱን መፍረስ ከኢትዮጵያ ጠላቶች በተሰጣቸው መሠረታዊ አገርን የማፈራረስ ሴራ አንዱ ስለነበር ጋዜጠኛው አጥብቆ ሲጠይቅ ነበር፡፡  ሐጫሉ የሞተባት ሌሊት ሳትነጋ ነበር ኦኤም ኤን በዋናነት የሚኒሊክ ሐውልት መፍረስ አለበት የሚል ሕዝብን ሲቀሰቅስ የነበረው፡፡ በቀጥታ ሲያሰራጭም ነበር፡፡ የሐጫሉ መሞት ጎዳያቸው አልነበረም፡፡ ዓላማቸው የሐጫሉ አስከሬን የእነሱ ጉዳይ አልነበረም፡፡ የሐውልት ማፍረሱና ስርጭቱ ሲቋረጥ አሁን አስከሬኑ ከአዲስ አበባ መውጣ የለበትም የሚል ሌላ ቡድን ቡራዩ ላይ አዘጋጁ፡፡ አዲስ አበባ ጀምረን አዲስ አበባ እንጨርሰዋለን ያሉን ለማድረግ ያላቸውን ሁሉ ሞከሩ፡፡ ሐጫሉን የገደሉበትን ዋናው ሕልማቸው አገርን ማፈራረስ ሁነኛ ምክነያት እንዲሆናቸው ነበር፡፡ በእርግጥ ነው ሐጫሉ በግሉም ጠላታቸው ሆኗል፡፡ እሱ ጠላቶቹ እንደሆኑ ባያስብም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢህአዲግ ከ70 ዓመት በፊት በአፄ ኃይለ ስላሴ ዘመን በተገነባ ስታዲዮም ውስጥ ሆኖ ግንቦት 20 እያከበረ ኢትዮጵያ አድጋለች ይላል

መንግስት ሆይ እነግዲህ ይሄን ሁሉ አይተን ዛሬም ሌላ ትርክት ተተረክልን ይሆናል፡፡ ከዛም የከፋ ይሄን አጋጣሚ ሌሎችን ለመበቀል ትጠቀምበት ይሆናል፡፡ ጀዋር መሐመድ ሐጫሉን ብቻ ሳይሆን እቅዱ ኢትዮጵያን ለመግደል ነበር፡፡ ለመሆኑ ይህ ወሮበላ ለሠራው ወንጀል ተባባሪው በዋናነት የመንግስት መዋቅር አልነበረም? ሕዝብ በአስቸኳይ የሐጫሉ ገዳዮች እንዲቀርቡ ማሳሰብ አለበት፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ አደለም፡፡ አያስፈልግም፡፡ በተለያዩ ሚዲያዎች ዓለም የመንግስት ተብዬውን ቁማር እንዲየውቀው ማድረግ ነው፡፡ በዚህ ወቅት ሠላማዊ የሚባ ሰለፍ በፍጹም አይታሰብም፡፡ ለጠላት መመቻቸት ስለሚሆን፡፡ በዚህ ላይ ለበሽታም መጋለጥ ነውና፡፡ ገና የኮረና ቫይረስ አሁን በተፈጠረው ሁከት ምን ያህል አደጋ እንደሚሆን አናውቅም፡፡ ማንም ከሕግ ውጭ እንደፈለገው እንዲሆን ዋና የሕግ አፍራሹ መንግስት ተብዬው ነው፡፡ ብዙ ወንጀሎችን አይተናል፡፡ በየዩኒቨርሲቲው የተገደሉ፣ ታፍነው የተወሰዱ፣ በይፋ ትልልቅ ባለስልጣን ሳይቀር የተገደሉበትን ሁሉ አይተናል፡፡ አንዳቸውን ግልጽ የሆነ ነገር የለም፡፡ ከሰኔ 16ቱ ቦንብ ጥቃት ጀምሮ እየቀረቡልን ያሉት ሁሉ አንድም ሊታመን የሚችል ነገር የለውም፡፡ የሰኔ 15 ግልጽ የሆነ ድራማ እንደነበር ታዝበናል፡፡ በባሕርዳሩም በታማጆር ሹሙም ሞት ገዳይ የተባለው ሰው እንዳለበት የሚያወራው መንግስት ብቻ ነው፡፡ መረጃ ግን ብሎ የሚያቀርባቸው ነገሮች አስቂኝ ናቸው፡፡ እዚህም ጋር የእዛው አይነት ዳርዳር አለ፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ መንግስት ራሱ በሐጫሉ ሞት እጁ አለበት ለማለት የሚያስችለን አንዳቸውም ፍንጭ ባናገኝም ቆይተን ግን መረጃ ብሎ በሚያቀርባቸው ነገሮች እንመዝነዋልን፡፡ ችግር አለ! የምንፈልግው ፍትህ እንጂ በሚዲያ እየወጡ ማቅራራት አደለም፡፡ ፍትህ፣ ሥርዓት ሕግ!

የሐጫሉ ሞት ሳምንት ሳይሞላ ወይ ሌላ አጀንዳ ይፈጥሩልንና ይረሳል፡፡ ከዛ መንግስት እሱ በሚመቸው ወጥቶ ያወራልናል፡፡ ለጊዜው ትኩሳቱ ስለሚበርድ ሁሉም ምን እናደርጋልን እንግዲህ ብሎ ይተዋል፡፡ በዚህ ሁኔታ ስንት ሰው ፍትህ አጥቶ እየኖረ ነው፡፡  ይሄን ለምደንዋል፡፡ ጌታቸው አሰፋን ልይዝ ነው በሚል አንድ ሰሞን ትልቅ አቧራ ሆኖ ነበር፡፡ እንደ እውነቱ እኔ ጌታቸው አሰፋን በግል እይዘዋለሁ የሚለው ተራ የሰውን ስነ ልቦና ለመማረክ እንጂ መሠረታዊ ፋይዳው አይታየኝም፡፡ ምን አልባትም የሰኔ 16 ጉዳይ ከጌታቸው አሰፋ ውጭም ሊሆን ይችላል፡፡ እንደሰማሁት ጌታቸው አሰፋ ራሱ መድረክ ላይ ነበር፡፡ ይሄ ከሆነ ደግሞ እንዲህ ያለ ቁማር የለም፡፡ጌታቸው አሰፋ ፈጸመ ለተባለው ወንጀል ይጠየቅ ግን የእሱ ጉዳይ ዝም ብሎ የግለሰብ ጉዳይ ነው? ደግሞስ ከሆን ለምን አልቀረበም፡፡ ክሱስ ምንድነው የሰኔ 16ቱ ብቻ?  በተመሳሳይ አንድ ክንፈ ዳኘውን ያዝሁ በሚል ትልቅ ማቅራራት የነበረበትን አስታውሳለሁ፡፡ እኔ ከንፈ ዳኘው ማን እንደነበረም አላውቅም ነበር፡፡ በወቅቱ ሐጢያቱን ያበዙበት ግለሰብ በሕግ ፊት ምን እንደሚመስልም አናውቅም፡፡  ፍትህን እንጂ በቀልን ፈልገን አደለም ሰዎች ለሕግ ይቅረቡ የምንለው፡፡ ወይም ለመጨፈር፡፡  መንግስት በሚባለው አካል ላይ ያለኝ እምነት እየተሟጠጠ ነው፡፡ በዙ ትልልቅ ወንጀሎች አይተናል፡፡ ወንጀሎቹ ከራሱ ከመንግስት ነኝ ከሚለውም ላለመሆናቸው እርግጠኛ አደለንም፡፡ የሚያሳዝነው ወንጀሎቹ ትኩረት እንዲያገኙ እንኳን አይፈልግም እንኳን ፍትህ ሊሰጥ፡፡ 17 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የት እንደገቡ ሳይታወቅ ይሄው ሰሞኑን ሲጠየቅ ለምን ተጠየቅሁ አይነት መልስ ነበር የሰማንው፡፡ አዝናለሁ፡፡ አሁን ጥሩ ጊዜ ላይ አደለንም!

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጋሼ አሰፋ ሞቱ፤ ለመግባት ከቤቱ.......! - በመስከረም አበራ

ቅዱስ እግዚአብሔር ለወገኖቻችን ፍርዱን ይስጥ! ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

2 Comments

 1. Fake Abiy Ahmed:

  Free the great, innocent and God-fearing Eskinder Nega and his comrade Sentayehu Chekol.

  Eskinder cannot and should be used as a gift to Takele goma and other baby killing extremist oromos.

  My fellow Ethiopians killed in the hands of barbaric and primitive herds called kero, I simply say RIP. I wish I could be there and defend you against the wild animals.

 2. “መሠረቱ የሐጫሉ ገዳይ ማን ነውና ለምን የሚለው ነው“

  ሰርፀ
  በስም ገዳዮች ማን እንደሆኑ አልተገለፀም ሆኖም 2 ወንዶችና አንድ ሴት መያዛቸውን ሌሎች በመፈለግ ላይ እንደሆኑ ተገልፆዋል:: ከሁሉም በላይ ሺመልስ አብዲሳ እምባው እየወረደ ይህን እኩይ ስራ የሰሩት ወያኔና ኦነግ ሸኔ መሆናቸውን አስረግጦ ተናግሯል:: አሁን ነገሮች እየጠሩ ነው:: ኢትዮጵይን ለማዳን እንደ ሀገር ህዝቡ ከዐቢይ ጋር ከመቆም ውጪ ምርጫው የጠበበ ነው:: የህዝብ ፍጅት የምናድነውም በዚህ መንገድ ነው:: እስክንድር etc የፖለቲካ ቅንጦት ጊዜ ላይ አይደለንም:: ሻሸመኔን ያየ ነገ በኔ ብሎ ይዘጋጅ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.