የአዲስ አበባ ወቅታዊ ሁኔታ- ልዩ ሃይል አመራሮች የተዋቀረ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የሚመራ ኃይል አገሪቱን እያረጋጋ ይገኛል

ከመንግሥት አካባቢ በወጣ መረጃ መሰረት በአሁኑ ሰዓት በመከላከያ በፖሊስ በደህንነት እና በየክልሉ ልዩ ሃይል አመራሮች የተዋቀረ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የሚመራ ኃይል አገሪቱን እያረጋጋ ይገኛል። ኢንተርኔት የዋይፋይም መቋረጥ በጥባጮች አቅም እንዳይኖራቸው እድርጓል ተብሎአል።

47965781 303ከመንግሥት አካባቢ በወጣ መረጃ መሰረት በአሁኑ ሰዓት በመከላከያ በፖሊስ በደህንነት እና በየክልሉ ልዩ ሃይል አመራሮች የተዋቀረ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የሚመራ ኃይል አገሪቱን እያረጋጋ ይገኛል። ኢንተርኔት የዋይፋይም መቋረጥ በጥባጮች አቅም እንዳይኖራቸው እድርጓል ተብሎአል። የሃጫሉን ሃዘን የኦሮምያ ክልል እና የፊደራል አመራሮች ከሃጫሉ ቤተሰብ ጋር በመሆን ልዩ ዝግጅት እያስተባበሩ ይገኛሉ ይላል መረጃዉ። ሁሉም ተረጋግቶ ሌላዉን እንዲያረጋጋ ሲል ከመንግሥት ኮሚኒኬሽን ቢሮ የደረሰዉ መረጃ ያመለክታል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ትናንት በሰጡት ማብራሪያ ድምፃዊ ሐጫሉ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ አራት ልዩ ስሙ ገላን ኮንደሚንየም አካባቢ ባልታወቁ ሰዎች በጥይት መገደሉን አረጋግጠዋል። “የተወሰኑ ተጠርጣሪዎች” መያዛቸውንም ፖሊስ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ለግድያው “ታጣቂዎችን” ተጠያቂ ማድረጉን ነዉ የገለፀዉ ። ዛሬ መዲና አዲስ አበባ እንዴት ዋለች?  የአዲስ አበባዉን ወኪላችንን ጠይቀነዋል።

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ

DW

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.