አቶ ጀዋርና አቶ በቀለ ገርባ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ

Jawar and Bekeleአቶ ጀዋር መሐመድ አቶ በቀለ ገርባ እና ሌሎች ታሳሪዎች ሁሉ በአሁኑ ሰዓት አዲስ አበባ ጊዮርጊስ አካባቢ ባለዉ የፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀረቡ።
በሌላ በኩል ፤ «በአዲስ አበባ የመከላከያ ሠራዊት ገባ ተብሎ የሚፃፈዉ ነገር ትክክል አለመሆኑ» ከአዲስ አበባ የደረሰን ዜና ያመለክታል። በመረጃዉ መሰረት «ድሮም ቢሆን የመከላከያ ሰራዊት የነበረዉ አዲስ አበባ ዉስጥ ነዉ።» ቀደም ሲል «የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን አሰቃቂ ግድያ ተከትሎ በሃገሪቱ ከ 80 ሰዎች በላይ በመገደላቸዉ፤ ልዩ የፀጥታ ኃይላት ወደ አዲስ አበባ መግባታቸዉን የዉጭ ዘገቦች አመልክተዋል።»
ከአዲስ አበባ በደረሰን መረጃ መሰረት ግን አዲስ አበባ ከትናንትና በተሻለ መረጋጋት ላይ ትገኛለች። «ወደ አዲስ አበባ ልዩ ኃይል ገባ ፤ አልያም ተጨማሪ ሰራዊት ወደ አዲስ አበባ ገባ የሚባለዉ ነገር ፈፅሞ ሃሰት ነዉ። የዉጭ ኃይሎች ከአገር ዉስጥ ኃይሎች ጋር በመተባበር የሚነዙት ወሬ ነዉ» ተብሎአል።DW – መረጃዎችን በፈጣን ወደ እናንተ ያደርሳል። ለሌሎች ማጋራታችሁን አትዘንጉ!

DW

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.