የሀጫሉ ሀዘን መታሰቢያ! – ከአባዊርቱ

hachalu 1
ይድረስ ለዝቃጮች ባላችሁበት ቦታ
ሃጫሉን ለመድረስ ወጥታችሁ ከፍታ
ጨለማን ለብሳችሁ ገላን ኮንዶ ሰፈር
ልጃችን ተበላ አወይ የግዜር ነገር።
ረስታችሁ  ከሆነ  የአምቦን ገጽታ
እስቲ ላስታውሳችሁ ከያኔው ትዝታ።
የጀግኖቹ አምባ ጅባትና ሜጫ
መቁላት ያቅበታል ተልባን በሙቀጫ።
ሃጫሉን ያፈራች ያች ፍል- ከተማ
ብዙ ደጀን አላት ምን ጠላት ቢግማማ።
ጥንትም ታሪካቸው ሲነገር የኖረ
ጀግኖችን ለመጣል አንድ ዘዴ ነበረ።
ወይ ጽልመት ይለብሳል ከአይን ተሰውሮ
ካልሆነም በሴት ነው የበጥራቆች ኑሮ።
ይህን ጀግና ወጣት ሀሞተ ኮስታራ
የወጣቶች ቁንጮ ምንም የማይፈራ
በመሰሪ  አውታር በክፉዎች ልሳን
መጠይቅ  አርጋችሁ እንዲቀርበው ሰይጣን
ሀጫሉ ጀግናው ልጅ ጥንትም ቀጥተኛ
ላመነበት ጉዳይ ያልሆነ ዳተኛ
ወጥመዳችሁ ገባ ወገንም ተንጫጫ
ግን እኮ መብቱ ነው የመናገር ምርጫ።
ይህን ባረጋችሁ ልክ በሳምንቱ
አይ እቅድ ፣ አይ ፕላን እናንት የሰው ከንቱ
ልጃችን ተበላ ያ ብርቅዬ ጎምቱ።
እናንት ክፉ ተምቾች መግደሉ አንሷችሁ
ደግሞ  ከአስከሬኑ  ምን ጉዳይ አላችሁ?
እኔ እንደገመትኩት በራሴው እይታ
የዚህ ጀግና አስከሬን እንዲያ ሲንገላታ
ድንገት ከተነሣ ድራሻችን ጠፋ
አስብሏችሁ ይሆን  ሃጬ ቢያንቀላፋ?
አይ ዶፍተር ተብዮች የእውቀት ነቀርሣ
የጫት ባለሟሎች የወጣት  አበሣ
የግብፅ ጃንጥላ ያዥ ቅጥረኛው ዘረጦ
የባንዳ ልጅ ሁላ ላይ ታች ተመራርጦ
ምን ብትጎሻሽሙት ህዝቡን ለማባላት
ለሀጭ ተዝረክርኮ ፣ደደቢት ተጸንሶ ፣ መቀሌ ቢዶለት
አልሰመረም ከሽፏል በሀጫሉ እልፈት
አምላክ ታድጎናል ሰውሮናል ከእልቂት።
እስቲ ባጋጣሚ ዳግም ላስታውሳችሁ
አምቦን አትሞክሩት ብለን ስንላችሁ
ለዋዛ አልነበረም ስሙኝ ያልሰማችሁ።
አምቦ ጀግናን ወልዷል ቆራጡን ከንቲባ
ምን ቢጎሻሽሙት በነጋ በጠባ
ቀጥ ብሎ በጽናት እንደ አምቦ መንገድ
ሸገርን ለማስዋብ ይዟል ልዩ እቅድ።
አምቦ ተስተምሮ ጀልዱ ላይ ተወልዶ
የጽንፈኛን ሴራ ሁሏንም ገማምዶ
አምና ያስቆጣንን አምና ላይ ወትፎ
ብቅ ብሏል ሺመላሽ በኢትዮጵያችን ገዝፎ።
አወይ አለማወቅ እነ አባ ተንኮሉ
“የቦረንቲቻ በግ” ሆነና ሀጫሉ
ህዝብን ለማባላት ቢያሴሩ በበርጫ
አምቦ ቡሩንዶ  እንጅ መች ለምዶ አልጫ!!! (*2)
እናሣ!
ታጠቅ አባ ቀልቢ ብልሀተኛው አቢይ
አማምል ሁሉንም እንዲቆም አንድ ላይ
ሀቁ ካንተ ጋር ነው የኢትዮጵያችን ጉዳይ
ወደሁዋላ የለም በተለይ በአባይ
አደባባይ አውጣው የዚን ጀግና ገዳይ!
ያባይ ጉዳይ ላንተ ሆኖብህ ሰቀቀን
እንደማትዘንፍ  ሲያውቁ ያባይ ሙሌቷ ቀን
ሃጫሉን ሰየፉት ቅያስ ፈለጉና
ቀድሞስ ለከርስ አደር  ምን ምግባር አለና?
እጅህ አመድ አፋሽ ሆነና ነገሩ
እነ ሎስ-አንጀለስ- ቀድሞ አማካሪ-  ቢላሽ ሆነው ቀሩ።-
እንደምን አስቻለው ያገሬ ዘበኛ
የመከላከያው የሁሉ ቤተኛ?
መቼስ መጠርጠሩ አይከፋም ብዬ ነው
ኮርቻ ከፈረስ  ወርዶ እያየነው።
በመጨረሻም!
ጽናቱን ይስጥልኝ ላጫሉ ቤተሰብ
ጀግናን ለተቀሙት ባልባሌ ሰበብ።
መቼስ ሞት አይቀርም ለሁሉም በፈርጁ
እልፍ ነው በቁጥር ያ-ጫሉ ወዳጁ
እናም እንዳታዝኑ ጠብቁ በጋራ
ሁሏም ትከፍላለች በዚህ ክህደት ሴራ።
እስቲ ምን ይባላል ንብረትን ማውደሙ
ዜጋውን በሞላ በጥይት መልቀሙ?
የዜጎች ሲገርመኝ ህይወትን ያጡቱ
ት/ቤት ማውደም ምንድን የሚሉቱ
እንኳንስ ወድሞልን እንዲሁም አልቀናን
ያገሬ ወላጆች ምን ፍዳ ጣለብን
ወጣቱን ይታደግ ወይስ ኮሮናውን?
ደግሞ ጉድ አይፈሩም ህዝን ይደርሳሉ
“ወይ ሀጫሉ” ብለው ከምር ያለቅሳሉ
ምን ገራገር ቢሆን ያገሬ ገበሬ
ለይቶ ያውቃታል ብስሏን ከጥሬ
በከንቱ ደከሙ እነ ጉድ አይፈሬ።
ያ-ጫሉ አብሮ አደግ አንች ብርሀኔ ቤካ
እምባሽ ተጠራቅሞ በቁጭት ይለካ።
ምን ልብሽ ቢረበሽ በሀጫሉ ቅስፈት
ሙዚቃውን አድምጭ እንዲሆንሽ ብርታት
“ማላንጂራ” ለኔ ሆኖኛል መድሀኒት።
እንግዲህ በሀዘን ልይት የሚሉቱ
መለዮ ብለናል ኤታማዦር ዊርቱ
ለማጠቃለያም
እስቲ በዖሮሚፋ እንዲህ ልበላቸው
ለጀግናው ቤተሰብ ድንገት ቢረዳቸው!
ሀጫሉ ጄታኒ ያምታኒ ማቃሣ
ኢሲኑ ኮርማ’ዳ ያ ኦቦ ሁንዴሣ።
ሁንዴንሳ ጫ-ላኖ ዲኒስ ካንባያቴ
ጃሪቲን ፉሌ’ዳን ዋራኑ ሶዳቴ
ሃልካኒን ዱካናን ኮሲ’ዳን ‘ዶካቴ
ኦዶ ጋ’ዴን ጂርቱ ሌንጫ ጋላፋቴ።
ያ  ሀርሜ ሃጫሉ ኦቦላዋን ሁንዳ
ኮርማ ናማቱ ዱኤ ቡልቲ ጢቆ ጋዳ።
ሲላስ ማሉምጎና ሁንዳቱ ጉባቴ
ካንጃሪቲ ቤክና – ኢጆሉማኬኛቱ – ኑጋላፋቴ
ዋራ ኦፊንቤክኔ ያርቱዋን ዖሮሙማ ጉርጉራቴ
ዳኢሙማሣቲፍ ጃባ’ዳ ካን ሃጫሉሌ ካሌሱማ ‘ዱማቴ።
ሁንዲኬኛ ጪስኔ ሂንቡሉ ጉማሳ ኦዶ ሂንዴቢሲን
ቢላቱማን ኢቲ ቃቃብና ኦልቴ ሂንቡልቱ ዱቢቲን!!!!
መታሰብያነቱ ለጀግናው ሃጫሉ ሁንዴሣ ይሁንልኝ።
የኢትዮጵያችን ልሳን ሚዲያዎች ቢቻል  በኦድዮ ካልሆነም በጽሁፍ  ለሀጫሉ ቤተሰብና አድናቂዎቹ ብርታት ይሆን ዘንድ ብታቀርቡልኝ ፈጣሪ ይስጥልኝ። አመሰግናለሁ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.