የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ለመስጠት አቅዶ የነበረውን 500 ሚሊዮን ዶላር አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ አገደ

በተስፋለም ወልደየስ

Abiy with WB president 3 696x464 1በዓለም ባንክ በሁለተኛ ምክንያትነት የተቀመጠው “በኢትዮጵያ የኢነርጂ ዘርፍ ላይ እየተካሄደ ያለው ማሻሻያ በእቅዱ መሰረት እየተከናወነ አይደለም” የሚል ይዘት ያለው እንደሆነ ምንጮቹ ገልጸዋል። ባንኩ ባለፈው ህዳር ወር ባወጣው ሰነድ ላይ ይህን ማሻሻያ የሚደግፈው በዘርፉ “ጾታዊ ተኮር ለውጦች እንዲካተቱ፣ ከዋናው የኃይል መስመር ውጭ ያሉ የኃይል አቅርቦቶች ገበያ እንዲጠናከሩ እና ሀገሪቱ ባላት ሰፊ የታዳሽ ኃይል ሀብት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግ” እንደሆነ ገልጾ ነበር።

የኢትዮጵያ መንግስት እየተገበረ ላለው የኢነርጂ ዘርፍ ማሻሻያ የዓለም ባንክ 200 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደሚያደርግ ከስምንት ወር በፊት ለንባብ በበቃው ሰነድ ላይ ይፋ ተደርጓል። ጉዳዩን በቅርበት የተከተታሉ የተቋሙ ምንጭ “ማሻሻያው ተግባር ላይ ውሎ ሳለ ባንኩ የአስቸኳይ ጊዜ የገንዘብ ድጋፉን ለማገድ በምክንያትነት ማስቀመጡ ግራ የሚያጋባ ነገር ነው” ሲሉ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። እኚሁ ምንጭ የአሁኑ የባንኩ እርምጃ “ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ላይ በያዘችው አቋም ላይ ግፊት ለማሳደር ያለመ ሳይሆን አይቀርም” የሚል እምነት አላቸው።

የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማልፓስ ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ባለፈው ሰኔ 11፤ 2012 ካካሄዱት ውይይት በኋላ በግል የትዊተር ገጻቸው ያሰፈሩት መልዕክት መሰል ጥርጣሬዎችን አጠናክረዋል። ማልፓስ በዚሁ መልዕክታቸው “ኢትዮጵያ እና ጎረቤቶቿ በውሃ ክፍፍል ላይ የሚያደርጉትን ገንቢ ውይይት እና ትብብር ዘላቂ ማድረግ እንደሚገባቸው” አሳስበው ነበር።

41910ca704eaf2b18cc54911372f46ae 2
David Malpass

@DavidMalpassWBG

Spoke with Ethiopian PM @AbiyAhmedAli on recent @WorldBank financing approvals.

Important to unify the expensive dual exchange rate & that Ethiopia and its neighbors sustain constructive dialogue + cooperation on water sharing.

Ethiopia’s success is key to Africa’s success.

504 people are talking about this

እርሳቸው የሚመሩት ተቋም ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን በዋሽንግተን ዲሲ ሲያካሄዱት በቆዩት የሶስትዩሽ ድርድር ላይ ከአሜሪካ ጋር በታዛቢነት ሲሳተፍ መቆየቱን የሚያነሱ ወገኖች፤ ባንኩ በቅርቡ ለኢትዮጵያ ያጸደቀውን የገንዘብ ድጋፍ አስመልክቶ ባደረጉት ውይይት ላይ የድርድሩን ጉዳይ ማንሳታቸውን አልወደዱትም። የባንኩን ፕሬዝዳንት አካሄድም በሀገሪቱ ላይ ጫና ለማሳደር ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ተርታ መድበውታል።

ማልፓስ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር ካደረጉት ውይይት አንድ ቀን ቀደም ብሎ፤ የአሜሪካ የብሔራዊ የጸጥታ ምክር ቤት “የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ከመጀመሩ በፊት ስምምነት ላይ መደረስ አለበት” ሲል በትዊተር ገጹ በተመሳሳይ መልኩ መልዕክት አስተላልፎ ነበር። ምክር ቤቱ “በምስራቅ አፍሪካ ያሉ 275 ሚሊዮን ህዝቦች ኢትዮጵያ ፍትሃዊ ስምምነት ላይ በመድረስ ጠንካራ አመራር ታሳይ ዘንድ እምነታቸውን ጥለዋል” ሲል አክሏል።

የአሜሪካንን ብሔራዊ ጸጥታ እና የውጭ ፖሊሲ ጉዳዮች በሚመለከተው ይህ ምክር ቤት በሊቀመንበርነት የሚመራው በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ነው። በህዳሴው ግድብ ላይ አሜሪካንን በመወከል በታዛቢነት ሲገኙ የቆዩት የትሬዥሪ ሴክሬተሪ ስቲቨን መኑሽንም የምክር ቤቱ አባል ናቸው።

7fdf32156d1b5ec390aab046a4aba6e1 2
NSC

@WHNSC

257 million people in east #Africa are relying on #Ethiopia to show strong leadership, which means striking a fair deal. Technical issues have been resolved – time to get the GERD deal done before filling it with Nile River water!

4,856 people are talking about this

አሜሪካ በዓለም ባንክ ላይ ያላትን ከፍ ያለ ተሰሚነትን ከግምት ውስጥ የሚያስገቡት የተቋሙ የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ምንጮች የባንኩን የገንዝብ ድጋፍ እገዳ ውሳኔ ከአሜሪካ አቋም ጋር ያገናኙታል። ባንኩ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስተዳደር ወደ ስልጣን ከመጣ ወዲህ ከፍተኛ የገንዝብ ድጋፍ ሲያደርግ የቆየ መሆኑን የሚጠቅሱት ምንጮች የገንዘብ ድጋፉ እገዳ ከዚህ ጋር የሚቃረን መሆኑን ይጠቁማሉ። ከማልፓስ የትዊተር መልዕክት አንድ ቀን አስቀድሞ እንኳ ባንኩ ለኢትዮጵያ 250 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ማጽደቁን በማነጻጸሪያነት ያነሳሉ።

ይህ የገንዘብ ድጋፍ ኢትዮጵያ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የሚደርስባትን የኢኮኖሚ ተጽዕኖ መቋቋም ያስችላት ዘንድ የተመደበ ነው። ከአጠቃላይ ድጋፉ ውስጥ 125 ሚሊዮን ዶላር ያህሉ በብድር የተሰጠ ሲሆን ቀሪው እርዳታ ነው። የዓለም ባንክ አካል በሆነው አለም አቀፍ የልማት ማህበር (አይ ዲ ኤ) አማካኝነት ፈሰስ የሚደረገውን ብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፓርላማ ባለፈው ሐሙስ ሰኔ 18፤ 2012 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው አጽድቋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

2 Comments

  1. Erpresser………………………………………………………!

    አደራህን ብቻ ደግሞ ነገ Human Rights በሚለው ገጣጣው ገፅህ ብቅ እንዳትል………….! ንጥረ ሃብት አሽታቹ..!

  2. At the drop of a hat this expected from America & its affiliates. Best of both worlds they have been working for Egypt’s advantage only but doesn’t work now. Instead why didn’t regret such World bank, IMF and others institutions lead by USA for interrupting many projects on use of Nile basin. It shows not a spark of decency for WB & USA.

    Making imposition poor country is not good, just Stealing someone’s thunder is not acceptable morally & ethically.
    It is shameful!!!!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.