የሐጫሉ ገዳዮች እነማን ናቸው? አይታወቁም? አይመስለኝም

106413914 3381279905226947 3888114694662323457 o e1593530320533እንግዲህ ማስተዋል ከጠፋ ምን እናደርጋለን፡፡ ነገሮችን በማስተዋል መመልከት እጅግ ይጠቅማል፡፡ እኔ ብሆን የሐጫሉን ጉዳይ እንድህ እመረምረዋለሁ፡፡

ከጥቂት ቀናት በፊት ሀጫሉ በኦኤምኤን ቀርቦ ስለሚኒሊክ ፈረስና ስለባንክ የገንዘብ ብድር አውርቷል፡፡ ሐጫሉ በተፈጥሮው ስለሚኒሊክ ሊመረው የሚችል አንዳች ታሪካዊ እውነት የለም፡፡ ሐጫሉ የነፍጠኛ ዘር እንጂ የባንዳ ዘር አደለም፡፡ ሐጫሉ ኦሮሞነቱን መውደዱ መልካም ነበር፡፡ ችግሩ ግን ከዛ ባለፈ ለሌሎች መጠቀሚያ መሆኑን ማስተዋል አልቻለም፡፡ ሚኒሊክን በኦሮሞ ሁሉ ዘንድ እንደጭራቅ የሚያሳዩት የኢትዮጵያ ጠላቶች ሐጫሉን በዚህ ቃለመጠይቁ ወቅት ሲጠቀሙበት በግልጽ እናያለን፡፡ እንግዲህ ከቃለ መጠይቁ ቀደም ብለውም ለእነደዚህ ያለ ንግግር አዘጋጅተውት ይሆናል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ጊዮርጊስ ፊት ለፊት ያለው የሚኒለክ ፈረስ የተቀረጸ ሀውልት እንጂ መቼም የተሰረቀ ፈረስ እንዳልሆነ ለመረዳት የሚያዳግት ነገር አደለም፡፡ ቀራጩ ደግሞ ጀርመናዊ እንደነገር ይነገራል፡፡ እንግዲህ በጥላቻና ዘረኝነት ሊያውሩህ ሲፈልጉ በየትኛውም ትርክት እውነት አስመስለው ያሳዩሃል፡፡ የሆነ ሆኖ ይህ ከሚኒሊክ ጋር በተያያዘ የነበረቸው የሐጫሉ መጠይቅ ሐጫሉን ለእርድ በሚያቀርቡበት ጊዜ ነፍጠኛ ወይም ሚኒሊካውያን ሐጫሉን ገደሉት ለማለት የተዘጋጀና በዚሁ ትልቅ ሁከት ለመፍጠር እንደነበር ሐጫሉም ሆነ ሌሎቻችን በዚህ ደረጃ ይመጣሉ ብለን አላስተዋልንም፡፡

ሁለተኛው የባንክ ገንዘብ ብድሩ ጉዳይ ነው፡፡ ሐጫሉ በዛ ንግግሩ አንድ በጣም የሚያደንቀው ሰው ገንዘብ ከባንክ ያለ ምንም ተያዥ እንደሰጠው ይናገራል፡፡ ይሄው ሰው ከዚህ በፊትም ለኮንሰርት ማዘጋጃ እንዲሁ ሰጥቶት ባኋላ ግን ኮንሰርቱ ስለተሰረዘ ገንዘቡን እንደመለሰ ሐጫሉ ይናገራል፡፡ ይህ ሰው ግን እውን ሐጫሉን ለመጥቀም ነበር ወይስ ሐጫሉን የሆነ ቀለበት ውስጥ ለማስገባት? እንግዲህ ሐጫሉ መልካም ሰው ብሎ ሲያደንቀው የነበረ ይህ ሰው በባንክ ገንዘብ አራጊ ፈጣሪ ሆኖ እንደፈለገው ገንዘብ ለግለሰቦች የሚያድል ማን ነው?ሥሙን አደለም ከበስተኋላው ያለውን የሴራ ሰንሰለት እንጂ፡፡ በቀደመው የኮንሰርቱ የገንዘብ ስጦታ ሐጫሉን ቀለበት ውስጥ ሊያገቡት አስበው በኋላ ሊያስከፍል የሚችለውን አደጋ ስለተረዱ ከዛ ይልቅ ኮነሰርቱን መሠረዝ አዋጭ ስለነበር ይመስላል ሂደቱ፡፡ ዛሬም ግን ያው ሐጫሉን ለማጥመድ ተልዕኮ የተሰጠው የባንክ ሰው (ብቻውን አደለም ሌሎች በዛው ባንክ ይኖራሉ) 10 ሚሊየን ብር ያለአንዳች ተያዥ በመስጠት ለዛሬው የሐጫሉ የሞት አደጋ ነገሮችን እያመቻቸ እንደነበር አለማሰብ ትልቁ ያለማስተዋላችን ችግር ነው፡፡ ይሄ ሴራ እንደዚህ ከሆነ በዛ ቃለመጠይቅ ጠያቂ የነበረው ጋዜጠኛ ጨምሮ ሌሎችም ሐጫሉ ላይና ቀጥሎም በኢትዮጵያ ላይ እየተሸረበ ላለው ሴራ ተባባሪ እንደነበሩ አለማስተዋል ሌላው አደጋ ነው፡፡

ከሐጫሉ ሞት በኋላ ተከትሎ እያየናቸው ያሉ ትዕይንቶች ከላይ የጠቅኳቸውን ሴራዎች ለሚያስተውል በግልጽ እያሳዩን ነው፡፡ የኦኤም ኤን ዘጋቢዎች ስለ ሐጫሉ ሞት አልደነገጡም አላዘኑም ለእነሱ ሰርግና ምላሽ የሆነላቸው ይመስላል፡፡ የሐጫሉን ሞት በቶሎ በአገር ደረጃ አመጽ ለመቀስቀስ ሲጠቀሙበት አንዳች አልዘገዩም፡፡ የእርስ በእርስ ግጭት እንዲቀሰቀስ አለን የሚሉትን ሁሉ ሲያደርጉ እየተመለከትን ነው፡፡ እንግዲህ የሐጫሉ ሞት ለጠላቶቹ ሌላ ግብዓት ሆኖላቸው ወደለየለት የሀግርና ሕዝብ ብጥብት ለማስገባት በአላቸው ሁሉ እየጣሩ ነው፡፡ ሁሉም ከዚህ ጀርባ ያሉት በኦሮሞና በሌሎች ኢትዮጵያውያን ሁሉ ላይ በአስከፊነቱ የምናስታውሰው የወያኔ ሆነኛ አጋር እንደሆኑ አይናችን እያየ ብዙዎች ክደናል፡፡ እንግዲህ ኦሮሞ ማስተዋል እንዳይችል ተደርጎ ለበርካታ ዓመታት በዘረኝነትና በጥላቻ ትርክት ከመረዙት በኋላ ዛሬ ለእነሱ እንደፈለጉ የሚያደርጉት የንግድ እቃ አድርገውታል፡፡ ወያኔ 27 ከፈጸመው የከፋ በእነዚህ ኦሮሞ ነን በሚሉ ወኪሎቹ እያደረሰ ያለው ጥፋት ሊበልጥ እንደሚችል የገመትነው ኦሮሞ ትልቅ ቦታ ሰጥቷቸው የነበሩ እነ በቀለ ገርባና ሌሎች ዛሬ ከዚህ ልጅ ሞት ጀርባ ሊኖሩ የሚችሉ መቀሌ ድረስ ሄደው የወያኔን ተልዕኮ ሲቀበሉ ለመሆኑ እናንት ማናችሁ ከጠላታችን ጋር የምታደቡ ብሎ የሚጠይቅ የጠፋ ጊዜ ነው፡፡ ዛሬ ለኦሮሞ ብቸኛ ጠላት ሚኒሊክ ነው፡፡ እነሱ የፈጠሩለት፡፡ አንዱም ዛሬ በሕይወት የሚኖር ኦሮሞ ሚኒሊክንም ሆነ በወቅቱ የሠሩትን አያውቅም፡፡ በዓይኑ ያየውን ሲገድለውና ስንት መከራ ሲያደርስበት የኖረውን ወያኔን ዛሬ መርሳት ብቻም ሳይሆን ወዳጄ ነው የሚል ብዙ ነው፡፡ እንግዲህ እንዲህ ነው የምትሆነው፡፡ ይሄ አዚም ካልሀነ ለሌ ምን እንላለን፡፡

በትልቁ ግን አሁን እነዚህ ከሐጫሉ ግድያ ጀርባ ያሉ ከግብጽ ጋር እንደሆኑ አለማስተዋል ሌላው ችግራችን ይሆናል፡፡ ኦኤምኤን ከጅምሩ ጀምሮ በግብጽ እየታገዘ እንዳለ እንደውም በግብፅ ማሰራጫ ሁሉ ከፍቶ እንደነበር እናውቃለን፡፡  ግብጽ ከምትተማመንባቸው አንዱ ይሄው ጀዋሪንና ኦኤምኤንን በማምለክ በሚባል ደረጃ የሚከተልን የኦሮሞ ወጣትን ነው፡፡ ግብጽ ኢትዮጵያ ጋር በፊት ለፊት ጦርነት ገጥማ እንደማይሳካላት ታውቃለች፡፡ ስለዚህ በኢትዮጵያ ለዘመናት በዘረኝነትና በጥላቻ የተመረዝን ትውልድ እንደመሣሪያ ልትጠቀምበት እያሴረች እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ አንዳንዴም በራሳቸው ሚዲያ ይሄንኑ ሲናገሩት እንሰማለን፡፡ ግብጽ የኦሮሞ ሕዝብ ከእኔ ጋር ነው ብላ ታምናለች፡፡ ኦሮሞ ማለት ምን አይነት ማህበረሰብ እንደሆነ በትክክል የተረዳችው ባይመስልም፡፡ ቢያንስ ግን በግልጽ የእኔ ኦኤም ኤንና መሰሎቹ ቡድኖች እንደፈለጋቸው የሚዘውሩት ትልቅ የወጣት ክፍርል እንዳለ በደንብ ታውቃለች፡፡ አንድ ጊዜ ግን ይሄንኑ ብጥብጥ የሚፈጥር ነገር መፍጠር ወሳኝ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ከሐጫሉ በላይ ሊሆን የሚችል ወሳኝ ሰው የለም፡፡ እንግዲህ ወያኔ፣ የኦኤምኤን፣ ኩሽ ሕዝብ ባዩ ቡድን፣ ፌደራሊስትና ወያኔ በሕብረት በዚህ ጉዳይ እንዳሉ አለማሰብ የአለማስተዋላችን ሁሉ ከፍተኛው አደጋ ነው፡፡

ለማንኛውም አሁን ሐጫሉን በመግደል ተሳክቶላቸዋል፡፡ ቀጥሎ ያሰቡት ሴራ ለማሳካት ያለ የሌለ አቅማቸውን እየተጠቀሙ ነው፡፡ እንዳሰቡት ግን የሚሳካላቸው አይሆንም፡፡ እንግዲህ መንግስት የሚባለው አካል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በዚህ ጉዳይ ላይ እርምጃ መውሰድ አለበት፡፡ እንዲህ የቧሀን እየተለቀሙ መገደል ሳያንስ የእነሱን ሞት ሌላ ጥፋት ገዳዮች እንደ መሣሪያ ሲጠቀሙበት እያየን ዝም ካልን ችግሩ የእኛ ይሆናል፡፡ ሕዝቡን ከጫኑበት የአስተሳሰብ ባርነት አውጥቶ አስተዋይ ማድረግ ሲጠበቅ በፖለቲካው ጫፍ ላይ ያሉትም ያችንው ተመሳሳይ የዘርና ጥላቻ ስልት ነው የሚጠቀሙት፡፡ ያኔ እነለማና ገዱ ጅምረውት በነበረ የኦረሞ ደም የእኔ ደም ነው በሚለው የጎንደሬዎቹ ኃይለቃል ገፍተውበት ቢሆን ዛሬ ይሄ ሁሉ ባልሆነ፡፡ የምንናፍቀውም ሠላም በመጣልን፡፡ መጀመሪያ አካባቢ በኢትዮጵያዊነት የተጀመረው ብዙም ሳይቆይ ነበር ወደ እውነትኛው የዘር ሱስ የገባው፡፡ የእነ አብይ የአሜሪካ ጉዙ በሚኒሶታ ትልቁ ስምምነት ከጀዋር ጋር በኦሮሞነት መሥራት ነበር፡፡ እሰከዛ ጊዜ ድረስ ጀዋር በወያኔ መውደቅ እጅግ ደንግጦ ነበር፡፡ አሁንም አላለሁ፡፡ ሁሉም ያስተውል፡፡ በአብዛኛውም ለራሳችን ስንል እናስተውል፡፡ ምንም የማያውቁና በዘረኝነትና ጥላቻ ስብከት የተመረዘ አእምሮ የያዙ ወጣቶችን የሞት ማገዶ በማድረግ ከኋላ የሚቆምሩትን አንዳች መደናገጥ ሳይኖር ሁሉም ሊዋጋቸው ያስፈልጋል፡፡ ዛሬ በየሰልፎቹ የምናየው ይሄው ነው፡፡ ነፍጠኛና የሚኒሊክ ሐውልት ናቸው ዋና አጀንዳዎች፡፡ እንግዲህ መግደል ብቻ ሳይሆን መሞትም አለ፡፡ ከሁሉም በላይ አደጋው ለኦሮሞ ሕዝብ እንደሆነ ማስተዋል ካልተቻለ ምን ማድረግ እንችላለን፡፡ የሐጫሉም ገዳዮች በዚህ አጋጣሚ እንደ ጀግና ተቆጥረው ሊቀሩ ይችላሉ፡፡ ሐጫሉ ከአራጆቹ ውሎ እሱም ሕዝቡንም ለአደጋ አጋልጧል፡፡ ቢያንስ እስካሁን የሆነው ሁሉ ሆነ የሐጫሉ ሞት ግን ፍትህ ሊያገኝ ይገባዋል እንላለን፡፡ የሐጫሉ ብቻም ሳይሆን የብዙዎች ደምን ለዘመናት ባፈሰሱ ላይ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል እንላልን፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር የወንድማችንን ነብስ በገነት ያኑር! ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ከጠላቶቿ ይጠብቅ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

7 Comments

 1. ሰርፀ፣
  አመለካከትህ የግል ቢሆንም አሳፋሪ ነው። ከምኔው ገዳዩን ለየህ ጃል? እጅህ ያለበት ይመስላል ወይም ግ ንኙነት ይኖርሃል። ምንሊክ እኮ እንደ ማንም ሰው ናቸው፣ አይወቀሱ ልትል አትችልም። “ኦሮሞ ማስተዋል እንዳይችል ተደርጎ ለበርካታ ዓመታት በዘረኝነትና በጥላቻ ትርክት ከመረዙት በኋላ ዛሬ ለእነሱ እንደፈለጉ የሚያደርጉት የንግድ እቃ አድርገውታል” በጅምላ ስትፈርጅ የአስተሳሰብህን ደካማነት እንጂ እውነታን ያገናዘበ አይደለም። “ኦማራና ትግሬስ ማስተዋል እንዳይችል ተደርጎ ለበርካታ ዓመታት በዘረኝነትና በጥላቻ ትርክት ከመረዙት በኋላ ዛሬ ለእነሱ እንደፈለጉ የሚያደርጉት የንግድ እቃ አድርገውታል?”

  የጥላቻህ ብዛት ሟች ሬሳው ሳይቀበር ክስና አሉባልታ ይዘህ ቀረብክ። በባለቤቱና ሕጻናት ልጆቹ ዘመዶቹ ላይ ርኅራኄ የለሽ ክስህ የሚያስከትለውን የቁም ስቃይ አስበህበታል? ነግ በኔ በል። ሃጫሉ ይሁን ማንም መገደል የለበትም! አንተም መገደል የለብህም።

 2. Solomon: Our culture sympathizes dead people and I feel it is fare as people who are not around will not defend themselves. However, the same logic should apply to all dead people. Why is then King Minilik, the founder of modern Ethiopia, we like it or not, is cursed by most Oromo politicians? Do you treat these people the way you treat Sertse?

 3. ያሳዝናል መገደሉ፡፡ መቼስ ምን ይባላል ነፍስ ይማር እንበል እንጂ! ምን አለበት የሚያውቀው ነገር ላይ ቢያተኩር ኖሮ ይህም ጋልኛ መዝፈን ነው። የኦሮሞ ታጋይ ነን የሚሉት እስካሁን የሚያሳዩት ተግባር ብስለት ይጎደላቸዋል፡፡ ወደ አማርኛ ተርጉመውልን የሰማነው ንግግር የልጁን ውርንጭላ አስተሳሰብ ነው የሚያስረዳው፡፡ የኦሮሞ ታጋይ ነን የሚሉት መቼ ነው ከእምዬ ሚኒሊክ! ከኢትዮጰያ ፀሃይ አባት መሪ ፡ከጥቁሮች መመኪያ ፡ የጥቁር ጀግና አባት ክሆኑት አልፈው በኢትዮጵያዊነታቸው የሚኮሩት? ገና ጠት ቆረጣውን ክስ አብላልተን ሳንጨርስ የፈረስና ያህያ ታሪክ ታሰሙን? እምዬ ሚኒሊክ እንኳን ገነት ነው ያሉት እረ ለእኛ ለቋሚዎቹ እንጭጭ አስተሳሰባችሁን ለምንሰማችሁ እዘኑልን፡፡ ወያኔ ቂጣቸውን ገልቦ እየገረፈ በረሃ የሰደዳቸው የትናንት ታሪክ እያለ ሚኒሊክ ፈረስ መጋልብ አይችልም ብሎ መዛለፍ ምን የሚሉት ነው? መቼም ጀግና ትረጉሙ የጠፋበት ዘመን ነው ይቺም የትናንት ውረንጭላ ማይክርፎን ጨብጣ ጀግና ተብላልች፡፡ ኧረ በሰል በሉ!

 4. ያሳዝናል መገደሉ፡፡ መቼስ ምን ይባላል ነፍስ ይማር እንበል እንጂ! ምን አለበት የሚያውቀው ነገር ላይ ቢያተኩር ኖሮ ይህም ጋልኛ መዝፈን ነው። የኦሮሞ ታጋይ ነን የሚሉት እስካሁን የሚያሳዩት ተግባር ብስለት ይጎደላቸዋል፡፡ ወደ አማርኛ ተርጉመውልን የሰማነው ንግግር የልጁን ውርንጭላ አስተሳሰብ ነው የሚያስረዳው፡፡ የኦሮሞ ታጋይ ነን የሚሉት መቼ ነው ከእምዬ ሚኒሊክ! ከኢትዮጰያ ፀሃይ አባት መሪ ፡ከጥቁሮች መመኪያ ፡ የጥቁር ጀግና አባት ክሆኑት አልፈው በኢትዮጵያዊነታቸው የሚኮሩት? ገና ጠት ቆረጣውን ክስ አብላልተን ሳንጨርስ የፈረስና ያህያ ታሪክ ታሰሙን? እምዬ ሚኒሊክ እንኳን ገነት ነው ያሉት እረ ለእኛ ለቋሚዎቹ እንጭጭ አስተሳሰባችሁን ለምንሰማችሁ እዘኑልን፡፡ ወያኔ ቂጣቸውን ገልቦ እየገረፈ በረሃ የሰደዳቸው የትናንት ታሪክ እያለ ሚኒሊክ ፈረስ መጋልብ አይችልም ብሎ መዛለፍ ምን የሚሉት ነው? መቼም ጀግና ትረጉሙ የጠፋበት ዘመን ነው ይቺም የትናንት ውረንጭላ ማይክርፎን ጨብጣ ጀግና ተብላልች፡፡ ኧረ በሰል በሉ!

 5. meseret”
  Minilik is dead and buried.
  Minilik was not murdered.
  Hachalu was murdered but was not buried when you criticized him.
  Sertse is no Minilik.
  It is ok to criticize Minilik.
  It is ok to comment on Sertse’s unsubstantiated statements.
  I don’t understand what your gripe is about.

  Zehab Publisher, pls publish my comments.

  • SOLOMON:

   Now I will say the truth and only the truth as you are comparing the incomparable because blood is thicker than water

   King Minilik is the one and only first African statesman who won a war against a white imperialist country, a person the whole black race is proud of. The fact is not like the “doma ras” tigre and oromo narrow-minded “gudelas” say.
   On the other hand, Hundesa is an ordinary man known for his oromo songs. Again for the sake of “Ethiopian Politeness” I do not want to say anything about the blunders this guy used to say with regard to Ethiopian history.

   FYI: The reason “the dead” are respected in the Ethiopian culture is because they cannot defend themselves, but has nothing to do with the fact that the dead person is already entered or not yet. Therefore, to be fair, let us stop humuilating the defenseless dead.

 6. አንድ ህዝብ ወይም ህብረተሰብ መብቱ የሚከበርለት በ ሁለት አይነት መንገድ ነው። እነሱም፡
  1) በ መንግሥት
  የ መንግሥት ተቀዳሚ ተግባር የ ዜጎችን ህልውና እና መብት ማስከበር ነው። አንድ መንግሥት ይህን ተግባሩን ለ መወጣት ዝግጁ ካልሆነ ወይም ካልቻለ ህዝብ ወደ ሁለተኛው አማራጭ ሳይወድ በ ግድ ይሸጋገራል። የ ህልውና ጉዳይ ነውና።
  2) ተደራጅቶ እራስን ማዳን
  በ አገራችን በ ተደጋጋሚ ጊዜ የ ኦሮሞ ወጣቶች በ ሌሎች ብሄሮች ላይ ብዙ ግድያ እና አካል ማጉደል፣ እንዲሁም ንብረት መዝረፍ እና ማውደም ፈፅመዋል። መቆሚያ ያለውም አይመስለም። በ አሁኑ ደቂቃ እንኳን በ አርሲ ውስጥ ብዙ ጉዳት እያደረሱ እንደሆነ ነው የሚሰማው። እስካሁን በ ትንሹ 52 ሰዎች ተገድለዋል። በአደባባይ ሰው ዘቅዝቀው የሚስቅሉ እና የሚገድሉ፣ ሰው ቀጥቅጠው የሚገድሉ፣ የሚያርዱ፣ ጡት የሚቆርጡ ወጣቶች ፈጽሞ ስበዕና የላቸውም።
  ለዚህ መፍትሄው ህዝብ ተደራጅቶ እራሱን መከላከል ብቸኛው አማራጭ ነው።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.