ምክትል ጠቅላ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በወቅታዊ ያስተላለፉት መልዕክት

Demeke

 • በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ በአሳዛኝ ሁኔታ መሞት ሁላችንንም ያሳዘነናየልብ ስብራት የፈጠረ ከስስተት ነው፡፡
 • ከዚህ ግድያ ጋር ተያይዞ በተደረገ የጥፋት ቅስቀሳ በተለያየ አካባቢዎች በአሳዛኝ ሁኔታ የብዙ ንፁኃን ህይወት አልፏል፡፡ ብዙ ንብረት እና ቅርስ ወድሟል፡፡
 • በዚህ ጭካኔ በተሞላበት ድርጊት ህይወታቸው ለጠፋ ዜጎች የተሰማኝን ልባዊ ሃዘን እየገለፅኩ ለቤተሰቦቻቸውና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መጽናናትን እመኛለሁ፡፡
 • የዚህ ዓይነት ጭካኔ የተሞላበት ግድያ በሃጫሉ ግድያ ለማቆም ሳይሆን ህዝብን ከህዝብ ጋር በማጋጭት ሃገርን ወደ ለየለት ብጥብጥ እና ትርምስ በማስገባት በውጭና በውስጥ ላሉት የጥፋት ሃይሎች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ነው፡፡
 • ከግድያ በኋላ የተላለፉት የጥፋት ጥሪዎች በአንዳንድ ቦታ በተግባር የተያዘው ድርጊት በቀጣይ የባሰ ጥፋት ለማቀጣጠል እየተካሄደ ያለው ዘመቻ ይዘህ ማሳያ ነው፡፡
 • ይህን ጉዳይ በአስተውሎት፣ በአብሮነትና በጥበብ መመከት ይገባናል፡፡
 • ሃገራችንን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር፤ ለዘመናት በቁጭት የምንጠብቀውን የህዳሴ ግድብ ግንባታ የውሃ ሙሌት የምንጀምርበት ወሳኝ ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡
 • ምድራችንን እያስጨነቀ ያለውን የኮሮና ወረርሽኝ ለመግታት እና የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ ከፍተኛ ጥረት ላይ እንገኛለን፡፡
 • ይሁንና ሃገራችን ወደ ዘላቂ ጥቅም ማስከበሪያ መምገድ ፊቷን እንድታዞር የማደናቀፍ ዘመቻ እየተካሄደ ነው፡፡
 • በዚህ ወቅት ኢትጵያውያን ለሉዓላዊነታቸው እና ለክብራቸው በአንድነት የምንዘመንትበት መሆን ሲገባው፤ በአንፃሩ ይህን ሚፈታተኑ፤ ውስጣዊ አቅማችንን የሚሸረሽሩ ጥረቶች ይስተዋላሉ፡፡
 • ይህ ተቀባይነት የሌለው ታሪካችንን ማይመጥን እኩይ ተግባር በመሆኑ መንግስትና ህዝብ በፅናት ሊታገሉት ይገባል፡፡
 • ስለሆንም ህዝባችን ለጥፋትና ለግጭት ለሚውሉ ነጥሪዎች ጆሮ ሳይሰጥ የለውጥ ጉዟችን ከዳር እንዲያደርስ ጥሪ አቀርባለሁ፡፡

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.