በአምቦ መረጋጋት የለም ፤ ወደ አምቦ መንገዶች ዝግ ናቸዉ

amboከአዲስ አበባ ወደ አምቦ የሚወስደዉ መንገድ በመዘጋቱ እና ማንንም ሰዉ ማለፍ ባለመቻሉ ጋዜጠኞች ወደ ቀብሩ ቦታ መድረስ አለመቻላቸዉ ተነገረ። ከአዲስ አበባ ወገን የፀጥታ ጥበቃዉ በጣም የጠበቀ ነዉ ። በአምቦ ግን በርካታ ወጣቶች አሁንም «የሙዚቀኛ ሃጫሉ ሁንዴሳ አስክሪን ወደ አዲስ አበባ ተወስዶ እና የክብር ሽኝት ተደርጎለት፤ የኦሮሞ እምብርት በሆነችዉ ፌንፌኔ መቀበር አለበት» እያሉ ከፍተኛ ተቃዉሞ እያሰሙ ነዉ ተብሎአል።
ትናንት ረቡዕ ማምሻዉን የኦሮምያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል አራርሳ መርዳሳ ፤ በአምቦ የሚታየዉን ተቃዉሞ እና ከፍተኛ ዉጥረት ተከትሎ በመንግስት ብዙኃን መገናኛዎች ቀርበዉ በሰጡት መግለጫ «ሙዚቀኛ ሃጫሉ ሁንዴሳ መቀበር ያለበት ከትግል ጓዶቹ ጋር በአምቦ ነዉ ፤ ይህ ዉሳኔ የተሰጠዉ በቤተሰቦቹ ፍላጎት እንጂ በመንግሥት ጫና አይደለም» ብለዋል።
የአምቦ ወጣቶች ግን የሃጫሉ አስክሪን ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ በክብር አዲስ አበባ መቀበር አለበት እያሉ ትናንት ምሽት ከፍተኛ ተቃዉሞ አስነስተዉ ነበር፤ ተብሎል። ይህን ተከትሎ « በሃጫሉ ቤተሰቦች አካባቢ ቦንብ ተወርዉሮ የሃጫሉ ሁንዴሳ አባት ወንድም «አጎቱ» ጉዳት ደርሶባቸዉ ወደ ሆስፒታል እንደተወሰዱ ሕይወታቸዉ ማለፉን ፖሊስ በመግለጫዉ አስታዉቋል። በዚሁ ጥቃት በሁለት የኦሮምያ ፖሊስ ላይ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ ገልፆአል።
የአርቲስቱን ግድያ ተከትሎ በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች በተቀሰቀሰ አመጽ እና የሃዘን መግለጫ ሥነ-ስርዓት 78 የማኅበረሰብ አባላት እንዲሁም ሦስት ፖሊሶች ሕይወታቸዉ ማለፉን ፖሊስ አስታዉቋል። አንዱ ፖሊስ ሕይወቱ ያለፈዉ እነ አቶ ጀዋር መሃመድ የሙዚቀኛዉ አስክሪን ወደ አምቦ መሄድ የለበትም በሚል ከአምቦ መንገድ ከኬላ ወደ አዲስ አበባ በቀጥታ ስቴድዮም አካባቢ ወደ ሚገኘዉ ወደ ኦሮምያ ብልጽግና ጽ/ቤት አምርተዉ ፤ በአንድ የኦሮምያ ፖሊስ ላይ ግድያ ፈጽመዉ ወደ ጽ/ ቤቱ የገቡ መሆኑን ፖሊስ አስታዉቋል።
ሁለቱ ፖሊሶች የተገደሉት ደግሞ አርሲ ዞን ኢራ የምትባል ትንሽ ከተማ «ማንነታቸዉ ባልታወቀ ከኅብረተሰብ መሃል በተተኮሰባቸዉ ጥይት» መሆኑን ፖሊስ በመግለጫዉ አስታዉቋል።
ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉት ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶችን በተመለከተ በተለይ «አቶ ጀዋር መሃመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ላይ ድብደባ የተፈፀመ በማስመሰል የሃሰት ዜናዎችን በማሰራጨጫት በሕዝብ መሃል ነዉጦች እና ግጭቶች እንዲበራከቱ እየተደረገ ነዉ» ሲል ፖሊስ ባወጣዉ መግለጫ ከስዋል። ጥንቃቄ እንዲደረግም አሳስቦአል።
DW

3 Comments

  1. የዶ/ር ኣብይ መንግስት የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎኑ እንዲቆም ጥሪ ኣቅርቦኣል።ህዝቡም ምላሹን ሀገር ኣቀጥቅጥ በሆነ ሰላማዊ ሰልፍ መግለጽ ይጠበቅበታል።የሚቀጥለው እርምጃ ክተት ኣውጆ ለሀገራችን መበጥበጥ መቀሌ ቁጭ ብሎ እዝ የሚያስተላልፈውን ኣካል ከኣልሻባብ ባልተለየ ሁኔታ በኣሸባሪነት ፈርጆ፣ ጥሉ ከወያኔ እንጂ ከትግራይ እንድልሆነ ኣስፈላጊው ገለጻ ተሰጥቶ፣ በቁጥጥር ስር ማረግ ነው ።
    ወያኔዎች ይህን ሁሉ ግፍ ሲፈጽሙ ፣ ለእኩይ ተግባራቸው ገንዘብ የሚሰሩ ድርጅቶቻቸው በነጻነት ይቀሳቀሳሉ፣በየኮንቴነሩ የታጨቀው ብር ብሄራዊ ባንክ በማያውቀው ሁኔታ በሀገር ውስጥ እየተቀሳቀሰ ደሀውን በ excessive inflation ይቀጣል፣ በውጩ ኣለም የገንዘብ ማዘዋወሪያ ከፍተው ሃገሪቱ ውስጥ ሊገባ የሚችለውን የውጭ ምንዛሬ በማስቀረት ከዘረፉት ብር በሀገር ውስጥ በጥቁር ገበያ ሂሳብ ለተላከለት ሰው በብር ባንክ ኣካውንት ያስገባሉ።ሌሎችንም ወንጀሎች እስከመቼ እንታገስ ??
    ማፈሪያ ምደኞቻቸውን በተጀመረው መንገድ ከየጉሮኖው እየለቀሙ ለተፋጠነ ፍርድ ማቅረብ ነው ።ከዚህ ያነሰ እርምጃ መውሰድ ራስን ለጥቃት ኣጋልጦ መስጠት ነው።

  2. FBI need to be asked for help to find out who killed Hachalu or was it a suicide same as Simegnew Bekele’s death was called a suicide.

  3. Hachalu’s living testament indicated he should have been buried in Addis Ababa. If Hachalu wanted to be buried in Addis Ababa , he should not have been prevented.

    From now on all Oromo who devoted our lives best for equality are going to be burried in Addis Ababa, we all are going to carry our living testaments in our pockets at all times signed , dated and declared by witnesses stating we wish to be burried in Addis Ababa.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.