“የተከበራችሁ ኢትዮጵያውያን  ኢትዮጵያ የሁላችን እንጂ የኣንድ ባለኣርማ ቡድን ኣገር ኣይደለችም: ወደፊትም ኣትሆንም!”- በዩናትድ ኪንግድም ኢትዮጵያውያን

hachalu 1በኢትዮጵያዊው ወገናችን በታዋቂው ድምጻዊ በሃጫሉ ሁንዴሳ መሞት እጅግ ኣዝነናል::
ዬሃጫሉን ገዳዮች በብርቱ እያወገዝን የፍትሕ ኣካላት ሞያን መሰረት ባደረገ እውቀት ኣጣርተው በኣፉጣኝ ለፍርድ እንዲያቀርቧቸው እንጠይቃለን::

ሞትን ኣስመልክቶ ጥልቅ ሃዘንን መግለፅ የወረስነው የኢትዮጵያዊነት ባህል ብቻ ሳይሆን የሰብኣዊነታችንም መግለጫ ነው:: ይህንን በሚፃረር መንገድ በኢትዮጵያ እየደረሰ ያለው የሕይወትና የንብረት ጥፋት ግን መለኪያ የማይገኝለት ኣረመኒያዊነትና ሰብኣዊ ከሚባል ባህርይ ፍፁም የራቀ የጭካኔ ተግባር ነው::ከሃዘን መግለጫ እሴቶቻችን የተለየና ለሟቹ ኣርቲስት ክብርም የማይመጥን በሕይወቱ እያለ ኣይቶት ቢሆን ኑሮ እኔንና ኦሮሞነቴን የሚፃረር ድርጊት ነው የተፈፀመው በሚል ኣጥብቆ ያወግዘው የነበረ ኦሮሞ የሆንነውን ጭምር ኣንገት ያስደፋ ድርጊት ነው::
ሟቹ ኣርቲስት ለሁላችንም በጎና ደህንነት የቆመ የከፍተኛ ስብእና ባለቤት ነበር::

የእርሱን ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ምክንያት በማድረግ በሚመስል መንገድ በለንደን ኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ የደረሰው ጥቃትም ሆነ ለኢትዮጵያ ክብር ከብዙ ኣመታት በፊት የቆመውን የንጉሠ ነገሥት ኃይለሥላሴ መኮንን ወልደማካኤል ጉዲሳን ኃውልት ማበላሸት የራስን ክብር ካለመገንዘብ ድንቁርና የተደረገ ጥፋት እንደሆነ እንቆጥረዋለን:: ከኤምባሲውም ግምባር ላይ የነበረውን የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ኣውርዶ መድፈርን ለኣገራቸው ከፍተኛ መስዋእትነት የከፈሉ ሕብረብሔራዊ ፀረ-ፋሺስቶችን: ንጉሠ ነገሥቱን: እነ ኣብዲሳ ኣጋንና ጃጋማ ኬሎን ኣቧራ ላይ ኣጋድሞ እንደመጎተት እንመለከተዋለን::

የሃጫሉን ሞት በምሬት ብናስብም የኢትዮጵያን ውርደት ማየት ኣንሻም:: 56ቱ የደቡብ ብሔረሰቦች : ጋምቤላዎች: ኣፋሮች: ኣማራዎች: ትግሬዎች: ሶማሌዎችና: ሓራሪዎች: ቤኒሻንጉል ጉምዞችና ኦሮሞዎች ሌሎች ያልዘረዘርናቸውም የጋራችን የሆነው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በሌላ የፖለቲካ ፓርቲ ኣርማ እንዲተካ መደረጉን እናወግዛለን:: ሕዝባችንም ባልወሰነልን መንገድ መመራት የማንችል መሆኑን እንገልፃለን::

ተጨማሪ ያንብቡ:  [ኢት-ኢኮኖሚ ET- ECONOMY] - "ጅብ ከሚበላህ ጅቡን ብላውና ተቀደስ!!!" የኢትዬጵያ ቢራ ፋብሪካዎች (Ethiopian Beers Factories)

በለንደን የተደረገውን ኣግባብነት የጎደለውን ተግባርም ሁሉ እንኮንናለን:: በኛ ስም የተደረገ ነገር ግን በማንኛውም ሚዛን እኛን የማይወክል ኣሳፉሪና ተልካሻ ድርጊት መሆኑንም እንገልፃለን:: ኢትዮጵያ የሁላችን እንጂ የኣንድ ባለኣርማ ቡድን ኣገር ኣይደለችም: ወደፊትም ኣትሆንም!

ኢትዮጵያ በሕዝቦችዋ እኩልነት ደምቃ ለዘለዓለም ትኑር:
በዩናትድ ኪንግድም ነዋሪ የሆንን (ሌሎች) ኣንግሎ-ኢትዮጵያውያን::

7 Comments

 1. It is sad and hurting to see a bunch of hooligans fight with a lifeless monument of the Emperor Hailesalassie who is a descendent of the Oromo. He brought victory to Ethiopians and it was a united sacrifice of all Ethiopians that the hooligans thought it was only for Oromos. It is also destructing and damaging the priceless humanity of the sculptor host of Hilda Seligman. My aim of my next visit to the UK was to visit that monument at cannizaro park in Wimbledon and I hope the UK government will bring to justice those who destruct it give them a fine penalty to erect back with their labour and money and time to get a good lesson. These hooligans if the did this with a sober mentality you can imagine the damage they could have done to other monuments with a twisted and drunk mood and state.
  God bless the soul of Emperor Haileselassie and the Sculptor Hilda Seligman.
  Muchfun.
  Canada

 2. በጫትና በመጠጥ ነብዘዉ ባንድራዉን ሊየወርደዉ ተቆናጦ የወጣዉ መሀይም ተፈጥፍጦ ቢሞት ደግሞ እነ ጁዋር ለኦሮሞ ነጻነት መስዋእት ለሆነዉ ጉርሜሳ ሐዉልት ይቁምለት ሊሉን ነበር በዛ ሰልፍ ላይ ወዲያ ወዲህ ብለዉ ያጡት ነገር ቢኖር አጠና ብቻ ነዉ። ጭንቅላታቸዉን ጸጉር ብቻ ከሚያሳድጉበት ምናለ ትንሽ ነገር ዉስጡ ቢጨምሩበት? ያ ቢሆን ጁዋርን የመሰለ የቀላል ሚዛን አሳቢን አትቀልድ ማለት በቻሉ ነበር። እድሜ ለወያኔ አእምሮቸዉን ባዶ አድርጎ ስላሳደጋቸዉ የተሰጣቸዉን ጨርቅና ባካባቢዉ ያገኙትን አጠና ይዘዉ መሮጥ ብቻ ነዉ አስተዋጽዋቸዉ። እነዚህ በእንሰሳ ማደሪያ ዉስጥ እንጂ ከህብረተሰብ ተቀላቅለዉ ለመኖር ያሉበት የአስተሳሰብ ደረጃ አይፈቅድም። ወያኔ እያኮላሸዉ ግምባር ግምባሩን እየመታዉ ዛሬም ሌንጮ በሰጠዉ ትርክት ላይ ነዉ ያለዉ።፡

 3. We put the peacock monument after destroying the Lion monument at the palace in Addis Ababa because peacock got colors.

 4. በዘመናችን የምናየው የጥቁር ህዝብ ትግል ፋይዳ እያጣ ያለው ሀውልት ከማፍረስ ስለማያልፍ ነው፡፡ ደግነቱ ታሪክ በድንጋይ ፍንገላ አይጠፋም፡፡ አገራችን ኦሮሞ ምኑ እንደተነካ መረዳት ያስቸግራል፡፡ ጠ/ሚስትሩ ፡ ስልጣን አለን ብለው መድረክ ላይ የሚወጡት ሁሉ ጋልኛ ተናጋሪዎች ናቸው፡፡ በወያኔ ግዜ የንበረውን አሁን ደግሞ ባለው አስተዳዳር ኦሮሞ ብሻ ነው የሚታየው፡፡ ኦሮሞዎቹ እርስ በእርስችሁ ካልተግባባብችሁ እንግዲህ ምን ይደረግ እንግዲህ? ወያኔስ ብልጥ ነበር አማርኛ ቋንቋን እየተማረ የኢትዮጵያን ባንዲራ እያውለበለበ ነው 27 ዓመት ጠፍሮ የገዛን፡፡ ኦሮሞ ደግሞ ግራ ገብቶት እኛንም ግራ እያጋባን ነው፡፡ ምን እንደሚፈልጉም የሚያውቁ አይመስልም፡፡ ወይ አገራችንን አክብራችሁ ባንዲራችንን አክብራችሁ ታሪካችንን አጥኑና ይግባችሁ በእኢትዮጵያዊነታችን እኩል እንኩራ እና የእናንተም ወተት ተፍልቅልቆ እስኪገንፍል ግዙንና ባለተራው ደግሞ እስኪመጣ ሰላም ስጡን፡፡

 5. የመንግሥት አካላት ቆመው እያዪ አይደል እንዴ ሰው ሲገደል ዝም ያሉት? በሃረር፤ በአርሲ፤ በአዳማ በሌሎችም ስፍራዎች አዲስ አበባን ጨምሮ የሆነው ይህ ነው። ቆንጨራና ሌላም ነገር ይዘው ሰው የሚያምሱትና የሃጫሉን አስከሬን ለፓለቲካ ጥቅማቸው ከመንገድ ጠልፈው ወደ አዲስ አበባ ያመጡት ለኦሮሞ ህዝብ ቆመናል የሚሉ ድውያኖች ናቸው። በአምቦ በለቅሶ ላይ ሰው እንዲገደል ለዚያውም የሟች አጎት እንዲሞት ያደረጉት ኦሮሞዎች ናቸው። የኦሮሞን ህዝብ እኛ እናውቅልሃለን የሚሉ ስብስቦች ጭራሽ ለኦሮሞ ህዝብ እንዳልቆሙ ገና ከጅምሩ ግልጽ ነው።
  በመሰረቱ የፓለቲካ ማጣጫ ለማድረግ በነገሩ ምንም ነገር የሌላባቸውን ሚዲያዎች፤ ተፎካካሪ ፓርቲዎች አባላት እና መሪዎች፤ የሰው ልጅ መብት ተከራካሪዎች እያፈሱ ማሰር ተገቢ አይደለም። ችግሩ አንድ ነው የዘርና የጎሳ ፓለቲካ ለማንም ሃገር በጅቶ አያውቅም። አሁን በኢትዮጵያ ያለው ፍትጊያ በኦሮሞ አክራሪዎች መካከል የሚደረግ ሽኩቻ እንጂ ሌላ ነገር አይደለም። የዘር ፓለቲካ ጢቢራቸውን ያዞረው የኦሮሞ ፓለቲካ አራማጆች በለንደን የቀ. ኃ. ሥ ሃውልት ማፍረሳቸው ላስጠለላቸው ሃገር እንኳን የሰላም ጸር መሆናቸውን ነው። እኔ በመሰረቱ በእንግሊዝ ሃገር ሃውልት መኖሩንም አላውቅም። ለእኔ ምኔም አይደለም። ግን በሃገር ቤት እሳት ለኩሰው ባስጠጋቸው ሃገር መንገድ የሚዘጉ፤ ንብረትና ሃውልት የሚያፈርሱ የጅምላ ፓለቲከኞች ለዝንተ ዓለምም ቢሆን ለሰው ልጆች የሚበጅ ነገር የላቸውም።
  ጨለማ ቤት አናስርም፤ አንጋረፍም እያሉ ሰውን በየሰበቡ እያጋፈፉ እሰር መክተት ተገቢ አይደለም። መታወቅ ያለበት አንድ ነገር አለ። ይኽውም ማን እንደሚረብሽ፤ ማን እንደሚገልና ንብረት እንደሚያቃጥል ግልጽ ነው። ግን በደልን ዝም ብላችሁ ተጋቱ የሚለው የዶ/ር አብይ መንግሥት ራስን ለመከላከል የቆምቱን ሁሉ የዘር ፍጅት ፈጣሪዎች እያለ በጅምላ እስርና እንግልት የሚከት ከሆነ ከወያኔ የሚለየው ምኑ ላይ ነው? አቶ ጃዋር “አመጸናል። አሳምጸናል” በማለት ከጥቂት ቀናት በፊት የተናገረውን ማዳመጥ ተገቢ ነው። ማን ነው በውሸት ተከበብኩ በማለት የ 87 ሰዎች ህይወት እንዲጠፋ ያረገው? በማን ትዕዛዝ ነው የሃጫሉ አስከሬን ተጠልፎ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ ያደረገው? ማን ነበር ከባህል ማከሉ በራፍ ላይ የቆን የጸጥታ አካል በጥይት መቶ የገደለው? የኦፌኮው አባል ጃዋር ነው። ታዲያ እድሜ ልኩን ፓለቲካ ሲቆረጥም የኖረው ዶ/ር መራራ አሁን የተናገረውን ለሰማ እጅግ ያሳምማል። “የባሰ ችግር እንዳይመጣ ጃዋርና ተከታዪቹ ቢፈቱ ይሻላል”. ምን ለማለት ተፈልጎ ነው። እስቲ የባሰ ችግር ይምጣና ማን አትርፎ ማን እንደሚከስር እንይ! አላማችሁ ሃገርን እንደ ሶሪያ ማድረግ ነው። ጾሙን ለሚያድረውና በነጻነት ስም አፉ የተለጎመው ሰፊው የኦሮሞ ህዝብ ከእናንተ ያተረፈው ምንም ያለም። የሃገራችን ፓለቲከኞች ቢዘፈን የሚያለቅሱ፤ ሲለቀስ የሚስቁ እቡያኖች ናቸው። መግደል፤ መገዳደል የሚቆመው መቼ ነው? ከሰለጠኑት ሃገሮች ረድፍ ህዝባችን ተሰልፎ በታሪኩና በሃገሩ የሚኮራው መቼ ነው? ከሰሜን እስከ ደቡብ፤ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ የዘር ፓለቲከኞች እስካልተወገድ ድረስ ሰላም የለም። ለመኖር መግደል፤ ለመኖር መዝረፍ፤ ለመኖር እንስሳ ይመስል በዘር መሰለፍ ባለበት ሃገር ውስጥ ሰላም ይሰፍናል ብሎ ማመን ጅልነት ነው። በሃገሪቱ የሚሰራው ስራ ሁሉ ግራ የሚያጋባ ነገር ነው። ችግሩ በየምክንያቱ ከሃገሩ ሸሽቶ በየስፍራው የተሸጎጠው ስደተኛ ሁሉ ነገረኛና እሳት ለኳሽ መሆኑ ነው። ተስፋ ያስቆርጣል። የህዝባችን እንባ መቼ ይሆን የሚቆመው? ጭራሽ አይታወቅም! በቃኝ!

 6. የለንደን ዳያስፖራ ጥሪያችሁን እንሰማለን:: በሃገሪቱ ማንም ቡድን ገናና ሆኖ በሌላው ላይ ጫና የሚያደርግበትን አብረናችሁ እናወግዛለን::በቀደሙት ግፈኛ መንግስታትም ሆነ በወያኔ የተፈበረኩ የሚለያዩን ምልክቶች ታሪኮች በሙሉ ሚዛናዊ ባለመሆናቸው በተገቢው መንገድ ህዝቦቻቻን የወከሉት ምክር ቤት እስከሚያጸድቅ ድረስ ባሉን ምልክቶች ደንቦች መቀጠል የግድ ነው ያለበለዚያ እንደመንግስት ያለው ምንግስት ህዝቡን የሚመራበት ህግ መመሪያ አርማ ያጣልና ይታሰብበት:: ከዚህ በተረፈ ባለፈው በሰላም የወጡትን የኢትዮጲያ አንድነት ያሉትን እየፎከሩ የረበሹ ለድብድብ የተዘጋጁትን በማየት ያፈርነው ስይረሳ የንጉሱን ሃውልትና ያለውን የሃገሪቱን ባንዲራ በማውረድ የአንድ የፖለቲካ ድርጅትን ኣአርማ የሰቀሉትን ህግ በሚከበርበት ሃገር ስላላችሁ ተግታችሁ ወንጀለኞቹ ለፍርድ ይቀርቡ ዘንድ ተባበሩ የደርግ ጨፍጫፊውች ቀልቤሳ ቤካና ከፈለኝ ኣአለሙን ተረባርበን ለፍርድ እንዳቀረብነው ሬድዋንን ኣአብዲአሌን እረፍት አሳጥተን ያባረርነውን ትምህርት ወስዳች ሁ በሎነደን ያሉትን የሰው ዘር ወንጀል ፈሳሚ የደርግንም ሆነ የወያኔ ነፍሰገዳዮች ለፍርድ የማቅረብ ግዴታ የእናንተው ይሆናል ::USA EthioAmercan

 7. The stories form Oromia region we hear are so graphic and objectionable. People who have lived for ages in the region specially in Asela and Zway area have been slaughtered and their head hanged up. You might already have seen the videos in you tube. This is not the first time happening in Oromia. We remember a lot more. This may not be the last, hope God helps.
  I am so confused and angry of what is happening in Ethiopia. I am worried about the poor, the powerless, the children, mothers and elderly people who are victims of atrocity in the so called Oromia region not even protected by regional security apparatus. We have cried and buried Hachalu; even political authorities the likes of Oromia head of state, perhaps the prime minster and other people cried and buried Hachalu. However, lots of other innocent Ethiopians who did not deserve dying, died because they simply worked, served the people, lived and owned property died in the harshest way imaginable. Their only sin might be they just spoke Amharic.
  I am not sure what the Oromo extremists and the misguided youth want now besides behaving like a zoo animal run amok killings destroying everything in their way. They said they were repressed; however they themselves were part of any imaginable repressive government in. They said they faced war atrocity in the period of unification of Ethiopia however they seemed to overlook that they ransacked, destroyed other Ethnics in the country and Oromized all (Mogasa, Gudifecha) grabbing a large swath of the Ethiopian land. They said they were not loved or whatever you have to say. Ethiopian people showed their patience and love even with killing and destruction. They are heads of the military, the bank, the prime minster, attorney general, other minsters, Mayors and what have you. They have all sorts of cultural and linguistic freedom of expression. The Ethiopian public patiently did not complain. Because we assumed they are our brothers, Ethiopians. Nobody cared for them to lead. What was sked for was justice, equity, peace, the right to live, work own property anywhere in the country and don’t repeat the atrocities of previous dictators. Well now let us put blame on TPLF since it is still alive, Egypt both of which could stoke the situation. That is genuine. But my question is what do the Oromo extremists want now? Is there problem the PM? Did not he promise free election for them to try their chance on the ballot? Who is the best Oromo if Dr Abiy is not Oromo enough!? He has responsibility of over 100 million Ethiopians, not Oromo alone. They want him sell everybody for the sake of Oromo interest? What is Oromo interest? He is head of state; he should deal the interest of ethnics in the context of Ethiopia. Misguided Oromo youth with stick, machete or axe on the road hunting the weak and fostering destruction is a very symbol of inhumane culture and lack of civilization. This has to be condemned if occurs in any part of the country or the globe. Civility is the most acceptable way of expression of freedom in 21 first century.
  It is my feeling, before the country descends into further chaos, the government has to search its soul. I don’t believe all PP leaders /cadres are clean from the blood. It is interesting not seeing the Minster of Defense, Obo Lemma, in situations like this (apology if I missed him) and PM is taking all responsibility by himself. Obviously, the leftovers of TPLF need to be finished. You can’t keep ex-general who managed a national security apparatus who says I would prefer Egypt to run GERD etc without bringing him to justice and assume nation will remain peaceful. You can’t allow criminals free and expect the nation to be peaceful. However difficult he dealing might be, this has to be addressed. Ethnic extremists from any region of the county and their media outlet need to be dealt legally. Specially Jawar et al. Jawar simply does not have the persona, the maturity to participate in any mature political conversation in Ethiopia. He is an emotionally unstable, manipulator and mob leader advantaged by OMN and internet. He is national and regional security risk. Government must legally address foreign citizenship holding people of Ethiopian descent who stoke ethnic cleansing on the internet and different ways.
  Lastly, on 7/4/2020 I was watching Al jazeera a program called “Inside story” which was a talk on current Ethiopian situation. The narrative was completely biased. The participants were Dr Awol Allo who is based in UK who thinks he knows all about Ethiopia but Oromo extremist sympathizer, David Shin and Human right lady (it looked she was interfering in what a country should and should not do). It was a biased conversation, no one from the Ethiopia government side to provide government view; it was played out as if Oromo are victims whereas they are representing just small pie of the nation while over 50% of the population actually are politically less advantaged than the Oromo at this time. Foreign living Ethiopians should do more on this regard. Some party has to stand up against the false narrative Oromo oppressed, Oromo that…The government also has to watch conversations in international media and provide response, file discontent like as mentioned in the case of Al Jazeera. I want to conclude with RIP Hachalu, Let God provide peace to his family. He was young aspiring Ethiopian whatever his mistakes were he fought TPLF risking his life. Ethiopians owe him
  Zereginet yiwdem!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.