የከሸፈው የሰኔው መፈንቅለ መንግሥት !!!! – ተድላ አስፋው

Jawar Politicsየመፈንቅለ መንግሥቱን መጀመር ምልክቱ በተባበሩት መንግሥታት ፀጥታው ምክርቤት ኅዳሤው ግድብ ዉይይት ወደመጠናቀቁ ገደማ ሀጫሉ ላይ ግድያ በመፈፀም ነበር።

ገደላዉን አስመልክቶ OMN የዘር ማጥፋት በኦሮሞ ክልል አዲስ አበባና አካባቢውን ለማከናወን ተነቃነቀ። አፍቃሪ ወያኔው TMH የተለመደውን ፀረ አማራ ቅስቀሳ አቀጣጠለው የግብፅ ዘጋቢዎችም ኢትዮጵያ መፈረካከስዋን እያበሰረ ኅዳሤ ግድብ ሙሌቱ አበቃለት ብሎ ፈነጠዘ።

የሃጫሉን አስከሬን ከመንገድ ጠልፎ ግርግር በመፍጠር የሰው ህይወት እንዲጠፋ ብሎም የመንግሥት ባለሥልጣናትን የመግደል ሙከራው ከሸፈ።

አስከሬኑን አዲስ አበባ ለማሳረፍ የነበረው ዕቅድ የመፈንቅለመንግሥቱ ዋናው ቁልፍ ነበር።

የኦሮሞን ማህበረሰብ ልጅህን ነፍጠኞች ገደሉብህ ምን ትጠብቃለህ መመሪያ የ OMN የፀረ አማራ የቀብር ጥሪ ፊንፊኔ ለመገናኘት ማወጁ ከሸፈ።

ይህ ባይከሽፍ ሊፈጠር የነበረዉን የ OMN ቦርድ ዛሬ ለመንግሥት በትዕዛዝ መልስ አቅርብዋል። በአዲስ አበባ የሚገኙትን የዐፄዎች ሀዉልት በሙሉ ከቀብር መልስ ለማፈራረስ የመፈንቅለ መንግሥቱ ዕቅድ ነበር።

ሃጫሉ በዘፈኑ ሀዉልቶችማፍረስ አለብን የሚል አንድም ዘፈን አልዘፈነም እንዲያዉም አፍቃሪ ወያኔ ኦሮሞ ታጋዮችን በቅርቡ ለ OMN በሰጠው ቃለመጠይቅ ማዉገዙን ሰምተናል።

በለንደን የጃንሆይን ሀዉልት ማፍረስ ዛሬ በሜኔሶታ ዳውን ዳውን ቴዲ አፍሮ ፉከራ የከሸፈው መፈንቅለ መንግሥት አካል መሆኑ የዛሬው OMN ባዶ ቀረርቶ ይመሰክራል።

በዚሁ ግርግር ከ ሰማንያ በላይ ንፁሀን ብዙ የግልና የህዝብ ሀብት ጠፍትዋል። መፈንቅለ መንግሥቱ ቢሳካ ኖሮ የአዲስ አበባንና አካባቢው ነዋሪ ለከፍተኛ የጎሣ ጥቃት መጋለጡ አይቀሬ ነበር ።

አዲስ አበባ የፌዴራል ጦር በፍጥነት በመግባቱ ጦሩም የሀገር እንጂ የጎሣ ጦር ባለመሆኑ መፈንቅለ መንግሥቱ ሊከሽፍ ችልዋል።

ሃጫሉን ገድለው የሃጫሉ አብዮትን ፈጥረው ፊንፌኔን በመቆጣጠር የምኒልክን ሀዉልትን በማፍረስ “ኦሮትግራይ” ዘረኛ መንግሥት የማቛቛም ሴራው ከሸፈ።

ከኦሮሞ ክልል ዉጭ ያለው ፍፁም መረጋጋት የሚያረጋግጠው መፈንቅለ መንግሥቱ ጅምሩም መጨረሻውም አፍቃሪ ወያኔ OMN እና ወያኔው TMH የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ህዝቡ ጠንቅቆ በመረዳቱ ነዉ።

ሠፊው የኦሮሞ ህዝብ የ ሃጫሉ ቤተሰቦች በፈቀዱት በቀብሩም የተናገሩትን በማክበር ያሳየው መረጋጋት እጅጉን ያኮራል።

ከኢትዮጵያ ዉጭ የሚደረግ የጥላቻ ቴሌቪዥን ዛሬ ከአየር የወረደው OMN ከ አጋሩ TMH አየር ሰዐት እንደሚሰጠው የታወቀ ነው።

የጥላቻ ማሰራጫ ጣቢያዎችን የማጋለጡ ስራ በዉጭ የምንኖር ኢትዮጵያውያን ዋናው ስራይሆናል።

የለንደን ሀዉልትአፍራሾች ላይ እንደተደረገው በ ሜኔሶታና ሌሎች ቦታዎች የተጀመረውን ፀረ ኢትዮጵያ ፉከራ ያንን የሚቃወም ስራ መስራቱም መበረታታት አለበት።

በከሸፈው መፈንቅለ መንግሥት ተዋንያን ከፍተኛ የጥላቻ የማስፈራራት ዘመቻ ከሁለት ዐመት በላይ ይደረግ የነበረበትን እስክንድር ነጋና ስንታየሁ ቸኮል ማሰር መፈንቅለ መንግሥት የሞከሩትን መለማመጥ ስለሆነ ይታሰብበት። ከአያያዝ ይቀደዳል ከአነጋገር ይፈረዳል !!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.