ለመሆኑ ስለግድቡ ምን እየተሰራ ነው? – ሰርፀ ደስታ

dam 4የዚህ የአባይ ግድብ ነገር አያያዝ ግራ የሚያጋባ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የግብጽን ግብዣ እየተከተለች በየአገሩ የምትዞርባት ምክነያት ምን እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ ሲጀምር ይህ የአባይ ጉዳይ ከናይል ተፋሰስ አገራት ወጥቶ በሶስትዮሽ ድርድር ሥር መውደቁ በተለይ ለግብጽ ትልቅ እድል የፈጠረላት ይመስላል፡፡ ሲቀጥል የአፍሪካ ሕብረት እያለ ወርልድ ባንክንና አሜርካን አደራዳሪ ሆነው ሲቀርቡ ኢትዮጵያ የግብፅን ግብዣ ተከትላ አሜሪካ ድረስ የሄደችበት ጉዳይ ለእኔ ሊገባኝ ያልቻለ ሌላው እንቆቅልሽ ነው፡፡ ወርልድ ባንክ የተባለ ተቋም ኢትዮጵያ በምንም ምክነያት እንዳታድግ ከግብጽ ጋር አብሮ የሚሰራ ተቋም እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ሌላ ቀርቶ ኢትዮጵያ ውስጥ በዚሁ ባንክ ድጋፍ ወይም ብድር የሚሰሩ ሥራዎች ሳይቀር በግብጽ እንዲሰሩ ሲደረግ ነበር፡፡ ለዚህ ጥሩ ማሳያ የግብርና ምርምርና ሥልጠና እገዛ ተብሎ በአንድ ወቅት ጉድ የተባለ ገንዘብ ለኢትዮጵያ በተሰጣት ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲገነቡ የነበሩ ሕንጻዎች በግብጽ ምስር በተባለ ድርጅት ነበር እንዲሰሩ የተደረገው፡፡ ለዚህ ደግሞ የዓለማያ ዩኒቨርሲትን ማየት ይቻላል፡፡ እነዛ ሕንጸዎች እየተሰሩ ሳሉ እራሱ እየፈሩሱና እያፈሰሱ ነበሩ፡፡ አሁን ምን ደረጃ ላይ እንዳሉ አላውቅም፡፡

ግብጽ የውሀ ችግር የለባትም፡፡ እድሜ ለናይል ለዘመናት ሲፈስ የነበረው ውሀ በከርሰ ምድሯ ተከማችቶ በዓለማችን ትልቁ የከርሰ ምድር ውሃ ባለቤት አድርጓታል፡፡ ሌላው ግብጽ የምታቀርበው ግድቡ በጥራት አልተሰራምና ከታች ላለንው አደጋ ነው ባይ ነች፡፡ ይሄንም በሪሞት ሴንሲንግ አጥንቻለሁ ብላ በታወቀው የአሳታሚ ድርጀት ስፐሪነገር ላይ የዛሬ ወር ገደማ አሳትማለች፡፡ አካሂዷ ለክርክር እያዘጋጀች መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ይሄን ጽሁፍ ለበርካታ ኢትዮጵያን ምሁር ለማሰራጨት ሞክሬ ነበር፡፡ የሳይንስና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ጨምሮ ለበርካታ ሌሎች እንዲደርስ በራሴም በጓደኞቼም በኩል አደርጌያለሁ፡፡ አዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ የተወሰነ ሙከራ እያደረጉ እንደነበር የተወሰነም ድራፍት ነገር ልከውልኝ አይቻለሁ፡፡ አሁን ባለሁ ሁኔታ ምን እንደሆነ አላውቅም፡፡ እትም ሆኖ ለመውጣት ትንሽ ጊዜ ይፈጃል ምን ዓልባትም ለአሳታሚ ልከውት ከሆነ፡፡ ሊያውም ጥራቱን ጠብቆ ለእትም የሚበቃ መሆኑ ከተረጋገጠ ነው፡፡ ግብጾቹ ግን ቀድመው በሳይንስ የተጠና መረጃ አለን ለማለት መረጃ ማዘጋጀታቸው ነው፡፡

ግብጽ ዓላማዋ ኢትዮጵያ የዚህ ግድብ ባለቤት ከሆነች የማደግ እድል ዓላትና ይሄን ግድብ እንደምንም ማስቀረት አለብኝ የሚል ነው፡፡ ከውሀም ከደህንነትም ስጋት ጋር አንዳች ግንኙነት የለውም፡፡ የግብጽ ፖለቲከኞች በአገራቸው የፖለቲካ ውጥረት ስላለባቸውም ይሄን ጉዳይ እንደ አንድ ትኩረት መቀየሪያ እየተጠቀሙበት ነው፡፡ የሆነ ሆኖ ግን በእኛ በኩል ምን እየተሰራ ነው? እነ አብይ ከወዲሁ የኢትዮጵያን ሕዝብ ስነ ልቦና ለማወቅ በወዳጅ ሚዲያዎቻቸው ግድቡ ሙሌት ይዘገያል፡፡ የሚል መረጃ ከለቀቁ በኋላ እንደገና በሁለት ሳምነት ውስጥ ስምምነት ላይ ይደረሳል ግድቡ በተያዘለት ጊዜ ይሞላል ይሉናል፡፡ እናያለን እግዲህ ቀኑ ሲደርስ፡፡ ለነገሩ ምንጣሮ አልተካሄደም ምናምን የሚል አዲስ ቀልድም የሰማሁ መሰለኝ፡፡ ይሄን የሚያህል ግድብ ለመክፈት ዝግጅት ሲደረግ ምን ያህል ጊዜ ሥራዎች ቀድመው ማለቅ እንዳለባቸው ማቀድ አልቻልንም አይነት ቀልድ ይመስላል፡፡ ይሄ ለዓመታት ሲሰራ የኖረ ፕሮጅክት ነው፡፡ መጀመር የሚባለው ነገር የሚታቀደው ቢያንስ ሥራዎች በዚህ ሰዓት ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ተዘጋጅተው ሲገኙ ነው፡፡  ጭራሽ ቀሪ ሥራዎች ይሉናል፡፡ እንዲህ ያለ ቀልድ ለግብጽ ግብዓት ለመስጠት ካልሆነ መቼም ባልታሰበም ነበር፡፡ አብይ ግድቡ ለፖለቲካ ፍጆታ የተጀመረ ሲል ብዙዎች እንደሰሙ ይናገራሉ፡፡ እኔ ስላልሰማሁ ይሄን ምስክር አደለሁም፡፡ ይሄን ብሎ ከሆነ ደግሞ ጥያቄያችን አልሲሲ ጋር ሳይሆን እራሳችን ቤተመንግስት ውስጥ እንደሆነ እናስተውል፡፡ በሌላ አገር እንዲህ ያለን መሪ በአገር ክህደት ወንጀል ሊጠይቁት በተገባ ነበር፡፡ በተመሳሳይ ነበር ሱሌይመን ደደፎ ከኢሚሬት በፌስቡኩ ለግብጽ ግብዓት ያለውን የነገረን፡፡

ግብጽ ኢትዮጵያን ለማጥቃት ባሰባሰበቸው አረብ ሊግ የተባለ ቡድን ሰሞኑን አባላት ሚኒስቴሮቹን ሰብስቦ ከሱማሌና ጂቡቲ በቀር ሌሎቹ ለግብጽ መቆማቸውን እንዳረጋገጡ አይተናል፡፡ በአፍሪካዊው ናይል ግብጽ አረብ ሊግን እንጂ የአፍሪካ ሕብረትን ድጋፍ አትፈልግም፡፡ የሆነ ሆኖ ያቺ አብይ በየቀኑ የሚሳለማት ኢሚሬት ከማን ጋር እንደሆነች የቁርጥ ቀን ግልጽ አድርጎታል፡፡ በኢትዮጵያ በኩል ምን እየተሰራ እንደሆነ ግልጽ አደለም፡፡ ለዚህ ደግሞ ዋና ተጠያቂው የቤተመንግስቱ አብይ ሊሆን እንደሚገባው አምናለሁ፡፡ የግድቡ ዋና ኢንጂነር የተባለው ሰው እንደ ዘበት ራሱን ገደለ በሚል ጉዳዩ የታለፈ ዕለት ነው ችግር እንዳለ እንኳን  አለማሰባችን የታወቀው፡፡  ከዛ በኋላ የሆኑ ብዙ እስካሁንም መልስ ያላገኙ ነገሮች አሉ፡፡  በሌላ በኩል  የአገሪቱን ወሳኝ የተባሉ መዋቅሮች ሁሉ በኦሮሞነት፣ ከከኦሮሞም በጴንጤነትና በእስላምነት ያሉትን እየተሞሉ እንደሆን እናያለን፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን፣ ገቢዎችን ሌሎችንም መጥቀስ ይቻላል፡፡ ሊያውም ለዘመናት ወያኔ  እንኳን በዘር ያልሞከራቸውን፡፡ ወያኔ ያልሞከረው አለ ወይ ካላችሁ፡፡ በግልጽ ልነግራችሁ እችላለሁ፡፡ ለጊዜው ግን ሥሙን አልጠራም፡፡ እነ አባ ዱላና ግርማ ብሩ  ጡረታ ወጡ ከተባለ በኋላ ይሄው አገር በመሸንሸን ሥራ ተሰማርተዋል፡፡ ውጬ ጉዳይን ሌንጮ ባቲን ከውጭ (ለመሆኑ ሌንጮ ባቲ ዜጋ ነው?) ዲና ሙፍቲን ከኬንያ አምባሳደርነት አምጥቶ (እንግዲህ የማናቃቸው ሌሎችም ይኖራሉ) ማንም ሳያውቅ ኃላፊ ሆነው ሲናገሩ እየሰማን ነው፡፡ ዲና ሙፍቲ  ከኬንያ አምባሳደርነት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርነት ቃልአቀባይነት ሲሾም፣ ሌንጮ ባቲ በየት በኩል እንደሆነ ባይታወቅም (ይታወቃል ግን በኦሮሞነት) ባለስልጣን ሆኖ እናያለን፡፡ አንዳንድ ሹመኞች ኦሮሞነት እንጂ ከእነጭርሱም ኢትዮጵያዊ ዜግነት እንደሌላቸው የሚነገርላቸውም አሉ፡፡  ሲጀምር ከአፋርም ሚኒስቴር ነበረን ሊያውም የመከላከያ፡፡ ለመሆኑ ወዴት ገፋት? ኦሮሞ ጴንጤ ብትሆን ወሳኝ ቢያንስ ሌላ ወሳኝ ቦታ ይሰጣት ነበር፡፡ እንደ የአቤቤ ልጅ፡፡ ትግሬ ምናምን ሙልጭ ብሎ የተወገደ መሰለኝ፡፡ አማራ የሚባሉት አገርን እያሻሻጡ ከአሉት ነው፡፡

ልብ በሉ እኔ በኦሮሞ ላይ አንዳች ጥላቻ ያለኝ ሰው አደለሁም፡፡ እንደውም በኦሮሞ ሥም እየተነገደና ሕዝቡንም ወደ ለየለት የንግድ ዕቃነት ቀይረው በሚነግዱበት እጅግ ከሚበሳጩ ነኝ፡፡ የኦሮሞ ፖለቲከኞች አያያዝ ቆይቶ እያመጣ ያለውን አደጋ ከወዲሁ ማሰብ ካልተቻለ እንግዲህ ችግሩ ሲመጣ ራሱ ያስተምረን ይሆናል፡፡ ግን እስከወዲያኛው አደጋ ይዞ እንዳይመጣ ነው፡፡ ዛሬ በኦሮሞነት ሥልጣን እየታደሉ ያሉት በዘመናት በኢትጵዮጵያዊነት ላይ የተመረዘ ትርክት ሲተረክላቸው የኖሩና ዛሬ ዋና የኢትዮጵያዊነት ጠላት ሆነው ባሉ ነው፡፡ እነዚህ ግለሰቦች እጅግ የከፋ ዘረኝነትና ሌላውን የመጥላት በተለይ ሁሌም በራሳቸው በፈጠሩት ትርክት ሁሌም የሚያባንናቸው የታላቁ የሚኒሊክን ደጋፊዎች ነፍጠኛ በሚል አማራን በተለይ እንደ ታሪካዊ ጠላት የሚያስቡ የጥላቻና ዘረኝነት መንፈስን በ30 ዓመት ትርክት የተጠመቁ ናቸው፡፡  ኢትዮጵያ ተወደደም ተጠላም የሚኒሊክ አገር ነች፡፡ ከሚኒሊክ በፊት ነጻነት እንደነበራቸው ዛሬ የሚያወሩን እነዚሁ የኦሮሞ ምሁር ተብዬ የጥላቻና ዘረኝነት አስተሳሰብ ባሪያዎች የኦሮሞም ሆነ የሌላው በባርነት ሥር የነበረውን ሕዝብ ሚኒሊክ ከባርነት እንዳላቀቁት ታሪኩን አጥተውት አደለም፡፡ ታሪክ የሚነግረን አባጅፋር እንጂ ሚኒሊክ አደሉም የባሪያ ነጋዴ፡፡ አብዛኛው ከሚኒሊክ በፊት የነበሩ የአካባቢ ገዥዎች የባሪያ ንግድ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያካሂዱ እንደነበር እናውቃለን፡፡

ኦሮሞን ከኢትዮጵያዊነት ለማውጣት ያልተሰራ ሥራ የለም፡፡ ከፊደል መቀየር እስከ ሀይማኖት መቀየር፡፡ ዛሬ ኦሮሞ ሆኖ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታይ መሆን በኦሮሞ የጥላቻና ዘረኝነት ባርነት ሥር ለወደቀው ትውልድ እጅግ የሚቀፈው ነው፡፡ እርግጥ ነው ኦሮቶዶክስ ሐይማኖትና ኢትዮጵያዊነት እጅግ ቁርኝት አላቸው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ኢትዮጵያ እንጂ እንደሌሎች አማራጭ አገር የላትም፡፡ ለዘመናትም ከብዙ የውጭ ጠላት ወረራ ኢትዮጵያ ተጠብቃ የኖረችበት ዋና ቁልፍ ሚስጢር ብዙ የዚች እምነት ተከታይ መኖሩ ነው፡፡ ይሄን የቅኝ ገዥዎችም አሳምረው ያውቁት ነበር፡፡ ፖርቺጊዞች ለጦርነት እርዳታ መጥተው በኋላ ሕዝብን ሐይማኖት ማስቀየር ሙከራ ባደረጉበት ወቀት ከገጠማቸው የሕዝብ ቁጣ ጀምረው አውሮፓውያን ኢትዮጵያን በቀኝ ግዛት መያዝ አደገኛ እንደሆነ አሳምረው ያውቃሉ፡፡  ኢንግሊዞች አጼ ቴድሮስን ለመውጋት መጥተው ቴድሮስ ሞተው ከአገኙዋቸው በኋላ የቴድሮስን ልጅ ይዘው ሹልካ ብለው የወጡበት ምክነያት ለብዙ ሰው አያስተውለውም፡፡ እንግዲህ ኢንግሊዝ በዛ ወቅት በተነበራት የቅኝ ግዛት ጥማት ነው የኢትዮጵያን ምድር ግን ያለ አንዳች ሙከራ ለቃ የወጣችው፡፡  ጣሊያን ኢትዮጵያን የወረረችው በድፍረት ነበር፡፡ በኋላም የገጠማት ሽንፈት ብዙዎች እንደሚሉት ያልተጠበቀ ሳይሆን ቀደም ብለው ሌሎች የሚያውቁትና የሚጠብቁት ነበር፡፡ ለዚህ ደግሞ እንደዋነኛ ምክነያት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ነች፡፡ ጣሊያንም በኋላ ይሄንኑ በጠላትነትም ቢሆን መስክሯል፡፡ ኦርቶዶክስና አማራና ማጥፋት ካልተቻለ ኢትዮጵያን መውረር አደገኛ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ለዛም ነው የባንዳ ዘሮች ይሄን የጣሊያንን ምክር የተከተሉት፡፡ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ኦሮቶዶክስንና አማራን ማጥፋት ወሳኝ ሥልት ተደርጎ በመዋቅር ሲሰራ ቆይቷል፡፡ የኦሮሞ ምሁር ለአለፉት 50 ዓመታት በተለይም ለ30 ዓመታት ሲጋት የነበረው ይሄንኑ በኦርቶዶክስና አማራ ላይ በደንብ ጥላቻው እንዲየዋሀደው ነው፡፡ እንደነ ተስፋዬ ገብረአብ ያሉ ተራ ግለሰቦች ሳይቀሩ ዛሬ ያለውን የኦሮሞ ምሁር የአስተሳሰብ ባርነትን ለማልበስ ትልቅ ሚና ነበራቸው፡፡ ይህ እውነት ነው! ኦሮሞም ሆነ ሌላው ያለ ኢትዮጵያዊ ግን መኖር እንደማይችሉ ሁሉም ተረድቶ ከወዲሁ ቢያስብበት እያልኩ ብዙ ጊዜ ለማሳሰብ ሞክሬያለሁ፡፡ አሁንም እላለሁ፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን፣ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

ሰርፀ ደስታ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.