የሰኔ 15ቱ አይነት ግድያን ለመድገም ታቅዶ እንደነበር የፌደራል ፖሊስ ገለፀ

113187867 whatsappimage2020 07 01at10.02.52pmየፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግሥቴ ዛሬ [ረቡዕ] ማምሻውን ከፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጋር በመሆን ለመንግሥት የመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ የማክሰኞው የጃዋር መሐመድ እንቅስቃሴ የሰኔ 15 ግድያ ለመድገም ያለመ ነበር ሲሉ ተናገሩ።

ኮሚሽነሩ አክለውም አዲስ አበባ ተጀምሮ አዲስ አበባ የሚያልቅ የአመጽ እንቅስቃሴ የመምራት እቅድ ወጥቶ፣ በጀት ተበጅቶለት አመራሮችን ለመግደል ሲመራ የነበረ ነው ሲሉ የተፈጠረውን ሁኔታ ገልፀውታል።

በፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የፌደራል ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ፈቃዱ ጸጋ በበኩላቸው ስለ እስክንድር ነጋ በአዲስ አበባ ሁከትና ግጭት እንዲፈጠር በመቀስቀስ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል።

ምክትል ኮሚሽነሩ በመግለጫቸው የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ አስከሬን ወደ ቤተሰቦቹ እየተወሰደ ሳለ “መንገድ በማስቀየር፣ በመቀማት አመፁን አዲስ አበባ ተጀምሮ አዲስ አበባ እንዲያልቅ ሲቀሰቀስ” ነበር ካሉ በኋላ የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በኦሮሞ ባህል ማዕከል ስብሰባ ላይ እንዳሉ እያወቁ በቀጥታ ወደዚህ ተቋም ጥበቃውን ሰብረው መግባታቸውን ተናግረዋል።

ከትናንት ጀምሮ በነበረው አለመረጋጋት ቢያንስ 50 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ
በድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት የተቆጡ ወጣቶች በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ ጥቃት አደረሱ
አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ 35 ሰዎችን መያዙን ፖሊስ አስታወቀ
በወቅቱ የተፈጠረውን ሲገልፁም ትጥቅ አቀባብለው በመግባት አመራሮቹ ላይ ጭምር ተጨማሪ የሰኔ 15 ዓይነት ተግባር ለመፈፀም እንቅስቃሴ ተደርጓል ብለዋል።

እንደ ኮሚሽነሩ ገለፃ ከሆነ በኦሮሞ ባህል ማዕከል የነበረው የፖሊስ ኃይል አመራሮቹ በሌላ አዳራሽ እንዳሉ በመናገር ወደዚያ እንዲሄዱ ማድረጋቸውን ገልፀው በመካከል ግን የአንድ የፖሊስ ህይወት ይዘውት ከመጡት ታጣቂ ቡድን በተተኮሰ ጥይት መሞቱን ገልፀዋል።

በስፍራው የነበረውን የፀጥታ ኃይልም “በዚህ መካከል የመልስ ምት አለማደረጉ እንጂ የበርካታ ሰዎች ህይወት፣ የበርካታ አመራሮች ግድያ በዚያ ባህል ማዕከል ለመፈፀም እቅድ ነበረ” ሲሉ ተናግረዋል።

የፖሊስ ምርመራ በዚህ መንገድ የእየተካሄደ መሆኑን የገለፁት ምክትል ኮሚሽነሩ “የታቀደ፣ የተጠና ረዥም ጊዜ የደም ማዕበል ለመፍጠር ሴራ የነበረ መሆኑ ለመግለጽ እንወዳለን። ምርመራችንም የሚያሳየው ይህንኑ ነው” ብለዋል።

ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግሥቴ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኀን ማምሻውን በሰጡት በዚህ መግለጫ ከዚህ በፊትም ወደኋላ ሄደን የበርካታ ሰዎች ሕይወት ያለፈበትን የጥቅምቱን ግርግር መነሻ ያደረገ ምርመራም ከዚሁ ምርመራ ጋር አብሮ የተያያዘ እንደሚሆን ገልፀዋል።

ኮሚሽነሩ የ97 ሰዎች ህይወት ያለፈበት ምርመራ በዚህ መንገድ አብሮ ይታያል ሲሉ አረጋግጠዋል።

“በተለያየ ጊዜ በሚዲያ ላይ እየወጡ የሚጠሯቸው የተለያዩ የጦርነትና ብሄርን ከብሄር ለማጋጨት፣ ስርዓት ለማፍረስ የሚደረጉ የተለያዩ ቅስቀሳዎች ጭምር በዚህ ውስጥ ተካትተው የሚታዩ ይሆናል።”

በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የፌደራል ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ፈቃዱ ጸጋ በበኩላቸው ስለ እስክንድር ነጋ ሲገልፁ “የመልስ ምት ያስፈልጋል፤ ኦሮሚያ ላይ እኔ የምወክለው እኔ የምታገልለት ህዝብ ነው እየተጎዳ ያለው፤ ስለዚህ አዲስ አበባ ያለህና ሌላ ቦታ ላይ ያለህ የዚህ ቡድን የሆንክ ተነስ” መልስ ስጥ የሚል ቡድን በአዲስ አበባ ውስጥ ተደራጅቶ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ነበር ብለዋል።

በዛሬው እለት እስከአሁን ድረስ በመረጃ 10 ወጣቶችን በተለያዩ 10 ቦታዎች በመመደብ ተሽከርካሪ በመመደብ የተለያዩ ሎጀስቲኮችን በማመቻቸት ቅስቀሳዎች ሲደረጉ እንደነበር ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋውየፎቶው ባለመብት,ETV
በአዲስ አበባ ውስጥ “የብሔር ግጭት ለመቀስቀስ” ተንቀሳቅሰዋል
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ በሰጠው መግለጫ የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ አብን እና ባልደራስ በአዲስ አበባ የብሔር ግጭት ለመቀስቀስ ሞክረዋል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ከትናንት ጀምሮ በመዲናዋ የጸጥታ መደፍረስ እንዳጋጠመ አስታውቀዋል።

የግል እና የመንግሥት ተሽከርካሪዎችን መሰባበር እና ማቃጠል፣ የዜጎችን ያፈሩትን ሃብት እና ንብረት የመዝረፍ እንቅስቃሴ ነበር” ያሉት ኮሚሽነሩ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም በከተማዋ ሁከት እና ብጥብጥ በመፍጠር ህብረተሰቡ እርስ በእርሱ እንዲጋጭ እንቅስቃሴዎች ሲካሄዱ እንደነበር ገልፀዋል።

የጸጥታ ችግር ለማረጋጋት ተልዕኮ ተሰጥቷቸው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፖሊስ አባላት ላይ ከቀላል እስከ ሞት ድረስ ጉዳት ደርሶባቸዋል ያሉት ኮሚሽነሩ “ዛሬ እና ትናንት 57 የሚሆኑ የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ላይ ጉዳት ደርሷል” በማለት ሁለት አባላት ህይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።

በዜጎች ላይ ደረሰ ባሉት ጉዳት “ትናንት እና ዛሬ 8 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል” ካሉ በኋላም፣ ነዋሪዎች ህይወታቸው ያለፈው “በቦምብ፣ ጥይት፣ በድንጋይ እና በመሳሰሉት ነው” ብለዋል።

• ፌደራል ፖሊስ ሃጫሉ ሁንዴሳ በጥይት የተመታው መኪናው ውስጥ መሆኑን ገለፀ

• “በሦስቱ ሰኔዎች ጉዟችንን የማደናቀፍና ደም የማፍሰስ ሙከራዎች ተደርገዋል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ

ንብረትነታቸው የግሰብ እና የመንግሥት የሆኑ 250 ተሽከርካሪዎች ተሰባብረዋል፣ 20 ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል ሲሉም አክለዋል።

“የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት ጭምር የተሳተፉበት በተለይ የባልደራስ እና አብን አመራሮች እና አባላት በግልጽ ቲሸርት በመልበስ እና የፓርቲያቸውን ባንዲራ በመያዝ የከተማዋ የተለያየ አከባቢ ላይ በመንቀሳቀስ የብሔር ግጭት ለመፈጥር ሰፊ እንቅስቃሴ ለመፍጥር ሲደረግ ነበር” ብለዋል።

“በተለያዩ የከተማው አቅጣጫ በመንቀሳቀስ አንዱ ብሔር ሌላውን ሊጠቃ እንደመጣ፤ እየተወረረ እንደሆነ” በማሳወቅ “እንዲከላከል” ቅስቀሳ ሲያደርጉ ነበር ብለዋል።

በከተማዋ ሰዎችን በማስቆም መታወቂያ የመጠየቅ እንቅስቃሴም እንደነበረ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

BBC Amharic

1 Comment

  1. Rest In Peace

    Numerous members of Balderas and Amara National Movement ANM are being displaced by the Querro undercover security apparatus , some Balderas and ANM members are said to be on the roads fleeing towards Kenya fearing for their lives and fearing of being imprisoned charged with conspiring to incite violent ethnic clashes charges , facing upto life in prison or even being punished with the capital punishment if deemed guilty , that is why they are resorting to being displaced before they get put in jails charged with these crimes.

    Ethiopians who reside along the way please assist those displaced who you see wearing the Balderas or ANM t-shirts traveling towards the border of Ethiopia mostly from Addis Ababa or from Northern Shewa directions. They were not ready mostly are not prepared to travel ,any little help will mean so much to them.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.